Historical Books Ezra

The Release of the Captives

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Promise Keeper Ezra 1-2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 319 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዛሬ ቀጣዩን የታሪክ መፅኀፍት ዕዝራን እንጀምራለን ፡፡ ዜና መዋዕል መጨረሻ ላይ ዘመናቸዉ ከኢዮስያስ ተከትሎ የሆነ እና ሁሉም በእግዚአብሄር ፊት ክፉ ነገር ያደረጉ በይሁዳ አራት ነገስታቶችን አይተናል ፡፡ አራቱም በእስራት ጨረሱ ቤተ መቅደሱና የኢየሩሳሌም ከተሞች ጠፉ ፡፡ በኤርምያስ በኩል የመጣዉ የእግዚአብሄር ቃል በፋሪስ ንጉስ በቂሮስ የተፈፀመ ነበር ፤ ሕዝቡ ለ70 አመታት በምርኮ ተቀመጡ ፤ በዕዝራ መፅሀፍ እግዚአብሄር ለሕዝቡ ቃል ኪዳኑን ጠበቀ (ዘፍ 12፡ 1-3) ፡፡ እግዚአብሄር በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደሱን እንደ ገና ለማቋቋም ዕዝራን ተጠቀመ ፤ በሚያስደንቅ ሁኔታ የዕዝራ መፅሀፍ በአዲስ ኪዳን በፍፁም አልተጠቀሰም ፡፡

የዕዝራ ስም እስከ ዕዝ (7፡ 1) ድረስ በመፅሀፉ አልታየም (አልተከሰተም) በዕዝ (7፡ 5) ከክህነት ዘር ከአሮን እንደ መጣ የተገለፀ ነው ፡፡ ዕዝራ የሚለዉ ስም “ ጅሆቫ (አምላክ) ይረዳል “ ማለት ነው ፡፡ የአይሁድ ልምዶች ነቢዩን ዕዝራን የዚህ መፅሀፉ እንደ ፀኀፊና እንዲሁም የነህምያን መፅሀፍንም እንደ ፀሀፊ ይቀበላሉ ፡፡ ምናልባት የዕዝራ እና የነህምያ መፅሀፍ እንደ አንድ መፅሀፍ ተፅፈዉ የነበሩና እና ቆይተዉ የተለያዩ ነበሩ ፡፡ በመጀመሪያዎቹ በስድስት ምዕራፎች የዕዝራ መፅሀፍ በሰዎስተኛ አካል ተፅፎ ነበር ከዚያ ግን በምዕራፍ (7-10) ወደ መጀመሪያዉ አካል ተዛወረ (ተንቀሳቀሰ) ፡፡ በተጨማሪም ዕዝራ የዜና መዋዕል ፀሀፊ እንደ ሆነ የሚታመን ነው ፡፡ የአይሁድ ልምድ “ ዕዝራ የብሉይ ኪዳን ሙሉ ህግ በመጀመሪያ በመደበኛ(በትክክለኛ) ሁኔታ ዕዉቅና የተሰጠበት የታላቁ ምኩራብ መስራች እንደ ነበር ያምናሉ “ ፡፡ ለዕዝራና ለነህምያ የጊዜ ሰሌዳዉ ይህን ይመስላል፡

  • 586 ከክርስቶስ ልደት በፊት የቤተ መቅደሱና የኢየሩሳሌም መጥፋት እና የመጨረሻዉ ስደት ፡፡
  • 538 ከክርስቶስ ልደት በፊት ዕዝ ራ (1-6) ፤ ዘሩባቤልና ኢያሱ በፋሪስ ንጉስ በቂሮስ አስተዳደር ስር እንደ መሪ ገቡ ፡፡
  • 458 ከክርስቶስ ልደት በፊት ዕዝራ (7-10) ፤ በንጉስ አርጤክስስ ስር ዕዝራ የአይሁድ ካህን ነበር ፡፡
  • 445 ከክርስቶስ ልደት በፊት ነህምያ (1-13) ፤ በንጉስ አርጤክስስ ስር ነህምያ የአይሁድ ካህን ነበር ፡፡

የመጀመሪያዉ ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም የሰለሞን ቤተ መቅደስ በመባል ይታወቅ ነበር ፤ በዕዝራ ሁለተኛዉ ቤተ መቅደስ የዘሩባቤል ቤተ መቅደስ በመባል ይታወቅ ነበር ፡፡ ሰዎስተኛዉ ቤተ መቅደስ የሄርዶስ ቤተ መቅደስ በመባል የሚታወቅ ሲሆን በአዲስ ኪዳን የነበረ ቤተ መቅደስ ነበር ፡፡ አራተኛዉ ቤተ መቅደስ ለመጨረሻዉ ጊዜ አሁንም ለመምጣት በዝግጅት ላይ ነው ፡፡ ሕዝቡ ከምርኮ ተለቀዉ ቤት ሲመለሱ በመጠኑ ሕዝቡ ከግብፅ ሲለቀቁ እና ወደ ተስፋይቱ ምድር መምጣታቸዉን የሚያሳይ ነው ፡፡ እግዚአብሄር ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱት ጋር ኪዳኑን እንደ ገና አቋቋመ ፡፡

ትምህርት

ዕዝራ (1፡ 1-4)፡ ለኤርምያስ የገለጠዉን ተስፋዉን ለመፈፀም እግዚአብሄር በመጀመሪያዉ አመቱ ላይ የፋሬስን ንጉስ ቂሮስን ተጠቀመ (ቁጥር 1) ፤ ይህ በ70 የምርኮ አመት መጨረሻ ላይ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር በቂሮስ ሀሳብ ዉስጥ ይሁዳን ከምርኮ ነፃ እንደሚያወጣና ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰዉ የእግዚአብሄርን ቤተ መቅደስ መልሰዉ እንዲሰሩ እንደሚፈቅድላቸው አዋጅ እንዲሰጥ አስቀመጠበት ፡፡ ቂሮስም አዋጁን በፅሁፍ አስቀመጠ (ቁጥር 2-4) (ኤር 25፡ 8-12) ፤ በኤር (25፡ 11) ያለዉ ትንቢት በዕዝራ መፅሀፍ ተፈፅሟል ፡፡ እግዚአብሄር በእጁ ይዞ ነበር (ምሳ 21፡ 1) ፡፡ ዋይርስቤ በዚህ አዋጅ ምክንያት 50,000 እስራኤላዊያን በመመለስ ምርኮኞቹ በሚኖሩበት በእያንዳንዱ በባቢሎን አካባቢ የተወሰደዉን ስጦታ አንዳመጡ ይገልፃል ፡፡ ስለ እነዚህ ስለተመለሱት እስራኤላዊያን የዜና መዋዕል መፅኀፍት ቤተ መቅደሱን መልሰዉ መገንባት እንደሚያስፈልጋቸዉ መረጃ ይሰጣቸዋል ፡፡

ዕዝራ (1፡ 5-11)፡ የተመለሱት እስራኤላዊያን ቤተ መቅደሱን መልሶ ለመስራት በእቃ እና በአላማ ተመልሰዉ መጡ ፡፡ ንጉስ ቂሮስ ለይሁዳ መስፍን ለሰሳብሳር የሰጣቸዉን ናቡከነደፆር በንብረት ክፍሉ ቁጥጥር ስር ከቤተ መቅደሱ ወስዶት የነበረዉን ነገር መለሰው (ቁጥር 5-8) ፡፡ በአጠቃላይ እቃዉ 5,400 ሲሆን በቁጥር (9-10) የተዘረዘሩ ናቸው ፤ ሰሳብሳር ሁሉንም ዘሩባቤል ቤተ መቅደሱን እንደ ገና ለመስራት ወደ ሚጠቀምበት ቦታ ወደ ኢየሩሳሌም ለመመለስ ኃላፊነቱን ወሰደ ( ቁጥር 11) ፡፡ አንዳንድ ምሁራን ለሰሳብሳርና ዘሩባቤል ተመሳሳይ ግለሰብ እንደ ነበሩ ይጠቁማሉ ምክንያቱም ሁለቱም የቤተ መቅደሱን መሰረት እንዳስቀመጡ ተጠቅሰዉ ስለ ነበር (ዕዝራ 3 እና 5) ፡፡

ዕዝራ 2፡ ምዕራፍ 2 ዘሩባቤል የስደተኞቹን ቡድን መልሶ ወደ ይሁዳ እንደ መራ ይመዘግባል ፡፡

መደምደሚያ

ዘፍጥረት ( 12፡ 1-3) እግዚአብሄር ሕዝቡን የሚባርኩትን እንደ ሚባርካቸዉ ይናገራል ፤ ምናልባትም ንጉስ ቂሮስ ከቤተ መቅደሱ የተሰረቀዉን እቃ ለመመለስ ፍቃደኛ የነበረበት ይህ ነበር - የእግዚአብሄርን ህዝብ ለመባረክ ፡፡ እኛም በደንብ እስራኤልን መባረክ መቀጠል አለብን ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ያን እንዴት እናደርጋለን ? በሮሜ (15፡ 25-27) ጳዉሎስ “ ወደዋልና የእነርሱም ባለ ዕዳዎች ናቸው ፤ አሕዛብ በእነርሱ መንፈሳዊ ነገር ተካፋዮች ከሆኑ በስጋዊ ነገር ደግሞ ያገለግሉዓቸዉ ዘንድ ይገባቸዋል “ (ቁጥር 27) ፡፡ እንዴት እንባርካቸዋለን ? ለራሳችን የሚመለስ ጥቅም ባለማሰብ በመስጠት የቁስ ፍላጎታቸዉን በማሟላት ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 518.

  2. MacArthur, p. 519.

  3. MacArthur, p. 518.

  4. Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Ezra (Colorado Springs, CO: David C. Cook Publishers, 2003), p. 604.

ጥያቄዎች

  1. ዕዝራ (1፡ 4) አንብቡ ፤ ይህ ትዕዛዝ ምን ያስስባችኋል ? (ዘጸ 3፡ 21-22)
  2. ንጉስ ቂሮስ በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሄር ቤትን እንዲሰራ እግዚአብሄር እንደ ሾመው አወጀ ፤ እግዚአብሄር ቤቱን መልሶ እንዲሰራ እስራኤላዊ ያልሆነ ሰዉን ለምን እንደመረጠ ምን ታስባላችሁ ?
  3. የእግዚአብሄርን ቤት መልሶ ለመስራት ለመሄድ ማን ተነሳ ? ከእነርሱ ጋር እንዲወስዱ ምን ተሰጣቸው ? (ዕዝራ 1፡ 6-11)
  4. የቤተሰባቸዉን የዘር ሀረግ ማረጋገጥ(ማወቅ) ባልቻሉት ላይ ምን ተፈጠረ (ዕዝ 2፡ 59, 62) ? ለመጠበቅ ምን አደረጉ ?
  5. አንዳንድ የቤተሰብ አለቆች በምን ሰጡ ? (ዕዝ 2፡ 68-69, 2ቆሮ 9፡ 7) ?
  6. በዕዝራ (1-2) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Ezra 1:1b–3

“The LORD put it into the mind of King Cyrus to issue a proclamation throughout his entire kingdom and to put it in writing. Whoever is among His people, may his God be with him, and may he go to Jerusalem in Judah and build the house of the LORD, the God of Israel, the God who is in Jerusalem.”

ለእግዚአብሔር የማይቻል ምንም ነገር የለም ፡፡ እስራኤላውያን በባቢሎን ምርኮኛ ሳሉ ፣ ለእግዚአብሔር ህዝብ ወደ ኢየሩሳሌም ይመለሱ ዘንድና የእግዚአብሔርን ቤት ዳግም እንድሰሩ አዋጅን እንድያስነግር እግዚአብሔር አህዛብ በሆነው በፋርስ ንጉስ በቂሮስ ልብ ውስጥ አኖረ ፡፡ ለአብርሃም የተሰጠው የእግዚአብሔር ተስፋ መፈጸሙን ቀጠለ ፡፡

ያለህበት ሁኔታ ምንም ይምሰል ፣ ይህንን አስታውስ እግዚአብሔር ቃሉን ጠባቂ ነው ፡፡ ተስፋ በሚያስቆርጡ አጋጣሚዎች ሳይቀር እግዚአብሔር ታማኝ ነው ፡፡ እስራኤላውያንን ወደ አገራቸው እንድመለሱ ለማድረግ እና የገባውን ቃል ለመፈጸም አማኝ ያልሆነ መሪን ኃይል ተጠቀመ ፡፡ እግዚአብሔር ማንንም ሊጠቀም ይችላል ምክንያቱም እርሱ ሁሉን አዋቂ ሁሉን ቻይ በሁሉም ቦታ የሚገኝ አምላክ ስለሆነ ፡፡ እርሱ በቃሉ ከተናገረው ያደርገዋል ፡፡ ዛሬ ተስፋ መቁረጥ ከተሰማህ ተስፋ ማድረግህን ቀጥል ፡፡ በክርስቶስ የሚገኘውን ተስፋ ፈጥነህ ያዝ ፡፡ በዚህ እርዳታን በምትፈልግበት ጊዜ ይረዳህ ዘንድ እግዚአብሔርን ጠይቅ ፡፡ አትሸበር ወይም አትዛል ይልቁንም በእግዚአብሔር ተስፋዎች ላይ ታመን ፡፡ እግዚአብሔር እንድትወድቅ አይተውህም ፡፡

“ እግዚአብሔር የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አስነሣ፤ እርሱም በመንግሥቱ ሁሉ አዋጅ አስነገረ፥ ደግሞም በጽሕፈት አድርጎ…….ከሕዝቡ ሁሉ በእንናተ ዘንድ ማንም ቢሆን አምላኩ ከእርሱ ጋር ይሁን፥ እርሱም በይሁዳ ወዳለችው ወደ ኢየሩሳሌም ይውጣ፥ በኢየሩሳሌምም ለሚኖረው አምላክ፥ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤት ይሥራ ፡፡ “

  • ዕዝራ 1፡ 1 ፤ 1፡3

ተጨማሪ ጥቅስ

ዘፍጥረት12:2 — “ ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም አከብረዋለሁ፤ ለበረከትም ሁን ፡፡ “

ዘዳግም 7:9 — “ አንተም አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ፥ ለሚወድዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደ ሆነ እወቅ “

ዕብራውያን 10:23 — “የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና እንዳይነቃነቅ የተስፋችንን ምስክርነት እንጠብቅ “