Historical Books Nehemiah

God Will Grant Us Success

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Builder Nehemiah 1-2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 323 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለነህምያ መፅሀፍ አንድ ቃላችን ገንቢ (ሰራተኛ) ነው ፡፡ በስነ መለኮት ት/ቤት ትምህርቴ ዶር. ህዋርድ ሄንድሪክስ የነህምያ መፅሀፍ ሕዝቡ እንደ ተመለሱ ቤተ መቅደሱን እና ከተማዉን መልሰዉ ሲገነቡ እንዴት እዉነተኛ መንፈሳዊ መሪ መተግበር እንደሚችል የሚያሳይ ስዕል እንደሆነ አጋርቷል ፡፡ ነህምያ የሚለዉ ስም “ የአምላክ ደስታ (የአምላክ መፅናናት) “ ማለት ሲሆን ከራሱ ከመፅሀፉ ዉጪ መፅሀፍ ቅዱስ ላይ የትም አልተከሰተም ፡፡ የአይሁድ ባህሎች ነቢዩን ዕዝራ የመፅኀፉ ፀሀፊ እንዲሁም ደግሞ የዕዝራ መፅሀፍ ፀሀፊ እንደሆነ ይቀበላሉ ፡፡ ምናልባትም የዕዝራ እና የነህምያ መፅኀፍ እንደ አንድ መፅሀፍ ተፅፎ እንደ ነበር እና ቆይቶም 2 ዕዝራ የተባለዉ ነህምያ በመባል ተከፋፈለ ፡፡

እግዚአብሄር ፋሪሳዊያንን እና ባቢሎናዊያንን ሁለቱንም ለኪዳኑ ስለ አለመታመናቸዉ በእስራኤላዊያን ላይ የስደትን 70 አመታት ፍርድ ለማምጣት ተጠቀመባቸው (ኤር 25፡ 11)፡

  • 722 ከክርስቶስ ልደት በፊት - ሶርያዊያን የእስራኤል የአስሩን ነገድ ሕዝቦች (የሰሜኑን መንግስት) ከአገራቸዉ በማስወጣት በሚታወቀዉ አለም ሁሉ በተኑዓቸው (2ነገስት 17) ፡፡
  • 605 – 586 ከክርስቶስ ልደት በፊት - ባቢሎናዊያን ኢየሩሳሌምን በማጥፋት በጣም ድሀ የሆኑት ነገዶች ቀሩ እንጂ ሁንም አስወጡዓቸው (2ነገስት 25) ፡፡

በእነዚህ 70 የምርኮ አመታት የአለም አመራርነት ተቀይሮ ነበር የባቢሎንም ግዛት በፋሪሳዊያን ወድቆ ነበር ፤ በዕዝራ የፋሪስ ንጉስ ቂሮስ ቤተ መቅደሱን መልሰዉ ለመስራት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለሱ የመጀመሪያዉን ቡድን ፈቀደላቸው (ዕዝራ 1፡ 1-2) ፡፡ በነህምያ ብዙ ስደተኞች በኢየሩሳሌም ያለዉን ቅጥር መልሶ ለመስራት ተመለሱ ፡፡

ነህምያ ለንጉስ አርጤክስስ እንደ ጠጅ አሳላፊ ያገለግላል ፡፡ ዘሩባቤል እና ኢያሱ የመጀመሪያዉ የስደተኛ መመለስ ማዕበል አካል ነበሩ (ዕዝራ 1-6) እንዲሁም ደግሞ በሁለተኛዉ የስደተኞች ማዕበል በኢየሩሳሌም የቤተ መቅደሱን መልሶ መገንባት ስራ መርተዋል (ዕዝራ 7-11) ፡፡ ዕዝራ በሁለተኛዉ ማዕበል ተመለሰ ፡፡ የነህምያ መፅኀፍ የኢየሩሳሌምን ቅጥር መልሶ ለመስራት የተመለሰዉን የስደተኞች ሰዎስተኛ ማዕበሉን ይመዘግባል ፡፡ ማክአርቱር በነህምያ መፅሀፍ “ ፍቃዱን ለመፈፀም የእግዚአብሄርን ቃል በትኩረት ተጠንቅቆ ማንበብ ቋሚ ጭብጥ (ፍሬ ነገር) እንደሆነ “ ይናገራል ፡፡ የኢየሩሳሌምን ቅጥር ሲሰሩ ምን እንደሚሰሩ በትክክል እንዴት አወቁ ? የእግዚአብሄርን ቃል ምክር ስለጠየቁ ፡፡ በመፅሀፉ ሌለኛዉ የማያቋርጥ ፍሬ ነገሩ የነህምያ መታዘዝ ሲሆን ስራዉን በማጠናቀቅ እንዲሁም ተቃዉሞ ሲገጥምም ታዛዥ መሆን ነው ፡፡ መልሶ ግንባታዉን ለማጠናቀቅ 52 ቀን ብቻ መዉሰዱ የሚያስደንቅ ነው ፤ የእግዚአብሄር እጅ በዚህ በሙሉ መፅሀፉ ላይ ያለማቋረጥ ነው ፡፡ የመፅሀፉ የጊዜ ሰሌዳ፡

445 ከክርስቶስ ልደት በፊት (ነህምያ 1-12) - አንድ አመት በመሸፈን እንደ አስተዳደር የነህምያን የመጀመሪያ ዙር (ተግባር) ይናገራል (ከ445-433 ከክርስቶስ ልደት በፊት ያገለገለውን) ፡፡

425 ከክርስቶስ ልደት በፊት (ነህምያ 13) - ተሸፍኖ ካልነበረዉ 20 አመት በፊት ምዕራፍ 13 የነህምያን ታሪክ መጨረሻና እንደ አስተዳደር ከ425 ወይም ከ424 ከክርስቶስ ልደት በፊት ምናልባትም እስከ 410 ከክርስቶስ ልደት በፊት ሁለተኛ ዙሩን (ተግባሩን) ይሰጣል ፡፡

በነህምያ 1 በሱሳ ከተማ ነህምያ ከይሁዳ መጥተዉ የነበሩ አንዳንድ ሰዎችን አገኘ በኢየሩሳሌም ስለ ቀሩት ቅሪቶችም ጠየቃቸው ፡፡ የከተማዋ ቅጥርች እንደፈራረሱና የቀሩትም በደህና እንዳልነበሩ ሰማ ፤ ነህምያም በሁኔታዉ በማልቀስ ወደ እግዚአብሄር በፀሎትና በፆም ተመለሰ ፡፡ ነህምያ የሆነ ነገር እንደሚቀየር ስለሚያዉቅ ለእርዳታ እግዚአብሄር ጠየቀ ፡፡ በከተማችሁና በሀገራችሁ ሁኔታ ላይ ለመጨረሻ ጊዜ ያለቀሳችሁትና ያዘናችሁት መቼ ነበር ? ነህ (1፡ 5-11) ለህዝቡ፣ ለከተማዉና ለሀገሩ የነህምያን ልብ ያሳያል ፡፡

ትምህርት

ነህምያ (2፡ 1-10)፡ በ445ከክርስቶስ ልደት በፊት በፀደይ ጊዜ ነህምያ እንደ ንጉስ ጠጅ አሳላፊ ንጉስ አርጤክስስን ወይን ሲያቀርብ ንጉሱ ነህምያ እንደ ተበሳጨ በማስተዋል ለምን ብሎ ጠየቀው (ቁጥር 1-2) ፤ ነህምያም አባቶቹ የተቀበሩባት ከተማ በመፈራረሷ እንዳዘነ ገለፀ (ቁጥር 3) ፡፡ ንጉሱ ነህምያን ምን እንዲያደርግለት በጠየቀዉ ጊዜ ነህምያ በመፀለይ አባቶቹ የተቀበሩባትን ከተማ መልሶ ይሰራት ዘንድ ወደ ይሁዳ እንዲሄድ እንዲፈቅድለት ጠየቀው (ቁጥር 4-5) ፡፡ ንጉሱም ነህምያን ለምን ያክል ጊዜ እንደሚቆይ ጠየቀዉ ነህምያም የተወሰነ ጊዜን ሰጠው (ቁጥር 6) ፤ ንግስት አስቴር የአርጤክስ ሚስት ነበረች የአርጤክስስም እንጀራ እናት ስለ ነበረች ምናልባትም እንጀራ ልጇን ስደተኞቹ ወደ እስራኤል መመለስ እንዲጀምሩ እንዲለቃቸዉ ተፅዕኖ አድርጋበታለች ፡፡ በተጨማሪም ነህምያ ንጉሱን በሚያልፍበት አካባቢ ላሉት ገዢዎች በሰላም እንዲያልፍ ዋስትና እንዲሰጡት ደብዳቤ ጠየቀው (ቁጥር 7) ፤ ከዚያም ነህምያ ለንጉሱ ደን ጠባቂዎች ለመልሶ መስሪያዉ እንጨት ማግኘት እንዲችል ደብዳቤን ጠየቀ ፡፡ ነህምያ ለመልሶ ግንባታ ስራዉ እርዳታን ከንጉሱ እየጠየቀ ነበር ንጉሱም ነህምያ የጠየቀዉን ሁሉንም ነገር አደረገለት ፡፡ ነህምያ ስለ ንጉሱ እርዳታ ክሬዲቱን (ዋጋዉን) ለእግዚአብሄር ሰጠ (ቁጥር 8) ፤ ነህምያ ጥያቄ ላይ ንጉሱ ነህምያን ወደ ኢየሩሳሌም ደህንነቱ የተጠበቀ ማለፍ(መሻገር) የሰጡትን ወታደሮችን ከእርሱ ጋር ላከ (ቁጥር 9) ፡፡ ነህምያ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ሖሮናዊዉ ሰንባላጥና አሞናዊዉ ጦባያ የነህምያን መኖር (መገኘት) በመስማት “ እጅግ ተበሳጩ “ (ቁጥር 10) ፡፡ ለነህምያ ስራ ወዲያዉኑ ተቃዉሞ መጣ ፡፡

ነህምያ (2፡ 11-20)፡ ነህምያ ጥቂት ሰዎችን ከመዉሰዱ በፊት ሰዎስት ቀናትን ጠበቀ በምሽትም የከተማዋን ቅጥሮችም አጠና (ቁጥር 11-15) ፤ በዚያ ለምን እንደነበር እንዲያዉቅ ለማንም ከመፍቀዱ በፊት አካባቢዉን በማጥናት ጊዜ ወሰደ (ቁጥር 16) ፡፡ ጥናቱን በጨረሰ ጊዜ ነህምያ በኢየሩሳሌም ላሉት ሕዝቦች ሁኔታዉን በመግለፅ የከተማዋን ቅጥር መልሶ ለመስራት እንዲረዱት ነገራቸው (ጠየቃቸው) (ቁጥር 17) ፤ የእግዚአብሄርም እጅ እንዴት ወደ እነርሱ እንዳመጣው አጋራቸው ፡፡ ሕዝቡም ጥያቄዉን በመቀበል ተበረታቱ (ቁጥር 18)፤ ስራዉን የሚቃወሙት የኢየሩሳሌም ሰዎች ላይ መቀለድ ጀመሩ በንጉሱም ላይ አምፀዉ እንደ ነበር ተናገሩ (ቁጥር 19) ፡፡ ነህምያም የእርሱ አገልጋዮች ስለ ሆኑ እግዚአብሄር ስኬትን እንደሚሰጣቸዉ መለሰላቸዉ (ቁጥር 20) ፡፡

መደምደሚያ

እንደ አንድ ጠጅ አሳላፊ ነህምያ የንጉሱ አገልጋይ ብቻ ነበር ነገር ግን ወደ ንጉሱየመድረስ እድል ነበረው ፡፡ በማህበረሰባችን ዉስጥ ከመንሰራው ዉጪ ሁላችንም የምንጫወተዉ ሚና አለን ፤ በሰጠና በማንኛዉም ተግባር በብዙ ስኬታማዎች መሆን እንችላለን ሁላችንም በፀሎት፣ በፆምና በእርሱ ጥንካሬ ወደ እግዚአብሄር የመድረስ እድል አለን ፡፡

ለተቃርኖ (ለተቃዉሞ) እንዴት ምላሽ ትሰጣላችሁ ? ከተማችንን መልሰን ለመገንባት እንደተጠራን ለሚሰማን ለእያንዳንዳችን መልሱ በነህምያ (2፡ 20) ላይ ይገኛል፡ “ የሰማይ አምላክ ያከናዉንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሰራለን “ ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 518, 533.

  2. MacArthur, p. 533.

  3. MacArthur, p. 534.

  4. MacArthur, p. 535.

  5. MacArthur, p. 535-536.

  6. MacArthur, p. 538.

ጥያቄዎች

  1. በመፅሀፍ ቅዱስ ዉስጥ በፀሎትና በፆም ከእግዚአብሄር ኃላ የተመለከቱ ሌሎች ሰዎችን ማሰብ ትችላላችሁ ? (ማቴ 4፡ 2፣ ሉቃ 2፡ 36-37፣ ሐዋ 13፡ 1-3)
  2. ፀሎታቸዉን ለመመለስ እግዚአብሄር የታመነ ነበር ? እግዚአብሄርን በዚህ መንገድ በህይወታችሁ የተመለከታችሁበት ጊዜ ነበራችሁ አዉ ከሆነ ምን ነበር ዉጤቱ ?
  3. በነህ (1፡ 8-9) ነህምያ እግዚአብሄርን ለሙሴ ብሎት የነበረው አስታወሰዉ ፤ ብዙ ጊዜ ስለ እግዚአብሄር ተስፋ እንዴት ትፀልያላችሁ ? እግዚአብሄር እነዚህን ፀሎቶች ይመልሳቸዋል ብላችሁ ታስባላችሁ ?
  4. የነህምያ ስልጣን ምን ነበር ከነህምያ ጥያቄ አንፃር ንጉሱ ላደረገው ዉሳኔ ላይ ተፅዕኖ ነበረዉ ብላችሁ ታስባላችሁስ ?
  5. የነህምያ ፀሎት ምን ነበር ? እግዚአብሄር ከነህምያ ግምት (ጥበቃ) በላይ እና ይበልጥ እንደሄደ ታስባላችሁ ?
  6. የራሱን ፀሎት ለመመለስ እግዚአብሄር እንዴት ነህምያን ተጠቀመበት (ነህ 2፡ 6) ? የራሳችሁን ፀሎት ለመመለስ እግዚአብሄር ባልተጠበቀ መንገድ ተጠቅሞባችሁ ያውቃል ?
  7. በነህምያ (1-2) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Nehemiah 1:4

“When I heard these words, I sat down and wept. I mourned for a number of days, fasting and praying before the God of heaven.”

ነህምያ በኢየሩሳሌም ጥፋት አለቀሰ አዘነም ፡፡ ቅጥሮቹ ፈርሰው በሮቹም በእሳት ተቃጥለው ነበር ፡፡ ነህምያ በለቅሶ ፤ በፆምና በሰማይ አምላክ በእግዚአብሔር ፊት በጸሎት ጊዜን ካሳለፈ በኋላ ፣ እግዚአብሔር ወደ ንጉሡ ፊት መራው ፡፡ ንጉሡም ነህምያን “ ምን ትለምነኛለህ ? “ ብሎ ጠየቀው ፤ ነህምያም መጀመሪያ ጸለየ ፡፡ ምንም እንኳ ነህምያ በጣም ቢፈራም ፣ በድፍረት እንደገና ከተማዋን ይሰራ ዘንድ ወደ ይሁዳ እንድላክ ጠየቀ ፡፡ ንጉሡ ጠጅ አሳላፊውን ነህምያን ወደ ኢየሩሳሌም እንድሄድ እንድልከው ሲጠየቅ ፣ የማይሆን የሚመስለው ነገር ሆነ ፡፡

ስለ አገርህ ሁኔታ ታለቅሳለህ ? ወይስ ጥፋት ወደ ቤትህ መቅረብ አለበት እናም ለትዳርህ ታዝናለህ ወይም በቤተሰብህ ውስጥ ላለው ግንኙነት ፡፡ ስታዝን ፣ እግዚአብሔርን ፈልግ እናም የነህምያን ምሳሌ ተከተል ፡፡ ጠጅ አሳላፊ ብቻ ነበር አቅም የሌለው በሚመስል ቦታ ላይ እናም እርሱ በጣም ይፈራ ነበር ፡፡ ይሁን እንጂ እራሱን አዋረደ ፣ ጸለየ እግዚአብሔርንም ፈለገ ፡፡ እግዚአብሔርም የማይቻለውን እንድቻል አደረገ ፡፡ በዙሪያህ ስላለው ጥፋት እግዚብሔርን ስትፈልግ ፣ ከመልስ ጋር እንደሚገለጥ ጠብቅ ፡፡ ጸሎትህን እንደሚሰማ ተናግሯል ፡፡ እናም ከዚያ በሮችን ሲከፍት ፣ በድፍረት ( በሙሉ ልብ ) በመታዘዝ ቀጥል ፡፡ እግዚአብሔር ያበረታሃል ፡፡

“ይህንም ቃል በሰማሁ ጊዜ ተቀምጬ አለቀስሁ፥ አያሌ ቀንም አዝን ነበር፤ በሰማይም አምላክ ፊት እጾምና እጸልይ ነበር “

- ነህምያ 1፡4

ተጨማሪ ጥቅስ

  • መዝሙር 5:3 — “ በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ፥ በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ፥ እጠብቃለሁም ። “
  • ነህምያ 2:8 — “ ንጉሡም በእኔ ላይ መልካም እንደ ሆነችው እንደ አምላኬ እጅ ሰጠኝ ። “
  • 1ኛ የዮሐንስ 5:14 — “ በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል ። “