Revival Under King Asa
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Royal Throne 2 Chronicles 15-16 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ሁሉም የመፅሀፍ ቅዱስ መፅሀፍት የታሪክም መፅኀፍትም ወደ ሚመጣዉ መሲህ ያመለክታሉ ፡፡ ለ 1ዜና መዋዕል ቃላችን የዳዊት ልጅ ነበር ፤ ለ 2ዜና መዋዕልቃላችን ንጉሳዊ ዙፋን ነው ፡፡ በ 2ዜና መዋዕል 10 የእስራኤል ህዝብ ወደ ሰሜን እና ደቡብ ነገድ መከፋፈላቸዉን አይተናል ፡፡ ቀሪዉ 2ዜና መዋዕልወደ ይሁዳ ነገስታቶች ያመለክታል ፡፡ ዛሬ ንጉስ አሳ ላይ የምንመለከት ይሆናል ፡፡
ትምህርት
2-ዜና መዋዕል (15፡ 1-2)፡ የእግዚአብሄር መንፈስ የእግዚአብሄርን ቃል ለንጉስ አሳ ባመጣዉ በአዛርያስ ላይ መጣ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ አዛርያስ ለንጉስ አሳ ያለዉ አብዛኛዉ በመሳፍንት ዘመንየተነገሩ ይሆናሉ ፤ ስለዚህ አዛሪያስ የሚለዉ በመሳፍንት መፅኀፍ ተብሎ ከነበረዉ ጋር ይመሳሰላል- ጥያቄዉ የእርሱን ትንቢታዊ ቃል የሰማዉ ሰዉ ምላሹ ምን እንደሚሆን ነበር ፤ አሳ እንደ ቀድሞዎቹ መሳፍንቶች ይመልሳል ወይስ እግዚአብሄር እንዲያደርግ በሚፈልገው በማድረግ ይመልሳል ?
በብሉይ ኪዳን ጊዜ (ወቅት) የእግዚአብሄር መንፈስ ለአንድ ጊዜ መምጣቱን እናስታውሳለን ፡፡ ይህ ከአዲስ ኪዳን እና ከአሁን በላይ የተለየ ነበር ምክንያቱም መንፈሱ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ሚያርማቸው፣ እንደ ሚመራቸዉ፣ እንደ ሚያስተካክላቸው፣ ምቾት እንደ ሚሰጣቸው እና በእነርሱ ዉስጥ እንደ ሚናገር በሚያምኑት ዉስጥ ስለ ሚያድር ፡፡
አዛርያስ አሳን የይሁዳን እና የብንያምን ሰዎች “ እናንተ ከእግዚአብሄር ጋር ስትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ይሆናል “ ብሎ ነገራቸው (ቁጥር 2) ፡፡ ንጉስ አሳ ለ41 አመት ያስተዳድራል በእግዚአብሄር መንገድ ወይም በራሱ መንገድ መጓዝን ይመርጣል ፡፡ “ ከእርሱ ጋር ስትሆኑ “ እና “ ስትፈልጉት “ የሚለዉ ሀረግ 2ዜና መዋዕል (7፡ 13-14) ያስታዉሰናል ፡፡
2-ዜና መዋዕል (15፡ 3-4)፡ ለአመታት እስራኤል ከእግዚአብሄር ዉጪ፣ ከአስተማሪ ካህናት ዉጪ እና ከትዕዛዝ ዉጪ ሆኗል ፡፡ ፀሀፊዉ ምናልባትም ዕዝራ እግዚአብሄርን ማግኘት ወደ ሚችሉበት ለማመልከት ተመልሰዉ እንዲያዉቁት ከግዞት ተመልሰዉ ለመጡት እየፃፈ ነበር ፤ ስለዚህ በተመሳሳይ በአሳም ጊዜ ለእነርሱ የነበረዉን ሁሉ ለመቅመስ ወደ እግዚአብሄር በመመለስ ይፈልጉታል ፤ ነገር ግንእግዚአብሄርን ካልፈለጉ ከእነርሱ ጋር አይሆንም ፡፡
2-ዜና መዋዕል (15፡ 5-7)፡የኔልሰን ማብራሪያ እስራኤላዊያን ባለማቋረጥ በጦርነት አደጋ ላይ እና የተዘረፉ የሆኑ ነበሩ ፤ ወንጀልን እየተፈፀመባቸው በሌሎች ህዝቦች ተወረዉ ነበር ፡፡ የአዛሪያስ መልዕክት እስራኤላዊያን በመሳፍንት (5፡ 6-7) ድቦራ እስክትነሳ ድረስ እና እስኪነቃቁ ድረስ ከገጠማቸዉ ጊዜ ጋር ተመሳሳይ ነበር ፤ የሆነዉ ሁሉ እንደ ድቦራ ወይም እንደ አሳ ለሆኑት አንዳንዶች ሰዎችን ወደ እግዚአብሄር መልሶ መምራት ነበር ፡፡ ባልተለመደ ሁኔታ አንዳንድ ጊዜ በራሳችን ከመንቀሳቀስ በላይ ሌሎች እንዲያነቁን እንጠብቃለን ፡፡ አዛርያስ ቀላል መፍትሄ ሰጠ - እግዚአብሄርን መፈለግ ፡፡
2-ዜና መዋዕል (15፡ 8-9)፡ አሳ በእነዚህ ቃሎች ጥንካሬ በማግኘቱ ከመላዉ ምድሪቱ ርኩስ ጣዖቶችን አስወገደ ፡፡ ከአመታት በኋላ ነገስታቶች ነገሮችን ትተዉ ነበርስለሆነም አሳ የቀድሞ ነገስታቶች ያልተጠነቀቁለትን ምድሪቱን እና መሰዊያዉን ያድሰዋል ፡፡ በአሁኑ ጊዜ መነቃቃት መጠራታችን ምን እንደ ሚመስል እያየን ነው ፡፡ አሳ ቢንያምን እና ይሁዳን እግዚአብሄርን እንዲፈልጉት በመራ ጊዜ ሰዎችይሁዳን ለመቀላቀል ከእስራኤል ኮበለሉ ምክንያቱም እግዚአብሄር ከእነርሱ ጋር እንደ ነበር ስላዩ ፡፡
በመፅሀፉ እግዚአብሄርንመቅመስ ሄነርይ ብላክቤይ ሰዎች እግዚአብሄር የሚሰራበትን ቦታ ለማየት በመከታተል በዚያ እንዲቀላቀሉት ያበረታታል ፡፡ እግዚአብሄርን ለመለማመድ ናፍቆት(ጉጉት) በሚኖረን ጊዜ ሌሎች ሰዎች በይበልጥ ይፈልጉታል ፡፡ እምነታችሁ በህይወታችሁ መንፈስ ቅዱስን በማየታቸዉ ምክንያት እንዲቀላቀሉዓችሁ ሌሎችን ይስባል ? ለእግዚአብሄር መነቃቃታችን እና ጉጉታችን ሰዎችን ወደ እግዚአብሄር መሳብ እንድንችል ነው (ኢሳ 60፡ 3) ፡፡ በማቴ (5፡ 14-16) ኢየሱስ የአለም ብርሀን ናችሁ በሏል ፤ ያን ብርሀን በምናበራዉ ጊዜ ሰዎች ለእግዚአብሄር ክብር ይሰጣሉ ፡፡ ሐዋ (13፡ 47) ለአሕዛብ ሁሉ መዳንን ለማምጣት ብርሃኖች እንደ ናችሁ ይላል ፡፡ ኢሳያስ እግዚአብሄር ለተቀደሰ አላማ እንደ ጠራን ይጠቅሳል - ለአሕዛብ ብርሃን እንድንሆን (ኢሳ 42፡ 6) ፡፡ ዘዳ (32፡ 21) እስራኤል ጣዖትን በማምለክ በወደቀ ጊዜ እግዚአብሄር በሌሎች ሕዝቦች እንዲቀኑ እንደሚያደርጋቸዉ ይናገራል ፤ በሮሜ (11፡ 11-12) ጳዉሎስ እስራኤል በተሰናከለ ጊዜ እስራኤልን ለማስቀናት ድነት ወደ አሕዛብ መጣ ፡፡
ሪክ ቶማስ ኑሮአችን ሌሎችን ወደ እግዚአብሄር መሳብ እንደ ሚችል ለማመልከት አንዳንድ ጥያቄዎችን አቅርቧል፡ “ በትክክል ሰዎች ከእናንተ ጋር መዛመድ(መገናኘት) ይችላሉ ? “ “ ሰዎች ከእናንተ ጋር መገናኘት (መዛመድ) ይፈልጋሉ ? “ “ የተለያየ ፍላጎት ያላቸዉ ሰዎች በዙሪያችሁ ይሆናሉ ? “ ስለዚህ እኛ እንዳወቅነዉ እግዚአብሄርን ለማወቅ እንዲፈልጉ በሌሎች ላይ እንዴት የቅናት መንፈስን እንፈጥራለን ? በ 1ቆሮ (11፡ 1) ጳዉሎስ አማኞችን “ እኔ ክርስቶስ እንደምመስል እኔን ምሰሉ “ በማለት አነቃቸው ፡፡ እዚህ በብሉይ ኪዳን ደግሞ ለዚህ አሳ ሞደል ነበር ፡፡ ሰዎች ወደ አሳ እየተሳቡ ነበር ምክንያቱም እግዚአብሄር በሕይወቱ እየሰራ ስለ ነበር፡፡ ህይወቱን እና ምድሩን ሲያነፃ ሌሎች በእርሱ ህይወት እየሰራ ወደ ነበረው ወደ እግዚአብሄር ተሳቡ ፡፡
ዕብ (10፡ 22) ላይ በመመልከት ይህ በህይወታችን እንዴት እንደሚሆን ማየት እንችላለን ፤ መጀመሪያ እዉነተኛ ልብ፣ ንፁህ ልብ እና ያልተከፈለ ልብ ሊኖረን ያስፈልገናል ፡፡ መዝ (24፡ 3-4) ሰዎች በንፁህ እጅ እና በንፁህ ልብ እግዚአብሄርን መቅረብ ይችላሉ ይላል ፡፡ በመቀጠል እርግጠኛ የሆነ እምነት ሊኖረን ይገባል ፡፡ ጣዖትን ከህይወታችን ባስወገድን ጊዜ ባዶነታችንን በመገኘቱ ለመሙላት እግዚአብሄር በጣም በቂ እንደ ሆነ እናውቃለን ፤ ልባችንም ልባችን የነፃ ስለሚሆን ንፁህ ሀሳብ ይኖረናል ፡፡
አሳ በመላዉ ምድሪቱ ያሉትን ጣዖቶች በማስወገድ ቤቱን ባነፃ ጊዜ ከጥፋተኝነት ነፃ ነበር ፡፡ ስንነፃ እና ከጥፋተ ነፃ ስንሆን ሌሎች የሚያስተዉሉት ንፁህ አሳብ ይኖረናል ፡፡ በመጨረሻም ንፁህ ሰዉነት ሊኖረን ይገባል ፤ ዮሐ (13፡ 10) የሚለው ከክርስቶስ ጋር ወደ ዝምድና(ትስስር/መቀራረብ) ዉስጥ በገባን ጊዜ ነፅተናል ይላል ፡፡ ስንነፃ ብርሃን ከእኛ በማብራቱ ሰዎች በክርስቶስ በእኛ ዉስጥ ይሳባሉ ወይም በብርሃኑ የተገፉ ይሆናሉ ፡፡ 1ዮሐ (1፡ 6-7) በክርስቶስ ብርሃን ስንጓዝ ከሌሎች ጋር ትስስር ሊኖረን ይጀምራል ፤ ያም እዉነተኛ አንድነት ስናይ ይጀምራል ፡፡
መደምደሚያ
ማድረግ ላለብን ነገር ንጉስ አሳ ምሳሌ ነው ፡፡ ቤትን ልናፀዳ ያስፈልገናል ያ ሲሆን ብርሃኑ ገብቶ ስለሚስፋፋ ሰዎች በእዉነት ወደ ኢየሱስ ሊሳቡ ይችላሉ ፡፡ አሳ ህዝቡን በአንድ ላይ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ እና መሳዋዕት እንዲያደርጉ በመምራት በሙሉ ኃሳባቸዉ እና በሙሉ ልባቸዉ እግዚአብሄር አምላክን ወደ መፈለግ ኪዳን ዉስጥ ገቡ (2ዜና መዋዕል 15፡ 12) ፤ አንድ ነቢይ ስለዚህ ነገር የሆነ ነገር እንዲያደርግ ለአንድ ንጉስ እዉነቱን ተናግሮታል ፡፡ ጣዖቶችን በማስወገድ ባህሉን፣ አካባቢዉን እና ህዝቡን ቀየረ ፤ የድፍረት ድርጊቱ ሌሎችን እግዚአብሄርን ወደ መፈለግ መራቸው ፡፡ ይህን ስናደርግ በዙሪያችን ላሉት እናደርጋለን ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville, TN: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 547.
Nelson’s Commentary, p. 547.
Henry Blackaby, Richard Blackaby, and Claude King, Experiencing God (Nashville: B & H Publishing Group, 2008), p. 69.
Rick Thomas, “How to relate to people through ministry, music, and mentoring”; https://rickthomas.net/how-to-relate-to-people-through-ministry-music-and-mentoring/.
ጥያቄዎች
-
2ዜና መዋዕል (15፡ 1) “ የእግዚአብሄር መንፈስ በዓዛርያስ ላይ እንደ መጣ “ ይጠቅሳል ፤ ይህ ምን ማለት ነው ? በአሁኑ ጊዜ ይህ ይሆናል ብላችሁ ታስባላችሁ ? በሌላ ሰዉ በኩል እግዚአብሄር ተናግሯችሁ ያውቃል ?
-
2ዜና መዋዕል ( 15፡ 13) እግዚአብሄርን የማይፈልጉ ሰዎች ይገደላሉ ይላል ፤ ይህ የፈጠነዉ(ብቸኛዉ) ቅጣት እንደ ነበር ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አላሰባችሁም ?
-
በቁጥር 16 “ ንጉሱም አሳ እናቱን መዓካን በማምለኪያ ዐፀድ ጣዖት ስላደረገች ከእቴጌነትዋ አዋረዳት ፤ አሳም ምስልዋን ቄርጦ ቀጠቀጠው በቄድሮንም ወንዝ አጠገብ አቃጠለው “ ፤ ይህ ከይሁዳ ህዝብ ጋር ስላደረገዉ ኪዳን ቁረጠኝነት ስለሚለዉ ምን ታስባላችሁ ?
-
በግል አስተያየታችሁ አሳ የእስራኤል ንጉስ ባዖስ በይሁዳ ላይ በመጣ ጊዜ እንዲረዳዉ እግዚአብሄርን ከመፈለግ ይልቅከሶርያ ንጉስ ወልደ አዴር ጋር ስምምነት ለማድረግ ለምን ወሰነ (2ዜና መዋዕል 16፡ 1-3) ? እግዚአብሄርን ያለመከተል ዉጤቶቹ ምን ነበሩ ? (2ዜና መዋዕል 16፡ 7፣ 9)
-
2ዜና መዋዕል (15፡ 9) አንብቡ ፤ ሰዎች ከእስራኤል እየኮበለሉ ወደ ይሁዳ ይመጡ የነበረዉ ለምን ነበር ? ሰዎች በእናንተ ወይም በምታዉቁት ሰዉ ወደ ዘላለም ሲሳቡ መቼ አይታችኋቸዋል ? (መክ 3፡ 11)
-
በ 2ዜና መዋዕል (15-16) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Chronicles 15:9
“Then he gathered all Judah and Benjamin, as well as those from the tribes of Ephraim, Manasseh, and Simeon who had settled among them, for they had defected to him from Israel in great numbers when they saw that Yahweh his God was with him.”
በጊዜ ሂደት ህዝቦቹ የእግዚአብሔርን መንገድ ተው ቤተ መቅደሱንም በጣዖት ሞሉ ፡፡ ነገር ግን ንጉሥ አሳ የእግዚአብሔርን ቃል በነቢዩ ዓዛርያስ በኩል በሰማ ጊዜ በመላው ይሁዳና ብንያም ምድር ያለውን ጣዖት በቆራጥነት አስወገደ ፡፡ ንጉሥ አሳ ቤተ መቅደሱን አጸዳ እንድሁም በተጨማሪ ህዝቡ በሙሉ ሀሳባቸውና ልባቸው እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ ሰበሰባቸው ፡፡ ንጉሥ አሳ ከሁሉም ህዝብ ቀዳሚ በመሆን ለእግዚአብሔር በድፍረት ኖረ ህዝቡም ያህዌ ከእርሱ ጋር እንዳለ አወቁ ፡፡
እስኪ ራስህን ጠይቅ ሰዎች ኢየሱስ ከአንተ ጋር እንደሆነ ያውቃሉ ወይስ አያውቁም ፡፡ ንጉሥ አሳ ቤተ መቅደሱን ባጸዳ ጊዜ ህዝቡ ያህዌ ከእርሱ ጋር እንደሆነ አወቁ ፡፡ ክርስቶስን ለማንጸባረቅ ትችል ዘንድ የህይወትህን ክፍል ለማጽዳት ጊዜው አሁን ይሆናል ፡፡ ዛሬ ህይወትህን ተመልከትና በሚያስፈልገው ቦታ ላይ “ ቤተ መቅደስህን አጽዳ “ ፡፡ እግዚአብሔር በልብህ በሚያሳስብህ ( ባስቀመጠው ) በአንድ ቦታ ላይ ጀምር ፡፡ ሃሜት ? ስስት ? ሱሰኝነት ? የስፖርት ቡድን ? ክርስቶስን ስታንጸባርቅ ጣልቃ የሚገባብህን ማንኛውንም የህይወትህን ጣዖት አስወግድ ፡፡ እግዚአብሔርን በሙሉ ልብህ ፣ ነፍስህና አሳብህ ልትወድና ኢየሱስን በትክክል ልታንጸባረቅ ጊዜው አሁን ፡፡ በማህበረሰብህ ውስጥ ለውጥን ማየት ከፈለክ የኢየሱስን ፍቅር በዙሪያህ ላሉት ከማንጸባረቅ ይጀምራል ፡፡ እነርሱም ከአንተ ጋር ያለውን ኢየሱስን ይፈልጉ ይሆናል ፡፡
“ አምላኩም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ ከእስራኤል ዘንድ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ተጠግተው ነበርና እርሱ ይሁዳንና ብንያምን ሁሉ፥ ከኤፍሬምና ከምናሴም ከስምዖንም መጥተው ከእነርሱ ጋር የተቀመጡትን ሰበሰበ ። “
- 2ኛ ዜና 15፡9
ተጨማሪ ጥቅስ
ዘዳግም 32:21 — “አምላክ ባልሆነው አስቀኑኝ ፤ በምናምንቴዎቻቸውም አስቈጡኝ ፤
እኔም ሕዝብ ባልሆነው አስቀናቸዋለሁ ፤ በማያስተውል ሕዝብ አስቈጣቸዋለሁ ። “
ኢሳይያስ 42:6 — “ እኔ እግዚአብሔር በጽድቅ ጠርቼሃለሁ፥ እጅህንም እይዛለሁ እጠብቅህማለሁ ፥ ለሕዝብ ቃል ኪዳን ለአሕዛብም ብርሃን አድርጌ እሰጥሃለሁ ። “
ሐዋርያት ስራ 13:47 — “ እንዲሁ ጌታ፦ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ለማዳን ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ ብሎ አዞናልና አሉ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።