Confession and Repentance
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promise Keeper Ezra 9-10 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ለዕዝራ መፅሀፍ ቃላችን ቃል ኪዳን ጠባቂ ነው ምክንያቱም እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን ከ70 አመታት ምርኮ በኋላ ወደ ገዛ ምድራቸዉ መመለስ እንደ ሚችሉ ተስፋ ገብቶላቸዋል እናም በዚህ መፅሀፍ እግዚአብሄር ያን ተስፋ ሲጠብቅ እናያለን ፡፡ 2ቆሮ (1፡ 20) እግዚአብሄር ተስፋዉን ብቻ እንዳልጠበቀ ነገር ግን ተስፋዉ በክርስቶስም እንደተጠበቀ ያብራራል ፡፡ ዛሬ ይህን መፅሀፍ እንደ ማጠቃለያ ዕዝራ 9 እና 10 እንመለከታለን ፡፡
ትምህርት
ዕዝራ (9፡ 1-3)፡ አለቆቹ ለዕዝራ የእስራኤል ሕዝቦች ካህናቱን እና ሌዋዊያኑን ጨምሮ ከዙሪያቸዉ ካሉት ጋር ተጋብተዉ ስለ ነበር “ የተቀደሰዉንም ዘር ከምድር አሕዛብ ጋር ደባልቀዋል “ (ቁጥር 2) በማለት ሪፖርት አደረጉለት፡፡ በኢያ (3፡ 10) እስራኤላዊያን እግዚአብሄር በተስፋይቱ ምድር የሚኖሩትን ጠላቶቻቸዉን ሁሉ እንደሚያስለቅቃቸው ተነግሯቸዉ ነበር ፤ ይሁን እንጂ እስራኤላዊያን ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሱ ዕዝራ አሁን እስራኤላዊያን ጠላቶቻቸዉን እያገቡ እንደ ነበር ገባው ፤ ዕዝራ ይህን በሰማም ጊዜ ደነገጠ ፡፡
ዕዝራ (9፡ 4-15)፡ ሌሎች በዙሪያዉ ሲሰበሰቡ ዕዝራ እስከ ሰርክ(ምሽት) መስዋዕት እነበረዉ ጊዜ ድረስ ደንግጦ ተቀመጠ (ቁጥር 4) ፡፡ ከዚያም በእግዚአብሄር ፊት በጉልበቶቹ ላይ በመደፋት ወደ እግዚአብሄር ጮኸ ((ቁጥር 5-15)፡፡ እስራኤላዊያን እግዚአብሄርን ከማመስገንና መነቃቃት ወደ ሚያስፈልጋቸዉ ከባድ ወደ ሆነዉ ንስሃ በፍጥነት ሄዱ ፡፡
ዕዝራ (10፡ 1)፡ዋረን ዋይርስቤ የአንድ ሰዉ ፀሎት ኃይልን በፍፁም አለመናቅ አስፈላጊነቱን አፅዕኖት ይሰጠዋል ፤ ያዕ (5፡ 16-18) የአንድ ፃድቅ ሰዉ ፈጣን ፀሎት ኃይለኛ የሆነ ተፅዕኖ እንደሚኖረዉ አመልክቷል ፡፡ የፀሎት ኃይል ሳቢ ነዉ ምክንያቱም ሰዎችን ወደ እግዚአብሄር ስለ ሚያመለክት ፡፡ እዚህ ጋር ዕዝራ በዙሪያዉ እንደ ተሰበሰቡ በመፀለይ የሕዝቡን ኃጢዓት ሲናዘዝ ከእርሱ ጋር በምሬት ሲያለቅሱ እናያለን ፡፡ የዕዝራ ድርጊት ዳዊት በመዝሙር (51፡ 17) እንደ ገለፀዉ የተሰበረ እና የተፀፀተን መንፈስ ያሳያል ፡፡ ስለዚህ በፀሎት ወደ እግዚአብሄር ስንመጣ በትዕቢት እና በእምቢተኝነት የፀሎት መንፈስ መምጣት አንችልም ፤ በተዋረደና በተሰበረ መንፈስ ልንመጣ ይገባናል ፡፡ ዕዝራ ወደ ፊቱ በለቅሶና በኃዘን መጣ ፡፡ ዋይርስቤ የዕዝራን ፀሎት አስፈላጊ የሆነበትን ሁኔታ ወደ ሚገልፀዉ ወደ ያዕ (4፡ 9-10) ያመለክታል ፡፡ ሳቃችን ወደ ለቅሶ ደስታችን ደግሞ ወደ ኃዘን ይቀየራል በእግዚአብሄር ፊት ራሳችን ስናዋርድ ደግሞ ከፍ ከፍ ያደርገናል ፡፡ ይህ የአገሩን አስቸጋሪ ሁኔታዉን በመረዳት ወደ እግዚአብሄር የሚዞር የአንድ የእግዚአብሄር ሰዉ ሂደት ነው ፤ ይህ ሰዎችን ወደ እግዚአብሄር የመሳብ በአንድ እግዚአብሄር ሰዉ በኩል የእግዚአብሄር መንቀሳቀስ ነው ፡፡ በፀሎቱ እና ኃጢዓታቸዉን በማመኑ ምክንያት እስራኤላዊያን ዕዝራን ከበቡት ፡፡ እንደ ሌላ ምሳሌ ዘፍጥረት (39፡ 9) ለክፉ ስራ ማባበል በሞከረች ጊዜ ለጴጢፋራ ሚስት የዮሴፍን መልስ ይገልፀዋል ፤ ዮሴፍ ማንኛዉም ኃጢዓት በእግዚአብሄር ላይ ኃጢዓት እንደሚሆን አዉቋል ፡፡ በመዝ (51፡ 4) ዳዊት ኃጢዓቱ በእግዚአብሄር እና በእግዚአብሄር ላይ ብቻ እንደ ሆነ እዉቅና ሰጠ ፡፡
በ 2ቆሮ (7፡ 9-10) ጳዉሎስ በኃጢዓት ላይ ማዘን ወደ ንስሐ እንደሚመራ ንስሐ ደግሞ ወደ ድነት እንደሚመራ አብራርቷል ፡፡ ኃጢዓትን ማመን ንስኃን ሲያመጣ ንስኃ ደግሞ ለዉጥ ያደርጋል ፡፡
ዕዝራ (10፡ 2-4)፡ ሴኬንያ ባለቤትነትን በመዉሰድ የሌሎች ሕዝቦች ሴቶችን በማግባታቸዉ ሕዝቡ ለእግዚአብሄር ያልታመነ እንደ ነበር ነገር ግን አሁንም ለእስራኤል ተስፋ አለ በማለት ለዕዝራ ለመናዘዝ ተነሳ ፡፡ ሕዝቡ ርምጃ ለመዉሰድ ኪዳን ያደርጋሉ - የሌሎች ሕዝቦች ሚስቶቻቸዉን እና ልጆቻቸዉን ለመስደድ ፤ የእስራኤላዊያን ንስኃ ወደ እርምጃ መራቸው ፡፡ ሴኬንያ እስራኤላዊያን ለዚህ ደርጊት ኃላፊነቱን እንደ ሚወስዱ ተናገረ ነገር ግን በመነሳት ኃላፊነቱን እንዲመራ ዕዝራ እንደሚያስፈላቸዉ ገልፃል (ቁጥር 4) ፡፡
ዕዝራ (10፡ 5-6)፡ ዕዝራ ካህናቱን፣ ሌዋዊያኑን እና የእስራኤልን ሕዝብ የሌሎች ሕዝቦች ሚስቶቻቸዉን እና ልጆቻቸዉን መላክ የሚለዉን መኃላ እንዲወስዱ መራቸው ፡፡ ዕዝራ እናደርገዋለን ብለዉ ተናግረዉት የነበረዉን እንዲያደርጉ አዘዛቸው ከዚያም በእስራኤል አለመታመን ላይ ምሽቱን በመፆም እና በማዘን አሳለፈ ፡፡
ዕዝራ (10፡ 7-8)፡ ሁሉም ስደተኞች ወደ ኢየሩሳሌም ሪፖርት እንዲያደርጉ በመጥራት በተጨማሪ የማይመጣ ማንኛዉም ንብረታቸዉ እንደ ሚወሰድ እና ከእስራኤል ዉጪ እንደሚሆኑ በመግለፅ አዋጅ አወጡ ፤ እነዚህ ነገሮች ሲካሄዱ ዕዝራ መፆሙንና መፀሉን ቀጥሏል ፡፡ ዋይርስቤ ለዉጥ የሚያመጣዉን ዘዴ ይገልፃልል ፤ መጀመሪያ ራሱን ዝቅ ያደረገ ትሁት ፀላይ መሪ ሲኖራችሁ ፤ ሁለተኛ ፍቃደኛ የሆነ ሕዝብ ሲኖራችሁ ፤ ከዚያም የሚታመን ድርጊት መፈፀም ሲኖራችሁ - የእርምጃዉን እቅድ የሚፈፅም ቡድን ሲኖራችሁ ፡፡ ይህ ለእስራኤል በጣም ያስፈለገው ለምን ነበር ? ምክንያቱም እግዚአብሄር እንደ ተለየ ሕዝብ ለይቶ አስቀምጧቸዉ ስለ ነበር እና በህጉ መስመር ላይ መሆን ስለሚያስፈልጋቸው ፡፡
ዕዝራ (10፡ 9-44)፡ የይሁዳና የቢኒያም ሰዎች በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ ፡፡ በዘጠነኛዉ ወር በሀያኛዉ ቀን ላይ ዕዝራ በፊታቸዉ በመቆም አለመታመናቸዉን ለእግዚአብሄር በመናዘዝ ራሳቸዉን ከአሕዛብ ሚስቶቻቸዉ እንዲለዩ አሳሳባቸው ፤ ሕዝቡም ዕዝራ ያለዉን ለማድረግ ተስማሙ ፡፡ ነገር ግን ንስኃ በሚገቡት ሕዝቦች ቁጥር ብዙ ስለ ነበርና ኃይለኛም ዝናብ ስለ ነበር ቤታቸዉ በመመለስ በከተሞቻቸዉ ለአለቆቻቸዉ ሪፖርት እንዲያደርጉ እንዲፈቀድላቸዉ ጠየቁ ፤ እስራኤላዊያንም እንዳቀዱት አደረጉ (ቁጥር 16) ፡፡ አለቆቹም በአስረኛዉ ወር በመጀመሪያዉ ቀን ምርመራቸዉን በመጀመር ከሰዎስት ወር በኋላ ጨረሱ ፡፡ ዋይርስቤ እና ማክአርቱር ካህናቱን፣ ሌዋዊያኑን፣ ዘማሪዎቹን፣ በር ጠባቂዎቹን እና ሌሎችን አካትቶ ከመቶ በላይ ሰዎች ጥፋተኞች ሆነዉ እንደተገኙ አስልተዋል ፤ እነዚህ ሰዎች ሚስቶቻቸዉን ለመላክ ተስማሙ ፡፡
እነዚህ ሕዝቦች እግዚአብሄርን በማምለክ ሌሎችን እንዲመሩ የተሸሙ ነበሩ ፤ ከዚህ ከእግዚአብሄር ሊደበቅ የሚችል ኃጢዓት እንደማይኖር መደምደም እንችላለን ፡፡ ዘፍ (3፡ 7-8) አዳምና ሒዋን ኃጢዓታቸዉን ለመሸፈን እና ከእግዚአብሄር ለመደበቅ እንደሞከሩ ያብራራል ፡፡ በመዝ (32፡ 3-4) ዳዊት ስለ ዝሙት እና ሰዉ መግደል ኃጢዓቱ ዝም በማለቱ በማቃሰት አጥንቶቼ ተሰበሩ አለ ፤ የእግዚአብሄር እጅ በእርሱ ላይ በመክበዱ አቅሙ እንደደከመ አዉቋል ፡፡ ኃጢዓታችንን ከእግዚአብሄር ለመደበቅ ስንሞክርበላያችን ላይ የሚጫን ከባድ ሸክም ይሆናል ፤ በመጨረሻም እግዚአብሄር ኃጢዓታችንን ለእግዚአብሄር በመናዘዝ ከዚህ ሸክም ነፃነት እንድናገኝ አቅዶናል ስለሆነምጥፋተኝነታችንን ሊወስድልን ይችላል (መዝ 32፡ 5-7) ፡፡ መቀየሪያዉን አይታችሁታል ? ዳዊት ኃጢዓቱን ከመደበቅ ወደ ከመደበቂያዉ ስፍራ እግዚአብሄር ወደ መፈለግ ሄድ ፡፡
ኃጢዓታችንን ከእግዚአብሄር መደበቅ አንችልም ፡፡ በ 1ሳሙ (16፡ 7) እግዚአብሄር ልብን እንደሚያይ አብራርቷል ፤ ሁል ጊዜ በልባችሁ ምን እንዳለና ለመደበቅ ምን እንደምትሞክሩ ያውቃል ፤ መዝ (69፡ 5) የጥፋተኝነት ድርጊታችን ከእግዚአብሄር አይደበቅም ፡፡ ዘኁ (32፡ 23) ኃጢዓታችን እንደሚይዘን እርግጠኞች መሆን እንችላለን ይላል ፤ በሉቃ (12፡ 1-2) ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን “ የማይገለጥ የተከደነ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለም “ በማለት ከፈሪሳዊያን እርሾ የተጠነቀቁ እንዲሆኑ አስጠነቀቃቸው ፡፡ ሮሜ እግዚአብሄር የልብን ሚስጥር ስለ መመርመሩ ይናገራል ፤ 1ቆሮንቶስ እግዚአብሄር እንዴት ነገርን ወደ ብርሃን እንደሚያመጣ ይናገራል ፡፡ ምሳሌ (28፡ 13) በዚህ መፅሀፍ ዕዝራ ለመፈፀም እየሞከረ የነበረዉን ሁሉንም ነገር ይገልፃል ፤ በሰፈሩ ኃጢዓት ሲኖር “ ኃጢዓቱን የሚሰዉር አይለማም ፤ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል “ (ምሳሌ 28፡ 13) ፡፡ ዕዝራና እስራኤላዊያን ምህረት አስፈልጓቸዋል ፡፡ 2ዜና መዋል (7፡ 14) እዚህ ምን እንደተፈጠረ ይገልፃል ፤ ራሳቸዉን በማዋረድ ወደ እግዚአብሄር ጮኹ ፀሎታቸዉንም በመስማት ምድራቸዉን ፈወሰ ፡፡
መደምደሚያ
1ዮሐ (1፡ 9) እግዚአብሄር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እንዴት ተስፋውን እንደሚጠብቅ የሚያስደንቅ ስዕል ይሰጣል ፡፡ ዕዝራ ለንስኃና ለመናዘዝ ጊዜ ተጣራ ፤ ተመሳሳይ ለእኛም ይተገበራል ፡፡ በክርስቶስ በእግዚአብሄር ፊት በመምጣት ለኃጢዓታችንን እዉቅና ስንሰጥ (መስራታችንን ስናምን) ይቅር ሊለናን ሊያነፃን የታመነ ነው ፡፡
Warren Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2007), p. 748.
Wiersbe, p. 749.
Wiersbe, p. 749.
Wiersbe, p. 749. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 532.
ጥያቄዎች
-
ዕዝራ የእስራኤላዊያን የተደባለቀ ጋብቻን ተግባራትን ለምን የማያውቅ መሰለ ? (ዕዝራ 9፡ 3)
-
እንደ ክርስቲያን ዕዝራ እንዳደረገው በምድሪቱ ላይ ለሚሄደዉ ኃጢዓት በሚገባ ተቃዉሟችንን እንዴት መግለጥ እንችላለን ?
-
እግዚአብሄር አንድም ቅሬት አልተወም ብላችሁ አምናችሁበት የነበር ጊዜ በማንኛዉም ትዉልድ እስካሁን ነበር ? አዎ ከሆነ መቼና ለምን በዚህ መንገድ ታምናላችሁ ?
-
የዕዝራ በሀዘን የተደባለቀ ንስሀ በእስራኤል መካከል እንዴት መነቃቃት አደረገ ?
-
በዕዝራ 10 ላይ 2ዜና መዋዕል (7፡ 14) እንዴት ነበር የተጫወተው ?
-
በዕዝራ (9-10) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Ezra 10:1–2, 4
“While Ezra prayed and confessed, weeping and falling facedown before the house of God, an extremely large assembly of Israelite men, women, and children gathered around him. The people also wept bitterly. Then Shecaniah son of Jehiel, an Elamite, responded to Ezra: ‘We have been unfaithful to our God by marrying foreign women from the surrounding peoples, but there is still hope for Israel in spite of this . . . Get up,for this matter is your responsibility, and we support you. Be strong and take action!’”
ዕዝራ በኢየሩሳሌም ስላለው ኃጢአት የእስራኤል ሕዝብ ፤ ካህናቱ ፤ ሌዋውያኑ ፤ አለቆቹና ሹማምንቱ ጭምር ከአህዛባን ጋር መጋባታቸውንና እግዚአብሔርን መተዋቸውን አወቀ ፡፡ ዕዝራ በእስራኤላውያን የኃጢአት መንገድ ደነገጠ ፡፡ ስለዚህም ጸለየ ፤ ተናዘዘ እናም በእግዚአብሔር ፊት ራሱን ዝቅ በማድረግ አለቀሰ ፡፡ ህዝቡም የዕዝራን ማዘን ባዩ ጊዜ ፣ ለንስሀና ኃጢአታቸውን ለመናዘዝ ከእርሱ ጋር ተቀላቀሉ ፡፡ የልብ ስብራታቸውንና የተደበቀ ኃጢአታቸውን በእግዚአብሔር ፊት ይዘው ቀረቡ ፡፡ እግዚአብሔር የህዝቡን የአኗኗር ዘዴያቸውን በመቀየር ወደ ፊት ለመምራት ዕዝራን ተጠቀመ እነርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋና ኃይል ተቀበሉ ፡፡
እግዚአብሔር ራስን በማዋረድና በተሰበረ ልብ በፊቱ ስትቀርብ ፈውስ እንደሚሆንልህ ተናግሯል ፡፡ በደልህን ብትደብቅ ፣ በቃ ያለመታዘዝህ ክብደት ይሰማሃል ፣ በትከሻህ ላይ ይቀመጣል ወይም ውስጥ ውስጥህን ቅር ቅር ይልሃል ፡፡ ከእግዚአብሔር የሚደበቅ ኃጢአት የለም ፡፡ ወደ ፊት ተራመድ እና ኃጢአትህን ተወው ፡፡ ለእግዚአብሔር በትህትና እና በተሰበረ ልብ ሁሉንም ተናዘዝ ፡፡ ከዚያም ወስንና ከቀድሞው መንገድህ ተመለስ ፡፡ እግዚአብሔር ኃጢአትህን ለእርሱ ስትናዘዝ ምህረትንና ይቅርታን እንድምታገኝ ተናግሯል ፡፡ እግዚአብሔር በደልህን ፤ ሀፍረትህንና ኃጢአትህን ምስራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ እንድሁ ከአንተ ያርቃል ፡፡ እርሱ በነጻነት እንድትመላለስ ይፈልጋል ፡፡ ይወድሃል ፡፡ በቃ ዛሬ በፊቱ ቅረብ ፡፡
“ዕዝራም እያለቀሰና በእግዚአብሔር ቤት ፊት እየወደቀ በጸለየና በተናዘዘ ጊዜ ከእስራኤል ዘንድ የወንድና የሴት የሕፃናትም እጅግ ታላቅ ጉባኤ ወደ እርሱ ተሰበሰበ፤ ሕዝቡም እጅግ አለቀሱ ። ከኤላም ልጆች ወገን የነበረም የይሒኤል ልጅ ሴኬንያ ዕዝራን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ አምላካችንን በድለናል፤ የምድርን አሕዛብ እንግዶች ሴቶችን አግብተናል፤ አሁን ግን ስለዚህ ነገር ገና ለእስራኤል ተስፋ አለ ። ይህም ነገር ለአንተ ይገባልና፥ እኛም ከአንተ ጋር ነንና ተነሣ፥ አይዞህ፥ አድርገው ። “
- ዕዝራ 10 ፡1-2 ፤ 10፡4
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 32:3–5 — “ ሁልጊዜ ከመጮኼ የተነሣ ዝም ባልሁ ጊዜ አጥንቶቼ ተበላሹ ፤ በቀንና በሌሊት እጅህ ከብዳብኛለችና፥ እርጥበቴም ለበጋ ትኵሳት ተለወጠ ። ኃጢአቴን ለአንተ አስታወቅሁ፥ በደሌንም አልሸፈንሁም፤ ለእግዚአብሔር መተላለፌን እነግራለሁ አልሁ፤ አንተም የልቤን ኃጢአት ተውህልኝ ። “
ምሳሌ 28፡13 –“ ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል ። “
1ኛ ዮሐንስ 1፡9 –“ በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።