Rebuilding the Temple
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promise Keeper Ezra 3-5 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ለ70 አመታት እስራኤላዊያን በምርኮ ነበሩ ነገር ግን አሁን ወደ ምድራቸዉ ለመመለስ ተለቀዋል ፡፡ ከ 1ዜና መዋዕል እና ከ 2ዜና መዋዕል እስራኤላዊያን እንዴት ምርኮኛ ለመሆን እንደ መጡ እና ወደ እግዚአብሄር ለመመለስ ምን ማድረግ እንደ ነበረባቸው ተምረዋል ፡፡ ንጉስ ቂሮስ እስራኤላዊያንን (ከፋሪስ፣ ከቀድሞዉ ከባቢሎን) በመልቀቅ ከተማቸዉን ኢየሩሳሌምን እና ቤተ መቅደሳቸዉን እንደ ገና እንዲሰሩ ፍቃድ ሰጣቸው ፡፡
ትምህርት
ዕዝራ (3፡ 1)፡ ዕዝራ ስለ ጉዞአቸዉ አላወራም ነገር ግን በሰባተኛዉ ወር ሕዝቡ በአንድ ላይ በኢየሩሳሌም እንደተሰባሰቡ ብቻ አሳወቀ (ተናገረ) ፡፡ አሌክሳንደር ማክላረን “ ሁሉንም በአንድ ላይ የደበቀ የአንድ ሰዉ የጉዞ መግለጫ የሆነ….የተፃፈ ነገር ግን መጀመሪያ እና መጨረሻ እንደሆነ ፤ በሁሉም ህይወት እነዚህ በአቅጣጫ እና በማግኘት ዋና ሀሳብ አይደሉም ? “ በማለት አስተያየት ይሰጣል ፤ ዘፍ (12፡ 4-5) ስለ አብራም ጉዞ ተመሳሳይ መግለጫ ሰጥቷል ፡፡ የእምነት ዉበት ያ ነው…ጉዞ ስናደርግ በእግዚአብሄር ላይ መደገፍ አለብን ፡፡
ዕዝራ (3፡ 2-3)፡ ዕዝራ የእግዚአብሄርን መሰዊያ መስራት የጀመሩትን ሰዎስ ስም ዘረዘረ ፡፡ ኢያሱ እና ዘሩባቤል የዚህ የእስራኤላዊ ቡድን መንፈሳዊ እና ህዝባዊ መሪ ነበሩ ፤ በዙሪያቸዉ የነበሩትን ሰዎች ቢፈሩም እንኳን ሁልግዚ ማለዳና ማታ ለእግዚአብሄር የሚቃጠል መስዋዕት አቀረቡ ፡፡ ቤተ መቅደሱ ሲያልቅ ይደረግ እንደ ነበረዉ የዳስ በዓልን አመለኩም አከበሩም ፤ ቤተ መቅደሱም አልቆ እንደ ነበረዉ መኖርን መረጡ ምክንያቱም መልሶ ለመገንባት ጊዜ ስለሚወስድ ፡፡ ይህን የሚመስል አንድ ጉባኤ ለ70 አመታት(የምረኮዉን ጊዜ) አልወሰደበትም ነበር ፡፡ መሰዊያዉን ሲሄዱ ቀርቶ በነበረዉ መሰረት ላይ ሰሩት ፤ እንደ ገና በዘፍ (12፡ 7) ከነዓን በደረሰ ጊዜ ወዲያዉኑ ለእግዚአብሄር መሰዊያን የሰራዉን የአብርሃምን ድርጊት ያስተጋባል ፡፡ በማቴ (6፡ 33) መጀመሪያ እግዚአብሄርን እንድንፈልግ ከዚያም ሁሉም እንደሚሰጠን ተነግሮናል ፤ ስለዚህ ወደ አዲስ ስራ፣ ወደ አዲስ ትዳር፣ ልጆች ሲመጡ ወይም ማንኛዉም ሁኔታ በመጣን ጊዜ ስለ ሚያስፈልጉን ነገሮች የምናስብ መሆን የለብንም ፤ ስለ እግዚአብሄር ብቻ የምናስብ መሆን ያስፈልገናል ፡፡ ለእስራኤላዊያን መሰዊያዉ የእምነታቸዉን እሳት አቀጣጠለው ስለዚህ መስራት የሚያስፈልጋቸዉን እንዲሰሩ አስቻላቸው ፡፡
ሕዝቦቹን ቢፈሯቸዉም እንኳን ይህ ፍራት መሰዊያዉን ከመትከል እና እግዚአብሄርን ከማምለክ እንዳልከለከላቸዉ አስታዉሉ እስራኤላዊያን የፈሯቸዉ በዙሪያቸዉ የነበሩት ሕዝቦች እነማን ነበሩ ? እንደ ማክአርቱር አገላለፅ እነዚህ ተቀማጮች (ሕዝቦች) እስራኤላዊያን ተወስደዉ በነበረ ጊዜ አሶራዊያን እና ባቢሎናዊያን አምጥተዋቸዉ የነበሩ ሰፋሪዎች ነበሩ ፤ እስራኤላዊያን ሲመለሱ ሰፋሪዎቹ እንደ ማስፈራሪያ አዩአቸው ፡፡
ዕዝራ (3፡ 4-6)፡ እስራኤላዊያን የዳስ በዓልን በዘኁልቁ 29 እንደ ተገለፀዉ ህጉ እንደሚጠይቀዉ አከበሩ ፡፡ ቤተ መቅደሱ እንኳን እንደ ገና የተገነባ ባይሆንም እግዚአብሄርን እያከበሩና እየፈለጉ ነበር ፡፡
ዕዝራ (3፡ 7-13)፡ በእነዚህ ቁጥሮች ላይ እስራኤላዊያን የቤተ መቅደሱን መሰረት ጣሉ ፡፡ ጠራቢዎችን እና አናጢዎችን ከፈሉ ፡፡ በንጉስ ቂሮስ እንደ ተፈቀደላቸዉም ከሊባኖስ የዝግባ እንጨት አመጡ ፡፡ ኢሳ (60፡ 10-14)
ቅጥራቸዉን ምፃተኞች እንደሚሰሩት ነገስታቶችም እንደሚያገለግሉዓቸው ለሊባኖስም ክብር ጥዶቿ፣ አስታናዋ እና ባረሰቱ የእግዚአብሄርን ማደሪያ ስፍራ ለማስዋብ ይመጣሉ ፡፡
በሁለተኛ አመት በሁለተኛዉ ወር መገንባት ጀመሩ ፤ ስራዉን እንዲቆጣጠሩም ሌዋዊያንን ሾሙ (ቁጥር 8) ፤ እንደ ዋይርስቤ አገላለፅ ይህ ማለት ለመስሪያ ማቴሪያል ሲሰበስቡና ሲዘጋጁ ሰባት ወር ቆይተዋል ማለት ነው ፡፡ በመዝ (11፡ 3) ዳዊት መሰረቱ ጠፍቶ በነበረበት ጊዜ ፃድቃን ማድረግ ስለሚችሉት ተደንቋል ፤ እዚህ ኢያሱ እና ዘሩባቤል በመሰረቱ ላይ መልሰዉ ለመስራት ሕዝቡን መሩ (ቁጥር 9-10) ፡፡ ይህ መፅሀፍ በዕዝራ የተሰየመ ቢሆንም እንኳን ዕዝራ በኢየሩሳሌም አልነበረም ፤ የዚህ ህንፃ ስራ በኢያሱና በዘሩባቤል የተመራ ነበር ይህም ቤተ መቅደስ የዘሩባቤል ቤተ መቅደስ በመባል ይታወቅ ነበር ፡፡ ከሕዝቡም መካከል አንዳንዶቹ ዘሩባቤል የሚመጣዉ ንጉስ እንደ ነበር አስበዋል ፡፡ በሐጌ (2፡ 23) እግዚአብሄር ዘሩባቤልን በመዉሰድ እንደ ቀለበት ማተሚያም አደርገዋለሁ አለ ፡፡ ዘካ (4፡ 6-10) ከሕዝቡ መካከል የሚመጣዉ ንጉስ እንደ ነበር የሚያምኑትን የመራዉን ዘሩባቤልን በተመሳሳይ ቋንቋ ገልፆታል ፡፡ ነቢያቶች ዘሩባቤል ቤተ መቅደሱን መልሶ ሰርቶ ባዩ ጊዜ እንደ ሚደሰቱ እስራኤልን ተናግረው ነበር ፤ ነገር ግን ዘሩባቤል የሚመጣዉ ንጉስ አልነበረም - ወደ ንጉሱ አመለከተ ፡፡
ሰራተኞቹ የቤተ መቅደሱን መሰረት በጣሉ ጊዜ ካህናቱና ሌዋዊያን እግዚአብሄርን ለማመስገን ስፍራቸዉን ወሰዱ (ያዙ) ፤ ዳዊት አዞ እንደ ነበረው (ቁጥር 10) ዘመሩም እግዚአብሄርንም አመሰገኑ ምክንያቱም ምህረቱ ለዘላለም ስለሆነ (ቁጥር 11) ፡፡ መዝሙር (136፡ 1) እግዚአብሄር መልካም እንደሆነና ምህረቱም ለዘላለም እንደ ሆነ ያሳስበናል፡፡ በትክክል የሚናገረው ከባርነት፣ ከምርኮ፣ ከአስቸጋሪ ሁኔታ፣ ከበሽታ ወይም ከፋይናንስ ሰልፍ መዉጣት እንችላለን ማለት ነው ፡፡ ምንም አድርጉ ምንም ይግጠማችሁ ችግር የለም እግዚአብሄር እዉነተኛ ቃል ጠባቂ ስለሆነ ፤ በዘፍጥረት 12 እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን መረጠ ፡፡ አሁን አልረሳችሁም ወይም አልተዋችሁም አለ - አሁንም የተመረጡ ሕዝቦቹ ናቸው ፤ ይህ ለዕዝራ ቃላችን ነው - እግዚአብሄር ቃል ኪዳን ጠባቂ ነው ፤ ከ70 ምርኮ አመታት በኋላ እስራኤላዊያን እግዚአብሄርን በመፈለግ ራሳቸዉን እንደገና አቋቋሙ ፡፡
ቤተ መቅደሱን እንደ ገና መስራት እንዴት ወደ መሲሁ ያመለክታል ? 2ቆሮ (1፡ 20) የሚለው “ እግዚአብሄር ለሰጠው የተስፋ ቃል ሁሉ አዎን ማለት በእርሱ ነዉና “ ፤ የእግዚአብሄር ተስፋዎች በመጨረሻም በክርስቶስ የተፈፀሙ ናቸው ፡፡ ይህ የመጨረሻዉ ቃል ኪዳን ጠባቂ የክርስቶስ ጥላ ነበር ፤ እግዚአብሄር እስራኤላዊያን ከምርኮ ሲወጡ የመረጣቸዉን ሕዝቡን አልረሳም እንዲሁም በአለም መዉደቅ(ማብቂያ) ጊዜ እናንተና እና እኔን አይረሳም ፡፡ እግዚአብሄርን መፈለግ ስንቀጥል እግዚአብሄር ተስፋዉን ይጠብቃል ፡፡
የመጀመሪያዉን ቤተ መቅደስ አይተዉ የነበሩት አብዛኞቹ የሸመገሉ ካህናቶች፣ ሌዋዊያኖች እና የቤተሰብ አለቆች በታላቅ ድምፅ አለቀሱ (ቁጥር 12) ፤ ይህ በአዲሱ ዉስጥ ከሰለሞን ቤተ መቅደስ ተመሳሳይ የሆነ ዉበት ባለማየታቸው መናደዳቸዉን ያሳያል (1ነገስት 5-7) ፡፡ ማክአርቱር እንዳለ ይህ ቤተ መቅደስ ትንሽ እና ከዳዊት ብልፅግና ዉጪና ከሰለሞን ቀን ዉጭ እና የኪዳኑ ታቦት ስላልነበረ ዉበቱ ያነሰ ነበር ብሏል ፤ መሰዊያዉ ከታቦቱ ጋር ተመሳሳይ አልነበረም ፡፡ መሰዊያዉ መስዋዕት ይደረግበት ነበር ነገር ግን ታቦቱ የእግዚአብሄር መገኘት የሚያርፍበት(የሚያድርበት) ነበር ፡፡ ሽማግሌ ሰዎቹ እያለቀሱ ነበር ምክንያቱም የእግዚአብሄር ታላቅ ክብር በዚያ ስላልነበር ፤ በተመሳሳይ ጊዜ ወጣቶቹ ደግሞ በደስታ ጮኹ ምክንያቱም አዲስ በሆነ ነገር የሚጓዙ ስለሆነ ተደስተዉ ነበር ፡፡ መዝሙር (126፡ 1-6) የፂዎን መታደስን እንደ ማክበሪያ መዝሙር ተፅፏል ፡፡
መደምደሚያ
እግዚአብሄር ነገርን መልካም ሲያደርግ ስንመለከት የእምነትን እሳት ማቀጣጠል አለብን ፤ ትንሽ ጅማሬዎችን መናቅ የለብንም ምክንያቱም እግዚአብሄር ተስፋዉን በልጆቹ የሚጠብቅ ነው ፡፡
በዕዝራ 4 ሳማሪታዊያን የቤተ መቅደሱን መልሶ መገንባት ተቃወሙ ንጉስ አርጤክስስም ግንባታዉን አስቆመው ፤ ነገር ግን በዕዝራ 5 ዘካሪያስ እና ሐጌ መልዕክታቸዉን ከንጉሱ በመቀበል የቤተ መቅደሱ ግንባታ ቀጠለ ፡፡ እግዚአብሄር መልካም ነገር ሲያደርግ ተቃዉሞ ከዉጪና ከዉስጥ ይመጣል ፡፡
Warren Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2007), p. 737..
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 524.
MacArthur, p. 524.
Wiersbe, p. 737.
MacArthur, p. 524.
ጥያቄዎች
-
ሕዝቡ መሰዊያዉን መልሰዉ ሲሰሩ የሀረጊቱን ነዋሪዎች ለምን ነበር የፈሩት ? በፍርኃትም ሆነዉ ቢሆን መስራታቸዉን ቀጠሉ ፡፡ ይህ እግዚአብሄር መታዘዝን ለመቀጠል እና ለክርስቶስ ፅኑ ምስክር ለመሆን እንዴት ያበረታታችኋል ?
-
ሕዝቡ በአንድነት ያደረጉዓቸዉ ሰዎስት ነገሮች ምን ነበሩ (ዕዝ 3፡ 1, 9, 11) ? በአንድ ላይ ለመፈፀም ዋና አላማቸው ምን ነበር ? በአሁኑ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን አንድነትን ታያላችሁ (ፊል 2፡ 2) ? ለምን ወይስ ለምን አታዩም ?
-
“ ታላቅ ተቃዉሞ ታላቅ እድል ነው “ በሚለዉ ንግግር ትስማማላችሁ (1ቆሮ 16፡ 9) ? በዚህ ምዕራፍ 4 ያ ሲጫወት እንዴት ታዩታላችሁ ? እግዚአብሄር ለሆነ ነገር እንደ ጠራን ስናዉቅ እንዴት ምላሽ እንሰጣለን ? (ፊል 1፡ 6)
-
በምዕራፍ 4 የቤተ መቅደሱን መልሶ መሰራትን ለማስቆም ጠላት ለመጠቀም የሞከሩባቸዉ ጥቂት ሴራዎች ምን ነበሩ ? ለእያንዳንዱ እስራኤላዊያን እንዴት መለሱ ?
-
ቤተ መቅደሱን መልሶ ለመስራት ፍቃድ ማን እንደሰጣቸዉ በተጠየቁ ጊዜ በምዕራፍ 5 ሕዝቡ መጀመሪያ እንዴት መለሱ ? ተቃዉሞ በመጣ ጊዜ ለኢየሱስ ታማኝነትን ትወስዳችሁ ? ከሌሎቹ ጊዜ በላይ በአንዳንድ ጊዜ ላይ ለምን በጣም አሰቸጋሪ ነው ?
-
በዕዝራ (3-5) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Ezra 3:11–12
“They sang with praise and thanksgiving to the LORD: ‘For He is good; His faithful love to Israel endures forever.’ Then all the people gave a great shout of praise to the LORD because the foundation of the LORD’s house had been laid. But many of the older priests, Levites, and family leaders, who had seen the first temple, wept loudly when they saw the foundation of this house, but many others shouted joyfully.”
ከሰባ የግዞት አመታት በኋላ ህዝቡ ቤተ መቅደሱን ለመገንባት እንደገና ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ ፡፡ አድሱ መሰረትም በተጠናቀቀ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ በታላቅ ድምፅ እልል አሉ ፡- “ ቸር ነውና፥ ለእስራኤልም ምሕረቱ ለዘላለም ነውና “ እያሉ አመሰገኑ ፡፡ ሆኖም ግን አንዳንዶች ሲያመሰግኑ የፊተኛውን ቤት ያዩ ሽማግሌዎች እስራኤል ያደረገውን ፤ እግዚአብሔር ሊያደርግ የነበረውንና የጠፋውን ሁሉ አስታውሰው አዘኑ ፣ በታላቅ ድምፅ ያለቅሱ ነበር ፡፡
ወደ እርሱ ስትመለሱ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ወደ ሕይወታችሁ ይመልሳል ፡፡ እርሱ የምድርን መሰረቶች ጥሏል እናም አናንተ እርሱን ስትከተሉ መሰረታችሁና ፅኑ ዓለታችሁ ይሆናል ፡፡ እንደገና መሰረታችሁን መጣል የሚኖርባችሁ ጊዜያት ይኖራሉ ፡፡ ከባርነት ትላቀቃላችሁ ወይም ከምሬት ጊዜያት ፤ ከተስፋ መቁረጥ ጊዜያት ወይም ከዝምታ ጊዜያት ትወጣላችሁ ፡፡ እንደገና መሰረታችሁን በእግዚአብሔር ስትመሰርቱ ፣ ስለ አድሱ ጅማሬያችሁና ከፊታችሁ ስላለው ነገር ሃሴት በማድረግ ታመሰግናላችሁ ምናልባትም ደግሞ ባለፈው ስለተፈጠረው ነገር ሀዘን ሊሰማችሁ ይችላል ፡፡ አዎንና አሜን የሆኑትን ተስፋዎቹን ማስታወሳችሁን ቀጥሉ ፡፡ ቸር ነው ታማኝ ፍቅሩም ለዘላለም ነው ፡፡ እግዚአብሔር ለማዳን ይችላል ፤ ለደካማውም ኃይልን ይሰጣል እያንዳንዱን ውጊያዎቻችሁንም ይዋጋል ፡፡ አለም እንደ አሸዋ በሚንሸራተትበት ጊዜ ፣ ክርስቶስ ብቻ ነው ፅኑ መሰረት የሚሆናችሁ ፡፡ በእርሱ አትሸበሩም ፡፡
“ ደግሞ፦ ቸር ነውና፥ ለእስራኤልም ምሕረቱ ለዘላለም ነውና እያሉ እግዚአብሔርንም እያመሰገኑና እያከበሩ እርስ በእርሳቸው ያስተዛዝሉ ነበር፤ የእግዚአብሔርም ቤት ስለ ተመሠረተ ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ በታላቅ ድምፅ እልል አሉ ። የፊተኛውን ቤት ያዩ ሽማግሌዎች የሆኑ ብዙ ካህናትና ሌዋውያን የአባቶችም ቤቶች አለቆች ግን ይህ መቅደስ በፊታቸው በተመሠረተ ጊዜ በታላቅ ድምፅ ያለቅሱ ነበር ብዙ ሰዎችም በደስታ ይጮኹ ነበር ፡፡ “
- ዕዝራ 3፡11-12
ተጨማሪ ጥቅስ
- መዝሙር 62:6 — “ እርሱ አምላኬ መድኃኒቴም ነውና፤ እርሱ መጠጊያዬ ነው አልታወክም ። “
- ማቴዎስ 16:18 — “ እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም ። “
- 2ኛ ቆሮንቶስ 1:20 — “ እግዚአብሔር ለሰጠው የተስፋ ቃል ሁሉ አዎን ማለት በእርሱ ነውና፥ ስለዚህ ለእግዚአብሔር ስለ ክብሩ በእኛ የሚነገረው አሜን በእርሱ ደግሞ ነው ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።