From Evil Leadership to Godly
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Royal Throne 2 Chronicles 28-29 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የይሁዳን ነገስታቶች አንዳንዶች በእግዚአብሄር ፊት መልካሞችን እና አንዳንዶች ደግሞ በእግዚአብሄር ፊት ክፉ መሆናቸዉን እያየን ነው ፡፡ ዛሬ ለመነቃቃት ከመጥፎ ወደ ባስ መጥፎ እንሄዳለን ፡፡ የኢዮአታም ልጅ አካዝ ሁሉንም የሚታሰብ የጣዖትን ተግባር በመፈፀም መንገድ ተገኘ ፡፡ ለ 2ዜና መዋዕል ጭብጣችን ንጉሳዊ ዙፋን ነው ፡፡ ዛሬ ለእናንተ ጥያቄው ማን በንጉሳዊ ዙፋኑ ላይ ታስቀምጡታላችሁ የሚል ነው ? ይህ በምዕራፍ 28 እና 29 ለእኛ ሁለት ዋና ገፀ ባህሪይ ዋና ጥያቄ ነበር ፡፡
ትምህርት
2-ዜና መዋዕል (28፡ 1-8)፡ አካዝ በ 20 አመቱ ንጉስ በመሆን ለ 16 አመታት ገዛ (ቁጥር 1) ፡፡ ዜና መዋዕል ቤተ መቅደሱ ላይ እና በባቢሎን ወደ ስደተኞች መንፈሳዊ ምርኮኝነት ስለ መራው እንደ ሚያተኩር እናስታዉሳለን ፡፡ እንደ ንጉስ አካዝ የሚታሰበዉን ሁሉንም የጣዖት ድርጊት ፈፀመ ልጆቹን በማቃጠል በመሰዋት ጭምር ፤ ይህ የእስራኤል ክፉ ነገስታቶች እንኳን በፍፁም አድርገዉት አልነበረም ( ቁጥር 2-3) ፡፡ ለከነዓናዊያን አማልዕክት ሞሎክ ልጆች ይሰዉበት የነበረዉ ስፍራ ገሃነም ለሚለዉ ቃል ሄኖም ተብሎ ወደ ሚጠራዉ ሸለቆ ያመራል ፡፡ በግሉ በኮረብታዎች ላይ ያመልክ ነበር (ቁጥር 4) ፡፡ ጥቂት ሰዎች በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ እንደ ይሁዳ ንጉስ አካዝ ወደ እግዚአብሄር በኃይል ይቃወሙ ነበር ፡፡
በቁጥር 4 እና 5 መካከል እግዚአብሄር ለአካዝ በእግዚአብሄር ላይ መደገፍ እንደ ሚችል አሳየው ( ኢሳ 7፡ 1-17) ፤ የእግዚአብሄርን ቃል እንዲያምን በኢሳያስ የቀረበለትን ጥሪ እግዚአብሄርን አልፈታተንም በማለት በዉሸት ኃይማኖት አጥባቂነት እምቢ አለ (ኢሳ 7፡ 12) ፡፡ እግዚአብሄር አሁንም ድንግል እንደ ምትወልድ ስሙም አማኑኤል ተብሎ እንደ ሚጠራ የሚል ትንቢት በመስጠት አንድ ምልክት ሰጠ (ኢሳ 7፡ 14) ፤ ይህ ለክርስቶስ እና ለሚመጣዉ የሶሪያዊያን ወረራ የወደፊት ትንቢት ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ክፉዉን አካዝ የይሁዳን ምርኮ ወደ ደማስቆ በመዉሰድ ለእስራኤል ንጉስ ለሰጠዉ ለሶሪያ ንጉስ አሳልፎ ሰጠው ፡፡ የእስራኤል ንጉስ በታላቅ ምት መታው (ቁጥር 5) ፡፡
ሐተታ ሰጪ ዊንፍራይድ ኮርዶዋን የፃፈው “ እግዚአብሄርን መተው የማይቀር በእግዚአብሄር መጣልን ያመጣል “ ፡፡ በቁጥር 5-8 የእስራኤል ሰራዊቶች በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የይሁዳ ሰዎችን ገደሉ የአካዝን ልጅ ምናሴን ገደሉት ፤ የቤቱን አዛዥ ዓዝሪቃምን እና የአካዚያስን ሁለተኛ ልጅ ሕልቃናን ገደሉ ፤ በተጨማሪም እስራኤላዊያን 200,000 ምርኮኞችን (ሴቶችን እና ልጆችን ጨምሮ) በመዉሰድ ወደ ሰማሪያ ዘረፉት (መዘበሩት) ፡፡ እግዚአብሄር ቅጣቱን በይሁዳ ላይ ለማምጣት ሰማሪያን ብቻ አልተጠቀመም ነገር ግን ለማሸነፍ ከሰሜን ከጣዖት አምላኪ መንግስት የእስራኤልን ሰራዊት ተጠቀመ ፡፡
2-ዜና መዋዕል (28፡ 9-15)፡ ቁጥር 9 የሚያስደንቅ የእረፍት ጊዜ ይጀምራል ፡፡ የእግዚአብሄር ነቢይ ዖዴድ ወደ ሰማሪያ የመጡትን የእስራኤልን ሰራዊት ለመገናኘት በመሄድ እድላቸዉን በእግዚአብሄር ላይ እየሳቡ እንደ ነበረ ነገራቸዉም ፡፡እግዚአብሄር ይሁዳን ለመቅጣት ተጠቀመባቸው ነገር ግን እንደ ፈለጉት እንዲያደርጉ ፍቃድ ስላልተሰጣቸው የወሰዱትን ወደ ይሁዳ መልሰዉ ይወስዳሉ (ቁጥር 9-11) ፡፡ በምላሹ የኤፍሬማዊያን አለቆች ምርኮዉን እና የዘረፉትን ወደ ይሁዳ ተመልሶ መሄድ አለበት አሉ ይህ ከሆነ የእስራኤላዊያን ጥፋተኝነት በኤፍሬም ነገድ ላይ የሚመጣ አይሆንም (ቁጥር 12-13) ፡፡ የኤፍሬም ሰዎች ለምርከኞቹ በመጠንቀቅ ጫማና ልብስ ለሚያስፈልጋቸዉ ጫማና ልብስ ሰጡዓቸው (አንዳንዶች እርቃናቸዉን ለነበሩት)፣ መገቡዓቸው፣ ቁስላቸዉን ጠረጉላቸው በተጨማሪም ለደከሙት ሁሉ አህያ ሰጡዓቸው ፤ ከዚያም ይሁዳዊያንን ወደ ኢያሪኮ መልሰዉ ወሰዱዓቸው (ቁጥር 14-15) ፡፡ በመልሱ ጉዞ ላይ ጉዳታቸዉን (ችግራቸዉን) ለመቀነስ ከሚችሉት መጠን በላይ አልፈዉ ሄዱ ፡፡ የእስራኤል ሰዎች የዖዴድን ማስጠንቀቂያ በመስማት ምላሽ ሰጡ ፡፡
2-ዜና መዋዕል (28፡ 16-27)፡ ይሁዳ በአካዝ ዘመን ስር መጥፋቱን ቀጠለ ፡፡ ቀጥሎም አካዝ ለእርዳታ የአሶርን ንጉስ ጠየቀ (ቁጥር 16) ፤ በምላሹም ኤዶማዊያን እና ፍልስጤማዊያን ይሁዳን አጠቁ፣ ወደ ምርኮም ወሰዱ፣ በከተሞቻቸዉም ላይ ተቀመጡባቸው አሶራዊያንም ደግሞ አጠቁዓቸው (ቁጥር 17-18, 20) ፡፡ “ የይሁዳም ንጉስ አካዝ እግዚአብሄር ክዷልና ከእርሱም እጅግ ርቆአልና እግዚአብሄርስለ እርሱ ይሁዳን አዋረደው “ (ቁጥር 19) ፡፡ አካዝ ለአሶራዊያን ለመስጠት ለመሞከረ የእግዚአብሄርን ቤተ መቅደስ መዝብሮ ነበር ነገር ግን አይረዱት (ቁጥር 21) ፤ ከዚያም አካዝ በይበልጥ ለእግዚአብሄር ባለመታመን ይረዱኛል ብሎ ተስፋ በማድረግ ለደማስቆ አማልዕክት ሰዋ (ቁጥር 22-23) ፤ “ ነገር ግን ለእርሱና ለእስራኤል ሁሉ ዕንቅፋት ሆኑ “ (ቁጥር 23) ፡፡
ወደ አምላክ ያህዌ በመመለስ ፋንታ አካዝ ለይሁዳ እርዳታ ለማግኘት የሌሎችን ሀገራት አማልዕክቶችን በማምለክ ለመገናኘት (ለመተሳሰር) መሞከሩን ቀጠለ ፡፡ ለአካዝ እግዚአብሄርን ወደ ማምለክ መመለስ መታሰብ የሌለበት ነገር አልነበረም ነገር ግን በደማስቆ የተቀላቀለዉ የሶሪያ ኃይማኖት፣ የከነዓናዊያንን አምላኮችን ከጥቂት ከራሳቸዉ አማልዕክቶች ጋር ማጣመር ለእርሱ ትክክል መስሎታል ፡፡ አካዝም የእግዚአብሄርን ቤተ መቅደስ እቃዎች ሰባበረ፣ ቤተ መቅደሱንም ዘጋ፣ በኢየሩሳሌምም በሁሉም ማዕዘን መሰዊያን በመስራት በይሁዳም ከተሞች ሁሉ መስገጃ ኮረብታዎችን አደረገ (ቁጥር 24) ፡፡ አካዝ በመንግስቱ ሁሉ የእግዚአብሄርን አምልኮ ለመተካት ፈለገ ፡፡ መልካሙ ዜና የንጉስ አካዝ ልጅ ሕዝቅያስ በእርሱ ቦታ ንጉስ መሆኑ ነው (ቁጥር 26-27) ፤ ይህ ክፉ ንጉስ ቢኖርም የዳዊት መስመር እንደ ተጠበቀ ነው ፡፡
በይሁዳ የእምነቱ ሁኔታ መጋኘት ከተቻለዉ በጣም ክፉ ነበር ፤ ቤተ ክርስቲያን በድካሟ ባላች እና የኮሌጅ ተማሪዎችም እንኳን በኢየሱስ ስላላቸዉ እምነት እዉቅና በማይሰጡበት ጊዜ በ 1790 በአሜሪካ ታሪክ ተመሳሳይ ጊዜ አለ ፤ በዚህ ጊዜ በኮነኪቱ በአዲስ ሰማይ ያሌ ዩንቨርስቲይ ላይ በአምስት ተማሪዎች ፀሎት ሁለተኛዉ ታላቅ መነቃቃት ጀምሮ ነበር ፡፡ ያ የፀሎት ንቅናቄ ወደ ያሌ መነቃቃት መራ በሀገራችንም ላይ የፈነዳ የመንፈስ እንቅስቃሴ ሆነ ፡፡
2-ዜና መዋዕል (29፡ 1-19)፡ ሕዝቅያስ ንጉስ በሆነ ጊዜ 25 አመቱ ነበር 29 አመትም ገዛ ፡፡ “ አባቱም ዳዊት እንዳደረገ ሁሉ በእግዚአብሄር ፊት ቅን ነገር አደረገ “ (ቁጥር 1-2) ፡፡ የሕዝቅያስ ስም ትርጉሙ “ ጆሆቫ አባቴ ነው “ ወይም “ የእግዚአብሄር ፍቃድ “ ማለት ነው ፡፡ የእናቱ ስም አቡ ነበር (ብዙ ጊዜ ለወንድ ስንጠቀምበት ያየነው ስም) የዘካሪያስ(ነቢይ ያልነበረው) ልጅ ነበረች ፡፡ ፀሀፊዉ ሕዝቅያስን ፀባዩን ከቀድሞ አያቱ ዳዊት በማነፃፀር ከፍተኛ አድናቆት (ምስጋና) ሰጥቶታል ፤ የሕዝቅያስ ታሪክ በጣም ትረጉም ያዘለ ነበር በብሉይ ኪዳንም ሰዎስት ጊዜ ተነግሯል፡ 2ነገስት፣ 2ዜና መዋዕል እና ኢሳያስ ፡፡
ሕዝቅያስ በፍፁም ራሱን በአባቱ የጥፋት ዘመን እንደ ተጠቂ አላየም ነገር ግን በዚያ ፋንታ በጋለ ስሜት በመሆን ሆን ብሎ ለጥፋት አባቱ ምክንያት የሆነዉን መልሶ ለመስራት ሄደ ፡፡ ሕዝቅያስ በቤተ መቅደሱ እንደገና መለየት ጀመረ ፤ ካህናቱን እና ሌዋዊያኑን ራሳቸዉን እንዲያነፁ ከዚያም ቤተ መቅደሱን እንደ ገና እንዲያቋቋሙ አዘዛቸው (ቁጥር 3-11) ፡፡ ንግግሩ ምናልባትም ከ250 አመት ለቤተ መቅደሱ በሰለሞን የመለየት ፀሎት ላይ የተመሰረተ ነበር (2ዜና መዋዕል 6፡ 14-42) ፤ በተጨማሪም ሕዝቅያስ ራሱን ለአዲስ ኪዳን በመስጠት ለይሁዳ መንግስት ለለዉጥ አርዕያነትን አነሳሳ ፡፡ ሌዋዊያንም ተግባራቸዉን እንደ ገና መያዛቸው በእግዚአብሄር እና በህዝቡ መካከል ለታደሰ ዝምድና ምልክት ይሆናል ፡፡ ሌዋዊያን እና የቤተ መቅደሱ ሙዚቀኞች በመቆም በትጋት አዲስ ተግባር ያዙ (ቁጥር 12-14) ፤ ራሳቸዉን በመቀደስ እንደ ንጉሱ ትዕዛዝ እና እንደ እግዚአብሄር ቃል ለመስራት ሄዱ (ቁጥር 15-19) ፡፡ ይህ መጥፎ ነገርን ማስወገድ ሁለት ሳምንት ወሰደ ፡፡
2-ዜና መዋዕል (29፡ 20-36)፡ ሕዝቅያስ በተለያዩ በአመታዊ የስርየት ድግስ ላይ(ዘሌ 16፡ 18) እና በትክክል ለጉዳዩ ከሚሆነዉ በላይ እንስሳት ተጠቅመዉት ከነበረው ዉጪ በኃጢዓት ስርየት(ዘሌዋን 4) ቤተ መቅደሱን እንደ ገና በመቀደስ መራ ፡፡ ንጉሱ እጆቹን በመስዋዕቱ ላይ ማስቀመጡ የካህናቱን ተግባር የመያዝ ምልክት አይደለም ነገር ግን የህዝቡን ፍላጎት ለማሳየት እንደ ሆነ አስታዉሉ ፤ በህጉ በትክክል ተጠቀመው (ቁጥር 20-24) ፡፡ በማክበሩ እና በመለየቱ የዳዊትን መዝሙሮች ዘመሩ በመጨረሻም የእግዚአብሄርን አምልኮ እንደ ገና ወደ ኢየሩሳሌም አመጡ (ቁጥር 25-26) ፡፡ ቁጥር (27-33) በእግዚአብሄር ፊት ስለ መጣዉ መስዋዕት ያወራል ፤ በአጠቃላይ 600 በሬዎች እና 3,000 በጎች እና ፍየሎች ተለይተዉ ነበር ፡፡ ሕዝቅያስም ሌሎችን መስዋዕታቸዉን እንዲያመጡ ጋበዛቸው ፡፡ የመስዋዕቱ እና የቁርባኑ ስጦታ ቁጥር ትልቅ ነበር - በጊዜዉ መስዋዕቱን መቆጣጠር የሚችል በቂ ካህናት አልነበሩም ምክንያቱም በቂ የካህናቱ ቁጥር የመንፃት ስርዓታቸዉን አልፈፀሙም ነበር (ዘሌ 8፡ 136) ፡፡
በቂ ካህናት ስላልነበር ሌዋዊያን እረዱዓቸው ፤ ከካህናቶቹ ይልቅ ራሳቸዉን ለመቀደስ በብዙ ያስቡ ነበር (ቁጥር 34)፡፡ ከመስዋዕቱና ከቁርባኑ በኋላ ሕዝቅያስ እና ሕዝቡ እግዚአብሄር ለሕዝቡ አዘጋጅቶት በነበረዉ ላይ ተደሰቱ ምክንያቱም በአንድ ወር ብቻ ሆኖ ስለ ነበር (ቁጥር 35-36) ፡፡ በሕዝቅያስ ዘመን በመጀመሪያዉ ወር (2ዜና መዋዕል 29፡ 3) ይሁዳ ከአካዝያስ ብሔራዊ ጣዖት ከአረንቋ ሕዝብ ከእግዚአብሄር ጋር ወደ ታደሰዉ ዝምድና (ግንኙነት) ተጉዘዉ ነበር ፡፡
መደምደሚያ
በእግዚአብሄር ኃይል ለእርሱ በአገልግሎት በምንድን ነዉ የጠራችሁ ? ከእግዚአብሄር ጋር በትስስራችሁ እግዚአብሄር እንድታደርጉት የሚያነሳሳችሁ ምንን ነው ? ለዉጥ በእኛ ጥንካሬ ሳይሆን በእግዚአብሄር ይመጣል ፡፡ በዙሪያችሁ ምንድን ነዉ እየተከናወነ ያለው ? ቤተሰቦቻችሁም ይሆናሉ ፤ ንጉስ ሕዝቅያስ ለዉጥ ማድረግ እንዳለበት ስላወቀ የሚያደርገዉ ስራ ነበረው ፡፡ በንጉሳዊ ዙፋን ላይ የምታስቀምጡት ማንን ነው ? በዚህ ስራ ለይቶ የሚጠራችሁ ማነው ? ይህን ለጌታ ታደርጉታላችሁ ? በንጉሳዊ ዙፋን ላይ አንድ ነው ፤ ሁሉም ይገባዋል ፡፡
Winfried Corduan, Holman Old Testament Commentary: 1 and 2 Chronicles (Nashville: Holman Reference Publishers, 2004), p. 324.
ጥያቄዎች
-
ንጉስ አካዝ በእግዚአብሄር ፊት በኃይለኛዉ ኃጢዓት አደረገ ፤ በ 2ዜና መዋዕል (28፡ 3) ልጆቹን በእሳት አቃጠላቸው ፡፡ ሌላ የት ላይ የልጅ መስዋዕት ታገኛላችሁ (2ነገ 21፡ 6፣ ኤር 32፡ 35) ? ለዚህ የእግዚአብሄር ምላሽ ምን ነበር ? (ዘሌ 20፡ 2-5፣ ኤር 32፡ 35)
-
በ 2ዜና መዋዕል (28፡ 15) ሰዎቹ ምርኮኞቹን እየተንከባከቡዓቸዉ ነበር ፤ ይህ ኢየሱስ ላስተማረው እንዴት ሞደል ይሆናል ? (ማቴ 25፡ 34፣ 40)
-
ንጉስ ሕዝቅያስ በእግዚአብሄር ፊት መልካም የነበረውን አደረገ ፤ እግዚአብሄርስ ምን አደረገለት (2ነገ 20፡ 1-6) ? ለምን ?
-
ንጉስ ሕዝቅያስ የአባቱን ልክ ያልሆነ ተግባርን በማንፃት ጀመረ ፤ ይህን ለመፈፀም በ 2ዜና መዋዕል 29 ምን እርምጃዎችን ወሰደ ?
-
በ 2ዜና መዋዕል (29፡ 34) ካህናቱ ተጨማሪ እርዳታ ለምን አስፈለጋቸው ? እርዳታቸዉን ከየት ሳቡ ? በግል አስተያየታችሁ ይህ በእግዚአብሄር ቃል በመስመር ነበር ? ለምን ወይስ ለምን አልነበረም ?
-
በ 2ዜና መዋዕል (28-29) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Chronicles 29:10–11
“It is in my heart now to make a covenant with Yahweh, the God of Israel so that His burning anger may turn away from us. My sons, don’t be negligent now, for the LORD has chosen you to stand in His presence, to serve Him, and to be His ministers and burners of incense.”
እግዚአብሔር ከሌለበት የንጉሥ አካዝ ዘመን በኋላ ልጁ ሕዝቅያስ ነገሠ ፡፡ ከአባቱም በተለየ በዙሪያው ያሉትን ነገሮችን ለእግዚአብሔር መቀየር ጀመረ ፡፡ በንግሥና የመጀመሪያ አመቱ የመጀመሪያ ወር የሃያ አምስት አመቱ ሕዝቅያስ ልክ አባቱ ዳዊት እንዳደረገው በእግዚአብሐር ፊት ቅን የሆነውን ለማድረግ አላመነታም ጊዜም አላጠፋም ፡፡ ንጉሥ ሐዝቅያስ እግዚአብሔር በልቡ ያስቀመጠውን ከእስራኤል አምላክ ጋር ኪዳን የማድረግ አሳብ ተከተለ እንድሁም ቤተ መቅደሱን መቀደስ ጀመረ ፡፡ የተሰበሩትን ነገሮች ጠገነ ፤ ያልተቀደሰውንም ማንኛውንም ነገር ከቤተ መቀደሱ አስወገደ ፡፡ ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሕዝቅያስና በዙሪያው ያሉት በደስታ ዘመሩ ፤ ለእግዚአብሔርም ክብር ሰገዱ ፡፡ በኢየሩሳሌም ድንገተኛ መነቃቃት ሆነ ይህም መልካም ነበረ ፡፡
በህይወትህ ነገሮችን ለመቀየር ጊዜው ነውን ? ትላንትናህ እንድሁም ደግሞ ከአንተ በፊት የነበረ ትውልድ ኃጢአት የአንተን ማንነት አይገልጽም ፡፡ ለመጠገን ፤ ለመፈወስ ፤ ከህይወትህም ቆሻሻን ለማስወገድ አስበሃልን ? ሊሆን ይቸላል ፡፡ የኢየሱስ ፍቅር ከርኩሰት ሁሉ እንድያጥብህ ፍቀድ ፡፡ ጸጋው ሁሉን ይሸፍናል ምህረቱ ደግሞ ማለዳ ማለዳ አድስ ነው ፡፡ በዚህ ጊዜ ፍቅርን ይሰጡህና ይደግፉህ ዘንድ ራስህን በሌሎች መካከል አድርግ ፡፡ እንደገናም ትደሰታለህ ፤ እንደገናም መዝሙር ትዘምራለህ ፡፡ በክርሰቶስ ፍቅር ነጻነት ውስጥ ትኖራለህ ፡፡ ሁሉንም ነገር ለመመለስ ትጋትና ሙሉ አቅምን መጠቀም ይጠይቃል ፡፡ ነገሮችን የመቀየር አሳብ በልብህ ካለ ፣ በል መፈጸሙን ጀምር ፡፡
“ አሁንም የቍጣው ጽናት ከእኛ እንዲመለስ ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን አደርግ ዘንድ በልቤ አስቤአለሁ ። ልጆቼ ሆይ፥ በፊቱ ትቆሙና ታገለግሉት ዘንድ፥ አገልጋዮቹም ትሆኑ ዘንድ፥ ታጥኑለትም ዘንድ እግዚአብሔር መርጦአችኋልና ቸል አትበሉ ። “
- 2ኛ ዜና 29፡10-11
ተጨማሪ ጠቅስ
ቲቶ 3:3-5 — “ እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን። ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ ፥ እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም ፡፡ “
1ኛ ጰጥሮስ 2:1-3 — “ እንግዲህ ክፋትን ሁሉ ተንኰልንም ሁሉ ግብዝነትንም ቅንዓትንም ሐሜትንም ሁሉ አስወግዳችሁ ፥ ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።
1ኛ ዮሐንስ 1:9 — “በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።