Historical Books 2 Chronicles

Doing Evil in God's Sight

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Royal Throne 2 Chronicles 34-36 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 318 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በምዕራፍ 34-36 የ 2ዜና መዋዕል ጥናታችንን እንጠቀልላለን ፡፡ ሁሉም ዜና መዋዕል እና መላዉ መፅሀፍ ቅዱስ እንደ ሚመጣ መሲህ ወደ ኢየሱስ እንደ ሚያመለክቱ እናስታዉሳለን ፡፡ ለ 2ዜና መዋዕል ጭብጣችን ንጉሳዊ ዙፋን ነው ፡፡ በምዕራፍ 35 ንጉስ ኢዮስያስ የፋሲካን ድግስ በማድረግ በበጉ ደም ላይ አተኮረ ፤ በምዕራፉ መጨረሻ ላይ ኢዮስያስ በግብፃዊያን ቀስተኞች ተገደለ ፡፡ ሁኔታዉ አደገኛ ቢመስልም መፅሀፉ በተስፋ ያበቃል !

ትምህርት

2-ዜና መዋዕል (36፡ 1-4)፡ የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአክስ በ609 ከክርስቶስ ልደት በፊት በኢየሩሳሌም ንጉስ ተደረገ ፤ (2ነገ 23፡ 31-33) እንደሚገዛ ኤርሚያስ የተነበየበት ትክክለኛ ጊዜ (ኤር 1፡ 3) ፡፡ ኢዮአክስ 23 አመቱ ሲሆን ለሰዎስት ወር ብቻም አስተዳደረ (ቁጥር 1-2) ፡፡ የግብፅ ንጉስ ኢዮአክስን ከዙፋን በማዉረድ ይሁዳን 7,500 ፓዉንድ ብር እና 75 ፓዉንድ ወርቅ ቀጣዉ (ጣለበት) ፡፡ ነገሮች በፍጥነት መቀየር ቻሉ ! የግብፅ ንጉስ የኢዮአክስን ወንድም ኤልያቄምን የይሁዳ ንጉስ በማድረግ ስሙን ወደ ኢዮአቄም ለወጠው ኢዮአክስም በግብፅ ስርቤት ነበር (ቁጥር 4) ፡፡

2-ዜና መዋዕል (36፡ 5-8)፡ ኢዮአቄም ለ 11አመታት (609-597 ከክርስቶስ ልደት በፊት) ገዛ በእግዚአብሄርም ፊት ክፉ ነገርን አደረገ (2ነገ 23፡ 34-24፡ 7) (ቁጥር 1) ፡፡ እግዚአብሄር በነቢዩ ኤርምያስ በኩል ለኢዮአቄም መልዕክቱን ላከለት ፤ ኢዮአቄምም ለእግዚአብሄር ሙሉ ንቀቱን በማሳየት እንደ ተነበበለት መልዕክቱን አጠፋው ፡፡ ከዚያም የባቢሎን ንጉስ ናቡከነደፆር አጠቃዉ በማሰርም ወደ ባቢሎን ከቤተ መቅደሱ እቃ ጋር ወሰደው (ቁጥር 6-7) ፡፡ በዚህ ተመሳሳይ ጊዜ በ605 ከክርስቶስ ልደት በፊት ዳንኤል ወደ ባብሎን ምርኮ ተወስዷል ፡፡ ኤርምያስ በዚህ ጊዜ መተንበዩን ቀጥሏል ፡፡

2-ዜና መዋዕል (36፡ 9-10)፡ የኢዮአቄም ልጅ ዮአኪን ቀጣዩ ንጉስ ሆነ ሰዎስት ወራትም ገዛ በእግዚአብሄርም ፊት ክፉ ነገር አደረገ (ኤር 22፡ 24-30) ፡፡ ዮአኪን በ597 ከክርስቶስ ልደት በፊት ላይ ገዛ ፤ (2ነገ 24፡ 8-16) ፤ በ597 ከክርስቶስ ልደት በፊት ሕዝቄልም ወደ ባቢሎን ምርኮ ተወስዶ ነበር ፡፡

2-ዜና መዋዕል (36፡ 11-21)፡ ንጉስ ናቡከነደፆር የዮአኪን ወንድም ሴዴቅያስን በይሁዳ ቀጣዩ ንጉስ አደረገው በኢየሩሳሌምም ገዛ (ቁጥር 11) ፡፡ ሴዴቅያስ 11አመታት (597-586 ከክርስቶስ ልደት በፊት) ገዛ በእግዚአብሄር ፊትም ክፉ ነገር አደረገ (2ነገ 24፡ 17- 25፡ 21፣ ኤር 32፡ 4-27) ፡፡ ኤርምያስ ሰቆቃዉ ኤርምያስን በ586 ከክርስቶስ ልደት በፊት ለተከናወነው ለኢየሩሳሌም እና ለቤተ መቅደስ መፍረስ ለማዘን ፃፈው ፡፡ ሕዝቅኤል እንደ አንድ ነቢይ በሴዴቅያስ ዘገዛዝ ጊዜ ተልዕኮዉን በመቀበል 592-560 ከክርስቶስ ልደት በፊት ተነበየ (ሕዝ 1፡ 1) ፡፡ ሴዴቅያስ በባቢሎኑ ናቡከደነፆር ላይ እና በያሕዌ ላይ አመፀ (ቁጥር 13) ፤ የካህናት አለቆችና ሕዝቡም የሴዴቅያስን ምሳሌ በመከተል በኢየሩሳሌም በመቅረት ቤተ መቅደሱን በማርከስ የጣዖት ተግባራትን ተከተሉ (ቁጥር 14) ፡፡ እግዚአብሄር መልሶ ወደ እርሱ ሊያመጣቸዉ መልዕክተኞቹን መላኩን ቀጠለ ነገር ግን አልሰሙትም (ቁጥር 15-16) ፡፡

ዜና መዋዕል ከዚህ ተመሳሳይ ምርኮ በባቢሎን በመጀመሪያ ስፍራ በምርኮ በተቀመጡበት ሆኖ የነበረውን ተለቀዉ ለነበሩት ለመግለፅ ተፅፎ እንደ ነበር አስታዉሱ ፡፡

እግዚአብሄርም የከለዳዊያንን ንጉሱ በእነርሱ ላይ አመጣባቸው ፤ ከለዳዊያንም የተመረጡ የይሁዳን ወንዶች በቤተ መቅደስ በመግደል ሁሉንም ወንዶችና ሴቶችን፣ ትንሽና ትልቅን ወደ ባቢሎን ምርኮ ወሰዱ (ቁጥር 17) ፤ በተጨማሪም ከለዳዊያን የቤተ መቅደሱን ሁሉንም ንብረት፣ ንጉሱን እና አለቆቹን ወደ ባቢሎን ወሰዱ (ቁጥር 18) ፤ በመጨረሻም ከለዳዊያን ቤተ መቅደሱን እና በኢየሩሳሌም ያለዉን የንጉሱን መኖሪያ አቃጠሉ፣ የከተማዋንም ቅጥር አፈረሱ በከተማዋ ያለዉን ሁሉንም አጠፉ (ቁጥር 19) ፡፡ በይሁዳ የቀረዉ ሁሉ ለከለዳዊያን እንደ አገልጋይ ተወሰደ (ቁጥር 20) ፤ ይህ ለኤርምያስ ያለዉን የእግዚአብሄር ቃል መፈፀም ሲሆን ምድሪቱም “ በባድማነት ቀናት ጊዜ “ ለ70 አመት ታርፋለች (ኤር 25፡ 8-12) ፡፡

መደምደሚያ

ለ70 አመታት ምድሪቱ አረፈች ሕዝቡም ወደ ምርኮ ከመወሰዳቸዉ በፊት ወደነበረችዉ ምድራቸዉ መመለስ ጀመሩ ፡፡ እግዚአብሄር ንጉስ ቂሮስን በኢየሩሳሌም አዲስ ቤተ መቅደስ መስራትን ለማገዝ እና በፋሬስ ሁሉንም ምርኮኞች ነፃ ለማዉጣት ጠራው (2ዜና መዋዕል 36፡ 22-23) ፡፡ የእግዚአብሄር ሰዎች እንደ ተመለሱ ከተማቸዉን እና ቤተ መቅደሱን እንደ ገና መገንባት ጀመሩ ፡፡

ጥያቄዎች

  1. በ 2ዜና መዋዕል (34፡ 3) ንጉስ ኢዮስያስ የአባቱን የዳዊትን አምላክ መፈለግ ጀመረ ፤ እግዚአብሄርን ወደ “ መፈለግ “ እንዴት እንደሄደ ምን ታስባላችሁ ? ይህን ካደረከ በኋላ የምድሪቱን ጣዖቶች ማፅዳት ለመጀመር ምን ያክል ጊዜ ፈጀበት ?
  2. ምድሪቱን ከርኩስነት ነፅታ ለማየት ንጉስ ሕዝቅያስ ምን ያክል ሄደ ? የራሳችሁን ህይወት እና ከማንኛዉም ከቀድሞ ተገቢ ካልሆነ ነገር መንፃታቸዉን ለማየት ምን ያክል ትሄዳላችሁ?
  3. የህጉ መፅሀፍ ንጉስ ኢዮስያስ በይሁዳና በአንዳንድ እስራኤል ምድሪቱን በማንፃት ከመጓዙ በኋላ ድረስ አልተገኘም ነበር ፤ ከህጉ መፅሀፍት ዉጪ ምድሪቱን ለማንፃት እንዴት አወቀ ? ሲነበብ ለሰማዉ እንዴት ምላሽ ሰጠ ? (2ዜና መዋዕል 34፡ 19-21)
  4. በ 2ዜና መዋዕል (34፡ 26-28) ለንጉስ ኢዮስያስ የእግዚአብሄር ምላሽ ምን ነበር ? ስለ እግዚአብሄር ይህ ምን ይገልጣል ? ንጉስ ኢዮስያስ ለእግዚአብሄር በመሰጠቱ እንዴት ተጓዘ ?
  5. 2 ዜና መዋዕል መጨረሻ መቃረቢያ በ2ዜና መዋዕል (36፡ 15) ላይ እግዚአብሄር ለሕዝቡ ምህረቱን እንዴት አሳዬ ? በዚህ መጨረሻ ምዕራፍ ላይ ከእያንዳንዱ ነገስታት በንግስና ዙፋኑ ላይ ማን የተቀመጠ ይሆናል ? በፅሁፉ ላይ ተስፋን የት ላይ ታያላችሁ ?
  6. በ 2ዜና መዋዕል (34-36) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Chronicles 36:15b–16

“For He had compassion on His people and on His dwelling place. But they kept ridiculing God’s messengers, despising His words, and scoffing at His prophets, until the LORD’s wrath was so stirred up against His people that there was no remedy.”

እስራኤላውያን በደላቸውን አበዙ ፤ በዙሪያቸው ያሉትን አህዛብ አስጸያፊ ድርጊቶች አደረጉ እንድሁም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ አረከሱ ፡፡ እግዚአብሔርም አዛኝ ስለሆነ ፣ ንስሀ ይገቡ ዘንድ እድልን ሰጣቸው ፤ ነገር ግን እነርሱ በእግዚአብሔር መልእክተኞች መሳለቁን ፥ ቃሉንም ማቃለሉን ፥ በነቢያቱም ላይ ማፌዙን ቀጠሉ ። በመጨረሻም እግዚአብሔር ናቡከደነፆርን ህዝቡን ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ለሰባ አመት ግዞት እንድወስድ ላከው ፡፡ በኋላም እግዚአብሔር አስራኤላውያን ወደ ሀገራቸው እንድመለሱ አዋጅን እንድያወጣና የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ እንደገና እንዲሰራ አማኝ ያልሆነውን የፋርስን ንጉሥ ቂሮስን ተጠቀመ ፡፡ እግዚአብሔር ለህዝቡ እንደገና ወደ መገኘቱ የሚመለሱበትን እድል ሰጠ ፤ የተናገረውንም ቃል ፈጸመ ፡፡

እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር መሆንህን ይናፍቃል ፡፡ እርሱ የሁለተኛ የሶስተኛ የአራተኛ እድል አምላክ ነው ፡፡ አንተን ከመፈለግ ፈጽሞ ተስፋ አይቆርጥም ፡፡ ፍቅሩ ሰፊ ነው ፤ ፍቅሩ ከፍ ያለ ነው ፡፡ ከእግዚአብሔር መገኘት እንደተከልከልክ ይሰማህ ይሆናል ፤ መንገድህን እንደሳትክም ይሰማህ ይሆናል እንድሁም ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ መንገድ እንደሌለም ይሰማህ ይሆናል ፡፡ ነገር ግን ዛሬ ከመንፈሱ የሚያስመልጥ ምንም ቦታ እንደሌለ አውቀህ እረፍ ፡፡ ወደ እርሱ እንድትመለስ ይፈልጋል ፡፡ በፍጹም ልብህ ልትሻው ጊዜው አሁን ነው ፡፡ እርሱ መልካም አባትህ ነው ይወድህማል ፡፡

“ የአባቶቻቸውም አምላክ እግዚአብሔር ለሕዝቡና ለማደሪያው ስላዘነ ማለዳ ፤ እነርሱ ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ እስኪወጣ ድረስ፥ ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ፥ በእግዚአብሔር መልእክተኞች ይሳለቁ፥ ቃሉንም ያቃልሉ፥ በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር ። “

  • 2ኛ ዜና 36፡15-16

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 139:7–10 — “ ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ ? ወደ ሰማይ ብወጣ ፥ አንተ በዚያ ነህ ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ ። እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር ፥ በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች ። “

ኤርምያስ 29:13–14 — “ እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ ። ከእናንተም ዘንድ እገኛለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ምርኮአችሁንም እመልሳለሁ፥ ከአሕዛብም ሁሉ ዘንድ እናንተንም ካሳደድሁበት ስፍራ ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እናንተንም ለምርኮ ወዳፈለስሁበት ስፍራ እመልሳችኋለሁ ። “

ኤፌሶን 3:17–18 — “ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር ፤ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ ፥ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል “