Public Reading of the Law, Festival of Booths Observed
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Builder Nehemiah 7-8 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ነህምያ 7 የተሰደዱትን ሰዎች ዝርዝር ይይዛል ፡፡ በቁጥር 1 ቅጥሩ መልሶ ተገነባ፣ ሳንቃዎቹ ተገጠሙ በተጨማሪም በር ጠባቂዎች፣ ዘማሪዎች እና ሌዋዊያን በተግባራቸዉ ተሾሙ ፡፡ ስራዉ አለቀ ሁሉም ሰዉ በስፍራዉ ነበር ፡፡ በቁጥር 7 መጀመሪያ ላይ የእስራኤል ስደተኞች ተዘርዝረዋል ፤ በቁጥር 39 መጀመሪያ ላይ ካህናቱ ተካተዋል ፤ በቁጥር 43 መጀመሪያ ላይ ሌዋዊያን ተካተዋል ፤ በቁጥር 44 መጀመሪያ ላይ መዘምራን ተካተዋል ከዚያም በቁጥር 45 በር ጠባቂዎቹ ተካትተዋል ፡፡ በቁጥር 46 የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች ተዘርዝረዋል ፤ በቁጥር 57 ላይ የሰለሞን አገልጋዮች ዘሮቻቸዉ እንኳን ተዘርዝረዋል ፡፡ በመሰረቱ እግዚአብሄር መታመኑን በፍፁም እንደ ማይረሳ ገለፀ እናም እዚህ ላይ በመታመኑ ከስደት ተመልሰዉ የመጡት ከሚጫዎቱት ተጋባራቸዉ ጋር ተዘረዘሩ ፡፡ ሁሉም ነገር በቦታዊ እንዳለ የመፅሀፍ ቅዱስ ጉባኤ የማዘጋጀት ጊዜዉ ነበር ፡፡ ዋረን ዋይርስቤ እስራኤል በእግዚአብሄር ቃል ወደ ደስታ መማር ያስፈለገው “ የመፅሀፍ ህዝብ “ እንደ ነበር ተናግሯል ፡፡ ነህምያ አሁን ነፃ ስለወጡ ከስደት የተመለሱት በእግዚአብሄር ላይ እንዲያተኩሩ ፈለገ ፤ መዝ (1፡ 2-3) ይህን ሀሳብ ያብራራዋል ፡፡ በሀሳቡ በዚህ አላማ ነህምያ በምድሪቱ ምርጥ መምህር የነበረዉን ዕዝራን ጠራው ፡፡
ትምህርት
ነህምያ (8፡ 1)፡ ህዝቡ በዉሃ በር ፊት ባለዉ አደባባይ ላይ ተሰበሰቡ ፡፡ ከአስራ ሰዎስት አመት በፊት ዕዝራ ወደ እስራኤል መልሶት የነበረዉን የሙሴን የህግ መፅሀፍት እንዲያመጣው ዕዝራን ጠየቁት ፤ አሁን ከዕዝራ የግል የህግ ጥናት ወደ ጉባኤ ጥናት እየተቀየሩ ነበር ፡፡ ዋይርስቤ ይህ ምዕራፍ ለእግዚአብሄር ቃል ሰዎስት ምላሾችን እንደ ሚገልፅ ተናግሯል ፤ በቁጥር 1-8 የእግዚአብሄርን ቃል መረዳት እንዳለብን ያብራራል ፡፡
በዮሐ (15፡ 3) ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ከሚነግራቸዉ ቃል የተነሳ እንደ ነፁ ነገራቸው ፡፡ ዕዝራ በዉሃ በር አጠገብ እንደ ቆሙ ለሕዝቡ የእግዚአብሄርን ቃል እያነበበላቸዉ ነበር ፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል መስማት በሰዎች ላይ የማንፃትና የማደስ ለዉጥ አለው ፤ በነህምያ ይህ ክስተት ስለ ኢየሱስ ስናወራ የሚሆነዉ ክስተት ጥላ ነው ፡፡ ኤፌ (5፡ 26) ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያንን በቃሉ በዉሃ አጥቦ በማንፃት ቅዱስ ያደርጋታል ይላል ፤ የእግዚአብሄር ቃል በዕዝራና በነህምያ ጊዜ ተመልሶ ወደ ቀድሞዉ ቦታ ሲመለስ እስራኤላዊያን በእግዚአብሄር ቃል የታጠቡ ነበሩ ፡፡ ወደ እግዚአብሄር ቃል ስንቆፍር መንፃትን እያገኘን ነው ፤ ቃሉ ሲለቀቅ ኃይለኛና የሚያነፃ ነው ፤ ስንረዳዉ የሚያድሰን ነው ፡፡ በዮሐ (7፡ 37) ኢየሱስም “ ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ ! “ ብሎ ተናገረ ፤ ኢየሱስ ቃል ነው (ዮሐ 1፡ 1-4፣ 14) ፤ ኢየሱስ “ በእኔ የሚያምን…የሕይወት ዉኃ ወንዝ ይፈልቃልና “ (ዮሐ 7፡ 38) ብሎ ተስፋን ሰጠ ፡፡ ወደ ኢየሱስ ስንመጣ በእግዚአብሄር መንፈስ የታደስን መሆን እንችላለን ፡፡
ነህምያ (8፡ 2-8)፡ ዕዝራም የህጉን መፅሀፍ በማምጣት ከማለዳ እስከ ቀትር ድረስ ሕዝቡ በትኩረት እያዳመጡት አነበበው ፤ የኔልሰን ማብራሪያ እንደሚናገረው ስድስት ሰዓት ነው ፡፡ ዕዝራ ከፍ ባለ የእንጨት መረባርብ ላይ በመቆም በህዝቡ ሙሉ እይታ ፊት መፅሀፉን ከፈተው ፡፡ ሕዝቡም በመቆም እጆቻቸዉን በማንሳት በፊቱ በግንባራቸዉ በመደፋት እግዚአብሄርን አመለኩ ፤ በእዉነትም የእግዚአብሄር ቃል አከበሩ ፡፡ 1ጢሞ (4፡ 13) ክርስቶስ ተመልሶ እስኪመጣ ድረስ ለጉባኤ ንባብ፣ ምክርና የእግዚአብሄር ቃል ትምህርት ትኩረት እንድንሰጥ ይነግረናል ፡፡ ለእግዚአብሄር ቃል አክብሮት ስንሰጥ መረዳታችን ያድጋል ፡፡ ቃሉ እየተነበበ ሌዋዊያን ለህዝቡ ህጉን ስለሚያብራሩ (ቁጥር 7) ህዝቡ መረዳት ይችላል (ቁጥር 8) ፡፡
ነህምያ (8፡ 9-12)፡ ቃሉን ከመረዳት በተጨማሪ ዋይርስቤ በቃሉ ደስተኞ እንደምንሆን ይናገራል ፡፡ ነህምያና ዕዝራ ሕዝቡን እንዳያለቅሱ ለምን ይነግሯቸዋል ? እንዲጠብቁት እግዚአብሄር የጠየቃቸዉን ስርዓት ጠብቀዉት እንደማያዉቁ ወይም እግዚአብሄርን አምልከዉት እንደ ማያዉቁት ስለተረዱ እያለቀሱ ነበር ፤ ነገር ግን ነህምያ ሕዝቡን በሀዘን ፋንታ እንዲያከብሩ አሳሰባቸው ፡፡ ይደሰታሉ ምክንያቱም ጥንካሬአቸዉ ከእግዚአብሄር ስለሚመጣ ፤ የእግዚአብሄርን መንቀሳቀስ እያገኙት ስለ ነበር ነህምያ በዚህ እንዲደሰቱ ፈለገ ፡፡ ሕዝቡ የእግዚአብሄርን ቃል መረዳታቸዉ ታላቅ በዓል ነበር የሆነላቸው ፡፡ ኤርምያስ የእግዚአብሄር ቃል ደስታና ሀሰቴ አመጣልኝ ብሏል (ኤር 15፡ 16) ፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ብቸኝነትንና ድብርትን እንድንዋጋ ሊረዳን ኃይል አለው ፡፡ መዝ (19፡ 8) የእግዚአብሄር ቃል ልብን ደስተኛ እንዲሁም ደግሞ አይንን ብሩህ ያደርጋል ይላል ፡፡ በቃሉ ስንሆን ልባችን ደስተኛ ነው ፡፡ መዝ (119፡ 162) በእግዚአብሄር ተስፋ ላይ ሀሴት እንድናደርግ ያበረታታናል ፡፡
ነህምያ (8፡ 13-18)፡ በመረዳት በቃሉ ሀሴት ከማድረግ በተጨማሪ ዋይርስቤ ልናከብረዉ እንደሚያስፈልገን ተናግሯል ፡፡ በቀጣዩም ቀን የህጉን ቃል ለማጥናት መሰብሰባቸዉን ቀጠሉ ፡፡ እግዚአብሄር ሙሴን በበዓሉ ጊዜ እስራኤል በዳሶቹ ዉስጥ እንደሚያድር (ዘሌዋዉያን 23) አዝዞት የነበረዉን ትዕዛዝ በፈለጉ ጊዜ ዳሶችን ለመስራት ከቅጠላም ዛፎች ቅርንጫፎችን ለመሰብሰብ ወደ ሀገሪቱ ተራራ ሄዱ ፤ የእግዚአብሄር ቃል ሰራተኞች(አድራጊዎች) እንደሚሆኑ ስለተረዱ ሄደዉ ቅርንጫፎችን በመሰብሰብ ለራሳቸዉ ዳሶችን ሰሩ ፡፡ ከኢያሱ ዘመን ጀምሮ እስራኤል ልክ እንደዚህ አክብሮ አያዉቅም ነበር ፡፡ ሁሉንም ቀን የህጉን መፅሀፍ ከሚያነበው ከዕዝራ ጋር በታላቅ ደስታ በዓሉን ለሰባት ቀን አከበሩ ፡፡ እዉነተኛ መነቃቃት ስሜታችን ላይ ተፅዕኖ በማምጣት ወደ ድርጊት በሚመራዉ ወደ እግዚአብሄር ቃል መቆፈር ላይ ያዉጠነጠነ (ያተኮረ) ነው ፡፡ በማቴ (28፡ 18-20) ኢየሱስ ተከታዮቹን “ እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው “ ብሎ አዘዛቸው ፡፡ ታላቁን ተልዕኮ እስከምናደርግ ድረስና በእግዚአብሄር ቃል ላይ እስከ ምንቀሳቀስ ድረስ እዉነተኛ መነቃቃት አናይም ፡፡ የስነ መለኮት ት/ቤት ወይም ት/ቤት አያስፈልገን ይሆናል የእግዚአብሄርን ቃል በመረዳት ብቻ በሚያደርገዉ ሀሴት በማድረግ በትክክል ልናከብረዉ እንችላለን ፡፡ ያዕ (1፡ 22) የቃሉ አድራጊዎች እንድንሆን እንጂ ሰሚዎች ብቻ እንዳልሆንን ይነግረናል ፡፡
መደምደሚያ
የእግዚአብሄርን እዉነተኛ መንቀሳቀስ (መገኘት) ለማየት ከፈለግን የቃሉ አድራጊዎች መሆን አለብን ፤ ማቴዎስ 28 በማካተት ሌሎች ነገሮችንም ሊያካትት ይችላል ፡፡ በተረዳነዉ ስናደርግ (ስንሰራ) በትክክል መነቃቃትን ማየት እንችላለን ፡፡
Warren Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2007), p. 775.
Wiersbe, p. 775.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville, TN: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 594.
Wiersbe, p.775
Wiersbe, p.775
ጥያቄዎች
-
ጠባቂ (ዘበኛ) የሚለዉ ትርጓሜዉ ምንድን ነው ? ነህምያ ለበሮቹ ለምን ጥበቃዎችን አስቀመጠ(ሾመ) ? ሌላ የት ላይ ነበር ጥበቃዎች ተጠቅሞ የነበረው ? (ነህ 6፡ 17)
-
የተወሰነዉ ሕዝብ ቡድን የካህናት ቤተሰብ ከነበሩ እንዴት ወሰኑ (ነህ 7፡ 64-65) ? ይህ ሌላ የት ላይ ጥቅም ላይ ዉሎ ነበር (ተጠቅሞ ነበር) ? (ዘጸ 28፡ 30፣ ዘኁ 27፡ 21)
-
ሕዝቡ ለምን የዳስ በዓልን አከበረ (ነህ 8፡ 14) ? ለበዓሉ እንዴት ፀለዩ ? በበዓሉ ጊዜ ምን አደረጉ ?
-
በነህምያ (7-8) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Nehemiah 8:5–6
“Ezra opened the book in full view of all the people, since he was elevated above everyone. As he opened it, all the people stood up. Ezra praised the LORD, the great God, and with their hands uplifted all the people said, ‘Amen, Amen!’ Then they bowed down and worshiped the LORD with their faces to the ground.”
ነህምያ ቅጥሩን እንደገና ከሰራ በኋላ ህዝቡን በአንድነት ሰበሰበ እናም እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን የሰጠውን የሙሴን ህግ መጽሀፍ ከፈተ ፡፡ ህዝቡም ተቀምጠው ቃሉ ሲነበብ አደመጡ ፡፡ ህዝቡም መረዳት እንድችሉ የተወሰኑ ሌዋውያን ቃሉን ይተረጉሙና ያብራሩላቸው ነበር ፡፡ ነህምያም ከእግዚአብሔር ቃል የተማሩትን ህዝብ ሁሉ እንድደሰቱ ነገራቸው ፡፡ በርግጥም የእግዚአብሔር ደስታ ኃይላቸው ነበር ! ይህ ደስታ ህዝቡ ቃሉን እንድሰሙ ብቻ አልነበረም ያነሳሳቸው ነገር ግን ለቃሉ እንድታዘዙም ጭምር እንጅ ፡፡
ለምን ይሆን የእግዚአብሔርን ቃል ለመግለጥ ደግሞም እንድሁ ለማንበብ ከባድ የሆነው ? በእርሱ ትመራለህ ፤ በመጽሀፍ መደርደሪያ ላይ ተቀምጦ ታየዋለህ ፤ በሻንጣህም ቀኑን ሙሉ አዝለኸው ትውላለህ ይህ ብቻ ሳይሆን በስልክህም ጭምር አለህ ……. ነገር ግን ትታወካለህ ፡፡ ልትገልጠውና ልታነበው ቸል ትላለህ ፡፡ ዛሬ የእግዚአብሔርን ቃል ግልጥና አንድ ወይም ሁለት ክፍል አንብብ ፡፡ እስራኤላውያን ቃሉን በማንበብ በደስታ በርትተው እንድሁም ቃሉ ለተግባር አነሳስቷቸው ነበር ፡፡ ውድቀት ፣ ብቸኝነት ፣ ድንጋጤ ወይም ምሪት እንደሚያስፈልግህ ከተሰማህ የእግዚአብሔርን ቃል ግለጥ ፡፡ የእግዚአብሔር እውነት በልብህ እንድገባ ፍቀድ ፡፡ የእግዚአብሔር ደስታ ኃይልህ ይሆናል !
“ ዕዝራም በሕዝቡ ሁሉ ላይ ከፍ ብሎ ሕዝቡ ሁሉ እያዩ መጽሐፉን ገለጠ፤ በገለጠውም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ቆሙ ። ዕዝራም ታላቁን አምላክ እግዚአብሔርን ባረከ ሕዝቡም ሁሉ እጃቸውን እየዘረጉ፦ አሜን፥ አሜን ብለው መለሱ። ራሳቸውንም አዘነበሉ፥ በግምባራቸውም ተደፍተው ለእግዚአብሔር ሰገዱ ። “
- ነህምያ 8፡5-6
ተጨማሪ ጥቀስ
ነህምያ 8:10 — “ እርሱም፦ ሂዱ፥ የሰባውንም ብሉ፥ ጣፋጩንም ጠጡ፥ ለእነዚያም ላልተዘጋጀላቸው እድል ፈንታቸውን ስደዱ፤ ዛሬ ለጌታችን የተቀደሰ ቀን ነው፤ የእግዚአብሔርም ደስታ ኃይላችሁ ነውና አትዘኑ አላቸው ። “
መዝሙር 19:8 — “ የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው፥ ልብንም ደስ ያሰኛል፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፥ ዓይንንም ያበራል ። “
ኤርምያስ15:16 — “ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።