Historical Books 2 Chronicles

Becoming Desensitized to God's Word

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Royal Throne 2 Chronicles 25-27 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 314 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የታሪክን መፅሀፍት ማጥናት ስንቀጥል በመፅሀፍት ነገስታት እና ነቢያት ላይ በመመልከት መከለሳችን ትርፋማ እንደ ሆነ እንደምታዩት ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡ ማታለልን እና ሴራን አይተናል ይሁን እንጂ አሁንም እግዚአብሄር ወደ መንግስቱ ብርሃን ለማምጣት የሚጠቀምባቸዉ አሉ ፡፡ የ 2ዜና መዋዕል ጭብጡ ንጉሳዊ ዙፋን ሲሆን በኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሄር በምድር ላይ የሚመሰርተዉን መንግስት ያመለክታል ፤ ዛሬም በእምነት በመንግስቱ መመስረት ላይ በመስራት እንቀጥላለን ፡፡ በ 2ዜና መዋዕል (25-27) በጥናታችን ሰዎስት ነገስታትን እናጠናለን፡ አሜስያስ፣ ዖዝያን እና ኢዮአታም ፡፡

ትምህርት

2-ዜና መዋዕል (25፡ 1-8)፡ የኢዮአስ ልጅ ንጉስ አሜስያስ ንግስናዉን በ25 አመቱ በመጀመር 29 አመታትን ገዛ (ቁጥር 1) ፡፡ አሜስያስ በእግዚአብሄር ፊት መልካም ነገር አደረገ ነገር ግን ፍፁም ልብ አልነበረዉም - በእግዚአብሄር ሙሉ እምነት ስላልነበረው ሙሉ በሙሉ በጥሪዉ ለመጓዝ ወኔ(መነሳሳት) አጠረው (ቁጥር 2) ፡፡ አሜስያስ የአባቱን ህይወት ያጠፉትን የአባቱን አገልጋዮች ገደላቸው (ቁጥር 3) ፤ ይሁን እንጂ በሙሴ መፅሀፍት መሰረት ልጆቹን አልገደለም ፡፡ የእምነቱን መርህ ያዉቃል (ቁጥር 4) ፤ ከዚያም አሜስያስ የይሁዳን ሰዎች በቡድን በማዋቀር 20 አመት እና ከዚያ በላይ የሆኑትን ቆጠረ 300,000 የተመረጡ ወታደሮችንም አገኘ (ቁጥር 5) ፤ በተጨማሪም አሜስያስ ከሰሜን መንግስት ከእስራኤል 100,000 ሰዎችን ቀጠረ (ቁጥር 6) ፡፡ መፅሀፍ አሜስያስ ከእስራኤል ጋር ፖለቲካዊ ጥምረት ያድርግ አያድርግ አይናገርም ነገር ግን አንድ የእግዚአብሄር ሰዉ (አንድ ነቢይ) አሜስያስን እግዚአብሄር ከእስራኤል ጋር ስለሌለ የእስራኤላዊያንን ወታደሮች ከእርሱ ጋር ከወሰደ በጦርነት እንደ ሚሸነፍ ነግሮታል (ቁጥር 7-8) ፡፡

በዚህ ሁሉ ጨዋታ የእግዚአብሄር ድርሻ ምንድን ነው ? “ እግዚአብሄር የመርዳት ኃይል “ እና “ አንዱ የማደናቀፍ ኃይል “ አለው (ቁጥር 8) ፡፡ እግዚአብሄር ለተናገረው ከመታዘዝ በተለዬ ዉሸት በምን ይሆናል ፡፡

2-ዜና መዋዕል (25፡ 9-27)፡ አሜስያስ ቀድሞ ለእስራኤል ወታደሮች እንደ ከፈለ አመለከተ ነገር ግን የእግዚአብሄር ሰዉ ከከፈላቸዉ ወታደሮች በላይ እግዚአብሄር ድጋፍ እንደ ሚሰጠው ጠቀሰ (ቁጥር 9) ፤ አሜስያስም ወደ ቤታቸዉ የላካቸዉን የእስራኤልን ወታደሮች ለየ በይሁዳም ህዝብ በጣም ተበሳጩ ምክንያቱም ከጦርነት ምርኮ ስለ ማይቀበሉ (ቁጥር 10) ፡፡ አሜስያስ ሰራዊቱን ለድል በሴይር ላይ መራ (ቁጥር 11) ፤ አሜስያስ ለእግዚአብሄር የታዘዘ መሆን ፈለገ ነገር ግን መልሶ የሴይርን ልጆች አማልዕክት በማምጣት አመለካቸው (ቁጥር 14)፡፡ የእግዚአብሄር ቁጣ በኃይለኛዉ በአሜስያስ ድርጊት እና በይሁዳ እምነት መዉረድ ላይ( በእነዚህ ሰዎስት ምዕራፎች ሁሉየሆነ ነገር እናያለን) ነበር ፡፡ እግዚአብሄር አሜስያስን እግዚአብሄር ድል በሰጣቸዉ ጊዜ ምንም ኃይል ያለነበራቸዉን ጣዖቶች ለምን ፈልጎአቸዉ እንደ ነበር እንዲጠይቀዉ አንድ ነቢይ ላከ (ቁጥር 15) ፡፡

በብስጭትና በኩራት አሜስያስ ምክር በመዉሰድ (ከእግዚአብሄር ሰዉ ካልሆነው ከአማካሪው) ከእርሱ ጋር ለመገናኘት ለእስራኤል ንጉስ ለኢዮአካዝ ጠራው (ቁጥር 16-17) ፡፡ አሜስያስ ተገፍቶ ከነበረዉ ከኢዮአካዝ ጋር ጥምረት ለመፍጠር ሞከረ ፤ ይህ ይሁዳ ወደ ተሸነፈበት ጦርነት እና ወደ አሜስያስ መያዝ መራ ፡፡ በመጨረሻም በለኪሶ ተገደለ (ቁጥር 18-27) ፡፡

2-ዜና መዋዕል (26፡ 1-23)፡ የአሜስያስ ልጅ ዖዝያን በ16 አመቱ ቀጣዩ ንጉስ በመሆን ይሁዳን ታደገ 52 አመትም ነገሰ (ቁጥር 1-3) ፤ ዖዝያን እግዚአብሄርን በመፈለግ በእግዚአብሄር ፊት ተክክል ነገር አደረገ (ቁጥር 4) ፡፡ በእዉነቱም ዖዝያን መልካም ንጉስ ቢሆንም እግዚአብሄር ከሚጠብቀዉ ህዝቡን የሚያደነዝዝ የሚሆን ይመስላል ፤ ዖዝያ በዘካሪያስ በኩል እግዚአብሄርን ተመለከተ ( ነቢይ ሳይሆን በብሉይ ኪዳን መፅሀፍ አለው) ፤ ዖዝያ የእግዚአብሄርን ፍቃድ እስከ ተመለከተ ድረስ አበለፀገው (ቁጥር 5-6) ፡፡ ስኬታማ በሆነ ጊዜ ዖዝያ የታበየ በመሆን ወደ ቤተ መቅደሱ በመሄድ ዕጣኑን አጠነ (ቁጥር 16) ፤ ካህኑም ዖዝያን ለእግዚአብሄር ዕጣኑን ያቀርብ ዘንድ መብት እንዳልነበረዉ ነገረው ምክንያቱም ካህን ስላልነበር (ቁጥር 17-18) ፡፡ ዖዝያ ተበሳጨ በዚያ ቅፅበትም በቤተ መቅደሱ ዉስጥ እያለ በለምፅ ተመታ (ቁጥር 19) ፡፡ እግዚአብሄር ትብብር እና መታዘዝ እንጂ ትዕቢት እና ኩራት አይፈልግም ፡፡ እንደ አንድ ለምፃም ዖዝያን ከኢየሩሳሌም በመወገድ እስኪሞት ድረስ በማቆያ ኖረ (ቁጥር 20-23) ፡፡

2-ዜና መዋዕል (27፡ 1-14)፡ የዖዝያን ልጅ ኢዮአታም በ 25 አመቱ ላይ ቀጣዩ ንጉስ በመሆን 16 አመት ገዛ (ቁጥር 1) ፡፡ ኢዮአታም በእግዚአብሄር ፊት ትክክል ነገር አደረገ አባቱም አድርጎት እንደ ነበረው ወደ ቤተ መቅደስ አልገባም ይሁን እንጂ ሕዝቡ በበደል ተመላለሱ (ቁጥር 2) ፡፡ ትክክል አደረገ ነገር ግን የእርሱ የተለመደዉ ነገር ምን ነበር ? በእግዚአብሄር ትክክል ለመሆን መስመሩን ለመሳል ለማወቅ እንደ ስብዕና አመልካች በእግዚአብሄር ቃል መነሻ መስመር ሊኖረን ያስፈልጋል ፤ ይሁን እንጂ ለእግዚአብሄር ቃል እና ጥሪ በኃይል የደነዘዝን ልንሆን እንችላለን ፤ በደነዘዘ አለም እንደ ምንኖር የማናምን ከሆነ ራሳችንን እያሞኘን ነው ፡፡

መደምደሚያ

የኃይልን ደረጃ ያሳዬ የቀጠለ የነገስታት ስራ ነበር ፤ ያን ኃይል መያዝ እንዴት አስፈላጊ ነበር ፡፡ ኃይል ወደ ኩራት፣ ወደ ጣዖት፣ በራስ ወደ መደገፍ እና በራስ ወደ ማስተዳደር፣ መሪነትን አክብሮትን ወደ ማጣት እና በህዝቡ ወደ መበላሸት ሊመራ ይችላል ፡፡

ዮሐ(10፡ 10) “ ሌባዉ ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፉም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም ፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸዉም መጣሁ “ በማለት ይናገራል ፡፡ ለማን የተሰጠን እና የተቀደስን መሆን እንዳለብን መወሰን ያስፈልገናል ፡፡ ጠላት መስራቱን ይቀጥላል ፡፡ ማንን ነዉ የምትከተሉት ?

ጥያቄዎች

  1. አሜስያስ ትክክል ነገር በማድረግ ጀመረ ነገር ግን ኤዶማዊያንን ካሸነፈ በኋላ ጣዖቶቻቸዉን መልሶ በማምጣት እንደ አማልክቶቹ በማቆም ሰገደላቸዉም እጣንም አቃጠለላቸው፤ እግዚአብሄርን በመተዉ እነዚህን አማልዕክቶች ለምን እንዳመለከ ምን ታስባላችሁ ? በህይወታችሁ እግዚአብርን በመተው ወደ ሌሎች “ አማልዕክቶች “ ስለ ዞሩ ሰዎች ማስረጃ አላችሁ ? አዎ ከሆነ ምን አደረጋችሁ ?
  2. እግዚአብሄር ወደ እርሱ ልኮት ለነበረዉ ነቢይ የአሜስያስ ምላሽ ምን ነበር (2ዜና መዋዕል 25፡ 15-16) ? ለመቀየር ፍቃደኞች ባለመሆናችሁ ምክንያት በኃጢዓታችሁ የተፈተናችሁ መሆንን አስወግዳችሁ ታዉቃላችሁ ? አዎ ከሆነ ዉጤቱ ምን ነበር ?
  3. 2ዜና መዋዕል (26፡ 5) እግዚአብሄርን እስከ ተመለከተዉ ድረስ እግዚአብሄር አበለፀገው ይላል ፤ ይህ ጥቅስ “ በስራ የተመሰረተ “ የእምነት ስርዓት ያላቸዉን ሊደግፍ ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ ? ይህ አሳብ ከሌሎች መፅሀፍት ፅሆፎች የተለየ መሆኑን እንዴት ታስረዳላችሁ ?
  4. የንጉስ ዖዝያን ትዕቢት በብልሽት እንዲሰራ እና ለእግዚአብሄር የታመነ እንዳይሆን ምክንያት ሆነው ፤ ያለመታመኑ ዉጤት ምን ነበር (2ዜና መዋዕል 26፡ 19) ? ለአለመታመን ዉጤቶቹ እኛን መቅጣት ማለት ነዉ ወይስ ለሌላ አላማ ለመስራት ያገለግላሉ ? መልሳችሁን ለመደገፍ ምን የመፅሀፍት ፅሁፍ(ክፍል) ትጠቀማላችሁ ?
  5. በ 2ዜና መዋዕል (25-27) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Chronicles 26:15–16

“He made skillfully designed devices in Jerusalem to shoot arrows and catapult large stones for use on the towers and on the corners. So his frame spread even to distant places, for he was marvelously helped until he became strong. But when he became strong, he grew arrogant and it led to his own destruction. He acted unfaithfully against the LORD his God by going into the LORD’s sanctuary to burn incense on the incense altar.”

እግዚአብሔር የይሁዳን ንጉሥ ዖዝያንን ኃያል አደረገው ፤ ዝናውም እስከ ግብጽ ድረስ ተሰማ ፡፡ ንጉሥ ዖዝያን የምሽግ ግንቦችን ቆፈረ ፤ ከተሞችን ሰራ ፤ በወጊያ ድል ተቀዳጀ እንድሁም ኃያል ሰራዊትን መራ ፡፡ ይህ አስደናቂና ጠንካራ ስልጣን ተለወጠና ንጉሥ ዖዝያን ትዕቢተኛ ሆነ ፡፡ ከዚህም በመከተል ራሱን ለጥፋት ያዳረገውን ፈጸመ ፣ እግዚአብሔር አምላኩን በደለ ፡፡ ንጉሥ ዖዝያን በበረታ ጊዜ በእግዚአብሔር ላይ መታመን አቆመ ፡፡ መንግስቱ ተናደ ፤ በመጨረሻም ለሞት ዳረገው ፡፡

ልክ ኢየሱስን የግል አዳኝህና ጌታህ አድርገህ ከተቀበልክባት ሰዓት ጀምሮ ፣ በየትኛውም የራስህ ስራ ሳይሆን ፣ በእምነት ድነሃል ፡፡ አይኖችህን በክርስቶስ ላይ አድርገህ ሰትኖር ብርታትህ ፤ ስኬትህ ፤ መከናወንህ ሁሉ የሚገኘው ከጌታ ብቻ ነው ፡፡ ምንም እንኳ አንዳንድ ሰዎች በዚህ አለም ነገር ላይ ቢታመኑም ፣ አንተ ግን እንደ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር በአምላክህ በእግዚአብሔር ስም ብቻ ታመን ፡፡ እግዚአብሔር በፊቱ ራስህን ዝቅ ብታደርግ ፣ በጊዜው ከፍ እንደሚያደርግህ ይናገራል ፡፡ ሰለዚህም ራስህን ከፍ ከፍ ማድረግ አይጠበቅብህም ፣ ጭራሽ ለራስህ ዋጋ በመስጠት ጊዜ እንዳታጠፋ ፡፡ እግዚአብሔርን አክብር ደግሞም ስለ ታማኝነቱ ፤ ስለ ኃያልነቱና ስለ ሁሉን ቻይነቱ አመስግነው ፡፡ ከአለም አንጻር ምንም ያህል ብርቱ ወይም ኃያል ሰው ሁን ፣ እግዚአብሔር ክብሩን ሁሉ ጠቅልሎ ይውሰድ ፡፡

“ በኢየሩሳሌምም በብልሃተኞች እጅ የተሠሩትን፥ በግንብና በቅጥር ላይ የሚኖሩትን፥ ፍላጻና መርግ የሚወረወርባቸውን መሣሪያዎች አደረገ፤ እስኪበረታም ድረስ እግዚአብሔር በድንቅ ረድቶታልና ዝናው እስከ ሩቅ ድረስ ተሰማ ። ነገር ግን በበረታ ጊዜ ለጥፋት ልቡ ታበየ፥ አምላኩንም እግዚአብሔርን በደለ፤ ወደ መቅደስ ገብቶ በዕጣን መሠዊያ ላይ ዐጠነ ። “

  • 2ኛ ዜና 26፡15-16

ተጨማሪ ጥቅስ

ምሳሌ 16:5 — “በልቡ የታበየ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነው፥ እጅ በእጅም ሳይቀጣ አይቀርም ። “

ኤፌሶን 2:8–9 — “ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም ፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም ። “

1 ጴጥሮስ 5:6 — “ እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ “