Historical Books 2 Chronicles

God is the Keeper of Promises

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Royal Throne 2 Chronicles 21-22 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 312 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዛሬ በምዕራፎቹ ነገሮች በመቀየር ከቀደሙት ጥቂት ምዕራፎች በተለዬ አቅጣጫ መሄዳቸዉን እናጠናለን ፤ ለዉጡ በ 2ዜና መዋዕል 21 ላይ ይጀምራል ፡፡

ትምህርት

2-ዜና መዋዕል (21፡ 1-4)፡ ኢዮሳፍጥ ዘመኑን በእግዚአብሄር መንገድ በመጓዝ ለይሁዳ አስደናቂ ነገሮችን አደረገ ፤ በሞተም ጊዜ ልጁ ኢዮራም ንጉስ ሆነ (ቁጥር 1) ፡፡ ኢዮሳፍጥ አንደ እግዚአብሄር ኃሳብ የሆነ ንጉስ ነበርነገር ግን ይሁዳን እና እስራኤልን በጋብቻ በኩል በአንድ ላይ ለማምጣት የሞከረው ችግር አመጣ ፡፡ በሚያስደንቅ ሁኔታ የእስራኤል ንጉስ የነበረው ኢዮራም የተለየ ሰዉ ነበር ፡፡ የኢዮራም ወንድሞች በቁጥር 2 የተዘረዘሩ ናቸው ፡፡ ኢዮሳፍጥ ከአክዓብ ሴት ልጆች አንዷን ኢዮራምን ለማጋባት አመጣ ፡፡ ኢዮሳፍጥ በሁሉም ልጆቹ ደግ ነበር ነገር ግን እንደ በኩር ልጅ ኢዮራም መንግስቱን ተቀበለ (ቁጥር 3) ፡፡ ኢዮራም ሁሉንም ወንድሞቹን እና የእስራኤልንም ልዑላንን(መሳፍንትን) በመግደል ስፍራዉን (ስልጣኑን) አጠነከረ (ቁጥር 4) ፡፡

ሁል ጊዜ መነቃቃት ሲኖር ሰይጣን የሚሆነዉን ለማጥፋት ለመሞከር ይመጣል ፡፡ ኢዮሳፍጥልጁን ኢዮራምን በእግዚአብሄር መንገድ እንዲጓዝ አሰልጥኖት ነበር ነገር ግን ኢዮራም ወንድሞቹን እና ሌሎች መዉረስ የሚችሉትን በገደለ ጊዜ ክፉ ወደ መንግስቱ ገባ ፡፡

2-ዜና መዋዕል (21፡ 5-7)፡ ኢዮራም የአክዓብን እና የእስራኤል ኤልዛቤልን ሴት ልጅ ጎቶልያን አገባ ፤ ነገር ግን የአክዓብ መጥፎ ተፅዕኖ ይሁዳ ዉስጥ ገባ ፡፡ በእርግጥ ፀኃፊዉ ስለ ኢዮራም ምንም መልካም ነገር አላለም ነበር ፡፡ ፀኃፊው በይሁዳ መንፈሳዊ ጤነኝነት ላይ እና ኢዮራም እንዴት እስራኤል የተከተለዉን ተመሳሳይ ተግባራት እና ፖሊሲዎች መከተል ላይ ያተኩራል (ቁጥር 5-6) ፡፡ ምንም እንኳን ኢዮራም የእስራኤል ነዉረኛ ነገስታቶች እያደረጉ የነበረዉን ቢያደርግም የእስራኤል ነገስታት ያልነበራቸዉ ለእርሱ ይቀጥል የነበረ አንድ ነገር ነበር - የዳዊት ቤት ዘር ነበር ፡፡ የኢዮራም ለእግዚአብሄር አለመታዘዝ ቢኖርም እግዚአብሄር ሙሉ ቤተሰቡን አያጠፋዉም (ቁጥር 7) ፤ እግዚአብሄር ዳዊትን በጣም ቀርቦ መጥቶ ቢሆንም እንኳን የኢዮራምን ቤተሰብ ከጥፋት የጠበቀው የሰለሞን ዘር ሁል ጊዜ በዙፋኑ ላይ እንደ ሚሆን ተስፋ ገብቶለት ስለ ነበር ነው (1ዜና መዋዕል 17፡ 14) ፡፡

2-ዜና መዋዕል (21፡ 8-11)፡ በኢዮራም ዘመን ጊዜ የኤዶም ሕዝቦች በይሁዳ ላይ በማመፅ የራሳቸዉን ንጉስ መርጠዋል (ቁጥር 8) ፡፡ ኢዮራም ወደ ኤዶምያስ ተሻገረ የኤዶምያስ ንጉስ እና አለቆቹ ለትንሽ አመለጡ (2ነገ 8፡ 21)፡፡ በልብናንም የሚኖሩት ሌዊያዊያንም አመፁ ምክንያቱም ኢዮራም እግዚአብሄርን ትቶ ስለ ነበር ፡፡ በቁጥር 10 ለልብና አመፅ ምክንያቱ በብዙ የኢዮራም ጣዖት አምላኪነት የሚመስል ነው (ኢያ 21፡ 13) ፤ በሚስቱ ተፅዕኖ ስር በነበረው በዚህ በኢዮራም ምን አሳማኝነት በሌለበት ! የጣዖት ማምለኪያ ስፍራዎችን በመስራት ህዝቡ እግዚአብሄርን እንዲክደዉ እና እንዲያመነዝርበት በመምራት ዋና ተግባሩን ወሰደ ፡፡

2-ዜና መዋዕል (21፡ 12-15)፡ ኤልያስ በሰሜን መንግስት አክዓብ እና ኤልዛቤል ተቃራኒ(ጠጋጣሚ) የነበረ ነቢይ ነበር ፤ በህግ ልጃቸዉ ለነበረው ለኢዮራም አንድ ደብዳቤ በመላክ ሰዎስት ክሶችን እና ሁለት ቅጣቶችን አቀረበለት (ቁጥር 12) ፡፡ ክሶቹ የሚያካትቷቸው፡ 1) ኢዮራም በእስራኤል ነገስታት መንገድ እንጂ በአባቱ በኢዮሳፍጥ መንገድ አልተጓዘም ነበር፣ 2) ኢዮራም ይሁዳን እና የኢየሩሳሌም መኖሪያዎችን (ስፍራዎችን) የአክዓብ ቤት እንዳደረገው ራሳቸዉ እንዲያመነዝሩ ምክንያት ነበር እና 3) ኢዮራም ወንድሞቹን በጭካኔ ገድሏል ፤ ስለዚህ ኢዮራም ይቀጣል ፡፡ መጀመሪያ ሙሉ ቤተሰቡ እና ሁሉም ንብረቱ በሚያስፈራ መቅሰፍት የሚመታ ይሆናል ፤ ሁለተኛ ኢዮራም ራሱ በብዙ በሽታዎች የተመታ ይሆናል አንጀቱ እስኪወጣ ድረስ ቀን በቀን በወጣዉ የአንጀት በሽታን ያካትታል (ቀጥር 14-15) ፡፡ ብዙ ጊዜ ትንቢቶች በቃል ይሰጡ ነበር ገር ግን ኤልያስ ይህን በፅሁፍ ማስቀመጥን ፈለገ - በማድመቅ አደረገው !

2-ዜና መዋዕል (21፡ 16-20)፡ እግዚአብሄር ኢዮራምን ለማጥቃት ይህን ኃሳብ በፍልስጤማዊያን እና በአረቦች አይምሮ ዉስጥ አስቀመጠ (ቁጥር 16) ፤ ከይሁዳ ጋር ለመዋጋት ሄዱ ኢዮራም የነበረዉን ሁሉ ልጆቹን እና ሚስቶቹንም ጨምሮ አንድ ልጅ አካዝያስን ብቻ በመተዉ ወሰዱ (ቁጥር 17) ፤ በተጨማሪም ከሚስቶቹ አንዷን በዚህ ጊዜ ተጠቅሳ ያልነበረችዉን ረሷት (ትተዋት) ሄዱ ፡፡ ከዚያም እግዚአብሄር ኢዮራምን በአንጀቱ በሽታ ቀሰፈው (መታው) ፡፡ ኢዮራም አንጀቱ በትክክል እስኪወጣ ድረስ ለሁለት አመት ታመመ ከስምንት አመት ንግስና በኋላ በ40 አመቱ ሞተ ፡፡ ህዝቦቹም የንጉሳቸዉን ሞት ለማክበር ምንም ነገር አላደረጉም(ቁጥር 19-20) ፤ ኢዮራም ከእርሱ በፊት እንደ ነበሩት በተመሳሳይ ስፍራ ለመቀበር የተፈቀደለት አልነበረም ፡፡ በሚያናድድ ሁኔታ ይሁዳን ተፅዕኖ ያደረገበት ክፉ ከእርሱ ጋር አልሞተም ፡፡

2-ዜና መዋዕል (22፡ 1-12)፡ የኢየሩሳሌም ሰዎች የተረፈዉን የኢዮራምን ልጅ አካዝያስን ንጉስ አደረጉት (ቁጥር 1) ፤ ንጉስ በተደረገ ጊዜ 22 አመቱ ነበር የጎቶልያም ልጅ ነበር (ቁጥር 2) ፡፡ አካዝያስ ከአያቶቹ ከክፉዉ ንጉስ አክዓብ እና ንግስት ኤልዛቤል የመጣዉን ኃሳብ እናቱን ተከተለ ፤ ወደ ጣዖት አምልኮ መንገድ አካዝያስን መራችዉ (ቁጥር 3-4)፡፡ አካዝያስ የአካዓብ ልጅ ከነበረው ከኢዮራም ጋር ከሶሪያ ንጉስ ጋር በሬማት ዘገለዓድ ለመዋጋት ተጣመረ (ተቀላቀለ) (ቁጥር 5) ፡፡ ንጉስ ኢዮራም በዉጊያዉ በመቁሰሉ ለማገገም ወደ ኢዝራኤል ተመለሰ (ቁጥር 6) ፤ አካዚያስ ኢዮራምን ሊያየው ወደ ኢይዝራኤል ሄደ (ቁጥር 6) ፤ በደረሰ ጊዜ የአካዓብን ቤት እንዲያጠፋ እግዚአብሄር ልኮት የነበረዉን ኢዩን ለማግኘት ከኢዮራም ጋር ሄደ (ቁጥር 7) ፡፡ ኢዩ አክዓብን የሚያገለግሉትን የአካዝያስን ቤተሰብ አባላት በመግደል በአክዓብ ቤት ላይ ፍርዱን ፈፀመ ፤ አካዝያስም ይፈለግ ነበር ስለሆነም ከአካዝያስ ቤት ማንም መንግስቱን ለማስተዳደር ጥንካሬ አልነበረውም (ቁጥር 8-9) ፡፡

አካዚያስ ሲሞት እናቱ (ስሟ የእግዚአብሄር ቁጣ የሚል የሆነው) ጎቶልያ ዙፋኑን ለራሷ በመዉሰድ ለዘመኗ (ለአስተዳደሯ) በመነሳት ሊያስፈራሩ የሚችሉትን ሁሉንም በጭካኔ አጠፋቻቸው (ቁጥር 10) ፡፡ ጎቶልያ በዳዊት ቤት በመሆን የተለዩ ሊሆኑ የሚችሉትን ሁሉ የልጅ ልጇን በመጨመር አፀዳች ፤ የዳዊትን ዘር የማጥፋት ሙከራዋየጎቶልያ እህት ዮሳቤት ከንጉሱ ልጆች አንዱን ህፃን ልጅ ኢዮአስን ለማዳን በአልጋ ክፍል ስትደብቀዉ ተበላሸባት (ከሸፈባት) (ቁጥር 11) ፡፡ እግዚአብሄር የዳዊትን ዘር መሲሁ እስኪመጣ ድረስ እንደ ሚቀጥል ተስፋን ስለ ሰጠው (2ሳሙ 7፡ 16) ከጥፋት አንድ ህፃን ልጅ ብቻ መጣ (ተረፈ) ፡፡ ጎቶልያ ትክክለኛ (ተገቢ) አስተዳዳሪ አልነበረችም ከዳዊት ቤት ስላልነበረች እና የባዕል አምላኪ ስለ ነበረች ፡፡ እስከ ስድስት አመት ለማስተዳደር ተቆጣጠረች (ቁጥር 12) ፤ በዚህ ስድስት አመት ጊዜ ዉስጥ እግዚአብሄር የሌለ ክፉ ደግሞ አሸንፎ እንደ ነበር ይሰማል ፡፡

መደምደሚያ

ኢዮስያስ ልጅ እስኪኖረዉ ድረስ የእግዚአብሄር ተስፋ ሁሉ - በኤደን ገነት ለሔዋን የተሰጠው፣ ከአብርሃም ጋር የተደረገው ኪዳን እና ከይስሐቅ እና ከያዕቆብ ጋር የታደሰው፣ ለዳዊት የተደረገዉ መኃላ - በልጅነት አካሉ ላይ አረፈ9ተቀመጠ) ፡፡ ኢዮስያስ ተገድሎ ቢሆን እግዚአብሄር በቀላሉ የሚሳሳት እንደ ሆነ የተረጋገጠ ይሆናል ፡፡

“ እግዚአብሄር ብስጩ (በችኮላ) የሚያደርግ አልነበረም ፤ ተስፋ አድራጊ ብቻ አልነበረም ቃል ኪዳንንም ፈፃሚ እንጂ” ፤ የተደበቀዉ ንጉስ ኢዮስያስን መገኘትንም ተመልከቱ ፤ ጎቶልያ በዙፋኑ ላይ ነበረች ነገር ግን ትክክለኛዉ ንጉስ ነበር ፡፡ ይህ ቀናችንን አያስታዉሳችሁም ? ሰዎች በዙፋን ላይ ናቸዉ ነገር ግን ትክክለኛው ንጉስ ኢየሱስ አለ !

  1. Don Finto, Your People Shall Be My People: How Israel, the Jews and the Christian Church Will Come Together in the Last Days (Bloomington, MN: Chosen Book, 2001, 2016), pp. 67–68.

ጥያቄዎች

  1. ኢዮሳፍጥ ለልጆቹ ምን አይነት በረከቶችን ሰጣቸው ? ኢዮራም ቀጣዩ ንጉስ እንዲሆን ለምን መረጠው ?
  2. በኢዮራም ቤት ላይ እግዚብሄር የቀረበ እና የማይለወጥ ቅጣት ለምን ያዘ ? (2ዜና መዋዕል 6፡ 16)
  3. ኢዮራም እግዚአብሄርን በመተዉ ምክንያት እየተፈጠሩ የነበሩት ጥቂት ነገሮች ምንድን ናቸው ? በክፉ አገዛዙ መሰረት ኤልያስ ለእርሱ ምን መልዕክት ሰጠው ?
  4. እግዚአብሄር በአካዝያስ መዉደቅ ምን ወሰነ ? ከአካዝያስ በኋላ ሌላ ንጉስ ለምን አልተከተለም ?
  5. ከልጇ አካዝያስ መሞት በኋላ ንግስት ጎቶልያ ምን ክፉ ነገር አደረገች ? እግዚአብሄር የዳዊትን መስመር ለማዳን እና ተስፋዉን ለመጠበቅ እንዴት ጣልቃ ገባ ?
  6. በ 2ዜና መዋዕል (21-22) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Chronicles 21:19b–20

“But his people did not hold a fire in his honor like the fire in honor of his fathers. Jehoram was 32 years old when he became king; he reigned eight years in Jerusalem. He died to no one’s regret and was buried in the city of David but not in the tombs of the kings."

ከንጉሥ ኢዮሳፍጥ ዘመን በኋላ የይሁዳ መሪዎች ዘዴ ተለወጠ ፡፡ የኢዮሳፍጥ ልጅ ኢዮራም ስድስት ወንድሞቹን በመግደል ዙፋኑን ካጸና በኋላ ነገሠ ፡፡ ልክ ነቢዩ ኤልያስ እንደተነበየው ፣ ንጉሥ ኢዮራም እንደ አባቱ በእግዚአብሔር መንገድ ስላልሄደ በአንጀት ህመም ተያዘ ፤ ያለ ክብርም ማንም ሳያዝንለት ሞተ ፡፡

እንደ ክርስቶስ ተከታይ ኢየሱስ እንድትሄድና ደቀ መዝሙር እንድታደርግ ያዝሃል ፡፡ በሰዎች ህይወት ውስጥ እንድታፈስ ፤ የክርስቶስን ፍቅር እንድታሳይ ይመክርሃል ፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር ወደ ቤቱ ሲጠራህ ፣ በሰዎች ላይ ያፈሰስከው የክርስቶስ ፍቅር ከራስህ ህይወት ጋር ይታሰብልሃል ፡፡ ስለዚህ አስብ እስኪ ፡- አንተ ነገ ብተሞት ፣ የሚያዝን አለ ? በአንተ ውስጥ ያለውን የኢየሱስን ፍቅር ያጡት ይሆን? የእግዚአብሔር ጸጋ አያልቅም ፡፡ ልክ እንደ እንተ ኢየሱስ ፍቅሩን ለአንተ አፍስሷል ፡፡ ፍቅሩን ለመቀበል እንደሚገባህ እመን ፡፡ ልክ አንተ የክርስቶስን ፍቅር ወደ ሀይወትህ በእምነት እንደተቀበልክ ሁሉ ሂድ የኢየሱስን ፍቅር በሆነ ሰው ውስጥ አሰቀምጥ ፡፡ የኢየሱስ ፍቅር የሆነን ሰው ለዘላለም መለወጥ ይችላል ፡፡

“ሕዝቡም ለአባቶቹ ያደርገው እንደ ነበር ለእርሱ የመቃብር ወግ አላደረገም ። መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሠላሳ ሁለት ዓመት ጕልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ስምንት ዓመት ነገሠ፤ ማንም ሳያዝንለት ሄደ፤ በዳዊትም ከተማ እንጂ በነገሥታት መቃብር አልቀበሩትም ። “

-2ኛ ዜና 21፡19-20

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ማቴዎስ28:19–20 — “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ ። “
  • 1 ጢሞቴዎስ 1:16 — “ለዚህ ግን፥ የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት በእርሱ ያምኑ ዘንድ ላላቸው ሰዎች ምሳሌ እንድሆን፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ዋና በምሆን በእኔ ላይ ትዕግስቱን ሁሉ ያሳይ ዘንድ፥ ምህረትን አገኘሁ ። “
  • 1 ዮሐንስ 4:19 — “እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን ። “