Joash Repairs the Temple
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Royal Throne 2 Chronicles 23-24 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ለ 1ዜና መዋዕል ቃላችን የዳዊት ልጅ ነበር ለ 2ዜና መዋዕል ደግሞ ንጉሳዊ ዙፋን ነው ፤ በአንድ ላይ እነዚህ ቃላቶች ወደ ኢየሱስ ዘር ያመለክታሉ ፡፡ ዛሬ እግዚአብሄር ለዚህ አላማ ስላዳነዉ በሰባት አመት አንድ ህፃን ልጅ በኩል መቀጠሉን እናያለን ፡፡
ትምህርት
2-ዜና መዋዕል (23፡ 1-11)፡ ኢዮአስ ዘዉድ የጫነ የይሁዳ ንጉስ ነበር ፡፡
2-ዜና መዋዕል (23፡ 12-15)፡ ጎቶልያ ተገደለች ፡፡
2-ዜና መዋዕል (23፡ 16-21)፡ ዮዳሄ በምድሪቱ ዉስጥ ተሀድሶ አደረገ ፡፡
2-ዜና መዋዕል (24፡ 1-3)፡ ኢዮአስ ዘዉድ የጫነ ንጉስ በነበር ጊዜ ሰባት አመቱ ብቻ ነበር በኢየሩሳሌምም ለ40 አመት ገዛ ፡፡ በመሰረቱ እንዲያድግ የረዳዉ እና በትክከለኛዉ ሂደት የመራዉ ሰዉ ነበረው ፤ ይህ የደቀ መዝሙርነት የሚያስደንቅ ምሳሌ ነበር ፡፡ ለዮዳሄ የመጨረሻ ግቡ ከኢዮስያስ ጋር ሲጓዝ ኢዮስያስ እንደ እግዚአብሄር መንገድ ያድጋል ፡፡ ዮዳሄ ካህን እስከሆነ ድረስ ኢዮአስ በእግዚአብሄር ፊት ትክክል የሆነዉን ያደርግ ነበር ፤ በሚያሳዝን ሁኔታ ዮዳሄ ሲሞት ኢዮአስ የይሁዳን አለቆች በመስማት የእግዚአብሄርን ቤተ መቅደስ በመተው የማምለኪያ ዐፀዶችን እና ጣዖቶችን አገለገለ (2ዜና መዋዕል 24፡ 17-18) ፡፡ በእርግጠኝነት ዮዳሄ እንደ ሞተ ወዲያዉኑ ኢዮአስ ከዮዳሄ ሀሳብ(ጭንቀት) ምንም ተምሮ እንዳልነበር ከእግዚአብሄር መመለሱን ሲያዉቅ በኃይል ይናደዳል ፡፡
2-ዜና መዋዕል (24፡ 4-5)፡ ኢዮአስ የእግዚአብሄርን ቤተ መቅደስ ለማደስ ወሰነ ፤ ኢዮአስ የይሁዳን ጥቂት መልካም ነገስታቶች አካሄድ ተከተለ ፡፡ በመላዉ ይሁዳ ቤተ መቅደሱን ለማደሻ ገንዘብ እንዲሰበስቡ ካህናቱን እና ሌዋዊያንን ላካቸው ፡፡ ኢዮአስም ሌዋዊያን ቸል ስላሉ “ በፍጥነት ድርጉ “ አላቸው ፡፡ በ 2ነገ (12፡ 6) የኢዮአስ 23 የስልጣን ዘመን አልፎ እንደ ነበር እንማራለን ይሁን እንጂ ካህናቱ ቤተ መቅደሱን አልጠገኑትም ነበር ፡፡ ኢዮአስ ንጉስ ሲሆን ሰባት አመቱ ስለ ነበር ካህናቱ እርሱን መስማት ከመጀመራቸዉ በፊት 30 አመቱ ነበር ማለት ነው ፤ ይህ የመጀመሪያዉ ስብስብ ወድቋል ፡፡ እዚህ ጋር ለኢዮአስ ዝም ለማለት ቀላል ይሆናል ፡፡
2-ዜና መዋዕል (24፡ 6-7)፡ ዉድቀት ማለት ወዳቂ ናችሁ ማለት አይደለም ፤ ጥረታችሁ ለመጀመሪያ ጊዜ አልሰራም ማለት እንጂ ፡፡ እግዚአብሄር የተለያዩ እቅዶች አሉት ፤ ነገር ግን በዚህ የዉድቀት ስፍራ የምትቆዩ ከሆነ እንደ ተጠቂ ትኖራላችሁ የእምነትንም አሸናፊነት አታገኙትም (አትቀምሱትም) ፡፡
በዚህ ጊዜ ሌዋዊያን ለንጉስ ኢዮአስ ትዕዛዝ የማይታዘዙ ነበሩ ምክንያቱም ታዛዥ ለመሆን ፍላጎት አልነበራቸዉም ፤ ስለዚህም ታላቁን ካህን፣ ተቆጣጣሪዉን እና አስተማሪዉን ዮዳሄን በመጥራት በሙሴ የተጣላዉን ግብር ሌዋዊያን እንዲሰበስቡ እንዳላዘዘ ጠየቀው ፤ የንጉሱ ጥያቄ ሌዊያያንን የንጉሱን ትዕዛዝ እንዲያደርጉ አድርጎ ስላልነበር ዮዳሄ ራሱም የታዘዘ እንዳልነበር ያመለክታል ፡፡ በዘጸ (30፡ 11-16) ሙሴ እግዚአብሄር እንዳዘዘዉ የቤተ መቅደሱን ግብር አቋቋመ (መሰረተ) ፤ እያንዳንዱ 20 አመት እና ከዚያ በላይ ሰዉ የመገናኛ ድንኳኑን ለማገልገል እንድ ስርየት ገንዘብ ግማሽ ሸቅል መስጠት ይጠበቅባቸዉ ነበር ፡፡ ኢዮአስም እግዚአብሄር በሙሴ በኩል አዝዞት የነበረዉን እንዲያደርጉት ሌዊያንን እየጠየቀ ነበር ፡፡ ለቤተ መቅደሱ ገንዘብ የሚቀበሉበት አንዱ መንገድ ይህ ነበር ፡፡ ሁለተኛዉ መንገድ ስለት ከተሳሉ ግለሰቦች ገንዘብ መቀበል ሲሆን ሰዎስተኛዉ መንገድ ደግሞ ከፍቃደኝነት ስጦታዎች ነበር (2ነገ 12፡ 4-5) ፡፡ ይህ ገንዘብ ያስፈልግ ነበር ምክንያቱም የርኩሷ ጎቶልያ ልጆች በቤተ መቅደሱ ዉስጥ የነበረዉን ሰብረዉት ስለ ነበርና የእግዚአብሄርን ቅዱስ እቃ ለባዖል ተጠቅመዉት ስለ ነበር (ቁጥር 7) ፡፡
2-ዜና መዋዕል (24፡ 8-12)፡ ንጉስ ኢዮአስ ሳጥን በመስራት ከእግዚአብሄር ቤተ መቅደስ መግቢያ በር ዉጪ ላይ ተቀመጠ ፡፡ ከዚያም በሙሴ ተጥሎ የነበረዉን ግብር ለቤተ መቅደሱ እንዲያመጡ አዋጅ አስነገረ ፤ አለቆች እና ሕዝቡ በደስታ ለቤተ መቅደሱ ግብር አመጡ ፡፡ ሌዋዊያን ግብሩን ለመሰብሰብ እምቢ በማለት ህዝቡን እግዚአብሄርን ከማምለክ ከልክለዉት ነበር ነገር ግን አሁን እንደ ገና ህዝቡ ማምለክ ቻለ ፡፡ በመሰረቱ ሌዋዊያን እግዚአብሄር በሕዝቡ መካከል እንዴት መስራት እንደሚችል የተወሰኑ ነበሩ ፤ እናም አሁን ኢዮአስ ለመሰብሰብ በሌዋዊያ ዙሪያ ሳጥን በመስራት አስቀምጦ ስለ ነበር ሕዝቡ በመደሰት ሳጥኑን ሞሉት ምክንያቱም ገንዘቡ ለእግዚአብሄር መንግስት ስራ እንደሚሆን ስላወቁ ፡፡ በየቀኑ ህዝቡ በጣም ብዙ ገንዘብ ስለሚሰጡ ሌዋዊያን ወደ ንጉሱ ፀኃፊ እና ወደ ዋነኛዉ ካህናት ሹም ያመጡታል (ይሰጡታል) ከዚያም ባዶዉን ሳጥን በቤተ መቅደሱ ፊት ቀድሞዉ ቦታ ላይ ይመልሱታል ፡፡ በኃይል ገንዘብ ሰበሰቡ ፡፡
ንጉሱና ታላቁ ካህንገንዘቡን የሚጠግኑትን፣ ጠራቢዎችን፣ እድሳት ሰራተኞችን፣ የብረትና የናስ ሰራተኞችን ለቀጠሩት በእግዚአብሄር ቤተ መቅደስ ስራ ላይ በኃላፊነት ለተሸሙት ሰጧቸው ፡፡ ሁሉም አካል ለማድረግ ድርሻዉን አገኘ - ሕዝቡ ሰጠ፣ ሰራተኞች ሰሩ - ስለዚህ መጨረሻ ላይ ሁሉም አካል የእግዚአብሄርን መገኘት ይቀምሳል (ያገኛል) ፡፡
2-ዜና መዋዕል (24፡ 13-14)፡ ሰራተኞቹ በራሱ ዝርዝር ቤተ መቅሱን በማደስ አጠናከሩት ፤ በጨረሱ ጊዜ የቀረዉን ገንዘብ ለንጉሱ እና ለቤተ መቅደሱ በዉስጡ ፅሁፍን ላዘጋጀዉ ታላቁ ካህን ዮዳሄ ሰጡአቸው ፡፡ ከዚያም ህዝቡ በዮዳሄ ዘመን ሁሉ ያለማቋረጥ የሚቃጠል መስዋዕት አቀረቡ ፡፡
ስለ መትረፍረፍ እና እግዚአብሄር እንዴት ፍላጎትን እንደ ሚያገኝ እናዉራ ፤ ኢዮአስ ጥሪ አደረገ ነገር ግን ሌዋዊያን ያን አላደረጉም ፤ ስለሆነም ህዝቡ ለ23 አመታት እግዚአብሄርን ከሚያለማምድ በረከት ዉጪ ሆኑ ፤ ነገር ግን ኢዮአስ በመከተል በመላዉ ይሁዳ አዋጅ ላክ ምክንያቱም ይህን እንዲያደርግ እግዚአብሄር ጠይቆት እንደ ነበር ስለ አወቀ ፡፡ በሂደቱ ሰዎቹ በመደሰት አስተዋፆአቸዉን ስላመጡ በግልፅ ሳጥኑ ሙሉ ነበር ፤ ስጦታዎቹ በጣም ትልቅ ስለ ነበሩ በእያንዳንዷ ቀን ሳጥኑ ይገለበጣል (ባዶ ይደረጋል) ፡፡ እግዚአብሄር ለሆነ ነገር ሲጠራችሁ ፍላጎታችሁን በማትረፍረፍ ይሞላል ፡፡ በእነዚህ ሁሉም ቀናት እስራኤላዊያን በደስታ በመደሰት ያለማቋረጥ ስለሰጡ ሁሉም በእግዚአብሄር መገኘት መደሰትን አገኙ ፡፡
2ቆሮ (9፡ 6-8) በጥቂት የሚዘራ በጥቂት ደግሞ ያጭዳል በበረከትም የሚዘራ በበረከት ደግሞ ያጭዳል ይላል ፤ እግዚአብሄር በደስታ የሚሰጠዉን ይወዳልና እያንዳንዱ ሰዉ ልቡ እንዳሰበዉ መስጠት አለበት ፡፡ ህዝቡ እዉነተኛ መነቃቃትን ቀመሱ ምክንያቱም ከሞላ ልባቸዉ ስለ ሰጡ ፡፡ ከመጀመሪያዎቹ 23 አመታት በኋላ ኢዮአስ አቁሞ ከነበር ምን ይፈጠራል ? ነገር ግን ኢዮአስ በመፅናቱ እግዚአብሄር በለጋስ ሰጪዎች ተገለጠ ፡፡
ምሳሌ (3፡ 9-10) እግዚአብሄርን ከኃብታችን እንድናከብር ከዚያም ጎተራችን እንደ ሚሞላ ይነግረናል ፤ ሉቃ (6፡ 38) እንድንሰጥ በምላሹ ደግሞ እንደሚሰጠን ይነግረናል ፡፡ እግዚአብሄርን ልንሰጠዉ አንችልም ፤ ብዙ ስትሰጡ እግዚአብሄር ብዙ ይሰጣችኋል ፡፡ ለማንኛዉም የኛ እንዳልሆነ ለማስታወስ በጣም አስፈላጊ ነው ፤ ሁሉም የእርሱ ነው ፡፡ ለቤተ ክርስቲያን እና ለአገልግሎቷ በለጋስነት መስጠት አስፈላጊ ነዉ እግዚአብሄርም የእግዚአብሄርን መንግስት ለማሳደግ ሊጠቀምበት ይችላል ፡፡ ይህን እንድታደርጉ ሲጠይቃችሁ በፍፁም አምላክን እንዳታሳንሱት ፤ ሌዋዊያን ለ23 አመታት እንዳደረጉት የእግዚአብሄርን ጉዞ ወደ ኋላ የምትይዙት ልንሆን እንችላለን ፡፡
መደምደሚያ
Bible.org ስለ እግዚአብሄር የተትረፈረፈ ስጦታ ፈጣን መልክን አብጅቷል፡
- ሁል ጊዜ እግዚአብሄር ለፍላጎቶቻችን በማትረፍረፍ ይሰጠናል - በቁሳዊ፣ በስሜት እና በመንፈሳዊ ነገር ፤ እግዚአብሄር ፍላጎቶቻችንን ያሟላል ፡፡
- እግዚአብሄር ለፍላጎቶቻችን በጊዜዉ ይሰጠናል ፡፡
- እግዚአብሄር በፍፁም በማንጠብቀዉ መንገድ ይሰጠናል ፡፡
- እግዚአብሄር በሽልማት(በጥቅም) ሳይሆን በፀጋ ይሰጠናል ፡፡
በምናደርገዉ ሳይሆን በፀጋዉ ምክንያት የእርሱ ከመጥን በላይ ብልፅግና ይመጣል ፡፡ ሽልማት እስኪሚመጣ ድረስ እግዚአብሄር ይሰጣችኋል ምክንያቱም የሆነ ነገር ስለምታደርጉ ሳይሆን በእዚያ የሆነ ነገር እንደ ምታደርጉ ስለ ሚያዉቅ ፤ ይህ እግዚአብሄር የሚሰራበት ነው ፡፡ ስስታም ሌዋዊ እንዳትሆኑ ወደ እግዚአብሄር መንግስት ያለማቋረጥ ሲያመጡ የነበሩትን ለጋስ እስራኤላዊያንን እንጂ በዚያ ምክንያት ብዙ ሕዝብ መገኘቱን መቅመስ ይችላል ፡፡
Steven J. Cole, “Lesson 75: God’s Abundant Provision”; available from https://bible.org/seriespage/lesson-75-god-s-abundant-provision-genesis-4516-28.
ጥያቄዎች
-
ካህኑ ዮዳሄ በጎትልያ ላይ አፀፋ ለመዉሰድ እና በዳዊት ዘር መንግስቱን እንደ ገና ለማቋቋም ለምን አምስት አመት እንደ ጠበቀ ምን ታስባላችሁ ?
-
ንጉስ ኢዮአስ በእግዚአብሄር ፊት ሚያደርገዉን መልካም ነገር የማቆሙ ምክንያት ምን ይመስላል (2ዜና መዋዕል 24፡ 2, 17) ? ከመስመር ዉጪ ምን አገኘው ?
-
2ዜና መዋዕል (24፡ 19) እግዚአብሄር ለንጉስ ኢዮአስ ነቢያትን በመላክ ሰራተኞቹ ወደ እግዚአብሄር መልሶ እንዲያመጡዓቸው አለ ነገር ግን አያዳምጡዓቸውም ፤ ወንጌልን ከእነርሱ ጋር በተጋራችሁ ጊዜ ሰዎች እንዴት ይመልሱላችኋል ?
-
በ 2ዜና መዋዕል (24፡ 22) የዘካሪያስ የሞት ፀሎት በሉቃ (23፡ 34) ከኢየሱስ ሞት ፀሎት እንዴት ይለያል ?
-
በሉቃ (11፡ 51) ኢየሱስ የዘካሪያስን እና ሌሎችን ሞት ጠቀሰ ፤ በእነዚህ ግድያዎች ማንን ከሰሰ ? ለምን ?
-
በ 2ዜና መዋዕል (23-24) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Chronicles 24:5
“So he gathered the priests and Levites and said, ‘Go out to the cities of Judah and collect money from all Israel to repair the temple of your God as needed year by year, and do it quickly.’ However the Levites did not hurry.”
ኢዮአስ ንጉሥ ሲሆን እግዚአብሔር ቤተ መቅደሱን የማደስ ሸክም በልቡ አስቀመጠ ፡፡ ንጉሥ ኢዮአስ ሌዋውያኑን ሰብስቦ በፍጥነት ገንዘብ እንድሰበስቡ አዘዛቸው ይህንንም በቶሎ እንድያደርጉት ነገራቸው ፡፡ ሆኖም ግን ሌዋውያኑ ቸል አሉ ፡፡ ስለዚህም ኢዮአስ የተለየ ዘዴን ተጠቀመ ፡፡ ሳጥን ሰርቶ በእግዚአብሔር ቤት በር አጠገብ በስተ ውጭ አኖረው ። በምላሹም የይሁዳና የኢሩሳሌም ሰዎች በልገስና እና በመታዘዝ ሰጡ ፡፡ የቤተ መቅደሱን ሙሉ ታድሶ ለማስቻል በየቀኑ ገንዘብ ይሰበሰብ ነበር ፡፡
“ ካህናትንና ሌዋውያንንም ሰብስቦ፦ ወደ ይሁዳ ከተሞች ውጡ፥ የአምላካችሁንም ቤት በየዓመቱ ለማደስ ከእስራኤል ሁሉ ገንዘብን ሰብስቡ፤ ነገሩንም ፈጥናችሁ አድርጉ አላቸው። ሌዋውያን ግን ቸል አሉ ። “
- 2ኛ ዜና 24፡5
ተጨማሪ ጥቅስ
ምሳሌ16:3 — “ ሥራህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፥ አሳብህም ትጸናለች ። “
መዝሙር 105:4 — “ እግዚአብሔርን ፈልጉት ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ ። “
መዝሙር 84:11 — “ እግዚአብሔር አምላክ ምሕረትንና እውነትን ስለ ወደደ፥ ሞገስንና ክብርን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር በቅንነት የሚሄዱትን ከመልካም ነገር አያሳጣቸውም ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።