The Grace of God
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Builder Nehemiah 9 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በብሉይ ኪዳን የታሪክ መጽሀፍትን ለማጥናት ለምን ብዙ ጊዜ እናጠፋለን ? ጆርጅ ሳንታያና “ የቀድሞዉን የማያስታዉሱት መልሰዉ ለማኖር እንደነቀፉ “ ተናግሯል ፤ ስለዚህም ከቀድሞዉ ትዝታዎቻችን ካልተማርን እንዴት ልናድግ እንችላለን ? ተበላሽቶ(ፈርሶ) የነበረዉን የቀድሞ ቤተ መቅደስ ታስታዉሱታላችሁ፣ ታሪኩን = የሱ ታሪክ ? በዚህ ጊዜ ዘሩባቤልና ኢያሱ ቤተ መቅደሱን መልሶ በመገንባት ሕዝቡን ሲመሩ ነህምያና ዕዝራ ደግሞ ቅጥሮቿን እና ከተማዋን መልሶ በመገንባት ሕዝቡን መሩ ፡፡ ሁሉም ነገር በስፍራዉ ሲሆን ዕዝራ ለሕዝቡ የእግዚአብሄር ቃል ማንበብ ጀመረ ፤ በታሪኩም ላይ እየቀጠሉ ነበር ፡፡ በዕዝራ፣ በነህምያና በዳንኤል መፅሀፍት ላይ የእስራኤል ብሄራዊ ፀሎት ይሆናሉ ተብለዉ የታሰቡ ሰዎስት ዋና ፀሎቶች አሉ ፤ በዕዝራ 9 ላይ ለሕዝቡ የዕዝራን ፀሎት አንብበናል እናም ዛሬ በነህምያ 9 ለህዝቡ የነህምያን ፀሎት እናነበዋለን ፡፡ በዳንኤል 9 ላይ የዳንኤልን ብሄራዊ ፀሎት እናነባለን ፡፡ ከእነዚህ ፀሎቶች እያንዳንዳቸዉ በ 2ዜና መዋዕል (7፡ 14) መሰረት መሆኑን መረዳት አስፈላጊ ነው ፡፡
ትምህርት
ነህምያ (9፡ 1-6)፡ዋረን ዋይርስቤ እነዘህን ጥቅሶች እንደ “ እግዚአብሄር ታላቅነት “ ጠቅሷቸዋል ፡፡ እስራኤላዊያን እንደተሰበሰቡ እየፆሙ፣ ማቅ ለብሰዉ እና በላያቸዉም ላይ ትቢያን ነስንሰዉ ነበር (ቁጥር 1) ፡፡ እንደ ዮሐንስማክአርቱር አገላለፅ ስለ ነበሩበት ስፍራ በእዉነት አዝነዉ ስለ ነበር ለኃጢዓታቸዉ ማሳያ እያሳደጉ (እየጎለጎሉ/እየፈለጉ) ነበር ፡፡ ከያዕቆብ (ከእስራኤል) ዘር የነበሩት ራሳቸዉን ከሌሎች ሕዝቦች ለዩ (ቁጥር 2) ፡፡ መጀመሪያ ዕዝራ የእግዚአብሄር ቃል ለእነርሱ ካነበበላቸዉ ጀምሮ አስራ ሰዎስት አመታት ነበር እናም አሁን እነዚህ ሰዎች በነህምያ ስር የሌሎች ህዝቦችን አግብተዉ የነበሩትን ኃጢዓታቸዉን እንዲያዉቁ እና ከሌሎች ሕዝቦች ሚስቶቻቸዉ ራሳቸዉን እንዲለዩ ጠራቸው ፡፡ በእግዚአብሄር ታላቅነት መገኘት ኃጢዓታቸዉን ተናዘዙ ፡፡ የቀኑን አንድ አራተኛ - ሰዎስት ሰዓቱን የእግዚአብሄር ቃል አነበቡ ከዚያም ሌላዉን ሰዎስት ሰዓት ኃጢዓታቸዉን በመናዘዝ እግዚአብሄርን አመለኩ (ቁጥር 3) ፡፡ በ 1ጢሞ (4፡ 13) ጳዉሎስ አማኞችን በጉባኤ ንባብ ላይ እንዲያተኩሩ ተናግሯል ፡፡ ሌዋዊያን ከፍ ባለዉ ስፍራ ላይ በመቆም እስራኤልን በመነሳት እግዚአብሄርን እንዲያመሰግኑ አበረታቱዓቸው (ቁጥር 4-5) ፡፡ በፀሎታቸው በእግዚአብሄር ላይ እንደ ፈጣሪ አተኮሩ (ቁጥር 6) ፤ እግዚአብሄር የማይነፃፀር እንደ ነበርና በእዉነት ሁሉንም ነገር የፈጠረ እንደ ነበር አወቁ ፡፡
ነህምያ (9፡ 7-12)፡ እንደ ዋይርስቤ አስተያየት እነዚህ ቁጥሮች ከእግዚአብሄር ታላቅነት ወደ እግዚአብሄር መልካምነት(ርህራሄ) ይዞራሉ ፡፡ በርህራሄዉ እግዚአብሄር አብርሃምን በመምረጥ (ቁጥር 7) የከነዓናዊያንን ምድር ሰጠው (ቁጥር 8) በዚህ ምዕራፍ 16 ጊዜ በእግዚአብሄር ቸርነት ምክንያት “ ሰጠ “ የሚለዉን ቃል አስራ ስድስት ጊዜ እናያለን ፡፡ ከአብርሃም ጋር የነበረዉ ኪዳን በእግዚአብሄር መታመን ላይ የተመሰረተ ነበር ፤ እግዚአብሄር ይህን ምድር ለአብርሃምና ለዘሩ ቃል ገባለት (ዘፍ 15፡ 18፣ ዘጸ 3፡ 8፣ 33፡ 2) ፡፡ በነህምያ 9 ሕዝቡ እግዚአብሄር አድርጎላቸዉ በነበረዉ ነገር አከበሩት ፤ ከግብፅ ሲያወጣቸዉ ለአባቶቻቸዉ አድርጎት የነበረዉን አስታወሱ (ቁጥር 9-12) ፡፡ በዚህ ሁሉ ድርርቦች- በአፈጣጠር፣ በኪዳነ፣ በመዉጣት፣ በቀይ ባህር - ከተማቸዉን መልሶ ወደ መገንባት በመድረስ ግባቸዉን እስኪያገኙ ድረስ መገንባታቸዉን ቀጠሉ ፡፡ እነዚህ ክስተቶች ለእነርሱ የእግዚአብሄርን ርህራሄ (ቸርነት) ገልጠዋል ፡፡ ሕዝቡ በዚህ ሁሉ የእግዚአብሄር ታሪክ ማወቅ ወደ ሚያስፈልጋቸዉ ቤተ መቅደሱ መልሶ ወደ ተሰራበት ስፍራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰዉ መጡ ፡፡
ነህምያ (9፡ 13-21)፡ እነዚህ ቁጥሮች በሲና ተራራ ላይ የተከሰቱትን ክስተቶች ገልጧል ፡፡ እግዚአብሄር መልካ ትዕዛዛትን (ቁጥር 13)፣ ሰንበትን (ቁጥር 14) በመስጠት በሙሴ በኩል ተናገራቸው ፡፡ እንጀራና ዉሃን በመስጠት ሄደዉ የሰጣቸዉን ምድር እንዲወርሱ ነገራቸው (ቁጥር 15) ፤ ነገር ግን አባቶቻቸዉ አንገተ ደንዳና በመሆን የእግዚአብሄር ትዕዛዝ ለመስማት ወይም ድንቁን ለማስታወስ እምቢ አሉ (ቁጥር 16-17) ፤ ይልቁንም ወደ ግብፅ ባርነት መልሶ የሚወስዳቸዉ መሪን ሾሙ (ቁጥር 17) ፡፡ ነህምያ የሱ ዘመን ሕዝብ የአባቶቻቸዉን ስህተት በመድገም አደጋ እንደገጠማቸዉ ያውቃል ፤ ነገር ግን ነህምያ እነርሱን ይቅር በማለት የእግዚአብሄር ርህራሄ እንደ ገና ጠራ ምክንያቱም ጣዖት በመስራት የወርቅ ጥጃ በማለኩ ጊዜ እንኳን ትቷቸዉ ስላልነበር (ቁጥር 18-19) ፤ ይልቁንም እግዚአብሄር እንዲያዛቸዉ መንፈሱን ላከላቸዉ መናን እና ዉሃንም አልከለከላቸውም (ቁጥር 20) ፡፡ እግዚአብሄር ለ40 አመታት በምድረበዳ መገባቸው (ቁጥር 21) ፤ ነህምያ ደግሞ “ ልብሳቸዉ አላረጀም እግራቸዉም አላበጠም “ በተናገረ ጊዜ በዘዳ (8፡ 4) ሙሴ ፅፎት የነበረዉን ደግሞ ተናገረው ፡፡
ነህምያ (9፡ 22-25)፡ እነዚህ ቁጥሮች በነዌን ልጅ በኢያሱ ስር ወደ ተስፋይቱ ምድር የእስራኤልን መግባት መልሰዉ አዉርተዋል ፡፡ እግዚአብሄር ምድሪቱን ሰጣቸው (ቁጥር 22) ዘራቸዉንም አበዛ (ቁጥር 23) ፤ እግዚአብሄር ጠላቶቻቸዉንም ዝም አሰኘ(አዋረዳቸዉ) (ቁጥር 24) ፡፡ አዋረደ የሚለዉ ቃል በዘጸ (15፡ 3) አዲሱ ትርጉም ያለዉን እዉነት “ እግዚአብሄር ተዋጊ ነዉ ስሙም እግዚአብሄር ነው “ የሚለዉን በሀሳብ ዉስጥ ያመጣል ፡፡
ነህምያ (9፡ 26-30)፡ እነዚህ ቁጥሮች ከመሳፍንት ዘመን እስከ ባቢሎን የምርኮ ጊዜ ይገልፃሉ ፡፡ ባለመታዘዝ በእግዚአብሄር ላይ አመፁ ፤ ነቢያቶቹንም ገደሉ (ቁጥር 26) ፤ እግዚአብሄርም ወደ እርሱ እስኪጮኹ ድረስ ለጠላቶቻቸዉ አሳልፎ ሰጣቸው (ቁጥር 27) ፤ ይህ የባህሪያቸዉ ሂደት ሆነ (ቁጥር 28) ፡፡
ነህምያ (9፡ 31-38)፡ የእግዚአብሄርን ታላቅነት እና የእግዚአብሄርን ርህራሄ ከተመለከተ በኋላ ነህምያ የእግዚአብሄር ፀጋ እንዲቀምሱ ጠራቸው ፤ አሳሳባቸዉም ምክንያቱም እግዚአብሄር ደግ እና ሩህሩህ ስለሆነ እስራኤልን ስላላጠፋና ስላልተወ (ቁጥር 31) ፡፡ በቁጥር 32 “ አሁንም “ የሚለዉ ቃል ዕዝራ የእግዚአብሄር ቃል ሲያነብ ታላቅ መነቃቃት እንደሆነ ያሳያል ፡፡ መነቃቃትን እንደ ቀመሱ ነህምያ የተከበረ ኪዳኑን የጠበቀዉን የእግዚአብሄርን ታላቅነቱን፣ ሁሉን ቻይነቱንና አስፈሪነቱን እንዳስታወሱ አብራርቷል ፡፡ ለእነርሱ የሆነላቸዉን እና አባቶቻቸዉ ያቀለሉትን መዉሰድ አልቻሉም ፤ ማክአርቱር እንዳመለከተው የነህምያ ፀሎት ወደ አለመታመናቸዉ የአሁን መናዘዝ ቀይሯቸዋል ፡፡ እስራኤላዊያን ቀምሰዉት በነበረዉ ሁሉም ነገር ታሪክ ዉስጥ በመቀጠል ከአባቶቻቸዉ የተሸለ ማንም እንደሌለ አስተዋሉ (አወቁ) (ቁጥር 35-36) ፤ በአለመታመናቸዉ ምክንያት እዚህ ጋር ደርሰዉ እንደ ነበር አዉቀዋል ፡፡ በቁጥር 38 ለሙሴ ኪዳን የታደሰ ቃል መግባት አደረጉ ፤ በሚታየዉ በዚህ ሁሉ እስራኤል በሁሉም ነበር ፡፡ እዚያ በኑሮአቸዉ ኃጢዓታቸዉን መናዘዝ ላይ እና ከእግዚአብሄር ጋር የሚያያይዝ ስምምነት ማድረጋቸዉ ላይ እንዲደርሱ እግዚአብሄር አድርጎላቸዉ የነበረውን አስተዋሉ ፡፡ ማክአርቱር እንዳለው ተመልሰዉ መሄድ ስላልፈለጉ እግዚአብሄር ለማክበር እና የአባቶቻቸዉን ኃጢዓት ንስሀ ለመግባት ስጦታንና ቃል ኪዳንን አደረጉ ፡፡ ለዉጥን ለማየት ፈለጉ ፡፡
መደምደሚያ
የህይወታችሁ አካል እንዲሆን ከፈቀዳችሁለት የእግዚአብሄር ቃል ለእናንተም ተመሳሳይ ነገር ያደርጋል ፡፡ እግዚአብሄር ምን ያክል ትልቅ እንደሆነ፣ ታላቅ እንደሆነ፣ እንዴት መልካም እንደሆነ እና የእግዚአብሄር ፀጋ አሁንም በኑሮአችን ላይ እንደሆነ የሚያስተዉሉትን ጥቂቶችን እየተመለከተ ስለሆነ በአገልግሎታችን መጓዝ (መቀጠል) እንችላለን ፡፡
Warren Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2007), p. 778.
Wiersbe, p. 778.
Wiersbe, p. 778.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 547.
MacArthur, p. 547.
Wiersbe, p. 778.
Wiersbe, p. 778.
MacArthur, p. 548.
MacArthur, p. 548-549.
ጥያቄዎች
-
እስራኤላዊያን በታላቅ ደስታ በተሞሉበት ስፍራ የዳስ በዓልን ጨርሰዉ ነበር ፤ በቁጥር 1 ሕዝቡ ይፆም እና ማቅ ልብስ ለብሰዉ የነበሩት ለምን ነበር ?
-
እስራኤላዊያን በፀሎታቸው መሰረት ለእግዚአብሄር ታላቅ ርህራሄ፣ ታላቅ ምህረት እና ታላቅ ቸርነት እንዴት ነበር መልሰዉ የነበሩት (ነህ 9፡ 18፣ 26) ? አመፃቸው በኃይል በምን መራቸው ? (ነህ 9፡ 37)
-
ለእስራኤላዊያን የራሳቸዉን ኃጢዓት ብቻ ሳይሆን የአባቶቻቸዉን/የአያቶቻቸዉን ኃጢዓት መናዘዝ ለምን ይጠቅማቸዉ ነበር ? ለመጨረሻ ግዜ ራሳችሁን በመፈተሸ እግዚአብሄር የገለጠላችሁን የተናዘዛችሁት መቼ ነበር ? (2ቆሮ 13፡ 5)
-
በቁጥር 6 የእግዚአብሄር ታላቅነት በምን አራት መንገድ ተገለፀ ?
-
ቁጥር 33 ለንስኃ እንዴት ታላቅ ምሳሌ ነው ? በተጨማሪ ይህ ቁጥር የእግዚአብሄርን ፅድቅ እንዴት ያረጋግጣል ? በአሁኑ ጊዜ አማኞች እንዴት ኃጢዓታቸዉን ይናዘዛሉ ? (ያዕ 5፡ 16፣ 1ዮሐ 1፡ 9)
-
በነህምያ 9 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Nehemiah 9:29–31
“You warned them to turn back to Your law, but they acted arrogantly and would not obey Your commands. They sinned against Your ordinances, which a person will live by if he does them. They stubbornly resisted, stiffened their necks, and would not obey. You were patient with them for many years, and Your Spirit warned them through Your prophets, but they would not listen. Therefore, You handed them over to the surrounding peoples. However, in Your abundant compassion, You did not destroy them or abandon them, for You are a gracious and compassionate God.”
የእስራኤል ልጆች ስለ ኃጢአታቸውና ስለ መንፈሳዊ ነገራቸው ጾመው፥ ማቅም ለብሰው፥ በላያቸውም ትቢያ ነስንሰው ተከማቹ ። ከዚያም ጸለዩ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ ፡፡ ለአብርሃም ስለ ገባው ኪዳን የእግዚአብሔርን ታማኝነት በማስታወስ ጊዜን አሳለፉ ፡፡ አለመታዘዛቸውን ተናዘዙ የእግዚአብሔርንም ይቅር ባይነት አወደሱ ፡፡ እርሱም ታደጋቸው ነጻም አወጣቸው ፡፡ እርሱ የተወደደ ኪዳኑን ስለጠበቀ ፈጽሞ አልተዋቸውም ፡፡ እንደ ቅሬታ እግዚአብሔርን ለመከተል ጽኑ ስምምነትን አደረጉ ፡፡
እግዚአብሔር ፈጽሞ አይጥላችሁም ፣ ፈጽሞም አይተዋችሁም ፡፡ እግዚአብሔር ነጻ አውጪና ታዳጊያችሁ ነው ፡፡ እርሱ ሩህሩህ አምላክ ነው ፡፡ በጭንቀት ስትጮኹ የሰማችኋል ፡፡ በሆነ ሰው እንደተተዋችሁ ይሰማችሁ ይሆናል ማለትም ፡- በወላጆች ፣ በውንድምና በእህት ፣ በጓደኛ ፣ በእግዚአብሔርም ጭምር ፡፡ ነገር ግን እንደሌሎቹ ሳይሆን እውነቱ እግዚብሔር ፈጽሞ አይተዋችሁም ፡፡ ሁልጊዜም ከእናንተ ጋር እንደሚሆን ተናግሯል ፤ ከታላቅ ፍቅሩም የሚለያችሁ ምንም ነገር የለም ፡፡ ምንም ነገር ፡፡ የእግዚአብሔር ፍቅር ነጻ ስጦታ ነው ፤ የምትቀበሉትም “ አዎ ጌታ ሆይ ጸጋህን እቀበላለሁ “ በማለት ነው ፡፡ ጽኑ ስምምነት አያስፈልግም ፡፡ ዛሬ የእርሱን ነጻ ስጦታ ተቀበሉ ፤ ቃሉንም እመኑ ፡፡
“ወደ ሕግህም ትመልሳቸው ዘንድ አስመሰከርህባቸው፤ ነገር ግን ታበዩ፥ ትእዛዝህንም አልሰሙም፥ ሰውም ባደረገው ጊዜ በሕይወት የሚኖርበትን ፍርድህን ተላለፉ፤ ትከሻቸውንም ሰጡ፥ አንገታቸውን አደነደኑ፥ አልሰሙምም ። ነገር ግን ብዙ ዓመታት ታገሥሃቸው፥ በነቢያትህም እጅ በመንፈስህ መሰከርህባቸው፤ አላደመጡም፥ ስለዚህም በምድር አሕዛብ እጅ አሳልፈህ ሰጠሃቸው ። ነገር ግን አንተ ቸርና መሐሪ አምላክ ነህና በምሕረትህ ብዛት ፈጽመህ አላጠፋሃቸውም፥ አልተውሃቸውምም ። “
- ነህምያ 9፡29-31
ተጨማሪ ጥቅስ
ዘዳግም 31:8—“ በፊትህም የሚሄድ እርሱ እግዚአብሔር ነው ከአንተ ጋር ይሆናል፥ አይጥልህም፥ አይተውህም አትፍራ፥ አትደንግጥ አለው ። “
ሮሜ 8:38–39—“ ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ ። “
ኤፌሶን 2:8–9—“ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም ፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።