Historical Books Ezra

Ezra Returns to Jerusalem

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promise Keeper Ezra 6-8 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 321 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በኢያሱ መፅሀፍ እስራኤላዊያን ወደ ተስፋይቱ ምድር ተጓዙ ፤ በመሳፍንት ዘመን ጊዜ እስራኤላዊያን እግዚአብሄር ሊያድናቸዉ የሆነ ሰዉ እስኪያመጣላቸዉ ድረስ ማንንም አይሰሙም ከዚያም እየደጋገሙ ተመሳሳይ ነገር አደረጉ ፡፡ የሩት ታሪክ በዚያን ጊዜ የጎላ ክስተት ነበር ፡፡ ከዚያም በ1 እና በ2ሳሙኤል የሳዖልን እና የዳዊትን መቀባት አይተናል ፤ በ1 እና በ2 ነገስት ሰለሞን በመስራት የቤተ መቅደስ አምልኮን መሰረተ ነገር ግን በኃጢዓት ምክንያት መንግስቱ ወደ እስራኤልና ወደ ይሁዳ ተከፍሏል ፡፡ ከዚያም 1 እና 2 ዜና መዋዕል የነገስታትን ታሪክ ይደግማል ፡፡ አሁን ዕዝራ ሁሉንም ከፃፈው የ 1 እና የ 2ዜና መዋዕል አካል ሊሆን የሚችለዉ ዕዝራን እያጠናን ነው ፡፡ ከአመታት ስደትና ምርኮ በኋላ እስራኤል ወደ ተስፋይቱ ምድር ተመለሱ ፡፡ ከፋሪስ ተመልሰዉ ወደ ኢየሩሳሌም 900ና ከዚያ በላይ ማይል ተጓዙ ፡፡

እስራኤላዊያን ወደ ምድሪቱ ሲመለሱ ቤተ መቅደሱን መልሶ መገንባት ጀመሩ ነገር ግን ተቃዉሞ ስራቸዉን አስቆማቸው ፤ ስለዚህም የእግዚአብሄርን ቤት መልሰዉ እንዲሰሩ ንጉስ ቂሮስ ልኳቸዉ እንደ ነበር ማረጋገጫ ለማግኘት ንጉስ ዳርዮስን ጠየቁ ፡፡

ትምህርት

ዕዝራ (6፡ 1-10)፡ ቤተ መቅደሱ በኢየሩሳሌም መልሶ በመስራት በተገኘዉ በእግዚአብሄር ቤት የወርቁን እና የብሩን እቃ እንዲመለስ የንጉስ ቂሮስ ድንጋጌ ነው ፤ ከዚያም ንጉስ ዳርዮስ የአገሪቱ ገዢ የሆነዉን ተንትናይን እስራኤላዊያን በቀድሞዉ ስፍራ ላይ የእግዚአብሄርን ቤት መልሰዉ እንዲሰሩ እንዲፈቅድላቸው አዘዘዉ (ቁጥር 6-7) ፡፡ በተጨማሪም ዳርዮስ የቤተ መቅደሱ ወጪ ከንጉሱ ግብር እንዲከፈል እና ሁሉም አቅርቦቶች እንደ ጠየቁት በኢየሩሳሌም ለካህናቶቹ እንዲሰጡ አዘዘ (ቁጥር 8-10) ፡፡ እግዚአብሄር በድብቅ ስፍራ መፅሀፉን ለማግኘት ስሙ ያልተጠቀሰ ሰዉ ተጠቀመ እቅዱም መቀጠል ቻለ ፡፡ እስራኤላዊያን አብርሃም ይስሐቅን ለመሰዋት ተዘጋጅቶበት በነበረዉ ተመሳሳይ ስፍራ በሞሪያ ተራራ ቤተ መቅደሱን መልሰዉ ገነቡት ፤ ይህ ተመሳሳይ ምድር ዳዊት ከኦናን በገዛዉ መዉቂያ ዉድማ ስፍራ ላይ ነበር ፤ ይህ ሰለሞን የመጀመሪያ ቤተ መቅደሱን ከሰራበት ስፍራ ጋር ተመሳሳይ ነበር ፡፡ በምድብቅ ስፍራ ዉስጥ አንድ ፅሁፍ በመገኘቱ ምክንያት እስራኤላዊያን “ ከሕዝቤ ጋር ነኝ ፤ ይህ ቤተ መቅደስን እሰራዋለሁ “ በሚላቸዉ በእግዚአብሄር ተስፋ ተጓዙ ፡፡

ዕዝራ ፡ (6፡ 16)፡ እስራኤላዊያን፣ ካህናቶቹ፣ ሌዋዊያን እና ሕዝቡ ይህን የእግዚአብሄር ቤት መለየትን በደስታ አከበሩ ፤ ይህ ሁሉ በምሳሌ (21፡ 1) ንጉስ እንዲሰራ የሚፈልገዉን እንዲያደርግ ልቡን እንዲያስገዛ እግዚአብሄር ይፈቅዳል ተብሎ እንደተገለፀዉ ንጉስ ዳሪዮስ ታዛዥ በመሆኑ ምክንያት ይህ ሁሏ ሆነ ፡፡ እግዚአብሄር ቃል ኪዳን ጠባቂ ነው ፡፡

ዕዝራ (7፡ 8)፡ ቤተ መቅደሱም መልሶ የተገነባ ቢሆንም ሰለሞን ሰርቶት እንደ ነበረዉ ቤተ መቅደስ ታላቅ እና አብይ አልነበረም ፤ በዚህ ምዕራፍ ዕዝራ የስደተኞቹን ቡድን ወደ እስራኤል መራ ፡፡ አሁን በትክክል ዕዝራ በስዕሉ ገባ ፤ የመጀመሪያዉ የስደተኛ ቡድን ወስዶት ከነበረዉ አንድ መንገድ የተለያዩ መንገዶችን ወሰደ ፡፡

ዕዝራ (8፡ 1-14)፡ ዕዝራ ከእርሱ ጋር ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሱትን የቤተሰብ አለቆች ስም ዘረዘረ ፡፡ ዕዝራ ከሴቶች እና ከልጆች ጋር 1,500 ያክል የመሩ አስራ ስምንት ሰዎችን ዘረዘረ ፤ ይህ ቡድን ከ80 አመት በፊት ከዘሩባቤል እና ከኢያሱ ጋር ተመልሶ ከነበረዉ ቡድን በጣም የሚበልጥ አልነበረም ፡፡ ዕዝራ የእያንዳንዱን ቤተሰብ አለቃ ዘረዘረ (በቁጥር 3 ዘካሪያስ፣ በቁጥር 4 ኤሊሆዔናይ፣ በቁጥር 5 ከሴኬንያ ልጆች) ዝርዝር በዕዝራ 2 ላይም የተካተተ ነበር ፡፡ በዚህ ዝርዝር ያሉት የቤተሰብ አባላት በዕዝራ 2 ከተዘረዘሩት ሰዎች ጋር የተሳሰሩ ነበር ፡፡

ዕዝራ (8፡ 15-20)፡ ዕዝራ ይህን ሁሉንም ዘር ወደ አኅዋ በሚፈስሰዉ ወንዝ ላይ ለሰዎስት ቀን እንዲሰፍሩ ሰበሰባቸው ፤ ከተሰበሰቡት መካከልም ዕዝራ ሌዋዊ አላገኘም ፡፡ ዕዝራ ወንዙን በመሻገር ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለሱ ለማዘጋጀት ይህን ጊዜ በመጠቀም ለእርዳት ሰዎችን ለመላክ ከጌደሶዋዊያን ዘር የነበረዉን እንደ ቤተ መቅደስ አገልጋይ ያገለገለዉን የናታኒም አለቃን አዶን ጠየቀው ፤ አዶንም 38 ሌዋዊያንን እና 220 ናታኒሞችን ከዕዝራ ጋር የሚመለሱትን እስራኤላዊያንን እንዲመሩ ላካቸው ፡፡ ሌዋዊያን መኖራቸዉ ለሚመለሱት ሌዋዊያን ለምን በጣም አስፈላጊ ነበር ? ሌዋዊያን ስለ ሕዝቡ መስዋዕትን እንዲሰዉና ቤተ መቅደሱን እንዲከባከቡ በእግዚአብሄር የተሸሙ ነበሩ ፡፡ እነዚህ ሰዎች ስለ ኢየሩሳሌም በሚሄዱት ፊት ተሰበሰቡ ፤ ይህ የመሪነት አንዱ ቁልፍ ነው ፡፡ ዕዝራ ከእግዚአብሄር ሰምቶ እንደ ነበር እርግጠኛ ስለሆነ ስራዉን እንዲሰሩት ሌሎችን አመናቸው ፤ አልተከተላቸዉም ወይም በብዙ አልተማመነባቸዉም ነገር ግን ስራዉን ለመስራት ሌዋዊያንና እና ናታኒምን እንደ ሚያገኙ በእግዚአብሄር ተማመነ ፡፡

ዕዝራ (8፡ 21-23)፡ በተጨማሪም ዕዝራ በአኅዋ ወንዝ አጠገብ ፆም አወጀ እስራኤላዊያንም በእግዚአብሄር ፊት ራሳቸዉን ዝቅ ማድረግ ለራሳቸዉ እና ለንብረታቸዉ ስለ ደህንነት ጉዞ ጠየቁ ፡፡ ማክአርቱር በቅርብ በሌቦች በተደጋጋሚ በሚያዘወተሩበት መንገድ ላይ ረጅም ጉዞ ይጀምራሉ አለ ፡፡ ዕዝራ ይህን አደረገ ምክንያቱም ስለ ጥበቃ ንጉስ ዳርዮስን ለመጠየቅ አልፈለገምምክንያቱም እስራኤላዊያን ንጉስ ዳርዮስን እግዚአብሄር እንደሚጠብቃቸዉ ነግረዉት ስለ ነበር ፡፡ በነህ (2፡ 7-8) ነህምያ ንጉስ አርጤክስስን በኤፍራጠስ አካባቡ ላሉት መንግስታት ወደ ኢየሩሳሌም ቡድኖቹ በጉዞአቸው በደህንነት እንዲያልፉ እንዲያረጋግጡላቸዉ እና በሮቹን፣ የከተማ ቅጥር እና ቤቶችን መልሶ ለመስራት ስለ እንጨቶች ወደ አሳፍም ደብዳቤዎችን ጠየቀው ፡፡ ዕዝራ ጥበቃን ከእግረኛ ጦርና ከፈረሰኛ አላገኘም ነገር ግን ነህምያ ለዚህ ጠይቋል ፡፡ እንደ አማኝ በጊዜዉ ለእርዳታ መጠየቅ ያስፈልገናል ፡፡ በሐዋሪያት ስራ 23 ጳዉሎስ ከኢየሩሳሌም ወደ ቂሳርያ በነበረዉ ጉዞዉ በሮማዉያን ወታደሮች በመጠበቁ ደስተኛ ነበር ፡፡ በጉዞአችሁ ላይ ጥበቃን ስትጠይቁ ደካሞች አይደላችሁም ፡፡ ዕዝራና እስራኤላዊያን በመፆም (ይህ ማለት ምግብ የለም (አይበሉም)) እግዚአብሄርን ጠየቁ መለሰላቸዉም ፡፡

ዕዝራ (8፡ 24-30)፡ ዕዝራ ንብረታቸዉንወደ ኢየሩሳሌም መልሰዉ የሚሸከሙ ከሰራብያን እና ከሐሸቢያ ጋር አስራ ሁለት ካህናቶችን እና አስር ወንድሞቻቸዉን መረጠ ፤ በዚህ ጉዞ ላይ ዕዝራ እነርሱን እና ዋጋ ያላቸዉን ንብረታቸዉን እግዚአብሄር እንደሚጠብቅላቸዉ በሙሉነት አምኖት ነበር ፡፡ ከፍተኛ መጠን ያለዉ ገንዘብ ነበራቸዉ ነገር ግን ፍፁም የሆነ ጥበቃ ከያህዌ ተቀበሉ ምክንያቱም ተስፋዎቹን ስለሚጠብቅ ፡፡ እግዚአብሄር ጥያቄአቸዉን ሰማ መለሰላቸዉም ፡፡

ዕዝራ (8፡ 31-36)፡ በመጀመሪያዉ ወር በአስራ ሁለተኛዉ ቀን ኢየሩሳሌም ለመሄድ ተነሱ ፤ እግዚአብሄርም በመንገዳቸዉ አበረታቸዉ ጠበቃቸዉም ፡፡ ከደረሱም በኋላ ለሰዎስት ቀናት በኢየሩሳሌም አረፉ ከዚያም በአራተኛዉ ቀን ለካህኑ ሜሪሞት ሁሉንም ነገር ሰጡ ፤ ከእነርሱ ጋር አምጥተዉት የነበረዉ ሁሉም ነገር ለመመዘን ነበር ፤ ከዚያም ለእግዚአብሄር የሚቃጠል መስዋዕት አቀረቡ ፡፡ በተጨማሪም በአገሩ ለነበሩ ገዢዎች የንጉሱን ትዕዛዞች ሰጡ ገዢዎቹም እስራኤላዊያንን እና የእግዚአብሄር ቤትን ይደግፋሉ ፡፡

መደምደሚያ

በዕዝራ (6-8) ገንዘቡ ለቤተ መቅደሱ ተሰጠ፣ ሕዝቡ እግዚአብሄርን ማምለክ እየጀመሩ ነበር ፤ ነገ የዕዝራን መፅሀፍ እንዘጋለን እግዚአብሄርም እንዴት ተስፋዎቹን እንደሚጠብቅ እናያለን ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 529.

  2. MacArthur, p. 529.

ጥያቄዎች

  1. በንጉስ ዳርዮስ ዘመን ጊዜ የተገነባዉ ቤተ መቅደስ በመጠን እና በአስገራሚነት (በድንቅነት) በንጉስ ሰለሞን ጊዜ ተሰርቶ ከነበረዉ ቤተ መቅደስ ጋር ተመሳሳይ ነበር ? (1ነገ 6፡ 2-3)
  2. ይህ ቤተ መቅደስ ለመቀደስ ተሰዉተዉ የነበሩት ብዙ ቁጥር እንስሳቶች በሰለሞን ከተሰራው ቤተ መቅደስ ጋር ስናወዳድረው ለምን በጣም የተለያየ ንደ ነበር ምን ታስባላችሁ ? (1ነገ 8፡ 63)
  3. በዕዝራ (6፡ 18) የትኛዉን የሙሴ መፅሀፍ እየጠቀሱ ነበር ?
  4. ዕዝራ (7፡ 6, 10) ዕዝራን በሙሴ ህግ ላይ እንደ ተማረ ፀሀፊ እና የእግዚአብሄር እጅ በእርሱ ላይ እንደሆነ በመናገር ይገልፃል ፤ ዕዝራ ባደረገው መንገድ እግዚአብሄርን በመፈለግ እና በመታዘዝ ልባችንን ስናዘጋጅ ለሌሎች የሚታወቅ ይሆናል ?
  5. በአንዳንድ ሀገራት ቤተ ክርስቲያን የአካባቢን፣ የግዛትን(የብሄርን) ወይም የሀገርን ግብሮች አይከፍሉም ፤ ይህ ከዕዝራ (7፡ 24) መጥቷል ብላችሁ ታስባላችሁ ?
  6. በዕዝራ (6-8) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Ezra 8:31–32

“We set out from the Ahava River on the twelfth day of the first month to go to Jerusalem. We were strengthened by our God, and He protected us from the power of the enemy and from ambush along the way. So we arrived at Jerusalem and rested there for three days.”

ዘሩባቤል እና ኢያሱ በግዞት የነበሩ እስራኤላውያንን ወደ ኢየሩሳሌም መልሰው ከመሩ ከሰማንያ ዓመት በኋላ ዕዝራ ከተለያዩ የእስራኤላውያን ማኅበር ጋር ተመለሰ ፡፡ ከመመለስ ጉዞአቸው በፊትም ለተጓዦቹና ለንብረታቸው መልካም ጉዞ እንድሆን ለመለመን ዕዝራ በእግዚአብሔር ፊት ሁሉም ራሳቸውን ያዋርዱ ዘንድ ፆምን አወጀ ፡፡ ይህም ማህበር ከጠባቂ ወታደር ወይም ፈረሰኛ ውጭ የእግዚአብሔርን ብርቱ እጅ ይጠብቃቸው ዘንድ በመለመን ተጓዙ ፡፡ በጉዟቸውም እግዚአብሔር አበረታቸው እንድሁም ከጠላቶቻቸውና ከተዋጊዎች ሁሉ አዳናቸው ፡፡ እግዚአብሔርም ወደ ኢየሩሳሌም ለሚያደርጉት ጉዞ የጸለዩትን ጸሎት መለሰ ፡፡

እርሱ ለሚመራህ ጉዞ እግዚአብሔር በቂ ነው ፡፡ ወደ እርሱ እየተመለስክ ይሁን ፤ በአድስ ጥሪ እርሱን እየተከተልክ ይሁን ወይም በጽናት ውስጥ መቆየት ፣ እንዳትፈራ ደግሞም እንዳትሸበር ፡፡ ጭንቀቶችህንና ፍርሃቶችህን ከእርሱ እግር ስር ጣል ፡፡ ጹም ፤ እግዚአብሔር እንደሚጠብቅህና አንደሚያበረታህ እመን ፡፡ እግዚአብሔር በጎንህ ጠላቶችህ እንድወድቁ ያደርጋል ፡፡ ጽና ፤ እግዚአብሔርንም ፈልግ እናም በመንገድህ በትህትና ተመላለስ ፡፡ እርሱ ይረዳህ ዘንድ ከአንተ ጋር ነው ፡፡ ብርሃንህና ደህንነትህ ነው ፡፡ ዛሬ በታማኝ ተስፋዎቹ ላይ እረፍ ፡፡ እግዚአብሔር ያይሃል ደግሞም ከአንተ ጋር ነው ፡፡

“ በመጀመሪያውም ወር በአሥራ ሁለተኛው ቀን ወደ ኢየሩሳሌም እንሄድ ዘንድ ከአኅዋ ወንዝ ተነሣን የአምላካችንም እጅ በላያችን ነበረ፥ በመንገድም ከጠላትና ከሚሸምቅ ሰው እጅ አዳነን ። ወደ ኢየሩሳሌም ደረስን፥ በዚያም ሦስት ቀን ተቀመጥን ። “

  • ዕዝራ 8፡31-32

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 27:1–3 — “ እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው ? ክፉዎች፥ አስጨናቂዎቼ ጠላቶቼም፥ ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ በቀረቡ ጊዜ፥ እነርሱ ተሰናከሉና ወደቁ ። ሠራዊትም ቢሰፍርብኝ ልቤ አይፈራም፤ ሰልፍም ቢነሣብኝ በዚህ እተማመናለሁ ። “

2ኛ ተሰሎንቄ 3:3 — “ ነገር ግን የሚያጸናችሁ ከክፉውም የሚጠብቃችሁ ጌታ የታመነ ነው ። “

2ኛ ጢሞቴዎስ 4:18 — “ ጌታም ከክፉ ነገር ሁሉ ያድነኛል ለሰማያዊውም መንግሥት ይጠብቀኛል፤ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን ። “