Historical Books Nehemiah

Continuing the House of the Lord

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Builder Nehemiah 10 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 328 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በነህምያ እየፈሰስን እንዳለ ይሰማል ! ለዚህ ሙሉ መፅኀፍ ጭብጡ ወይም ርዕስ ገንቢ ነው ፡፡ ይህ በጣም ተግባራዊ መፅሀፍ ነው ፡፡ ነህምያ የኢየሩሳሌምን ቅጥር እየገነባ ነበር ፤ ነህምያ 9 መጨረሻ ላይ በእስራኤል ታሪክ ላይ አጥንቶ የነበረ የሰዎች ቡድን ነበር ፡፡ በምዕራፍ 10 ይህ ቡድን እግዚአብሄርን ለመከተል እንደወሰኑ የሚያሳይ መረጃን ለመፈለግ ወሰነ ፤ ይህ መረጃ የተፈረመበትና የታተመበት ነበር ፡፡

ትምህርት

ነህምያ (10፡ 1-27)፡ እነዚህ ቁጥሮች ለእግዚአብሄር ቃል ይታዘዙ እና ይተጉ የነበሩትን ሁሉንም ሰዎች ይዘረዝራል ፤ ሁሉም ነበሩ !

ነህምያ (10፡ 28-30)፡ እንደ እግዚአብሄር ሕዝብ የእስራኤላዊያንን መለየት ማየት ትጀምራላችሁ ፤ ይህ ከአለማዊ ነገርና ሰዎች በግልፅ ራሳቸዉን በመለየት የእግዚአብሄር ሕግ የሚያከብሩትን ሁሉንም ያካትታል ፡፡ ሁለት ዋና ዋና የመለያ ነገሮች አሉ ፤ የመጀመሪያዉ መለየት ከጋብቻ ነበር ፡፡ የእስራኤላዊያን በጠላቶቻቸዉ ወይም በሌሎች ህዝቦች ሴቶች በኃይል የተሳቡ መሆኑ ይህን ጭብጥ ለመሆን ዝንባሌ አለ ፡፡ ችግሩ እስራኤላዊያን ወደ ሌሎች ምድር በመምጣት የሌሎች ህዝቦችን ሲያገቡ አለማዊ በመሆን የእግዚአብሄር ቃል አለማክበራቸዉ ነበር ፡፡

ስለዚህም እስራኤላዊያን ሴት ልጆቻቸዉ ከእምነታቸዉ ዉጪ እንዲያገቡ አይፈቅዱም ፤ ይህ ለእኛ ትርጓሜ እራሳችንን የተለየን ማድረግ ነው ፡፡ በእኩል ከማትጠመዱት ጋር በግንኙነት ወይም በትዳር ራሳችሁን ለማስተሳሰር ስትጀምሩ ግንኙነቱ አይሰራም (ዘጸ 34፡ 10-17) ፡፡ ከመጀመሪያዉ ጀምሮ የእስራኤል መዉደቅ ከሌሎች ሴቶች ጋር መጋባታቸዉ እንደ ነበር አስባለሁ ፤ በፍፁም አልሰራም ! ጋብቻ በጣም አስፈላጊ ነው ! እንደ እግዚአብሄር ተከታዮች የተለየን እና ልዩ እንሆናለን ፡፡

ነህምያ (10፡ 31)፡ ሁለተኛዉ የመለያ ሁኔታ በሰንበት በኩል ነው ፡፡ እግዚአብሄር የፈለገዉ እና አሁንም የሚፈልገዉ ህዝቦቹ እንዲያርፉ ነው ፡፡ ሰንበት የእረፍት ቀን እንጂ የልፋት ቀን የሚሆን አይደለም ፡፡ ራሳችንን መጠየቅ እንደሚያስፈልገን አስባለሁ “ ቀኑን ሙሉ በእግዚአብሄር ላይ በመደገፍ ሙሉ በሙሉ ማረፍ እንችላለሁ ? “ እስራኤላዊያንን ወደ ባቢሎን የመራቸዉ (የወሰዳቸው) በሰባተኛዉ አመት አለማረፋቸዉ ነበር - ሰንበትን ስላላደረጉ ፤ ይህ ለነህምያና “ አዎ ከሰንበት ጋር እንጣበቃለን “ ላሉት ለሌሎቹ ትልቅ ንግግር የሚሆን ነው ፡፡

ነህምያ (10፡ 32-39)፡ በእስራኤላዊያን የመታዘዝ እና የመለየት ሂደት ለእግዚአብሄር ቤት ድጋፋቸዉን እናያለን ፤ ለእግዚአብሄር ቤት ለመስጠት በራሳቸዉ ፍላጎት ትዕዛዝ መጡ ፤ የህዝቡን ትኩረት ለመጠበቅ ይህን አደረጉ ፤ “ የአምላካችንን ቤት ከቶ አንተዉም “ ተብሎ ተፅፏል (ቁጥር 39) ፡፡ ይህ ምዕራፍ ለህዝቡ የእግዚአብሄር ፍላጎት ማጠቃለያ እንደ ሆነ ይሰማኛል ፤ የእግዚአብሄር ለህዝቡ ወደ እግዚአብሄር ቃል እንዲቀርቡ፣ ከአለማዊ ነገር ራሳቸዉን እንዲለዩ እና የእግዚአብሄር ቤት መደገፍ እንዲቀጥሉ ይናፍቃል ፡፡

በእነዚህ ቁጥሮች ላይ በተጠቀሱት የተለያዩ ስጦታዎች ላይ መመልከት እፈልጋለሁ ፡፡ ዋረን ዋይርስቤ እነዚህን ስጦታዎች በሚከተሉት መንገድ ከፋፍሏቸዋል፡

የቤተ መቅደስ ግብር (ቁጥር 32-33) ፡፡

  • በዘጸዓት መፅሀፍ እነዚህ ቀረጦች ለቤተ መቅደሱ የብር መለኪያዎችን እና ሌሎች ነገሮችን ለመስራት ጠቅመዉ ነበር ፡፡
  • በአዲስ ኪዳን እና በአሁኑ ጊዜ መስጠት ደምዎዞችንዎችን ለመከፈል ይሆናል (ሉቃ 10፡ 7) ፤ ከችግረኞች ጋር መካፈል (1ቀ0ሮ 16፡ 1-3) እና የመልካም ባላደራነትን ተግባር ያሳያል (2ቆሮ 8፡ 9) ፡፡

የእንጨት ስጦታ (ቁርባን) (ቁጥር 34) ፡፡

በነሀሱ መሰዊያ ላይ ያለዉ እሳት ሁሌ እየበራ የሚቀጥል ነበር (ዘሌ 6፡ 12-13) ፡፡

ይህን መስዋዕት ማን እንደሚያመጣ ለማየት እስራኤላዊያን እጣ ጣሉ ፡፡

የሚያስፈልግ ብዙ እንጨት ነበር !

በኩራት (ቁጥር 35-37) ፡፡

በኩራት ለእግዚአብሄር የሚሰጥ የመጀመሪያና ምርጡ ነው ፡፡

እነዚህ ስጦታዎች በመሬት (ዘጸ 23፡ 16)፣ በዛፎች (ዘሌ 19፡ 23-25) እና በወንድ ልጆች (ዘኁ 18፡ 15) የሚቤዡ ነበሩ ፡፡

እነዚህ ሁሉ ነገሮች ለእግዚአብሄር ቤት ስለ ማዋጣት ናቸው (ኤር 2፡ 3) !

የእግዚአብሄር በኩሮች እስራኤላዊያን ናቸው ፤ እራሳቸዉን የሚሰጡ ናቸው ፡፡ ቆይቶ በ 1ቆሮ (15፡ 23) ክርስቶስ ህይወቱን ለእኛ አሳልፎ የሰጠ የመጨረሻዉ በኩራት መሆኑን እናያለን ፡፡

ዛሬ ለእኛ ምን ማለት ነው ? እነዚህ ቤተ መቅደሱንና የእግዚአብሄር ቤት መርዳት የምንችልባቸዉ መንገዶች ናቸው ፡፡

እግዚአብሄር ከእያንዳንዳችን ከበኩራታችን እንድንሰጠዉ ይፈልጋል ፡፡

የቢዝነስ ኃሳብ ካላችሁ “ መጀመሪያ ምን መስጠት እንችላለን ? “

መስጠት ደስታ ይሆናል (2ቆሮ 9፡ 7) ፡፡

እንደ ተሰጠን መስጠት አለብን (ማቴ 6፡ 2-4፣ 1ቆሮ 16፡ 1-2) ፡፡

ስለ በኩራት መስጠት የምወደዉ መርህ ያላችሁን መስጠታችሁን ነው !

አስራት (ቁጥር 37-39) ፡፡

አይሁድ ለቤተ መቅደሱ አስራት ይሰጣሉ (ዘኁ 18፡ 23-32፣ ዘዳ 26፡ 11) ፡፡

መደምደሚያ

እስራኤላዊያን ለእነርሱ በተሰጣቸዉ ስራ ወደ ፊት ለመጓዝ ለእግዚአብሄር ቃል መታዘዝ ያስፈልጋቸዋል፣ ራሳቸዉን መለየት እና የእግዚአብሄር ቤት መደገፍ ያስፈልጋቸዋል ፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ወደ እግዚአብሄር ነገር አመልክተዋል አሁንም ያመለክታሉሰ ፡፡ አካላዊዉ ህንፃ ማደግ በማቆሙ ምክንያት ብቻ የእግዚአብሄር ቤት ማደግ አያቆምም ፡፡

  1. Warren Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2007), p. 686-687.

  2. Steve Diggs, Thy Principles of Godly Giving, Crosswalk.com: Family Finances; available https://www.crosswalk.com/family/finances/three-key-principles-of-godly-giving-1426486.html.

ጥያቄዎች

  1. አስተዳዳሪዎቹ፣ አለቆቹ፣ ካህናቱ እና ሌዋዊያኑ በመፈረም በማስረጃዉ ላይ ማህተማቸዉን በማስቀመጥ በፅሁፍ ስምምነት አደረጉ ፤ ይህ ስምምነት ለማን ነበር የተደረገው ? የሚያደርጓቸዉ ነገሮችስ ምን ነበሩ ? እግዚአብሄርን ለማገልገል በራሳችሁ ምን ነገሮችን ፈፅማችኋል ?
  2. በነህ (10፡ 29) “ በእግዚአብሄር ስርዓት (ሕግ) ይሄዱ ዘንድ በራሳቸዉ ላይ እርግማንና መሀላን አደረጉ “ ሲል ምን ማለቱ ነው ?
  3. በነህ (10፡ 30) መሰረት የሌሎች ጎሳዎችን ሰዎች ማግባት ስህተት ነው ? (2ቆሮ 6፡ 14፣ ቆላ 3፡ 11)
  4. ሕዝቡ ለእግዚአብሄር ቤት አገልግሎት በየአመቱ ሲሶ ገንዘብ ለመስጠት ቃል ገቡ ፤ የአንድ ሸቅል ዋጋን ሲሶም አገኙ ፤ በተለዬ ይህን ገንዘብ የተጠቀሙት ለምን ነበር ?
  5. ይህ ምዕራፍ ወደ እግዚአብሄር ቤት መምጣት ስላለባቸዉ በኩራቶች ይናገራል ፤ በኩራት የምን ጥላ ነው ? መልሳችሁን በብዙ የመፅሀፍ ቅዱስ ማጣቀሻዎች አስደግፉ
  6. በነህምያ 10 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Nehemiah 10:28–29

“The rest of the people—the priests, Levites, gatekeepers, singers, and temple servants, along with their wives, sons, and daughters, everyone who is able to understand and who has separated themselves from the surrounding peoples to obey the law of God—join with their noble brothers and commit themselves with a sworn oath to follow the law of God given through God’s servant Moses and to carefully obey all the commands, ordinances, and statutes of Yahweh our Lord.”

የእስራኤል ልጆች ወደ ያህዌ ተመለሱ በመንገዱም ለመሄድ ወሰኑ ፡፡ እነርሱም የእግዚአብሔር ልጆች ፣ የያህዌ ተከታዮች በመሆናቸው ራሳቸውን በዙሪያቸው ካሉ አህዛብ ለመለየት ቆረጡ ፡፡ በአንድ ቃል ለመግለጽ “ እግዚአብሔርን እንወደዋለን ቃሉንም እናነባለን “ አሉ ፤ ነገር ግን ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔርን ከማይከተሉት ከአህዛብ ኑሮ በተለየ መንገድ ኑሯቸውን መኖር አስፈለጋቸው ፡፡ የእስራኤል ልጆች የእግዚአብሔርን ቃል በጋብቻቸው ለመታዘዝና ለመከተል ፤ ሰንበትን ለማክበርና በበኩራታቸው የእግዚአብሔርን ቤት ለመደገፍ ማሉ ፡፡

አምላካችሁን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁ ፣ ነፍሳችሁና አሳባችሁ በእውነት ከወደዳችሁ ፣ ከዚያ ባህሪያችሁ ፣ተግባራችሁ እንድሁም ጊዜያችሁን ፣ ገንዘባችሁንና እውቀታችሁን የምታውሉበት መንገድ ይቀየራል ፡፡ እንደ አዲስ ኪዳን ክርስቲያን እምነታችሁ ስለ ተዘረዘሩ ህጎችና ደንቦች አይደለም ፤ ይልቁንም ልባችሁን በየቀኑ ለእግዚአብሔር አሳልፋችሁ የምትሰጡበትና ወደ እርሱ መልክ የሚለውጣችሁን ጸጋና ኃይል የምትቀበሉበት ጉዳይ እንጂ ፡፡ ህይወታችሁ ኢየሱስን ይመስላል ወይስ አለምን ? በአለም ከኖራችሁ ፣ አለምን ትመስላላችሁ ፡፡ ነገር ግን በክርስቶስ ስትኖሩና በመንፈስ ስትመላለሱ ብዙ ፍሬን ታፈራላችሁ ፤ እነርሱም ፡- ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ፡፡ አለማውያንም የመንፈስ ፍሬ በህይወታችሁ መገለጡን ሲያዩ ፣ ስለ አናንተ የሆነ ነገር እንደተቀየረ ያውቃሉ ፡፡ ያም ልዩነት ኢየሱስ ኃይል እየሰጣችሁ መሆኑ ነው ፡፡

“ የቀሩትም ሕዝብ፥ ካህናቱም፥ ሌዋውያኑም፥ በረኞቹም፥ መዘምራንም፥ ናታኒምም፥ ከምድርም አሕዛብ ወደ እግዚአብሔር ሕግ ራሳቸውን የለዩ ሁሉ፥ ሚስቶቻቸውም፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም፥ የሚያውቁትና የሚያስተውሉትም ሁሉ ወደ ወንድሞቻቸው ወደ ታላላቆቻቸው ተጠጉ ፤ በእግዚአብሔርም ባሪያ በሙሴ እጅ በተሰጠው በእግዚአብሔር ሕግ ይሄዱ ዘንድ፥ የጌታችንንም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ ፍርዱንም ሥርዓቱንም ይጠብቁና ያደርጉ ዘንድ እርግማንና መሐላውን አደረጉ ። “

- ነህምያ 10፡28-29

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ዮሐንስ 15:4—“ በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም ። “
  • 2ኛ ቆሮንቶስ 3:18 — “ እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን ። “
  • ፊልጵስዩስ 1:27—“ ይሁን እንጂ፥ መጥቼ ባያችሁ ወይም ብርቅ፥ በአንድ ልብ ስለ ወንጌል ሃይማኖት አብራችሁ እየተጋደላችሁ፥ በአንድ መንፈስ እንድትቆሙ ስለ ኑሮአችሁ እሰማ ዘንድ፥ ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ ። “