God is Our Warrior
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Royal Throne 2 Chronicles 32-33 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ወደ 2ዜና መዋዕል መጨረሻ ላይ ቀርበናል ፤ ለ 1ዜና መዋዕል ሐረጉ የዳዊት ልጅ የሚል ሲሆን ለ 2ዜና መዋዕል ደግሞ ንጉሳዊ ዙፋን ነው ፡፡ ሕዝቅያስ በእግዚአብሄር የታደሱ እንዲሆኑ ሕዝቡን ጠራቸው ፡፡ ከዳዊት ዘር የሆነው ሕዝቅያስ በመጨረሻዉ በኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሚመጣዉ ንጉሳዊ ዙፋን አመለከተ ፤ ይሁን እንጂ በ 2ዜና መዋዕል 32ይህን ሁሉ ለማጥፋት ሰይጣን ለመምጣት ሲሞክር እናያለን ፡፡ እግዚአብሄር እና ሰይጣን ሁለቱም በአለም ላይ የትኛዉም ስፍራ ላይ አንዱን ለእግዚአብሄር ክብር ሌለኛዉን ደግሞ ለማጥፋት በበሞከር ገዢዎችን ሊጠቀሙ ይችላሉ ፡፡ በመጨረሻም እግዚአብሄር በስልጣን ስለሆነ ለስራዉ መጥፎ ገዢዎችን ሊጠቀም ይችላል (ምሳ 21፡ 1) ፡፡ በሕዝቅያስ ላይ እንደ መጣዉ አይነት መነቃቃት ስንመለከት ሁል ጊዜ ሰይጣን ለማጥፋት እንደ ሚሞክር መጠበቅ አለብን ፡፡
ትምህርት
2-ዜና መዋዕል (32፡ 1-8)፡ ከሕዝቅያስ ታሐድሶ በኋላ የአሶር ንጉስ ሰናክሬም በይሁዳ ዉስጥ በመግባት በተመሸጉ ከተሞቻቸዉ ከበባን አደረገ (ቁጥር 1) ፡፡ 2ነገ 18፡ 13) ሰናክሬም ሁሉንም የተመሸጉ 46 ከተሞች ያዘ ይላል ፡፡ ሕዝቅያስ ሰናክሬም በኢየሩሳሌም ላይ ጦርነትን እንዳቀደ አስተዋለ (ቁጥር 2)፤ ሰለሞን እነዚህን ከተሞች በመስራት ሕዝቡን በዉስጣቸዉ ያስቀመጠ ንጉስ ነበር (2ዜና መዋዕል 8፡ 2-6) ፡፡ ሕዝቅያስ አለቆቹን እና ኃያላኑን ከከተማዉ ዉጪ ያለዉን ምንጭ ስለ ማቆም አማከረ ረዱትም (ቁጥር 3) ፡፡ ሕዝቅያስ የሰናክሬምን ጥቃት ለማስቆም ሰዎስት መንገዶችን ሰራ ፡፡
መጀመሪያዉ እሱ (አለቆቹ) ከኢየሩሳሌም ከተሞች ቅጥር ዉጪ ያሉትን ምንጮች ማስቆም ይህ ከሆነ ሰናክሬምና ሰራዊቱ ዉሃ አያገኝም (ቁጥር 3-4) ፤ ከዚያም ሕዝቅያስ ከጊዎን ምንጮች ወደ ሰሊሆም ገንዳ የሚሄድ መተላለፊያን ሰራ የኢየሩሳሌም ከተሞችም ብዙ ዉሃ ይኖራቸዋል ፡፡ ሁለተኛዉ ሕዝቅያስ የተሰበረዉን ጠቅላላ የቅጥሩን ክፍል እንደ ገና በመስራት በላዩም ላይ ግንብን ሰርቶ ነበር (ቁጥር 5) ፤ ሰዎስተኛዉ ሕዝቅያስ ጦሩን እንደ ገና አዋቀረም አጠነከረም(አዘጋጀም) (ቁጥር 5-6) ፡፡ ልክ እንደ ይሁዳና እንደ ሕዝቅያስ ለጦርነት (ለዉጊያ) የሰለጠንን (የተጠናከርን) እና የተዘጋጀን ነን (ኤፌ 6፡ 10-18) ? ሕዝቅያስ የኢየሩሳሌምን ሕዝብ በአሶር ንጉስ ፊት የፈሩና ተስፋ የቆረጡ ከመሆን ይልቅ የበረቱና የጠነከሩ እንዲሆኑ አበረታታቸው (ቁጥር 7) ፡፡ ሕዝቅያስ ሰናክሬም በሰራዊቱ ከነበረዉ በላይ በእነርሱ የሚበልጥ እንደ ነበሩ አመለከቱ (ቁጥር 7) ፤ ይህ ንጉስ የዉሃ አቅርቦቱን፣ ቅጥሮችን እና ኃያላኑን አዘጋጅቶ በመመሸግ ለጦርነት ተዘጋጀ ፡፡ ለዉጊያ ዝግጁ ነን ? ቤተ ክርስቲያን ለዉጊያ ዝግጁ ነች (ኤፌ 6፡ 10-18) ?
ንጉስ ሕዝቅያስ ትክክለኛ አማካሪዎችን በመስማት ለጦርነት ተዘጋጀ ፤ አንዳንዶች ሕዝቅያስ ሌላ ድርጊት ሳይወስድ በእግዚአብሄር ላይ ብቻ ተደግፏል ይላሉ ፡፡ ሕዝቅያስ ከተማዋን ለማዘጋጀት በወሰደዉ ድርጊት ላይ መለኮታዊ ጥበብን አያለሁ ፤ ሕዝቅያስ በዙሪያው “ ፈረሶች እና ሰረገሎች “ እንደ ነበሩ በማወቁ እደነቃለሁ (2ነገ 6፡ 16-17) ፡፡ በቁጥር 8 ሕዝቅያስ የይሁዳ ሕዝብ ጦርነታቸዉን ለመዋጋት የእግዚአብሄር ኃይል ሲኖራቸው ሰናክሬም የሰዉ ኃይል ብቻ እንደ ነበረዉ ተናገረ ፡፡ ሕዝቅያስ አድርጎአቸዉ ከነበራቸዉ መሻሻሎች ይልቅ በእግዚአብሄር ታመነ ፤ ( እግዚአብሄር የመታመን ተቃራኒን ኢሳ (22፡ 8-11) ተመልከቱ) ፡፡ ማርቲን ሰልማን እግዚአብሄርን የመታመን ብዙ ምሳሌዎችን አስቀምቷል፡
- ዘዳ (31፡ 7-8፣ 23)፡ ሙሴ ሕዝቡን ጠንካራና ብርቱ እንዲሆኑ ጠራቸው ፤ የፈሩና ተስፋ የቆረጡ እንዳይሆኑ ፡፡
- ኢያሱ (1፡ 6-9)፡ ኢያሱ ሕዝቡን ጠንካራና ብርቱ እንዲሆኑ ጠራቸው !
- 1ዜና መዋዕል (22፡ 13)፡ ዳዊት ሕዝቡን ጠንካራና ብርቱ እንዲሆኑ ጠራቸው ! አትፍሩ አትደንግጡም፡፡
በመጀመሪያዎቹ 8 ቁጥሮች ሕዝቅያስ ሕዝቡን ከጥቃት ለመከላከል ተዘጋጀ ምክንያቱም “ እንደ ዉጊያ የስዓቱ ትግል በሕዝቦች መካከል ብቻ ሳይሆን በኃይማኖታዊ ስርዓት እና አስተሳሰብ መካከልም የሆነ ፉክክር እንደ ሆነ አዬ “ ፡፡ ሕዝቅያስ እንደ ኃያል በያሕዌ ላይ ለመደገፍ ዝግጁ ነበር ፡፡
ሕዝቅያስ ሕዝቡን ወደ እግዚአብሄር መልሶ በማምጣቱ ምክንያት እሱ እና ሕዝቡ ለሰይጣን አስፈሪ ሆኑ ፡፡ ሰዎችን ወደ እግዚአብሄር የማታመጡ ከሆነ ለሰይጣን የምታስፈሩ አይደላችሁም !
2-ዜና መዋዕል (32፡ 9-19)፡ ሰናክሬምና ጦሩ ከኢየሩሳሌም ምዕራብ በኩል በምትገኘዉ በለኪሶ ከተማ ተቀመጡ (ቁጥር 9) ፤ ሊኪሲን መያዝ ኢየሩሳሌምን ከምዕራብና ከባህሩ መለየት ይሆናል ፤ ሰናክሬምም ለምን ሕዝቡ በከበባ ስር በኢየሩሳሌም በተለይም የተራቡ እና የተጠሙ ከሚሆኑበት ጀምሮ ለመቀመጥ ፍቃደኞች እንደ ነበሩ ጠየቀ ( ቁጥር 10-11) ፡፡
ሰናክሬም እስራኤላዊያን በቤተ መቅደሱ አንድ መሰዊያ ላይ ማምለክ ስለሚያስፈልጋቸዉ ሕዝቅያስ ኮረብታዎችን እና መሰዊያዎችን ለማስወገድ አድርጎት የነበረዉን ሁሉ አፌዘበት (ቁጥር 12) ፡፡ ከዚያም ይህ የአሶር ንጉስ እርሱ እና አባቶቹ የይሁዳን ከተሞች በሚገባ ያሸነፉባቸዉ ታሪክ እያላቸዉ ለምን ሰዎች ሊያቆሙት እንደ ሚችሉ እንዳሰቡ ጠየቀ (ቁጥር 13-14) ፡፡ በመሰረቱ ሰናክሬም የሕዝቅያስን እምነትና ተሐድሶ አሳንሶት(ንቆት) ነበር ፡፡ ዛቻዉ እግዚአብሄርን የማይታመኑትን እንዴት የሚያስደነግጥ ሊሆን እንደ ሚችል አስቡት ፡፡ ሰናክሬም የማንኛዉም ሕዝብ አማልዕክት በእርሱ ላይ አሸናፊ ለመሆን በቂ የሆነ እንዳልነበረ እየፎከረ ነበር (ቁጥር 15) አገልጋዮቹም በእግዚአብሄር እና በሕዝቅያስ ላይ ብዙ ተናገሩ (ቁጥር 16) ፡፡ ሰናክሬም ስለ እግዚአብሄር በእነዚህ ተመሳሳይ ዉሸቶች የማስመሰል ደብዳቤ ፃፈ (ቁጥር 17) እናም በመጨረሻ አገልጋዮቹ እስራኤላዊያንን ለማስፈራራት በዕብራዊ ተናገሩ ፡፡ ዉሸቶቹ፣ ማስፈራራቱ እና ክሶቹ በቁጥር 18-19 ዉስጥ ቀጠሉ ፡፡
2-ዜና መዋዕል (32፡ 20-23)፡ ነገር ግን ሕዝቅያስ እና የአሞፅ ልጅ ነቢዩ ኢሳያስ በሰናክሬም ሰፈር ላይ ሁሉንም ኃያላን፣ መሪዎች እና አዛዦች ለማጥፋት መለዓክት ወደ ላከላቸዉ ወደ እግዚአብሄር ጮኹ (ቁጥር 20-21) ፡፡ ሰናክሬም በእፍረት ቤቱ ተመለሰ የገዛ ልጆቹም ገደሉት (ቁጥር 21) ፡፡ እግዚአብሄር ሕዝቡን ከሶሪያዊዉ ሰናክሬም እና ከሌሎች ሁሉ በማዳን ሰላምን እና ረፍት ሰጣቸው (ቁጥር 22) ፡፡ ብዙዎች ለሕዝቅያስ ስጦታን አመጡ በሁሉም ሕዝብ ፊት የበለጠ (የከበረ) ሆነ (ቁጥር 23) ፡፡ ሕዝቅያስ ሁሉንም ነገር አዘጋጀ እግዚአብሄር ግን ለእነርሱ ዉጊያዉን ተዋጋ ፡፡
መደምደሚያ
ዮሐ (8፡ 31-32) የሚገልፀው “ እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእዉነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ እዉነትንም ታዉቃላችሁ እዉነትም አርነት ያወጣችኋል “ ፡፡ እዉነት ከምንድን ነፃ ያወጣናል ? ኢየሱስ የኃጢዓት ባሪያ እንደ ሆንን ገልፃል ነገር ግን ልጁ ነፃ ሊያወጣን ችሏል ፡፡
ይህ የእግዚአብሄር ቃል ነዉ በማለት በራሳችን ላይ ማቋቋም(መመስረት) በመቻል በአሁኑ ጊዜ ምን እንሰማለን ? ለሪቫይቭ ት/ቤት ምክንያቱ ያ ነው !
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 561.
Nelson’s Commentary, p. 561.
ጥያቄዎች
-
በ 2ዜና መዋዕል (32፡ 7-8) ሕዝቅያስ ሕዝቡ እንዲበረቱና እንዲፀኑ እየነገራቸዉ ነበር ፤ በግል አስተያየታችሁ ከእኛ በኩል ስለ እኛ የሚዋጋ እግዚአብሄር ኖሮን ልንሸነፍ እንችላለን ? ሌላ የት ላይ እንድንበረታ፣ እንድንፀና እና እንዳንፈራ ተነግሮናል ? (ዘዳ 31፡ 6፣ ኢያ 1፡ 9)
-
በ 2ዜና መዋዕል (32፡ 21) እግዚአብሄር ሰናክሬምንና ሰራዊቱን ለመዋጋት መለዓክትን ላከ ፤ ምን ያክል ሰዎች ተገድለዉ ነበር (2ነገ 19፡ 35) ? ቆይቶ ሰናክሬም በምን ወደቀ በማንስ ?
-
እግዚአብሄር ለሕዝቅያስ ሰምቶት እና ፈዉሶት እንደ ነበር ምን ምልክት ሰጠው ? (2ነገ 20፡ 8-11)
-
በምዕራፍ 23 ምናሴ በእግዚአብሄር ፊት በክፉ እየገዛ እና እያደረገ ነበር ፤ መንገዱን እንዲቀይር ሲያደርገዉ ምን ተፈጠረ ? ባህሪዉን በመቀየር እግዚአብሄርን መከተል ቢጀምርም እንኳን ከአባቱ ጋር ሲነፃፀር የት ነበር የተቀበረው ?
-
በ 2ዜና መዋዕል (32-33) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Chronicles 32:7–8
“‘Be strong and courageous! Don’t be afraid or discouraged before the king of Assyria or before the large army that is with him, for there are more with us than with him. He has only human strength, but we have Yahweh our God to help us and to fight our battles.’ So the people relied on the words of King Hezekiah of Judah.”
ከንጉሥ ሕዝቅያስ ህዝቡን ወደ አምላካቸው እንድመለሱ በመምራት ካሳየው አምነት በኋላ የአሶር ንጉሥ ሰናክሬም ወደ ተመሸጉት ከተሞች ሰብሮ ሊገባ ፈልጎ ወደ ይሁዳ ገባ ፡፡ ንጉሥ ሕዝቅያስም ጠላት እንደ መጣ አይቶ ፣ በችግር ውስጥ እንዳለ ተረዳ ወድያውኑም ተማከረ ፡፡ ከዚያም ህዝቡን በአንድነት ሰብስቦ አበረታቸው ፡- “ጽኑ፥ አይዞአችሁ ……. ሰናክሬም ጋር የሥጋ ክንድ ነው፤ ከእኛ ጋር ያለው ግን የሚረዳንና የሚዋጋልን አምላካችን እግዚአብሔር ነው ፡፡ “ እግዚአብሔር ድልን አቀዳጃቸው ፤ ሐዝቅያስንም ከመላው ኢየሩሳሌም ጋር ታደገ ፤ በሁሉም አቅጣጫም እረፍትን ሰጣቸው ፡፡
ብዙ ጊዜ ለእግዚአብሔር ከተደረገ ታላቅ የታማኝነት ጊዜ በኋላ ፣ ጠላት ሊሰርቅ ሊገድልና ሊያጠፋ ይመጣል ፡፡ በድፍረት ሀይወትህን ለእግዚአብሔር ስትኖር በዙሪያህ ሰላለው ውጊያ አወቅ ፡፡ ነገር ግን አትፍራ ፡፡ ልክ እግዚአብሔር ለሙሴ ለእያሱ ለዳዊት እና ለሕዝቅያስ ህዝቡን ሲመሩ እንደተናገረው ሁሉ ፣ አንተም ለውጊያ እንድትዘጋጅ ይነግርሃል ፡፡ በእግዚአብሔር ጽና ፡፡ የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ ፡፡ ሁልጊዜ በመንፈስ ጸልይ ፡፡ ንቁ ፡፡ አምላክህ እግዚአብሔር ውጊያህን ይዋጋ ዘንድ ካንተ ጋር ነው ፤ ስለዚህ ስለ ወንጌሉ ሚስጥር በድፍረት መናገርህን ቀጥል ፡፡ ሌሎቹ ያላቸው የሰው ብርታት ብቻ ነው ፤ አንተ ግን እግዚአብሔር ከጎንህ አለ ፤ በእምነት ውጣ አትፍራ ፡፡
“ ጽኑ፥ አይዞአችሁ ከእኛም ጋር ያለው ከእርሱ ጋር ካለው ይበልጣልና ከአሦር ንጉሥና ከእርሱ ጋር ካለው ጭፍራ ሁሉ አትፍሩ፥ አትደንግጡም ። ከእርሱ ጋር የሥጋ ክንድ ነው፤ ከእኛ ጋር ያለው ግን የሚረዳንና የሚዋጋልን አምላካችን እግዚአብሔር ነው ብሎ አጸናናቸው። ሕዝቡም በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ቃል ተጽናና ። “
- 2ኛ ዜና 32፡7-8
ተጨማሪ ጥቅስ
ዘዳግም 31:7–8 — “ሙሴም ኢያሱን ጠርቶ በእስራኤል ሁሉ ፊት፦ አንተ ከዚህ ሕዝብ ጋር እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው እንዲሰጥ ወደ ማለላቸው ምድር ትገባለህና፥ እርስዋንም ለእነርሱ ታወርሳለህና ጽና፥ አይዞህ ። በፊትህም የሚሄድ እርሱ እግዚአብሔር ነው ከአንተ ጋር ይሆናል፥ አይጥልህም፥ አይተውህም አትፍራ፥ አትደንግጥ አለው ። “
ኢያሱ 1:7 — “ ነገር ግን ጽና፥ እጅግ በርታ፤ ባሪያዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግ ሁሉ ጠብቅ፥ አድርገውም፤ በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል ። “
ኤፌሶን 6:10-11 — “ በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ ። የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።