Be Serious! Be Alert!
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Builder Nehemiah 3-4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ለነህምያ ሀረጋችን (ቃላችን) ገንቢ (ሰራተኛ) ነው ፡፡ ነህምያ ለእግዚአብሄር ታዛዥ በመሆን ለከተማዉ ለኢየሩሳሌም እና በዚያ ለሚኖሩት ሕዝቦቹ ሁኔታ አሰበ ፡፡ ይሁዳ በመሄድ በዚያ ያለዉን የከተማዋን ቅጥር የማደስ ስራን ለመምራት ፍቃድ ተቀበለ ፡፡ ነህ (2፡ 20) በምዕራፍ 1 እና 2 እስካሁን ያየነዉን ያጠቃልለዋል፡ “ የሰማይ አምላክ ያከናዉንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሰራለን “ ፡፡ ጉዳቱን ካጠና በኋላ ነህምያ በቅጥሩ ላይ ስራዉን እንዲጀምሩ ሕዝቡን መራ (ምዕራፍ 13) ፤ ስራቸዉን በበሮች ጀመሩ፡ የበጎች በር (ቁጥር 1-2)፣ የአሳ በር (ቁጥር 3-5)፣ የቀድሞ ከተማን በር (አሮጌዉ በር) (ቁጥር 6-12)፣ የሸለቆዉ በር (ቁጥር 13)፣ የጉድፍ መጣያ በር (ቁጥር 14)፣ የምንጭ በር (ቁጥር 15)፣ የዉሃዉ በር (ቁጥር 26-27)፣ የፈረስ በር (ቁጥር 28)፣ የምስራቅ በር (ቁጥር 29-30)፣ የቁጥጥር በር ወይም የፍተሸ በር (ቁጥር 31) እና ተመልሶ ወደ በግ በር (ቁጥር 32) ፡፡
ትምህርት
ነህምያ (4፡ 1-6)፡ በእግዚአብሄር ጥሪ መጓዝ ተቃዉሞን ይስባል (ዕብ 11፡ 36) ፡፡ ሰንባላጥም የቅጥሩ ስራ እየተካሄደ እንደ ነበር በሰማ ጊዜ “ በመበሳጨት “ በወንድሞቹና በሰማሪያ ሰራዊት ፊት አይሁድን አላገጠባቸዉም ቀለደባቸዉም ፡፡ ሰንባላጥም የአይሁድን “ በማዘን ሁኔታ “ በመጥራት በኃይማኖት ልምዳቸው ቀልድ በማድረግ የተቃጠለዉን የቅጥሩን ድንጋዮች መመለስ ስለ መቻል ችሎታቸው ጠየቁ (ቁጥር 1-2) ፡፡ ከዚያም አሞናዊዉ ጦብያ የሚገነቡት ማንኛዉም ግንብ የአንድ ቀበሮ ክብደት እንኳን ለመያዝ ጠንካራ እንደማይሆን በማለት በአይሁዶች ጥረት ላይ በመቀለድ ተቀላቀለ (ቁጥር 3) ፡፡ በምላሹም ነህምያ በመፀለይ እግዚአብሄር ዛቻቸዉን በእነርሱ ላይ እንዲመልሰዉ ጠየቀ (ቁጥር 4-5) ፡፡ ሕዝቡም ተቃዉሞዉ እያለ በቅጥሩ ላይ መስራታቸዉን ቀጠሉ (ቁጥር 6) ፡፡
ነህምያ (4፡ 7-14)፡ የጠላቶቻቸዉ ዛቻዎቹች እና ዘለፋዎች በነህምያ በመጀመሪያዎቹ ሰባት ምዕራፎች ዉስጥ ቀጠሉ፡፡ ሰንባላጥና ጦብያ በቅጥሮቹ ስራ ላይ የተበሳጩ ሌሎችን አመጡ - አረባዊያንን፣ አሞናዊያንን እና አሽዶዳዉያን (ቁጥር 7) ፡፡ ኢየሩሳሌምንም እንዴት እንደሚወጉ በአንድ ላይ አሴሩ (ቁጥር 8) ፤ በምላሹም ነህምያ ሕዝቡን በፀሎት በመምራት በሁሉም ሰዓት ጠባቂዎችን በዙሪያ አስቀመጠ (ቁጥር 9) ፡፡ ቅጥሩ መልሶ መገንባት ከመቻሉ በፊት የሚወገድ ብዙ ኮረት እና ቆሻሻ ስለ ነበር ሰራተኞቹ ቀድመዉ በመፍራት ከስራቸዉ ደክመዉ ነበር (ቁጥር 10) ፡፡ የተጣመሩት ጠላቶቻቸዉ አይሁዶችን ለማስፈራራት በመሞከር ቀድሞዉኑ አሸንፈዋቸዉ እስከ ነበረዉ ድረስ ምን ሆኖ እንደ ነበር በፍፁም እንደማያዉቁ ነገሯቸው (ቁጥር 11) ፤ አይሁዶችም ከሁሉም አቅጣጫ እንደሚጠቁ ተሰማቸው (ቁጥር 12) ፤ ስለዚህም ነህምያ ሕዝቡን በቤተሰብ ወገን በመለየት በጣም አደገኛ በሆኑት በግንቡ አካባቢዎች ላይ በሰይፍ፣ በጦር እና በቀስት አሰለፋቸው (አቆማቸዉ) (ቁጥር 13) ፤ ከዚያም ጠላቶቻቸዉን መፍራት እንደሌለባቸው ሕዝቡን ነገራቸዉ ምክንያቱም አይሁድ “ ከታላቅና ከሚያስፈራዉ አምላክ “ ድጋፍ ስለ ነበረው ፤ ለወንድሞቻቸዉ፣ ለቤተሰቦቻቸው እና ለቤታቸዉ ይዋጋሉ (ቁጥር 14) ፡፡
ነህምያ (4፡ 15-23)፡ ጠላቶቻቸዉ አይሁዶች ግማሹ ሰዎች ሲሰሩ ግማሾቹ ደግሞ በሰይፍ፣ በጋሻ፣ በቀስት እና በጦር እቃዎች ለመጠበቅ እንዲቆሙ የስራ ዝርዝር መፍጥራቸዉ ሰሙ (ቁጥር 16) ፡፡ ሰራተኞቹ በአንድ እጃቸዉ የሚቀርበዉን ክብደት በመሸከም በሌላኛዉ ደግሞ መሳሪያ ሲይዙ ግንበኞችም ደግሞ ሰይፋቸዉን በወገባቸዉ ላይ በማንገት ይሰራሉ (ቁጥር 17-18) ፡፡ ነህምያ መለከት ነፊን ስራዉ በጣም የተሰራጨ ስለነበር በሁሉም ጊዜ ከእርሱ ጋር አደረገ ፤ የመለከቱ ድምፅ ሰራተኞቹን በእግዚአብሄር ጠላቶቻቸዉን በጋራ ለመዋጋት በአንድ ላይ እንዲሰበሰቡ ይስባቸዋል (ቁጥር 19-20) ፡፡ ስራዉም ከማለዳ እስከ ማታ ድረስ ቀጠለ ሁሉም ሰራተኞችም በማታ የከተማዋ ጥበቃ አካል ለመሆን በኢየሩሳሌም ተቀመጡ (ቁጥር 21-22) ፡፡ ነህምያና ሰራተኞቹ ለማረፍ በፍፁም ልብሳቸዉን አያወልቁም ግን ሲታጠቡም እንኳን መሳሪያቸዉን ተሸክመዉ ነው (ቁጥር 23) ፡፡
መደምደሚያ
የኢየሩሳሌም ሰዎች ቅጥሩን እየሰሩ ከፍተኛ ተቃዉሞ ከጠማቸው ፤ በሞት ማሳፈራራት፣ በፍርሃት፣ በማቂያቃል እና በዛቻ ተቃዉሞ ገጠማቸዉ ፡፡ በፀሎትና በፅናት ከዚህ ተረፉ - እንደ ንቁ ሰዉ(ጥበቃ) በማገልገል ፡፡ ዴቭ ቡትስ የጥብቃ ሰዉን ስራዎች https://www.harvestprayer.com/resources/personal-2/task-of- watchman ላይ ዘርዝሯል ከታች ያለዉ ማጠቃለያዉ ነው፡
- ጥበቃዎች ቅጥሮቻቸዉን “ በቀንና በሌሊት …አትረፉ….ለእርሱም እረፍት አትስጡ ….የተጋራ በመሆን በጋለ ስሜት “ ይጠብቃሉ ፡፡
- ጥበቃዎች አይኖቻቸዉን በመክፈት ቅጥሮቻቸዉን ይጠብቃሉ ፤ በፀሎት በመሆን እግዚአብሄር የሚያደርገዉን ለመለየት ለመለየት የተከፈተ መንፈሳዊ አይንንም ያካትታል (ማቴ 26፡ 40-41) ፡፡
- ጥበቃዎች የጠላትን ድርጊት የሚያዉቁ መሆን አባቸው (2ቆሮ 2፡ 11) ፡፡
- ጥበቃዎች የእግዚአብሄር ሰዎች የሚያስፈልጋቸዉን ለመለየት መስራት አለባቸው ፡፡
ለራሳችሁ እና ለትምህርታችሁ ተጠንቀቁ (ሐዋ 20፡ 28, 1ጢሞ 4፡ 16) ፤ “ በመጠን ኑሩ ! ንቁም ! ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚዉጠዉን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ ይዞራልና “ (1ጴጥ 5፡ 8) ፡፡
ጥያቄዎች
-
በነህምያ 3 የተወሰኑ ሰዎች የቅጥሩን እያንዳንዱን ክፍል መስራታቸዉ በአጋጣሚ ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ ወይስ ከኋላዉ አላማ ነበረው ብላችሁ ታስባላችሁ ?
-
በነህምያ 4 ሰንበላጥና ጦብያ ከኢየሩሳሌም ጋር ለመዋጋት አሲረዉ እንደ ነበር በሰማ ጊዜ ነህምያ ምን አደረገ ? ነህምያ ምን አደረገ ሰራተኞቹስ ምን መለሱ ?
-
በቅጥሩ መሰራት ላይ ነህምያ ምን ድርሻ ተጫወተ ? (ነህ 4፡ 4-5፣ 16-23)
-
በነህምያ (3-4) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Nehemiah 4:14
“After I made an inspection, I stood up and said to the nobles, the officials, and the rest of the people, ‘Don’t be afraid of them. Remember the great and awe-inspiring Lord, and fight for your countrymen, your sons and daughters, your wives and homes.’”
ነህምያ እና ህዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርን ተከተሉ የከተማዋንም ግንብ ለመስራት ተባበሩ ፡፡ እናም ከዚያ ግን ከጠላት ተቃውሞ መጣ ፡፡ ጠላቶችም ኢየሩሳሌምን ለመውጋት ፣ ሽብርን ለመፍጠርና ህዝቡን ተስፋ ለማስቆረጥ በአንድነት አቀዱ ፡፡ በዚህ ጊዜም ነህምያ ህዝቡን በጸሎት ወደ እግዚአብሔር መራ ፡፡ እነርሱም ጠላትን አልፈሩም ነበር ፡፡ ቅጥሩንም እንደገና ይሰሩ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ጠራቸው አስታወሱ ነህምያም “ አትፍሩ ! “ በማለት አበረታቸው ፡፡ እግዚአብሔርም ቀንና ሌሊት ይጠብቁ ዘንድ እንድያቅዱ ጥበብን ሰጣቸው ፡፡ እነርሱም እግዚአብሔር እንደሚዋጋላቸው አመኑ ፡፡
ከኢየሱስ ጋር በመታዘዝ ስትራመድ ፣ ሊያደናቅፍህና ሊያሸብርህ ጣላት በመንገድህ ይመጣል ፡፡ አንተም እንድህ ታስብ ይሆናል ፡- ይሄ በጣም ከባድ ነው ፤ እውነት እኔ ጌታን እተከተልኩ ነውን ? በጥሪህ ላይ ጽና ፡፡ አስታውስ እግዚአብሔር የእጆችህን ስራ ሲያጸናልህ ፡፡ በእርሱ ጽና ደግሞም የነቃህ ሁን ፡፡ እግዚአብሔር ለአንተ ይዋጋል ጥበብንም ይሰጥሃል ፡፡ በጠላቶችህ እንደተከበብክ በሚሰማህ ጊዜ እግዚአብሔር በፈተና ውስጥ ይጠብቅሃል ፡፡ በአለም ካለው ይልቅ በአንተ ወስጥ ያለው እርሱ እንደሚልቅ ጌታ ተናግሯል ፡፡ ይህን ማድረግ ትችላለህ ! አትጠፋም ፡፡
“ አይቼም ተነሣሁ፥ ታላላቆቹንና ሹማምቱንም የቀሩትንም ሕዝብ፦ አትፍሩአቸው ታላቁንና የተፈራውን ጌታ አስቡ፥ ስለ ወንድሞቻችሁም ስለ ወንዶችና ስለ ሴቶች ልጆቻችሁም ስለ ሚስቶቻችሁም ስለ ቤቶቻችሁም ተዋጉ አልኋቸው ። “
- ነህምያ 4፡14
ተጨማሪ ጥቅስ
ሐዋርያት ሥራ 20:28 —“ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ ። “
2ኛ ቆሮንቶስ 2:11 —“ በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና ። “
1ኛ የጴጥሮስ 5:8–9 —“ በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና ፤ በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።