Historical Books 2 Chronicles

The Call for Revival

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Royal Throne 2 Chronicles 30-31 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 316 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

አሁን በሪቫይቭ ት/ቤት 316 ክፍል ጨርሰናል በዚህ ሳምንት ደግሞ የ 2ዜና መዋዕል ጥናታችንን እንጨርሳለን ፡፡ የ 2ዜና መዋዕል የመጨረሻ ሰዎስት ጥናቶቻችን ከዚህ በፊት ያጠናነዉን በምንም የማይመስል ጡዘት ይሰራል ፡፡ የንጉስ ሕዝቅያስን በንርራሄ መጓዝን እናያለን ፡፡

ማክአርቱር “ ሕዝቅያስ ምናልባት መንግስቱ ከተከፋፈለ ከ215 አመታት ቀድሞ በሆነ ጊዜ በግልፅ በየዓመቱ እና በትክክል እየተደረገ ያልነበረዉን የቂጣ በዓልን እና የፋሲካን ለማደስ መልሶ እንደ ደረሰ “ ይናገራል ፡፡ ሕዝቅያስ በልምዳቸዉ ዉስጥ ከተረሳ ረጅም ጊዜ የነበረዉን የእግዚአብሄርን ቃል እንደ ገና አቋቋመ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ሕዝቅያስ ከሁሉም ከ12 ነገዶች ጋር እግዚአብሄር አድርጎት የነበረዉን ኪዳን እዉነት ምልከታ በፍፁም ያጣ ስላል ነበር ሁሉንም ተስፋዎች እንዳካተተ “ ይገልፃል ፡፡

ትምህርት

2-ዜና መዋዕል (30፡ 1-9)፡ ሕዝቅያስ እና አለቆቹን(ሰራተኞቹን) እና የኢየሩሳሌም ሰዎች ፋሲካን በሁለተኛዉ ወር(በተለመደዉ ጊዜ ላይ ፋሲካን ለማክበር ግራ ተጋብተው ነበር) ለማክበር በመወሰን ከእነርሱ ጋር ለመሳተፍ እንዲመጡ ለእስራኤል ሁሉ እና ለይሁዳ ሁሉ እንዲሁም ከኤፍሬምና ከምናሴ ለሆኑት ቃል ላኩላቸው (ቁጥር 1-3)፡፡ አንድ ወር አራዝመዉ ማስቀመጣቸው በቤተ መቅደሱ ስራን እንዲጨርሱ፣ በቂ ካህናትን እንዲቀድሱ እና ለሕዝቡ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመጡ ጊዜ እንዲኖራቸዉ ፈቅዶላቸዋል ፡፡ ሁሉም በእቅዱ በመስማማት ከሰሜን ከተሞች (ከዳን) እስከ ደቡብ ስፍራ (ቤርሳቤህ) በሁሉም እስራኤል መልዕክቱን አሰራጩ (ቁጥር 4-5) ፡፡ ንጉሱም በሁለቱም መንግስት ህዝቡን ለማነቃቃት በመጥራት “ ወደ እግዚአብሄር ተመለሱ “ በሚል በእጅ የተፃፈ መልዕክት በመልዕክተኞቹ ላከ (ቁጥር 6) ፡፡ እነዚህ መልዕክተኞች በሁለቱም ምድር ዉስጥ ለንጉሱ እንደ አምባሳደሮች ተገበሩ ፤ ሕዝቅያስ በመልዕክተኞቹ ዉስጥ እንዳስተላለፈዉ እግዚአብሄርም በእኛ ዉስጥ ያስተላልፋል (ሐዋ 1፡ 8) ፤ ይህ በአሁኑ ጊዜ መነቃቃት ምን እንደ ሚመስል ስዕል ነው ፡፡ የሕዝቅያስ መልዕክት በእግዚአብሄር በግ በኢየሱስ መመለስ እንደ ምንችለዉ ሕዝቡ በፋሲካ በግ ወደ እግዚአብሄር መመለስ እንደ ሚችሉ ነበር ፡፡ የመልዕክተኞቹ ስም እንዳልተመዘገበ አስታዉሉ ነገር ግን ያ የንጉሱን መልዕክት ከማድረስ አላስቆማቸውም ፡፡ ለእግዚአብሄር ዋጂ መልዕክትም “ የደብዳቤ ተሸካሚ “ እና “ የመልዕክት ተሸካሚ “ እንድንሆን ስልጣን ተሰጥቶናል (ሐዋሪያት ስራ 10-11) ፡፡

ሪቻርድ ኤል. ፓርትይ ጄይር በ 2ዜና መዋዕል (30፡ 6-9) የተመዘገበ በንጉሱ መልዕክት ላይ ስምንት ልባዊ ምክሮችን ያመለክታል፡

  1. መንገድ መሪ መርህ መመለስ (ቁጥር 6) ፡፡
  2. አሉታዊ መስፈርት አባቶቻችሁን እንዳትመስሉ (ቁጥር 7) ፡፡
  3. አሉታዊ መስፈርት አንገተ ደንዳና ወይም ግትር አለመሆን (ቁጥር 8) ፡፡
  4. አዎንታዊ መስፈርት መታዘዝ (ቁጥር 8) ፡፡
  5. አዎንታዊ መስፈርት መምጣት (ቁጥር 8) ፡፡
  6. አዎንታዊ መስፈርት ማገልገል (8) ፡፡
  7. መንገድ መሪ መርህ ብትመለሱ (ቁጥር 9) ፡፡
  8. መንገድ መሪ መርህ ብትመለሱ (ቁጥር 9) ፡፡

ሁሉም ነገር ሕዝቅያስ ለእስራኤልና ለይሁዳ ሕዝብ የፃፈው መነቃቃትን ለማግኘት በአሁኑ ጊዜም ለቤተ ክርስቲያን በተመሳሳይ የሚያስፈልግ መልዕክት ነው - ወደ እግዚአብሄር መመለስ አለብን !

2-ዜና መዋዕል (30፡ 10-15)፡ ከነዋሪዎቹ አብዛኞቹ የሕዝቅያስን መልዕክት ለመስማት እምቢ በማለት በመልዕክተኞቹ ላይ ሳቁባቸው (ቁጥር 10) ፤ ነገር ግን አሴር፣ ምናሴ እና ዛብሎን ራሳቸዉን በማዋረድ መልዕክቱን ተቀብለዉ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ (ቁጥር 11-12) ፡፡ በጣም ትልቅም የሆነ የሕዝብ ጉባኤ በበዓሉ ላይ ለመሳተፍ በኢየሩሳሌም ተሰበሰበ (ቁጥር 13) ፡፡ መዋረድ(ትህትና) ባለበት አንድንት መኖር ይችላል ፡፡

2-ዜና መዋዕል (30፡ 16-27)፡ በዓሉ በደህና ስለ ሄደ ሕዝቡ ብዙ በመፈለግ ለሌላ ሰባት ቀን ለማምለክ ቀጠሉ (ቁጥር 23) ፡፡

መደምደሚያ

ሕዝቡ የእግዚአብሄርን መገኘት በቀመሱት ጊዜ ብዙ ስለሚፈልጉ መነቃቃት ሰብሮ(ፈንቅሎ) ይወጣል !

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 512.

  2. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 559.

  3. Richard L. Pratt, Jr., “The Reunited Kingdom, part 4,” Reformed Perspectives; available at http://reformedperspectives.org/article.asp/link/http:%5E%5Ereformedperspectives.org%5Earti-cles%5Eric_pratt%5EOT.Pratt.2Chr.30.1-12.html/at/The%20Reunited%20Kingdom,%20part%204.

ጥያቄዎች

  1. ንጉስ ሕዝቅያስ የፋሲካን ቀን ለምን ቀየረው ? የፋሲካ ትርጉሙ ምንድን ነው ? እግዚአብሄር ስለ ፋሲካ ትዕዛዝ የት ሰጣቸው ? (ዘጸ 12፡ 11-14)
  2. በ 2ዜና መዋዕል (30፡ 18) ከሕዝብ አብዛኞቹ አልነፁም ነበር ግን በሉ ፤ በዚያን ጊዜ ለፋሲካ ትክክለኛዉ ቅደም ተከተል ምን ነበር (ዘዳ 16፡ 1-8) ? ሕዝቅያስ ሲፀልይላቸዉ ምን ተፈጠረ ?
  3. በ 2ዜና መዋዕል (31፡ 5-6) ሕዝቡ በኩራታቸዉን አመጡ ፤ ሌላ የት ላይ እግዚአብሄር ይህን አቅጣጫ ሲሰጥ ታዩታላችሁ ? (ዘዳ 26፡ 2፣ ምሳ 3፡ 9)
  4. በ 2ዜና መዋዕል (31፡ 10-21) ንጉስ ሕዝቅያስ የተሰራ ጎተራ ነበረው ፤ ለምን ? የእግዚአብሄር ተስፋ የት ተሰጥቶ እናየዋለን (ሚል 3፡ 10፣ ማቴ 6፡ 33) ? አንድን ሰዉ እግዚአብሄር ሊሰጠዉ ይችላል ? ለምን ወይስ አይሰጠዉም ?
  5. በ 2ዜና መዋዕል (30-31) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Chronicles 30:6

“So the couriers went throughout Israel and Judah with letters from the hand of the king and his officials, and according to the king’s command, saying, ‘Israelites, return to Yahweh, the God of Abraham, Isaac, and Israel so that He may return to those of you who remain, who have escaped from the grasp of the kings of Assyria.’”

ንጉሥ ሕዝቅያስ ለትንስ ግዜ መደረግ ያቆመውን የእስራኤል አምላክ የእግዚአብሔርን ፋሲካ ያድርጉ ዘንድ በኢየሩሳሌም ወደ ሚገኘው ቤተ መቅደስ አነድመጡ ለመላው አስረኤልና ይሁዳ ሕዝብ ደብዳቤ ጻፈ ፡፡ ደብዳቤን ጻፈ መልዕክቱንም ለማሰራጨት መልዕክተኞችን ላከ ፡- “ ወደ እናንተ ወደ ተረፋቸሁት ( ቀራችሁት ) ይመለስ ዘንድ ወደ አብርሃም ወደ ይስሃቅና ወደ ያዕቆብ አምላክ ለመመለስ ጊዜው አሁን ነው ፡፡ “ መልዕክቱንም ሲሰሙ አንዳንዶች ሳቁ በመልዕክተኞቹም ላይ ተሳለቁ ነገር ግን ሌሎቹ ራሳቸውን አዋርደው ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ ፡፡ የእግዚአብሔር ኃይል ሁሉንም አንድ አደረጋቸው ፤ ንጉሥ ሕዝቅያስ የእግዚአብሔር ኃይል የሚሰራበት መሳሪያ ነበር ፡፡

አንዳንድ ጊዜ በመታዘዝ እንደ እግዚአብሔር መልዕክተኛ ወደ ሆነ ሰው ህይወት መሄድ ያስፈልግህ ይሆናል ፤ የእግዚአብሔር ኃይል ቀድሞህ እንደ ሄደ በማመን ፡፡ ዘሬ ደቂቃ ውሰድ እስኪ በህይወትህ ወደ እግዚአብሔር መመለስ የሚያስፈልገው ሰው ካለ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ፡፡ አትጨነቅ ፣ ሊሰሙህ ካልፈለጉ ወይም ከሳቁብህና ካሾፉብህ ፤ አንተን ሳይሆን ኢየሱስን ነው እምቢ ያሉት ፡፡ ሆኖም ግን ቅን ምላሽን ልትሰማ ትችላለህ እናም ደግሞ ልባቸውን ወደ እግዚአበሔር ሲመለሱ ልታይ ትችላለህ ፡፡ የእግዚአብሔር ምህረት ወደ እርሱ የሚመለሱትን ሁሉ ይሸፍናል ፡፡ ስለዚህ ሂድ መልዕክቱን ላክ ፤ ኢሜይሉን ጻፍ ፤ ወይም ስልክህን አንሳና ደውል !! በአንድ ሰው ህይወት ውስጥ ለውጥ እንድጀምር የሚያስችል መሳሪያ ሁን እናም የእግዚአብሔር ጸጋ እንድፈስ አስችል ፡፡

“ እንደ ንጉሡም ትእዛዝ መልክተኞቹ እንዲህ የሚለውን የንጉሡንና የአለቆቹን ደብዳቤ ይዘው ወደ እስራኤልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ሄዱ። የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር ከአሦር ነገሥታት እጅ ወዳመለጠ ቅሬታችሁ እንዲመለስ ወደ አብርሃምና ወደ ይስሐቅ ወደ እስራኤልም አምላክ ተመለሱ ። “ - 2ኛ ዜና 30፡6

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ኤርምያስ 15:19 — “ ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ብትመለስ እመልስሃለሁ በፊቴም ትቆማለህ፤ የከበረውንም ከተዋረደው ብትለይ እንደ አፌ ትሆናለህ፤ እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ፥ አንተ ግን ወደ እነርሱ አትመለስም ። “
  • ኢዮኤል 2:13 — “ ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ፥ ቍጣው የዘገየ፥ ምሕረቱም የበዛ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ ። “
  • 1ኛ ቆሮንቶስ 15:1-4— “ወንድሞች ሆይ፥ የሰበክሁላችሁን ደግሞም የተቀበላችሁትን በእርሱም ደግሞ የቆማችሁበትን በእርሱም ደግሞ የምትድኑበትን ወንጌል አሳስባችኋለሁ ፤ በከንቱ ካላመናችሁ በቀር፥ ብታስቡት፥ በምን ቃል እንደ ሰበክሁላችሁ አሳስባችኋለሁ ። እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ፦ መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም ፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ ፡፡ “