Hearing the Word of the Lord
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Royal Throne 2 Chronicles 17-18 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በ 2ዜና መዋዕል ጥናታችንን እንቀጥላለን በተለየም ምዕራፍ 17-18 ፤ እዚህ በአሁኑ ስዓት እኛን ሊያስተምሩ የሚችሉ በጣም ብዙ አሉ ፡፡
ትምህርት
2-ዜና መዋዕል (17፡ 1-9)፡ በምዕራፍ 15 ንጉስ አሳ ከነቢዩ አዛርያስ ሰማ አሳም ወደ እግዚአብሄር በመመለስ ቤቱን ማንፃት በመጀመር ህዝቡን መነቃቃት ጊዜ ላይ መራቸው ፡፡ በአሳ መሞት ልጁ ኢዮሳፍጥ መግዛት ጀመረ (ቁጥር 1) ፡፡ ኢዮሳፍጥ የይሁዳን ሕዝብ በማጠንከር በተመሸጉት በይሁዳ ከተሞች ዉስጥ ጦርን አስቀመጠ (ቁጥር 2) ፤ እግዚአብሄር ከኢዮሳፍጥ ጋር ነበር ምክንያቱም በዳዊት መንገድ ስለ ተጓዘ (ቁጥር 3-4) ፡፡ ይሁዳም ሁሉ እንደ ሚገዛ ንጉስ ኢዮሳፍጥን እጅ መንሻ አመጡለት ኢዮሳፍጥም በይሁዳ ኮረብታዎችን እና የጣዖት ጢሻዎችን በማንፃት ምላሽ ሰጠ (ቁጥር 5-6) ፡፡ በአስተዳደሩ በሰዎስተኛዉ አመት ኢዮሳፍጥ ሰራተኞቹን እና ሌዋዊያንን ለህዝቡ የህጉን መፅሀፍ እንዲያስተምሩ ወደ ሁሉም ይሁዳ ከተሞች ላካቸው (ቁጥር 7-9) ፡፡
2-ዜና መዋዕል (17፡ 10-18)፡ ሁል ጊዜ የእግዚአብሄር ቃል ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ትኩረት ላይ ያመጣል ፡፡ የይሁዳ ሰዎች ክርስቶስን አያዉቁትም ነገር ግን በጊዜአቸዉ በሚከተሉት የእግዚአብሄር ቃል የእግዚአብሄር መገለጥ እያዩ እንደ ነበር ተረድተዋል ፤ ነገር ግን የእግዚአብሄርን ቃል ማንበብ ብቻ ሳይሆን “ ሰዉ በእንጀራ ብቻ አይኖርም “ (ዘዳ 8፡ 1-3፣ ማቴ 4፡ 1-4) የሚለዉን ያደርጋል ፡፡
በምዕራፍ 17 እና በምዕራፍ 18 መካከል በኢዮሳፍጥ ትልቅ ንፅፅር እናያለን ፡፡ ለዉጡን ተመልከቱ ፤ አሳ ልጁን በእግዚአብሄር መንገድ እንዲጓዝ ነገረው ፡፡ ኢዮሳፍጥ በእግዚአብሄር ቃል ሲጓዝ የይሁዳ ሰዎችም እንደ ሚያገኙት እርግጠኛ ነው ፤ የእግዚአብሄር ቃል የይሁዳን ሰዎች መቀየር ጀመረ ፡፡ “ በይሁዳም ዙሪያ በነበሩ መንግስታት ሁሉ ላይ ከእግዚአብሄር ዘንድ ድንጋጤ ሆነ ከኢዮሳፍጥም ጋር አልተዋጉም “ (ቁጥር 10) ፤ ሌሎች ህዝቦችም በግንባታ እቅዱ አገሩን በመምራት በይበልጥ የተሳካለት እንዲሆን ኢዮሳፍጥን በመፍቀድ እጅ መንሻዎችን ላኩለት (ቁጥር 11-18) ፡፡ ይህ በዙሪያችን ያሉትን ሌሎችን እና ሌሎች ህዝቦች ላይ ተፅዕኖ እንደ ሚያደርግ በእግዚአብሄር የሚያስታምን ነው ፡፡
ኢዮሳፍጥን በይሁዳ ግዛቱ በምዕራፍ 18 በራሱ በምዕራፍ 17 ልናነፃፅረዉ ስንዘጋጅ ሁሉም ክፉ ነገስታት ወደ ነበሩት ወደ እስራኤል ንጉስ ስፍራ ይተላለፋል ፡፡ ኢዮሳፍጥ ህዝቡን ወደ መነቃቃት የመራ ከይሁዳ መልካም ነገስታቶች አንዱ ነበር ፡፡ እስራኤል በፍፁም መነቃቃትን አልቀመሰም (አላገኘም) ነበር ፡፡
2-ዜና መዋዕል (18፡ 1-7)፡ ኢዮሳፍጥ በራስ መተማመን መጓዙን በመቀጠል ከእስራኤል ክፉ ነገስታቶች ከአክዓብ ጋር ዝምድና አደረገ (ቁጥር 1) ፡፡ ከብዙ አመት በኋላ ኢዮሳፍጥ አክዓብን በሰማሪያ ሊያየዉ ሄደ ፤ አክዓብ ኢዮሳፍጥ በደረሰ ጊዜ ታላቅ አቀባበል አድረገ ከዚያም በሬማት ዘገለዓድ ላይ ለመዋጋት ከእርሱ ጋር እንዲቀላቀል ኢዮሳፍጥን አባበለው ፤ ኢዮሳፍጥም በአክዓብ እቅድ ተስማማ (ቁጥር 2-3) ፤ ነገር ግን ኢዮሳፍጥ ከመሄዳቸዉ በፊት የእግዚአብሄርን አቅጣጫ በመፈለግ ጠየቀ (ቁጥር 4) ፡፡ አክዓብ በአንድ ላይ 400 ነቢያትን በአንድ ላይ በመጥራት ሬማት ዘገለዓድ እንሂድን ብሎ ጠየቃቸው ፤ ነቢያቶቹም እግዚአብሄር ሬማት ዘገለዓድ ለእነርሱ እንደሚሰጣቸው ነገሩዓቸው (ቁጥር 5) ፤ ኢዮሳፍጥ 400 ነቢያቶቹ ባሉት ስላረከ ሊጠይቁዓቸዉ የሚችሉዓቸዉ ሌሎች ነቢያቶች እንዳሉ ጠየቀ (ቁጥር 6) ፡፡ አክዓብ ሌላ አንድ ተጨማሪ ስሙ ሚክያስ የሚባል ነቢይ እንዳለ ነገር ግን አክዓብ መስማት የሚፈልገዉን ስለማይተነብይ ንጉሱ እንደ ሚጠላዉ ነገረው (ቁጥር 7) ፡፡ ኢዮሳፍጥ የእግዚአብሄርን ቃል ያከብር ነበር አክዓብ ደግሞ መስማት የሚፈልገዉን የሚነግሩት ቡድኖች ሰርቶ ነበር ፡፡
2-ዜና መዋዕል (18፡ 8-11)፡ አክዓብ ለነቢዩ ሚክያስ ላከበት (ቁጥር 8) ፤ የእስራኤል እና የይሁዳ ነገስታቶች (አክዓብ እና ኢዮሳፍጥ) ንጉሳዊ ካባቸዉን በመልበስ በሰማሪያ በር ላይ በመቀመጥ የአክዓብ ምርጫ 400 ነቢያቶች መልዕክታቸዉን ሲናገሩ ተመለከቱ (ቁጥር 9) ፡፡ አንድ ነቢይ የብረት ቀንዶችን በመስራት አክዓብ ሶሪያዉያንን ሙሉ ለሙሉ እንደሚያጠፋቸዉ ትንቢት ተናገረ (ቁጥር 10) ፤ የአክዓብ ነቢያቶች የአክዓብን ጠላቶች እግዚአብሄር አሳልፎ እንደሚሰጠዉ በሚለዉ ኃሳብ የተስማሙ ነበሩ (ቁጥር 11) ፡፡
2-ዜና መዋዕል (18፡ 12-14)፡ አክዓብ አንድ መልዕክተኛን ሚክያስን በማግኘት ሌሎቹ ሁሉም ነቢያቶች ስለተስማሙ ትንቢቱ ተመሳሳይ መሆን እንዳለበትእንዲነግረዉ ላከው (ቁጥር 12) ፡፡ ሚክያስም እንዲናገረ አምላኩ የነገረዉን ማንኛዉንም እንደሚናገር መለሰለት (ቁጥር 13) ፤ በንጉስ አክዓብ ፊት ሚክያስ 400 ነቢያቶች ብለዉት የነበረዉን ተመሳሳይ ነገረ ደገመ (ቁጥር 14) ፡፡
በአንድ ንጉስ መሾም (መቀባት) ላይ በንጉሱ ህይወት ላይ የንጉሱ ነቢያቶች ብቻ ሳይሆኑ የእግዚአብሄር መንፈስ የቅባቱ(የሹመቱ) አካል መሆን እንደ ነበረበት የተመከረ ነበር ፡፡ በንጉሱ ህይወት ዉስጥ የሆነን ነገር ከእግዚአብሄር የሆነን ወይም ያልሆነን ለማወቅ መለኮታዊ የሆነ ነገር ሊኖረዉ ይገባል ፤ ኢዮሳፍጥ የእግዚአብሄርን እዉነት መለየት የሚችልበት ስፍራ ነበር አክዓብ ግን አልነበረም ፡፡
2-ዜና መዋዕል (18፡ 15-22)፡ ንጉስ ኢዮሳፍጥ ሚክያስን ሌሎቹ ያሉትን መድገም እንደ ለለበት ነገር ግን እዉነቱን እንዲነግረው ነገረው (ቁጥር 15) ፡፡ ሚክያስም የባለ ራዕይ/ነቢይን ተግባር የነበረውን “ አየሁ “ አለ ፤ ሚክያስ እስራኤል ሁሉ በተራራዉ ላይ ያለ ጠብቂ ተበትነዉ አየሁ እግዚአብሄርም ሁሉንም ቤታቸዉ ላካቸው አለ (ቁጥር 16) ፤ አክዓብም ሁል ጊዜ ለእርሱ ሚክያስ መጥፎ ምላሽ እንደ ነበረው ተነገረ (ቁጥር 17) ፡፡
ከዚያም ሚክያስ እግዚአብሄር በዙፋኑ ላይ ሆኖ የሰማይን ሰራዊትን አክዓብ የተሸነፈ እንዲሆን ወደ ሬማት ዘገለዓድ እንዲሄድ ማን እንደሚያስተዉ ጠየቀ በሚል ራዕይ ምላሽ ሰጠ (ቁጥር 18-20) ፤ በራዕዩ እግዚአብሄር ወደ ጦርነቱ እንዲሄድ ለማሳመን “ በሁሉም ነቢያቶቹ አፍ የስህተት መንፈስ እንዲቀመጡ “ በማለት እግዚአብሄር መንፈስን ላከው (ቁጥር 21-22) ፡፡
2-ዜና መዋዕል (18፡ 23-27)፡ ሚክያስ ከተናገረ በኋላ ከአክዓብ ነቢያቶች አንዱ ሚክያስን በጉንጩ ላይ በጥፊ በመምታት ሚክያስን የጌታ መንፈስ እንዴት እኔን አለፈኝ በማለት ከሰሰው (ቁጥር 23) ፡፡ ሚክያስም የአክዓብ ሁሉም ነቢያት በጊዜዉ እዉነቱን እንደ ሚያዩ መለሰላቸው (ቁጥር 24) ፡፡ ንጉስ አክዓብ አገልጋዮቹን ሚክያስን በእስር ቤት በማስቀመጥ የመከራ ዉኃ እና እንጀራ እንዲመግቡት ነገራቸው (ቁጥር 25-26) ፤ ከመወሰዱም በፊት ሚክያስ ከጦርነት አክዓብ በሰላም ከተመለሰ ሚክያስ የእግዚአብሄርን እዉነት እንዳልተናገረ ታዉቃለህ አለው (ቁጥር 27) ፡፡
2-ዜና መዋዕል (18፡ 28-34)፡ አክዓብ እና ኢዮሳፍጥ ወደ ሬማት ዘገለዓድ ሄዱ ኢዮሳፍጥ ንጉሳዊ ልብሱን እንደ ለበሰ አክዓብ ራሱን ለመለወጥ ወሰነ (ቁጥር 28-29) ፡፡ የሶሪያ ንጉስ ሰራዊቱን ከእነርሱ ጋር ከሚገጥሙት ወታደሮች ጋር እንዳይገጥሙ ነገር ግን የእስራኤልን ንጉስ ብቻ እንዲገጥሙ ነገራቸው (ቁጥር 30) ፤ ይሁን እንጂ የሶሪያ ወታደሮች ኢዮሳፍጥን በንግስና ልብሱ ባዩት ጊዜ የእስራኤል ንጉስ ብለዉ አስበዉ ስለ ነበር ከበቡት ፡፡ ኢዮሳፍጥ ወደ ሚያድነዉ ጌታ ጮኸ (ቁጥር 31) ፤ ወታደሮቹም ከኢዮሳፍጥ ተመለሱ ፤ ከእነርሱ አንዱ በአጋጣሚም አክዓብን ያቆሰለ ቀስት በመወርወር (ቁጥር 32-33) በጦርነቱም አክዓብ ሞተ (ቁጥር 34) ፡፡
መደምደሚያ
ዮሐ (8፡ 31-32) “ እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእዉነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ ፤ እዉነትንም ታዉቃላችሁ እዉነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው “ ፤ እዉነት ከምን አርነት ያወጣናል ? ኢየሱስ የኃጢዓት ባሪያዎች እንደ ሆንን ገልጧል ነገር ግን ልጁ ነፃ ሊያወጣን ይቻለዋል ፡፡
በአሁኑ ጊዜ በራሳችን ላይ መመስረት በመቻል ይህ የእግዚአብሄር ቃል ነው በማለት የምንሰማቸዉ ነገሮች ምንድና ናቸው ? ለሪቫይቭ ት/ቤት ምክንያቱ ያ ነው !
ጥያቄዎች
-
በ 2ዜና መዋዕል (17፡ 7-9) ንጉስ ኢዮሳፍጥ ያደረገዉ በዘዳ (4፡ 5) ሙሴ ካደረገው እንዴት ነዉ የሚመሳሰለው ?
-
በብሉይ ኪዳን ንጉስ ኢዮሳፍጥ ማንን ሌላ ንጉስ ያስታዉሳል ? (1ነገ 4፡ 21-28)
-
ንጉስ ኢዮሳፍጥ እንደ ንጉስ አክዓብ አይነት ከሆኑ ክፉ ነገስታት ጋር ራሱን አንድነት ዉስጥ ለማስገባት ሊኖረዉ የሚችለዉ ምክንያት ምን ሊሆን ይችላል ? (2ዜና መዋዕል 18፡ 1)
-
ንጉስ አክዓብ ነቢዩን ሚክያስን ወደ እስር ቤት ዉስጥ ለምን ወረወረው ? (2ዜና መዋዕል 18፡ 7፣ 18-22)
-
የእስራኤል ንጉስ “ በድንገት በቀስት መመታቱ “ አደጋ (በአጋጣሚ) ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ ? (2ዜና መዋዕል 18፡ 29፣ 33)
-
በ 2ዜና መዋዕል (17-18) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Chronicles 18:29
“But the king of Israel said to Jehoshaphat, ‘I will disguise myself and go into battle, but you wear your royal attire.’ So the king of Israel disguised himself, and they went into battle.”
ንጉሥ አካብ በሬማት ዘገለዓድ በተደረገው ውጊያ ራሱን ደበቀ ፡፡ በሌላ በኩል የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ የራሱን የንግሥና ልብስ ለበሰ ፡፡ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ጥሪውን ያስቀደመው በእግዚአብሔር ላይ በመታመን እንጅ በራሱ በመታመን አልነብረም ፡፡ ጣላቶቹም በከበቡት ጊዜ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ይረዳው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ እግዚአብሔርም ጣለቶቹን መለሰለት ኢዮሳፍጥንም ታደገው ፡፡ በሌላ በኩል ንጉሥ አካብ በተደበቀ ማንነቱ ድንገተኛ ቀስት በጥሩሩ መጋጠሚያ ላይ ወግቶት ሞተ ፡፡
በፍርሀት ንጉሥ አካብ ሁኔታውን ለመቀየር ሞከረ ፡፡ በእምነት ንጉሥ ኢዮሳፍጥ በእግዚአብሔር ላይ በመታመን ተራመደ ፡፡ የራስህን ጦርነት ስትገጥም ምርጫ አለህ ፡- ልትቆጣጠርና ልታስተካክል ወይም በእግዚአብሔር ላይ ልትታመንና በእውነት ልትራመድ ፡፡ አስተውል የተጠራኸው እንደ ተመረጠ የንጉሥ ልጅ ነው ፡፡ ተወደሃል ፡፡ የንጉሥ ካህናት ወገን ነህ ፡፡ መደበቅ አያስፈልግህም ወይም ደግሞ በዙሪያህ ካለው ጋር መደባለቅ ፡፡ በክርስቶስ በእምነት ተራመድ ፡፡ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ የእግዚአብሔርን ቃል አንብቧል ከቃሉም እውነት ብርታትን አግኝቷል ፡፡ እንደ አማኝ እግዚአብሔር የጠራህ ጦርነቱን ትዋጋ ዘንድ በቃሉ እንድትኖር ነው ፡፡ ያልሆንከውን ለመሆን አትሞክር ፡፡ መቆጣጠሩን ተወውና በክርስቶስ ባለህ ማንነት ተመላለስ ፡፡ እግዚአብሔር ውጊያህን ይዋጋል !
“ የእስራኤል ንጉሥም ኢዮሣፍጥን፦ ልብሴን ለውጬ ወደ ሰልፍ እገባለሁ፤ አንተ ግን ልብስህን ልበስ አለው። የእስራኤልም ንጉሥ ልብሱን ለወጠ፥ ወደ ሰልፍም ገቡ ። “
-2ኛ ዜና 18፡29
ተጨማሪ ጥቅስ
- ማቴዎስ 4:4 — “ እርሱም መልሶ፦ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው ። “
- ኤፌሶን 3:12 — “ በእርሱም ዘንድ ባለ እምነታችን በኩል በመታመን ድፍረትና መግባት በእርሱ አለን ። “
- 1ኛ ጴጥሮስ 2:9 — “ እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።