Historical Books Nehemiah

Nehemiah's Leadership

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Builder Nehemiah 11 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 329 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በነህምያ አዲስ ህይወት እየመጣ ነበር ምክንያቱም ሕዝቡ ተዘጋጅቶና ነቅቶ ስለ ነበር ፡፡ በምዕራፍ 11 ኢየሩሳሌም ስታድግ ሰዎች ከከተማዋ ዉጪ ወዳሉት ወደ ከተማ ዳር እንደተጓዙ እናያለን ፤ ይህ ለአንዳንድ እስራኤላዊያን መስዋዕት ለማድረግ እና በከተማዋ ለመኖር አስፈላጊ ነበር ፡፡ በኢየሩሳሌም ማን እንደሚኖር ለመወሰን ሕዝቡ እጣን ጣሉ ፤ በነህምያ 11 የምናየዉ ይህ ነው ፡፡ የሚያምረዉ አካል ነህምያ በጣም በማዋቀርና በማስተካከል እነዚህን ሁሉ ነገሮች መፈፀም መቻሉ ነበር ፡፡

ትምህርት

ነህምያ (11፡ 1)፡ የእስራኤል አለቆች በኢየሩሳሌም መሀከል ላይ ተቀመጡ ፤ ከአስሩ ሰዉ አንዱም በከተማይቱ እንዲኖር ተስማሙ ፡፡ ሀተታ ሰጪ ዋረን ዋይርስቤ “ ነህምያ የእስራኤል ህዝብ ኢየሩሳሌም ደካማ እስከሆነ ድረስ ጠንካራ መሆን እንደ ማይችል ያውቃል ፤ ነገር ግን ኢየሩሳሌም ጠንካራ መሆን ካልቻለች ህዝቡ ለመሰዋት ፍቃደኛ እንደነበር “ ፅፏል ፡፡ ከተማዋ ከተሰራች በኋላ ነህምያ አሁንም ስራዉ አልቆ እንዳልነበር ያውቃል ፤ በዚህ ስፍራ ማስተዳደር ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ አስተዋለ ፤ ነህምያም በኢየሩሳሌም ላይ እንዲኖሩ ህዝቡን ተጣራ ፡፡

ነህምያ (11፡ 2)፡ ሕዝቡ ወደ ኢየሩሳሌም ለመጓዝ ፍቃደኞች የሆኑትን ባረኩአቸው ፡፡ ሁሉም ነገዶች የከተማዋን ቅጥሮች መልሶ ለመገንባት ተመልሰዉ በአንድ ላይ መጡ ግን ቤታቸዉ ተመልሰዉ ሄዱ ፤ ሕዝቡ በሰሯት ከተማ ! በኢየሩሳሌም ለመኖር የሚፈልጉ አለመምሰላቸዉ የሚያስገርም ነው ፤ ያ ለምን እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ? ነህምያ ሕዝቡን በኢየሩሳሌም ያለዉ ለዉጥ አካል እንዲሆኑ ፈለጋቸው ፡፡

ነህምያ (11፡ 3-36)፡ እነዚህ ቁጥሮች በኢየሩሳሌም የሚኖሩት ሁሉም ሰዎች ዝርዝር ጅማሬዎች ናቸው ፤ እነዚህ በከተማዋ በመርዳት የለዉጡ አካል የሚሆኑ ሕዝቦች ነበሩ ፡፡ በኢየሩሳሌም የተመለሱ ሁለት ነገዶች አሉ - ይሁዳና ቢንያም ፤ የቀሩት አስሩ ነገዶች በሌላ ስፍራ የተበተኑ ነበሩ ፡፡ በዚህ ፅሁፍ ዉስጥ ስታነቡ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ሰዎች ቁጥር ታያላችሁ ፤ እነዚህ ወንዶችና ሴቶች የኢየሩሳሌምን ከተማ በማቆየት የተለዬ ሚና ነበራቸው ፤ እነዚህ ሰዎች እኔና እናተ ዛሬ ወደ ኢየሩሳሌም መሄድ እንድንችል አድርገዋል ፡፡ ምን አይነት የሚያስደንቅ መልክ(ስዕል) ነው !

ነህምያ 11 በማህበረሰቡ በአጠቃላይ ስለ መረጋጋት ነው ፤ ህዝቡ እንደ መሪያቸዉ ነህምያን አመኑት ፤ እግዚአብሄር በህይወቱ እንዴት እየተንቃሳቀሰ እንደ ነበር በማየት አመኑት (ተደገፉት) ፡፡ በሎቬት ሀ.ዌምስ ጄይር “ ከነህምያ አስር የመሪነት ትምህርት “ ተፅፏል ፡፡ ከነህምያ ልንማር የምንችለዉን አስር ነገሮች ያቀርባል፡

  1. የእግዚአብሄር መሪ ለጥሪዉ መልስ ይሰጣል ፡፡
  • የከተማይቱን ቅጥር መልሶ መስራት የሚለዉ ጥሪዉ ከእግዚአብሄር እንደ መጣ ነህምያ ያውቃል (ነህ 2፡ 12) ፡፡
  • ነህምያ ጥሪዉን በማክበር ለመልሶ ግንባታዉ የሚያስፈልገዉን ለማጥናት መጣ (ነህ 2፡ 11-16) ፡፡
  • አንድ መሪ ሁል ጊዜ ለጥሪ መልስ ይሰጣል !
  1. የእግዚአብሄር መሪ ለህዝቦቹና ለሁኔታቸዉ ይጠነቀቃል ፡፡
  • አንዴ ነህምያ ለጥሪዉ ምላሽ ሲሰጥ ከዚህ ኋላ የእግዚአብሄር ልብ ይታያል ፡፡
  • ነህምያ ራሱን “ እኛን “ ወይም “ ለእኛ “ የሚሉትን ቃላት በመጠቀም የሁኔታዉ አካል አደረገ (ነህ 2፡ 17, 20) ፡፡
  • ነህምያ “ ችግር ዉስጥ ነን “ ሲል እሱና የእስራኤል ሰዎች አንድ እንደ ነበሩ ገለፀ ፡፡
  • እንደ እዉነተኛ መሪ ነህምያ ጉዳዉን በመረዳት ከመሸሽ ይልቅ በችግሩ ዉስጥ ማለፍን መረጠ ፡፡
  1. የእግዚአብሄር መሪ የሁኔታዉን እዉነታ ለመግለፅ ይረዳል ፡፡
  • እንደ እግዚአብሄር መሪ ነህምያ ጉዳዩን አስተዋለዉ ነገር ግን በትዕቢትና በእብሪት መንገድ አይደለም ፡፡
  • ነህምያ ሁኔታዉን የእስራኤል ሰዎች ገጥሟቸዉ የነበረዉን መዘነው (ገመገመዉ) (ነህ 2፡ 17) ፡፡
  • ነህምያ ህዝቡን ማድረግ የሚያስፈልጋቸዉን ሁሉ እና የገጠሟቸዉን ችግሮች እዉነታ እንዲወያዩ መራቸው፡፡
  1. የእግዚአብሄር ምሪትና ራዕይ በመሪዉ እና በሕዝቡ የታዩ ናቸው ፡፡
  • ነህምያ ለሚሰራዉ ስራ ከእግዚአብሄር በሚመጣው ምሪት እና ራዕይ ላይ ተደግፏል ፡፡ ለምሪታችን ፍቃዱን በይበልጥ መፈለግ ያስፈልገና ፡፡
  • ነህምያ ያለማቋረጥ እየፀለየ ነበር ፡፡
  1. ፀሎት የእግዚአብሄርን ፍቃድ ለማወቅ አስፈላጊ ነው ፡፡
  2. የእግዚአብሄር ራዕይ ቀላል ነው ፡፡
  • ለነህምያ የእግዚአብሄር ራዕይ ቀላል ነበር - ቅጥሩን መልሶ መስራት ነው ፡፡
  • አንድ ራዕይ እንድንረዳዉ ቀላል መሆን ያስፈልገዋል ፡፡
  • ነህምያ በእግዚአብሄር መንገድ ላይ ቆዬ (ተቀመጠ) ፡፡
  • አንድ ራዕይ ወይም ምሪት ከምታስቡት የተለዬ ይመስላል ነገር ግን ራዕይ አሁንም ተመሳሳይ ነው ፡፡
  1. የእግዚአብሄር መሪ ቡድን ይገነባል ፡፡
  • ነህምያ የህዝቡ እምነት ስለ ነበረው ስራዉን ለመምራት ቡድን መስራት ይችል ነበር ፡፡
  • እስራኤላዊያን የእግዚአብሄር ራዕይ ማጠናቀቅ የሚችሉበት ብቸኛዉ መንገድ ስራዉን እንዲሰሩት እግዚአብሄር ሰጥቷቸዉ የነበረዉን ችሎታ መጠቀም ነበር (ነህ 2፡ 18) ፡፡
  • ስራዉ እንዲያልቅ ለመራዳት ከእግዚአብሄር ብዙ ችሎታዎች ተሰጥተዉናል ፡፡
  1. የእግዚአብሄር መሪ ከሕዝቡ ፊት ትክክለኛዉን አላማ ይጠብቃል ፡፡
  • ነህምያ ሕዝቡን እየሰሩ የነበሩት ቅጥሩን መልሶ መገንባት ብቻ እንዳልነበር ነገር ግን እንደ እግዚአብሄር ሕዝብ ስፍራቸዉን እንደ ገና እያቋቋሙ እንደ ነበር እንዲያስተዉሉ ረዳቸው ፡፡
  • ነህምያ ከእስራኤል ሕዝብ ምንም ነገር በፍፁም አልደበቀም ፡፡
  1. የእግዚአብሄር መሪ በመከራ ተስፋ አይቆርጥም ፡፡
  • እስራኤላዊያን ሲሰሩ በጠላቶቻቸዉ ቀልድ እና ማስፈራራት ተደርጎባቸዉ ነበር ፡፡
  • ነህምያ በግሉ ተዝቶበት ነበር ፡፡
  • ይሁን እንጂ ነህምያ እየሰራ የነበረዉ ለእግዚአብሄር አስፈላጊ እንደ ነበር ተረድቷል (ነህ 6፡ 3) ፡፡
  1. እግዚአብሄር ሁል ጊዜ ሌላ ራዕይ አለው ፡፡
  • የመጀመሪያዉ ራዕይ ቅጥሩን መልሶ መገንባት ነበር ነገር ግን በማብቃቱ ለቀጣይ እርምጃ የእግዚአብሄር ራዕይ ለመፈለግ ጊዜዉ ነበር ፡፡
  • ሁል ጊዜ እግዚአብሄር መስርቶት በነበረዉ ላይ የሚሰራ ሌላ ራዕይ አለው ፡፡

መደምደሚያ

የለዉጡ ሁኑ ፤ ወደ ኢየሩሳሌም የተጓዙ የእስራኤላዊያን ቅሪቶች የለዉጡ አካል መሆን ችለዉ ነበር ፡፡ ዛሬ እባካችሁ ለኢየሩሳሌም ሰላም መፀለይ እንዳታቆሙ አበረታታችኋለሁ ፤ አሁንም እግዚአብሄር ለዚች ከተማ ትልቅ እቅድ አለው !

3 Weems.

4 Weems

5 Weems.6 Weems.

7 Weems.

8 Weems.

9 Weems.

10 Weems.

11 Weems.

12 Weems.

  1. Warren Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2007), pp..

  2. Lovett H. Weems, Jr., Ten Lessons from Nehemiah; from Church Leadership, available at www.churchleadership.com/leading-ideas/ten-leadership-lessons-from-nehemiah/.

ጥያቄዎች

  1. በኢየሩሳሌም እንዲኖሩ ከአስሩ ሰዎች አንዱን ለማምጣት አይሁዶች ለምን እጣ አወጡ ?
  2. በነህ (11፡ 1) ኢየሩሳሌም እንደ ቅዱስ ከተማ ተጠቅሳለች ፤ “ ቅዱስ ከተማ “ የሚለዉ ማጣቀሻ በራዕ (21፡ 2) ላይ የሚገኝ ሲሆን ማንን ያመለክታል ?
  3. ንጉሱ (አርጤክስስ) መዘምራኑ የቀን ድርሻቸዉ እንዲሰጣቸዉ ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር ፤ ይህ የተለዬ ቡድን በየቀኑ አቅርቦት እንደ ነበራቸዉ እርግጠኛ ለማድረግ ለምን እንደለዬ ምን ታስባላችሁ ?
  4. በነህምያ መፅሀፍ የነህምያን ድርጊት ክርስቶስን እንዴት ሲያንፀባርቅ ታዩታላችሁ ?
  5. በነህምያ 11 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Nehemiah 11:1

“Now the leaders of the people stayed in Jerusalem, and the rest of the people cast lots for one out of ten to come and live in Jerusalem, the holy city, while the other nine-tenths remained in their towns.”

የእስራኤል ልጆች ወደ ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ፡፡ ቅጥሩንና ከተማዋን እራሳቸው እንደገና ሰሩ ፡፡ እንደገናም ያህዌን አመለኩ ወደ መንገዱም ተመለሱ ፡፡ መሬታቸውና በኩራታቸው ሳይቀር ለእርሱ ሰጡ ፡፡ እንደ ህዝብ አንድቀጥሉ ሊያደርግ እግዚአብሔር እንድቀመጡና እንድደራጁ ሲያደርግ ይህ ለመቀበል ጊዜው ነበር ፡፡ ነህምያም ህዝቡ እግዚአብሔር ለእስራኤል ህዝብ ያለውን አሳብና እቅድ ለመፈጸም የሚከተሉት ጠንካራ መሪ ነበረ ፡፡

ለሁሉም ጊዜ አለው ፡፡ መወሰን ማለት ቁርጠኝነት ነው ፤ ግን ከባድ ሊሆን ይችላል ፡፡ ያለህበትን ጊዜ ሙሉ በሙሉ ተቀብለሃል ? አንድ ቤት የራስህ አንደሆነ እንድሰማህ ልትቀመጥበት ይገባል ፡፡ ሰጥኖችህን ክፈት ፣ግርግዳዎቹን ቀባ ፣ ፎቶ ተነስ ፣ ለጓደኞችህ ህብረትን አዘጋጅ ፡፡ አድስ ቤቴ ክርስቲያን እየተከታተልክ ነው ? ለመጋቢው እራስህን ልታስተዋውቅ ጊዜው ነው ፤ ወደ አባላት ፕሮግራም ሂድ እናም በነርሲንግ ወይም በመኪና ማቆምያ ተቆጣጣሪነት ለማገልገል ጠይቅ ፡፡ የሆነ ቦታ ላይ ስትቀመጥ ቀጣይነት ይሆናል ፤ እና ይሄ መልካም ነገር ነው ፤ ይህም ማለት ለለውጡ ቆርጠሃል ማለት ነው ፡፡ ለውጥ ከእግዚአብሔር እንደሆነ ካወቅህ የሚያስፈራ ነገር አይደለም ፡፡ እግዚአብሔር በአንተ ላይ የሚያመጠውን ጊዜ ተቀበል ስትቀበል የእርሱ ሰላም ያስቀጥልሃል ፡፡

“የሕዝቡም አለቆች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፤ ከቀሩትም ሕዝብ ከአሥሩ ክፍል አንዱ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም፥ ዘጠኙም በሌሎች ከተሞች ይቀመጡ ዘንድ ዕጣ ተጣጣሉ ። “

  • ነህምያ 11፡1

ተጨማሪ ጥቅስ

ምሳሌ 16:3—“ ሥራህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፥ አሳብህም ትጸናለች ። “

ኤርምያስ17:7 — “ በእግዚአብሔር የታመነ እምነቱም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው ። “

ሉቃስ 9:62—“ ኢየሱስ ግን፦ ማንም ዕርፍ በእጁ ይዞ ወደ ኋላ የሚመለከት ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለም አለው ። “