Jehoshaphat's Prayer
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Royal Throne 2 Chronicles 19-20 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
እግዚአብሄር ነቢያቱን በይሁዳ እና በእስራኤል ነገስታቶች ኑሮ ዉስጥ እንዲናገሩ ተጠቀመባቸዉ ምላሽም ሰጡ ፡፡ በችግር ጊዜ መሀከል ላይ እንኳን በጊዜዉ እግዚአብሄር ለእናንተ ማለት የሚፈልገዉን ለመስማት ክፍት ከሆናችሁ በዚያ ዉስጥ ያገኛችኋል ፤ ይሁን እንጂ ለመስማት በራችንን የምንዘጋባቸዉ ጊዜዎች አሉ ምክንያቱም “ እግዚአብሄር ሆይ በቀደሙት ነገሮቼ ዉስጥ አግኝተኸኛል ነገር ግን አሁን አታስፈልገኝም “ ስለ ምንል ፡፡ የ 2ዜና መዋዕል (7፡ 14) ተስፋ ራሳችንን ዝቅ ባደረግን እና በፀለይን፣ ፊቱን በፈለግን እና ከክፉ መንገዳችን በተመለሰን ጊዜ እግዚአብሄር እንደ ሚሰማን ነው ፡፡
ትምህርት
2-ዜና መዋዕል 19፡ ኢዩ ንጉስ ኢዮሳፍጥን ገሰፀው (ቁጥር 1-3) ፤ ከምዕራፍ 19 ቀሪዎቹ የይሁዳን ህዝብ መልሶ ወደ እግዚአብሄር ለመምራት ኢዮሳፍጥ ወደ ስፍራዉ የመቀመጡን ተሐድሶ ይገልፃል ፤ በዚህ ሂደት በምዕራፍ 20 አስቸጋሪ ጊዜዎች እየመጡ ነበር ፡፡
2-ዜና መዋዕል (20፡ 1-4)፡ ሞዓባዊያን፣ አሞናዊያን እና ምዑናዉያን (ከኤዶማዊያን) በኢዮሳፍጥ ላይ ለመዋጋት መጡ ፡፡ በጣም ብዙ የጠላቶች ቁጥር ቀድሞዉን በይሁዳ ምድር ነበሩ ፡፡ የኢዮሳፍጥ የመጀመሪያው ስሜት ፍራት ነበር ፤ ነገር ግን በመመለስ በፍጥነት እግዚአብሄርን በመመልከት በይሁዳ ሁሉ ፆም አወጀ ፡፡ ፆሙ ትኩረታቸዉን ከጠላቶቻቸዉ ጥንካሬ ይልቅ ወደ እግዚአብሄር ጥንካሬ ያዞራቸዋል ፤ በእግዚአብሄር ጥንካሬአቸዉን ለማግኘት በ 1ዜና መዋዕል (16፡ 11) ያለዉን ትዕዛዝ ተከተሉ ፡፡ መዝ (14፡ 2) እግዚአብሄር የሚፈልጉትን ለማየት ከሰማይ ወደ ታች ይመለከታል ይላል ፡፡ በዚህ ሁኔታ ራሱን እስኪገልጥላቸዉ ድረስ እግዚአብሄርን ለመፈለግ ወሰኑ (ሆሴ 10፡ 12)፡፡ ኢዮሳፍጥ ከፍርሃት ወደ እምነት ገብቷል ፤ ህዝቡም ኢዮሳፍጥ እንደ መሰለላቸዉ ይከተላሉ፡ ከሁሉም ይሁዳ ከተሞች ለመፆም፣ ለመፀለይ እና እግዚአብሄርን ለመፈለግ መጡ ፡፡
2-ዜና መዋዕል (20፡ 5-9)፡ ኢዮሳፍጥ ፀሎቱን እግዚአብሄር ብቻዉን በአለም መንግስታት ላይ ሁሉ ሊያሸንዉ የሚችል እንደ ሌለ ራሱን፣ ህዝቡን እና እግዚአብሄርን በማሳሰብ ጀመረ ፤ በዚያ ፀሎት ኢዮሳፍጥ ከፍርሀት ወደ እምነት ተቀየረ ፡፡ ኢያሱ ወደ ምድሪቱ በመጣ ጊዜ እግዚአብሄር ህዝቦቹን እንዳጠፋቸው አስታወሰ (ቁጥር 7) ፤ በእርሱ ፊት እንዳሉት ህዝቦች ኢዮሳፍጥ በቤተ መቅደሱ ፊት በመቆም ወደ ሚሰማቸዉ እና ወደ ሚያድናቸዉ አምላክ ጮኸ (ቁጥር 9) ፡፡ ይህ በ 2ዜና መዋዕል (7፡ 13-14) ለሰለሞን ከነበረዉ መልዕክት ጋር ተመሳሳይ ነበር ፡፡
2-ዜና መዋዕል (20፡ 10-12)፡ ኢዮሳፍጥ እግዚአብሄርን እስራኤል ከግብፅ በወጣ ጊዜ የአሞናዊያንን፣ የሞዓባዊያንን እና የሴይርም ተራሮች ምድሮችን እንዲወሩ ፈቅዶላቸዉ እንዳልነበር አሳሰበው ፡፡ ይህ ኢዮሳፍጥ “ ከእኛ ጋር እየተዋጉ አሁንም አትፈርድባቸዉም ? “ እያለ እንደ ነበር ነው ፡፡ ኢዮሳፍጥ ለማስተካከል የእርሱ ችግር የነበረዉን ወደ እግዚአብሄር ጮኸ ፤ ከዚያም ኢዮሳፍጥ ምን እንደ ሚያደርጉ እንደ ማያዉቅ ስለወሰነ ለእርዳታ ወደ እግዚአብሄር ተመለከተ ፡፡ ይህ የእምነት የሚያስደንቅ ትርጓሜ ነው ፡፡
2-ዜና መዋዕል (20፡ 13-17)፡ ከይሁዳ ሁሉም (ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች) እግዚአብሄር ፊት ቆሙ ፤ ከዚያም የእግዚአብሄር መንፈስ “ ስሙ ፤ እግዚአብሄር እንዲህ ይላችኋል፡ አትፍሩም አትደንገጡም “ ባላቸው በአንድ ሌዋዊ በየሕዚኤል ላይ መጣ ፤ የሕዚኤል ከፍርሃት ወደ እምነት እንዲሄዱ ጠራቸው ፡፡ እስራኤልስለዚህ ዉጊያ መፍራት አያስፈልጋቸዉም ዉጊያዉ የእግዚአብሄር ስለ ነበር ፡፡ ስፍራቸዉንም በመያዝ መቆም እንደሚችሉና ስለ እነርሱ እግዚአብሄር ሲዋጋ እንዲመለከቱ ነገራቸው ፡፡ በእዉነቱ እስራኤል በእምነት እግዚአብሄር ላይ ወደ ሚሰራበት ስፍራ እንደሚጓዙ አስታዉሉ ፤ መዝሙር 46፡ “ ዕረፉ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ “ ይላል ፡፡ ኢዮሳፍጥ እና እስራኤል በእምነት የእግዚአብሄር ማዳንን ማየት ቻሉ ፡፡
2-ዜና መዋዕል (20፡ 18-19)፡ ኢዮሳፍጥ በፍራት ሳይሆን በእምነት ምላሽ መስጠቱን ቀጠለ ፤ ሌዋዊያን፣ ቀዓትዋዊያን እና ቆሪያዊያን በታላቅ ድምፅ እግዚአብሄርን ሲያመሰግኑ እሱና መላዉ ይሁዳ እግዚአብሄርን ሰገዱለት፡፡
2-ዜና መዋዕል (20፡ 20-23)፡ በጥዋት በማለዳ ኢዮሳፍጥህዝቡን ከምድረበዳ በማዉጣት በእግዚአብሄር በማመን ድል ማድረግን እንዲያዩ በመታገል መራቸው ፡፡ ራሱን እግዚአብሄራዊ ምክር በሚመክሩ አስከበበ አንዳንዶችንም ለእግዚአብሄር ምስጋና እንዲዘምሩ ሾማቸው ፡፡ በምስጋና መጮኽ በጀመሩ ጊዜ እግዚአብሄርጠላቶቻቸዉን በመዉጋት አጠፋቸው ፡፡ የእግዚአብሄር የጨዋታ እቅድ ከመጀመሪያው “ እመኑኝ ! “ ነበር በፍርሀት በምንጓዝ ጊዜ ምንም ነገር አይቀየረም ፡፡ በዚህ ጊዜ እግዚአብሄር የኢዮሳፍጥ ጠላቶች እስኪጠፉ ድረስ እርስ በእርሳቸው እንዲዋጉ ምክንያት ሆናቸው ፡፡
2-ዜና መዋዕል (20፡ 24-26)፡ ይሁዳ የጠላቶቹን ሰራዊት በተመለከተ ጊዜ ከሬሳዎች በስተቀር ምንም አላዩም ፡፡ ኢዮሳፍጥ እና ህዝቦቹ ከጠላቶቻቸዉ ምንም መቅረት እስከማይችል ድረስ ለሰዎስት ቀን በመሰብሰብ በዘበዙ ፤ በአራተኛዉ ቀን ላይ በበረከት ሸለቆ ላይ በመሰብሰብ እግዚአብሄርን አመሰገኑ ፡፡
2-ዜና መዋዕል (20፡ 27-28)፡ ኢዮሳፍጥ እና የይሁዳ ሰዎች ወደ ኢየሩሳሌም በመመለስ በቤተ መቅደሱ እግዚአብሄርን አመሰገኑ (ሰገዱ) ፡፡
ሁሉም በመፅኀፍ ዉስጥ እግዚአብሄር ሰዎችን ሞኝ ነገር እንዲያደርግ ጠየቀ ፡፡ ኢያሱ እስራኤላዊያንን በኢያሪ መያዝ ላይ በከተሞቿ እንዲዞሪ መራ (ኢያ 6፡ 1-5) ፤ ንዕማን ከለምፁ የተፈወሰ ለመሆን በዮርዳኖስ ወንዝ ሰባት ጊዜ ታጠበ (2ነገ 5፡ 1-19) ፡፡ በእምነት በምንጓዝ ጊዜ እግዚአብሄር ይገለጣል ፡፡ ኢየሱስ ጴጥሮስን ግብሩን ለመክፈል ከአሳዉ አፍ ዉስጥ ሳንቲም እንደ ሚያገኝ ነገረው (ማቴ 17፡ 27) ፤ ደቀ መዛሙርቱ በአንድ ትንሽ ልጅ ምሳ 5,000 ሰዎችን መገቡ (ዮሐ 6፡ 1-15) ፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር መጓዝ በጣም የተሟላ ነገር ሲሆን በህይወታችሁ የሚያስቅ ጀብድ ታገኛላችሁ ፡፡ ስትጓዙ እንደ ሚገለጥላችሁ ታምኑታላችሁ ? እግዚአብሄርን በመፈለግ ከፍራት ወደ እምነት ስንጓዝ ነገሮች ትርጉም አይኖራቸውም ፡፡
መደምደሚያ
“ ልዩ መፅኀፍ ቅዱሳዊ ትዕዛዞች “ ተብሎ የሚጠራዉ አንድ ፅሁፍ በእምነት ስንጓዝ እግዚአብሄር ትርጉም አይሰጥም ዝም ብሎ ትዕዛዙን መጠበቅ ብቻ ያስፈልጋል ይላል ፡፡ የእግዚአብሄር እቅድ ለእኛ ትርጉም በማይሰጥ ጊዜ የእግዚአብሄር እቅድ እንደ ሆነ እናስታዉላለን ፤ በተጨማሪም እንደንሰራ የእግዚአብሄርን ጥያቄ አንረዳዉም፡፡ እግዚአብሄር እግዚአብሄር እንደ ሆነና እኛ ሰዎች እንደሆንን እናሳታዉላለን፡፡ ከፍርሃት ወደ እምነት በምንጓዝ ጊዜ ምን እንደ ምናደርግ ባላወቅን ጊዜ ነገር ግን ወደ እግዚአብሄር ስንመለከት እግዚአብሄር ይገለጣል ፤ ስለዚህ እባካችሁ በእምነት በመጓዝ እግዚአብሄር በማይቻለዉ ላይ እንዲገለጥ እንፍቀድለት ፡፡
Hook Publications, “Strange Bible Instructions”; available from http://www.hookpublications.com/truth/strange-bible-instructions.
ጥያቄዎች
-
በ 2ዜና መዋዕል (19፡ 1) በኢዮሳፍጥ በደህና ቤት መድረስ ላይ የእግዚአብሄርን ሞገስ እና ምህረት እንዴት ታዩታላችሁ (2ዜና መዋዕል 18፡ 1፣ 28-31) ? የአክዓብን ፍርድ ከኢዮሳፍጥ ጋር አነፃፅሩ
-
በንጉስ ኢዮሳፍጥ እና በንጉስ አሳ መካከል አንድ ተመሳሳይነት ምን ነበር ? (2 ዜና መዋዕል 16፡ 7)
-
ሰራዊቱ በእርሱ ስለ ጦርነት ዜና ሲታወጅ በሰማ ጊዜ ኢዮሳፍጥ ምን ሁለት ነገሮችን አደረገ ? በ 2ዜና መዋዕል እግዚአብሄርን የተመለከተዉ ሌላ ማነው ? (2ዜና መዋዕል 11፡ 16፣ 14፡ 2-4፣ 15፡ 10-13፣ 31፡ 21፣ 34፡ 3)
-
በህዝቡ ላይ ለመናገርየእግዚአብሄር መንፈስ በማን ላይ መጣ ? መልዕክቱ ምን ነበር ? መልዕክቱን እንዴት ነበር የተቀበለው ?
-
ንጉስ ኢዮሳፍጥን ወደ ጦርነት ሰራዊቱን እንዲመራ ማን ሾመዉ (መረጠው) ? ወደ እግዚአብሄር ማዳመጥ እና በእምነት መተግበር ዉጤቱ ምን ነበር ? (ዕብ 11፡ 6)
-
በ 2ዜና መዋዕል (19-20) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Chronicles 20:12
“Our God, will You not judge them? For we are powerless before this vast number that comes to fight against us. We do not know what to do, but we look to You.”
በጣም ብዙ ቁጥር ያላቸው ሞዓባውያን ፣ አሞናውያንና ምዑናውያን በአንድነት ተሰብሰበው ንጉሥ ኢዮሳፍጥን ለመውጋት መጡ ፡፡ ይህንንም በመፍራት ንጉሥ ኢዮሳፍጥ እግዚአብሔርን ሊፈልግ ፊቱን አቀና ፤ በይሁዳም ሁሉ ጾም አወጀ ። ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ምን ማድረግ እንዳለበት አላወቀም ፤ የሚያውቀው አነድ ነገር እግዚአብሔርን መፈለግ እንዳለበት ብቻ ነበር ፡፡ ስለዚህም ህዝቡ እግዚአብሔርን አመሰገኑ ፤ የተናገረውንም ተስፋ አስታወሱ ፤ ውጊያቸውንም እርሱ እንደሚዋጋላቸው አመኑ ፡፡ እግዚአብሔርም መለሰላቸው እንዲህም “ ነገ በእነርሱ ላይ ውረዱ ……. እናንተ በዚህ ሰልፍ የምትዋጉ አይደላችሁም ፡፡ ተሰለፉ፥ ዝም ብላችሁ ቁሙ፥ የሚሆነውንም የእግዚአብሔርን መድኃኒት እዩ ፡፡ ” ህዝቡም በአምላካቸው በእግዚአበሔር በመታመን ወጡ እግዚአብሔርም ድልን አቀዳጃቸው ፡፡
ዛሬ የሆነ ነገር እየፈራህ ነው ? በደንብ ተንፍስና እግዚአብሔርን ፈልግ ፡፡ እንደዚህ የሚል እምነት ይኑርህ “ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም ነገር ግን እግዚአብሔር ሆይ አንተን እፈልጋለሁ ፡፡ “ እመን እግዚአብሔር እንደሚረዳህ ፤ እመን እግዚአብሔር ታማኝ እንደሆነ ፤ እመን እግዚአብሔር እንደሚመራህ ፤ እመን እግዚአብሔር ጠላቶችህን ከአንተ እንደሚመልስ ፡፡ ልክ ኢዮሳፍጥን እግዚአብሔር በውጊያ እንዳዘዘው ዛሬም አንተ ተነስተህ በመሄድ ወጊያውን መግጠም በአምላክህም በእግዚአብሔር መታመን አለብህ ፡፡ እርሱ እንድህ ይልሃል “ ቁም ፣ እኔም ስለ አንተ እዋጋለሁ “ ፡፡ እግዚአብሔርን ዘላለማዊ ስለሆነ ታማኝ ፍቅሩ አመስግን ፡፡
“ አምላካችን ሆይ፥ አንተ አትፈርድባቸውምን? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን እንቃወም ዘንድ አንችልም፤ የምናደርገውንም አናውቅም፤ ነገር ግን ዓይኖቻችን ወደ አንተ ናቸው ። “
- 2ኛ ዜና 20፡12
ተጨማሪ ጥቀስ
2ኛ ዜና 20፡20 –“ ማልደውም ተነሡ፥ ወደ ቴቁሔም ምድረ በዳ ወጡ፤ ሲወጡም ኢዮሣፍጥ ቆመና፦ ይሁዳና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ፥ ስሙኝ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር እመኑ፥ ትጸኑማላችሁ፤ በነቢያቱም እመኑ፥ ነገሩም ይሰላላችኋል አለ ። “
መዝሙር 46፡10 –“ ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ ። “
መዝሙር 136፡1 –“ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።