Experiencing Opposition
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Builder Nehemiah 5-6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
እንድታደርጉት እግዚአብሄር የጠራችሁን ስታደርጉት ተቃዉሞ ይደርስባችኋል ፡፡ ኢየሱስ ስንከተለዉ መስዋዕትነት እንደሚገጥመን ተናግሯል ፤ ስንከተለዉ ሰዎች ስለ እኛ ሀሰት ነገር እንደሚናገሩብን ኢየሱስ ተናግሯል ፡፡ ዋረንዋይርስቤ “ በተሰጠ በነህምያ መሪነት ስር ሕዝቡ የቅጥሮቹን መልሶ መገንባት ጨረሱ ፤ አሁን ለመስራት የበሮቹ መታደስ እና በቅጥሮቹ ዉስጥ የነበረዉን ምህበረሰብ ማጠንከር እንደ ነበር የቀረው “ ተመልክቷል (ተናግሯል) ፡፡
ሀርይ ትሩማን ፋምወስልይ “ ሙቀቱን መቋቋም ካልቻልክ ከኩሽና ትወጣለህ “ ይልላ ፡፡ ጠላት ሁልጊዜ በመሪዎች ላይ ተቃዉሞን ይልካል ፤ በዚህ ምዕራፍ ስራዉ እየተጠናቀቀ እንዳለ ተቃዉሞ መጣ ፡፡
ትምህርት
ነህምያ (6፡ 1-4)፡ ሳንቃዎቹ በበሮቹ ላይ እስካልተደረጉ ድረስ በቅጥሩ ላይ አሁንም ትንሽ ክፍተቶች ነበሩ ፤ ነገር ግን ጠላቶቻቸዉ ያን አያዉቁትም ፡፡ ቅጥሩ እያለቀ እንደ ነበር ብቻ ስለሚያዉቁ አንዴ ለመጨረሻ ጊዜ ነህምያን ለመቃዎም ሞከሩ ፡፡ እግዚአብሄር የሰጣችሁን ስራ እያጠናቀቃችሁ ስትሄዱ ጠላት ጥቂት ነገሮችን እንድታደርጉ ይሞክራል ፤ መጀመሪያ ጠላት እንድታመቻምቹ ለማድረግ ይሞክራል ፡፡
የነህምያ ጠላቶች በተደጋጋሚ እርሱን ለመጉዳት ወደ አኖ ሸለቆ ለመዉሰድ ማባበል ለመሞከር መልዕክትን ላኩ ፤ ነገር ግን በእያንዳንዱ አራት ጊዜ ለነህምያ ጥያቄአቸዉን ላኩ ነህምያም እንደማይመጣ መለሰላቸዉ ምክንያቱም ታላቅ ስራ እየሰራ ስለ ነበር ፡፡ ጥያቄአቸዉ የፀና ነበር ምክንያቱም ነህምያ እንዲያመቻምች ስለ ፈለጉ ፡፡ “ ጨርሰኃል ብትመጣ ምንድን ነዉ ጉዳቱ ? “ የሚመስል ነገር በማለት ፤ ጠላት እንድንሰራዉ እግዚአብሄር ከጠራን ነገር መዉጣት እንድንጀምር ትንሽ ነገር እንድናመቻምች ይፈልጋል ፡፡ ከረጅም በፊት ትንሽ ማመቻመች ወደ መንሸራተት ይመራል ወዲያዉኑም እግዚአብሄር እንድንሆን ከሚፈልገዉ ስፍራ ርቀን ራሳችንን እናገኘዋለን ፡፡
ነህምያ (6፡ 5-7)፡ዋይርስቤ ማመቻመችን ስንቋቋም ጠላት ስማችንን ያጠፋል ፡፡ የነህምያ ጠላቶች እርሱን ማስፈራራት ለመሞከር የአሉባልታ ፋብሪካ ፈጠሩ ፤ ዮሐንስ ማክአርቱር “ የተፃፈዉ ግልፁ ደብዳቤ በተለይም የተጠቀለለ ነበር እናም በደብዳቤ ላኪዉ ወይም ከሰራተኞቹ አንዱ በግልፅ ማህተም የታተመ እንደ ነበር “ ፅፏል ፡፡ እዉነቱ “ የተከፈተዉ “ ይህ ደብዳቤ ያለማክበር እና የታወቀን መኮነን ምልክት ነበር ፤ በተጨማሪም ይዘቱ በአደባባይ የመታወቅ ምልክት ነበር ፡፡
በደብዳቤዉ በፍጥነት የተሰራጨዉ አሉባልታ ሆኖ ነበር ፤ የደብዳቤዉ ክስ ነህምያ የፋሬስ ንጉስን እምነት ክዶት እንደነበር ነበር ፡፡ ነህምያ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለስ ፍቃድ ሲሰጠዉ ወደ ፋሬስ ከመመለሱ በፊት ስራዉን ለማጠናቀቅ ንጉሱን ግልፅ የሆነ የጊዜ መዋቅር ሰጥቶታል ፡፡ ንጉሱ በደብዳቤዉ ላይ ያለዉን ክስ ሲሰማ ራሱን እንደ ንጉስ ለማድረግ ነህምያ ከድቶት እንደ ነበር ይሰማዋል ፤ የተባለዉ ክስ እዉነት ከነበር …ንጉሱ ችግሩን ለመፍታት ወታደሮችን ሳይልክ አይቀርም ፡፡
ነህምያ (6፡ 8-9)፡ ሀሜት ሲሆን መረበሽ አይሆንም ፡፡ ሁልጊዜ ማመቻመች እና ኃሜት ነህምያ ላይ ተወረወረ በእግዚአብሄር ላይ ባለዉ ግንኙነት ተደገፈ ፤ ነህምያ ያለማቋረጥ ከእግዚአብሄር ጋር አዉርቷል ፡፡ መዝሙረኛዉ የፃፈው “ የብዙ ሰዎችን ስድብ ሰምቻለሁና ፤ በዙሪያዉ ፍርሃት ነበረ ፤ በላዬ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ ነፍሴን ለመንጠቅ ተማከሩ ፡፡ አቤቱ እኔ ግን በአንተ ታመንሁ ፤ አንተ አምላኬ ነህ አልሁ “ (መዝ 31፡ 13-14) ፡፡ ምሳ (4፡ 27) “ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል ፤ እግርህንም ከክፉ መልስ “ በማለት ያበረታታናል ፡፡ የአሉባልታ ተናጋሪዎች ንግግር እንዲያገኙአችሁ አትፍቀዱ ፤ በስራችሁ መስመር ላይ ቆዩ ፡፡
ነህምያ (6፡ 10-14)፡ዋይርስቤ ጥፋቱና ኃሜቱ ሲወድቅበት ጠላት በእኛ ላይ ማስፈራራት ዕንደሚያደርግ ይጠቅሳል ፡፡ ነህምያም ጠላቶቹ ሊገድሉት እየመጡ ስለ ነበር በቤተ መቅደሱ ዉስጥ እንዲደበቅ የመከረዉን ሸማያ ለመጎብኘት ሄደ ፤ ነህምያም ሸማያን ከከተማዋ ቅጥር ስራዎች ላይ ለማቋረጥ እንዲሞክሩ ለጦብያና ለሰንበላጥ እየሰራ እንደ ነበር አስተዋለ ፡፡ ነህምያን ከከተማዉ መሳብ ስላልቻሉ በቤተ መቅደሱ ዉስጥ ማስፈራራት ለማድረግ ሞከሩ ፤ ነገር ግን ነህምያ ካህን አልነበረም ፤ ልክ እንደዚያ ወደ ቤተ መቅደስ መሄድ እንደማይችል ያዉቃል ፡፡ እስራኤላዊያን ከቤተ መቅደሱ ዉጪ መሰዊያዉ ላይ መማፀናን መመልከት ይችላሉ ነገር ግን ወደ ቤተ መቅደሱ መግባት አይችሉም (ዘጸ 21፡ 13-14) ፤ ይህ ለማምታታት እና ነህምያን ከንቱ ለማድረግ ጉጉት ነበር ፡፡ ማንም በዚያ ይሆናል ብሎ የሚያስብ አልነበረም ምክንያቱም ሁሉም በዚያ እንዲሆን እንዳልተሰየመ ስለሚያዉቁ ፡፡
ነህምያ በቤተ መቅደሱ ከተደበቀ በህዝቡ ፊት አድርጎት የነበረዉን ድፍረትም ዋጋ ያሳጣዋል ፤ ነህምያ እንደሌሎቹ ሁሉም ታማኝነት እንደ ጎደላቸዉ አይሁዶች ይመስላል ፤ ኃጢዓት ያደርጋል መሪነቱም በህዝቡ ፊት ዋጋ ያጣል ፡፡
ነህምያ (6፡ 15-19)፡ዋይርስቤ ጠላት ተስፋ እንደ ማይቆርጥ ፅፏል ፡፡ ለነህምያና ለህዝቡ ቅጥሮቹን መልሶ ለመስራት አምሳ ሁለት ቀን ብቻ ፈጀ ነገር ግን የነህምያ ጠላቶች በሁሉም እያንዳንዱ ቀናቶች ዉስጥ ተፈታተኑት ፡፡ ዋይርስቤ “ አብዛኞቹ ግድየለሽ ክርስቲያኖች ጦርነቱን አሸንፈዋል ነገር ግን ከዚያ በኋላ ግን ድሉን እንዳጡት “ ተናግሯል ፡፡ ጠላቶቹ ተግባሩ እንዳበቃ አዉቀዋል ነገር ግን ስራዉን በመቃወም ቀጠሉ ፤ በቅጥሩ ላይ ያለዉ ስራም እንኳን ካበቃ በኋላ ከአይሁድ አንዳንዶች ወደ ነህምያ ጠላት ወደ ጦብያ መሳብ ጀመሩ ፡፡ ለአይሁድ አለቆች(ባላባቶች) በሚመጡት ደብዳቤዎች በኩል ጦብያ አሁንም ነህምያን ለማስፈራራት ሞከረ ፡፡ ህዝቡ በስራቸዉ እና ያደርጉለት ለነበረዉ አንዱ ትኩረታቸዉን አጡ ፡፡
መደምደሚያ
ስራዊ ሲያልቅ የሕዝቡ ታማኝነት ከነህምያ ይቃወሟቸዉ ወደ ነበሩት ጠላቶቻቸዉ ተቀየረ ፡፡ እግዚአብሄር በጠራችሁ ስራችሁ የእናንተ የመጨረሻዉ ታማኝነታችሁ ለክርስቶስ ነው ፤ ሌላ ነገር ልክ እንደ ቤተሰብ መልካም ነገር እንኳን ቢሆን በእግዚአብሄር ከተጠራችሁበት ስራችሁ ሀሳባችሁን የሚበትን ሊሆን ይችላል ፡፡ ድል ስናደርግ በመረጋጋት አለመቀመጥ እና ምቾት አለማግኘት ለእኛ አስፈላጊ ነው ምክንያቱም እግዚአብሄር በመጫን ላይ የሚበልጥ እንድናደርግ ስለሚፈልግ ፡፡ ጦርነቱን አለማሸነፍ የእግዚአብሄርን ድል ቸል ማለት ነው ፡፡
Warren Wiersbe, Be Determined (Nehemiah): Standing in the Face of Opposition (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1992), p. 83.
Wiersbe, p. 84.
Wierse, p. 86.
John Macarthur, The MacArthur Bible Commentary: Nehemiah. (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), pp. 542–543..
Wiersbe, p. 88.
Wiersbe, p. 89.
Wiersbe, p. 89.
ጥያቄዎች
-
ነህ (5፡ 1-5) ስታነቡ የእኛን ዘመን ጊዜ ከነህምያ ጋር ስታወዳድሩት ብዙ ልዩነቶችን አላስተዋላችሁም ? እነዚህ ፅሁፎች ለአሁኑ ዘመንም መሆን ይችላሉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን አሰባችሁ ወይስ ለምን አላሰባችሁም ?
-
በነህምያ (6፡ 10-13) አንድ ነብይ ነህምያን አንድ ቃል ሰጠው ነገር ግን ነህምያ ሀሰት እንደ ነበር አወቀ ፤ መፅሀፍ ቅዱስ ስለ ሐሰተኛ ነቢያቶች ምን ይላል ? (ዘዳ 18፡ 20፣ ማቴ 7፡ 15፣ 2ጴጥ 2፡ 1)
-
ነህምያ ቅጥሩን በ52 ቀን ጨረሰ ፤ የእስራኤላዊያን ጠላቶችም ፈሩም አፈሩም ፤ ለምን ? ከእግዚአብሄር ጋር እስራኤላዊያን በተመዘገበዉ ጊዜ ቅጥሩን መጨረስ ይችሉ ስለ ነበር ፡፡
-
በነህምያ (5-6) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Nehemiah 6:8–9
“Then I replied to him, ‘There is nothing to these rumors you are spreading; you are inventing them in your own mind.’ For they were all trying to intimidate us, saying, ‘They will become discouraged in the work, and it will never be finished. But now, my God, strengthen me.’”
ነህምያ እና ሰራተኞቹ ጥሪያቸው በሆነው ቅጥሩን እንደገና መስራት ላይ ቀጠሉ ፡፡ ወሬው በተሰማ ጊዜ ነበር ፣ አምስተኛው ነህምያን ለመጉዳትና ተሰፋ ለማስቆረጥ ሙኩራ የተደረገው ፡፡ የቅጥሩ ስራ እንዳይጠናቀቅ ጠላት ሰራተኞቹን ማስፈራራቱንና ተስፋ ማስቆረጡን ቀጠለ ፡፡ ነህምያ ግን በእግዚአብሔር በረታ ፡፡ በስራው ላይ አተኮረ ፤ እግዚአብሔርም በጠላቶቹ ወጥመድ ውስጥ እንዳይወድቅ ጥበብንና ማስተዋልን ሰጠው ፡፡ ከአምሳ ሁለት ቀናትም በኋላ እስራኤላውያን ቅጥሩን ጨረሱ ፡፡ ይህም ጠላቶቻቸውን አስፈራ ተዋረዱም ፡፡ በመጨረሻም የእስራኤላውያን ጠላቶች ቅጥሩን የሰራው እግዚአብሔረ አምላክ መሆኑን አወቁ ፡፡
እግዚአብሔር እንድትሰራው የጠራህን ስራ ስትሰራ ሊያደናቅፍህ የሚሞክረው ጠላት የት ነው ? የተዋሀደ ትዳርን መፈለግ ? ከገንዘብህ በልግስና መስጠት ? አድስ አማኝን ደቀመዝሙር ማድረግ ? በጌታ ኃይል ከጌታ ጋር ስትራመድ ፣ ጠላት ይከተልሃል ፡፡ አታወላውል ፣ ወደ ግራም ወደ ቀኝም አትበል ፣ ወደ ኋላ አትመልከት ፣ አታመቻምች ፡፡ ክፉና ደጉን ትለይ ዘንድ እግዚአብሔርን ፈልግ ፡፡ ፈተናውን መቋቋም እንደማትችል ከተሰማህ ኃይልህ ሁሉን ከሚችል አምላክ ከእግዚብሔር ዘንድ እንደሆነ አስታውስ ፡፡ እርሱ ስላአንተ ይዋጋል ፡፡ እግዚአብሔር እንድትሰራ የሰጠህን ስራ ትፈጽማለህ ፤ ሌሎችም የእግዚአብሔር ስራ እንጂ የአንተ እንዳልነበር ያያሉ ፡፡ ለእርሱ ክብር ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን አሜን !
“ እኔም፦ አንተ ከልብህ ፈጥረኸዋል እንጂ እንደ ተናገርኸው ነገር ምንም የለም ብዬ ላክሁበት ። እነርሱም ሁሉ ሥራው እንዳይፈጸም፦ እጃቸው ይደክማል ብለው ያስፈራሩን ዘንድ ወደዱ፤ አሁንም፥ አምላክ ሆይ፥ እጄን አበርታ ። “
- ነህምያ 6፡8-9
ተጨማሪ ጥቅስ
ነህምያ 6:15–16—“ ቅጥሩም በኤሉል ወር በሀያ አምስተኛው ቀን በአምሳ ሁለት ቀን ውስጥ ተጨረሰ ። ጠላቶቻችንም ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ በዙሪያችን የነበሩ አሕዛብ ሁሉ ፈሩ፥ በራሳቸውም አሳብ እጅግ ተዋረዱ፥ ይህም ሥራ በእግዚአብሔር እንደ ተደረገ አወቁ ። “
መዝሙር 31:13–15—“ የብዙ ሰዎችን ስድብ ሰምቻለሁና፤ በዙሪያው ፍርሃት ነበረ በላዬ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ ነፍሴን ለመንጠቅ ተማከሩ ። አቤቱ፥ እኔ ግን በአንተ ታመንሁ፤ አንተ አምላኬ ነህ አልሁ ። ርስቴ በእጅህ ነው፤ ከጠላቶቼ እጅና ከሚያሳድዱኝ አድነኝ ። “
ምሳሌ 4:26–27—“ የእግርህን መንገድ አቅና፥ አካሄድህም ሁሉ ይጽና ። ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል፤ እግርህንም ከክፉ መልስ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።