God Fights for Us
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Royal Throne 2 Chronicles 13-14 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በአንድ ላይ ያጠናነዉ የእግዚአብሄር ቃል 308ተኛ ቀናችን ነው ፡፡ እስካሁን በ 2ዜና መዋዕል ነገስታቶችን እያጠናን ነው፡ ዳዊት፣ ሰለሞን፣ የይሁዳ ሮብዓም እና የእስራኤል ኢዮሮብዓም ፡፡ ሮብዓም ለመንግስቱ መከፋፈል ያመራ ለእግዚአብሄር ያልታመነ ነበር ፡፡ ይሁዳ ከምድሪቱ አስሩን ነገዶች አጣ እነዚህ አስሩ ነገዶች የእስራኤል መንግስት ሆኑ፡፡ ምዕራፍ 13 ንጉስ አቢያ ይሸፍናል ፤ በቁጥር 2-22 አቢያ ኢዮሮብዓምን ተዋጋው አብያም በምዕራፍ 14 ቁጥር 1 ላይ ሞተ ፡፡ የዛሬዉ ጥናት ከምዕራፍ 14 የንጉስ አሳን ዘመን ይሸፍናል ፤ አብያ እና አሳ ሁለቱም በይሁዳ ላይ ንጉሶች ነበሩ ፡፡
ትምህርት
2-ዜና መዋዕል (14፡ 1-7)፡ አሳ ለ14 አመታት ንጉስ ነበር ለአስር አመታት ጊዜ በምድሪቱ ሰላም ነበር ምክንያቱም አሳ በእግዚአብሄር ፊት ልክ የነበረዉን ስላደረገ (ቁጥር 1-2) ፡፡ በቁጥር 3 መጀመሪያ ላይ ፀሀፊዉ አሳ ያደረጋቸዉን ትክክል ነገሮች መዝግቧል፡ ንጉስ አሳ ምናልባትም በሰለሞን ጊዜ በአሕዛብ ሚስቶቹ ተመልሰዉ የተቀመጡትን የጣዖት መሰዊያዎችን እና ኮረብታዎችንአስወገደ፣ ሐዉልቶችንም አፈራረሰ እንዲሁም የማምለኪያ አፀዶችንም ሰባበረ (ቁጥር 3) ፡፡ ሁሉንም የጣዖት ማምለኪያ ስፍራዎች አሳ አላጠፋቸዉም ነበር ወይም በሚመጡት አመታት ብዙ ተሰርተው ነበር ( ዘዳ 12፡ 2-3፣ 1ነገ 15፡ 14፣ 2ዜና መዋዕል 15፡ 17) ፡፡ አሳም በ 2ዜና መዋዕል (7፡ 14) ልክ እንዳነበብነዉ የይሁዳን ሰዎች እግዚአብሄርን እንዲፈልጉ(እንዲሹት) እና ትዕዛዙን እንዲከተሉት አዘዛቸው (ቁጥር 4)፡፡ አሳ የይሁዳን ጣዖት አምልኮ የዕጣን መሰዊያዎችን በማስወገድ ማፅዳቱን ቀጠለ (ቁጥር 5) ፡፡
ይህ መንፃት በምድሪቱ ላይ ሰላም በማምጣት በይሁዳ አዲስ የተመሸጉ ከተሞች እንዲሰራ ለአሳ ጊዜን ሰጠው ፡፡ ያለጦርነት ይሁዳ እረፍትን አገኘ እንደ በረከተም ይታያል (ቁጥር 6-7) ፤ ሰሩም በደረጉትም ተከናወነላቸው (ቁጥር 7) ፡፡ አሳ እግዚአብሄርን ተመለከተ የእግዚአብሄርንም ምሪት በመከተል ከእርሱ ጋር ወደ አዲስ ኪዳን ገባ (2ዜና መዋዕል 15፡ 12) ፤ ይሁን እንጂ በዘመኑ ሰላሳ ዘጠነኛዉ አመት ላይ አሳ ለኃይለኛ የህመም ስሜት ምክንያት የሆነ በእግሩ ላይ ህመም ወጣበት ፤ በዚህ ጊዜ እግዚአብሄርን አልፈለገም ነገር ግን ወደ መድኃኒተኞች ሄደ (2ዜና መዋዕል 16፡ 12) ፡፡
2-ዜና መዋዕል (14፡ 8-15)፡ በቁጥር 8 ሰላሙ አለቀ ፡፡ አሳ ሁሉም ጀግና ተዋጊዎች ጋሻ እና ሰይፍ የያዙ ከይሁዳ 300,000 ሰዎች እና ከብንያም 280,000 ሰዎች ሰራዊት ነበረው ፡፡ ዝሪም የኩሻዊያንን አንድ ሚሊዮን ሰራዊት ሰዎች እና 300 ሰረገሎችን በአሳ ላይ አመጣ ፡፡ ኩሻዊያን ለምሽግነት ገንብቷት ወደ ነበረችዉ ወደ ሰሜን ወደ ምትርቀዉ መሪሳም ዘመቱ ፤ አሳ ለጦርነቱ ለመዋጋት ወታደሮቹን አሰለፈ ፡፡ ዝሪም ወታደሮቹን ከአሳ ሰራዊት አሰላለፍ በተቃራኒ አሰለፈ (ቁጥር 9-10) ፡፡ የአሳ ሰራዊት ለመዋጋትበጣም ብዙ ሰራዊት ገጠሞት ነበር ነገር ግን አሳ ወደ እግዚአብሄር ጮኸ ለእግዚአብሄር ሁሉን ቻይነት እና ዝና እዉቅና ሰጠ (ቁጥር 11) ፡፡
አሳ እግዚአብሄር በሚያደርገዉ ታላቅ እምነቱን አሳየ ፤ እግዚአብሄር የአሳን ሰራዊት ኩሻዊያን ለመኖር በሸሹበት መንገድ መራቸው(ቁጥር 12) ፡፡ አሳና ሰራዊቱም ኩሻዊያንን በመከተል ሁሉንም ወታደሮች በመግደል ብዙ ምርኮ ወሰዱ (ቁጥር 13) ፡፡ አሳ ወታደሮቹን በዉጊያ ግንባር ላይ ሲያስቀምጥ በዉጊያዉ እግዚአብሄር እንደ ሚረዳዉ በመጠበቅ ትልቅ እምነት ነበረው፡፡ በተጨማሪም የአሳ ሰራዊትበጌራራ ዙሪያ ያሉትን ከተሞችን በማጥቃት ከተሞቻቸዉን እና የከብቶቻቸዉን ድንኳን በመመዝበርሩ (ቁጥር 14) ከበጎቻቸዉ እና ከግመሎቻቸዉ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ (ቁጥር 15) ፡፡
አሳ በወታደሮቹ ፊት ለፊትለጥቅማቸዉ በእግዚአብሄር ላይ ሊቆም የሚችል ማንም እንደሌለ ማወቁን መሰከረላቸው (አረጋገጠላቸው) ፤ በፀሎቱ (ቁጥር 11) አሳ በእግዚአብሄር የበላይነት ሙሉ እምነቱን በመናገር በድክመታቸዉ እግዚአብሄር እንዲረዳቸዉ ጠየቀ በእርሱም ላይ እንደ ተደገፉ አብራራ ፡፡ በመጨረሻም አሳ እግዚአብሄር በእርሱ ላይ የተነሱብትን ሰዎች አሳልፎ እንደ ሚሰጠው አመለከተ (ቁጥር 14) ፡፡
መደምደሚያ
አሳ እግዚአብሄር ለይሁዳ ሰራዊት እንደ ሚዋጋ ጠብቋል ፡፡ ደባይ ማክዳንኤል እግዚአብሄር ለኛ እደሚዋጋ ዘጠኝ ማንቂያዎችን ይሰጣል፡
- ዘዳ (20፡ 4)፡ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ይሄዳል ፡፡
- ሮሜ (8፡ 31)፡ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ሊቃወመን ይችላል ?
- ኢያ (1፡ 9)፡ ሁል ጊዜ በርታ ጠንክር ፡፡
- መዝ (44፡ 5፣ 23)፡ አትፍራ ፡፡
- ዮሐ (10፡ 10)፡ ጌታ ህይወት ሊሰጠን መጣ ፡፡
- ዘዳ (3፡ 22)፡ አትፍሩ እግዚአብሄር ስለ እናንተ ይዋጋልና ፡፡
- ኢሳ (40፡ 31)፡ እግዚአብሄር ኃይልን እንዲሰጠን እንጠብቃለን ፡፡
- ኢያ (23፡ 10)፡ እግዚአብሄር ስለ እኛ ይዋጋል ፡፡
እግዚአብሄር መሸሸጊያ እና ጠንካራ ጠበቃችን ነው ፤ በዉጊያ ጊዜ ከእኛ ጋር ይሆናል፡
1ቆሮ (15፡ 57)፡ “ ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድል መንሳትን ለሚሰጠን ለእግዚአብሄር ምስጋና ይሁን “ ፡፡
ሮሜ (8፡ 37)፡ “ በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን “ ፡፡
ጦርነቱን አሸንፈናል፤ በድል እንደ ሚጓዝ እንጓዛለን ፤ ይህ የአሳ እግዚአብሄር ስራዉን እንደ ሚሰራለት እና ጦርነቱን እንደ ሚያሸንፍለት አሳብ ነበር ፡፡ በአዲስ ኪዳን አስተሳሰብ ይህን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በማድረግ ዉጊያዉን ያሸነፈበት ስለሆነ በድል መጓዝ ያስፈልገናል ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 503.
Debbie McDaniel, “When Life Is Hard: 9 Reminders that God fights for Us”; available at https://www.crosswalk.com/blogs/debbie-mcdaniel/when-life-is-hard-9-reminders-that-god-fights-for-us.html.
ጥያቄዎች
-
በ 2ዜና መዋዕል (13፡ 5) ንጉስ አብያ ንጉስ ኢዮሮብዓምን የዳዊት ዙፋን ለዘላለም እንደ ነበር አስታወሰው ፤ የአብያ አላማ ምን ነበር ?
-
በ 2ዜና መዋዕል (13፡ 9) ኢዮሮብዓም የእግዚአብሄርን ካህናት በማስወጣት የሌሎች ምድር ሰዎችን የመሰለ እንደ ሚሆን የተነገረው ነበር ፤ እስራኤላዊያን ያሳደዱአቸዉን ህዝቦች የመሰሉ እንደ ሚሆኑ እግዚአብሄር ቀድሞ ምን ነግሯቸዉ ነበር ? (ዘዳ 18፡ 9፣ 28፡ 14-68፣ ኢያ 23፡ 15-16)
-
ንጉስ አብያ እና የእርሱ ሰዎች በእስራኤል ላይ ድል አድራጊ የሆኑት ለምን ነበር ? ከተለመደ ጠላታችሁ ጋር ባላችሁ ዉጊያ ድል ማድረግን እንዴት ማረጋገጥ ትችላላችሁ ? ( 2ዜና መዋዕል 13፡ 18፣ ምሳ 3፡ 5፣ ኢሳ 12፡ 2፣ ኤር 17፡ 7)
-
አሳ የሰለሞን የልጅ ልጅ ነበር ፤ የአሳን በጥበብ መጓዝ እንዴት ታዩታላችሁ ? ጥበብ ከየት ይመጣል ? (2ዜና መዋዕል 9፡ 23፣ ኢዮብ 28-31፣ መዝ 111፡ 10፣ ምሳ 2፡ 6፣ ቆላ 2፡ 2-3)
-
በ 2ዜና መዋዕል (13-14) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Chronicles 14:11
“Then Asa cried out to the LORD his God: ‘LORD, there is no one besides You to help the mighty and those without strength. Help us, LORD our God, for we depend on You, and in Your name we have come against this large army. Yahweh, You are our God. Do not let a mere mortal hinder You.’”
ንጉሥ አሳ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ቅን የሆነውን ነገር አደረገ ፡፡ ከንጉሥ አሳ ጦር እጥፍ የሆነው የኢትዮጵያውያን ጦር በይሁዳ ላይ በተነሳ ጊዜ እንኳ አሳ በእግዚአብሔር ላይ ጸንቶ ነበር ፡፡ አሳ በእምነት ተራመደ ፣ በጣላቶቹ ላይ ወጣ ደግሞም ለጦርነት ተሰለፈ ፡፡ በዚያም ጊዜ “ ኃያላኑንና ደካሞችን ይረዳ ዘንድ ካንተ በቀር ማንም የለም ፡፡ በአንተ ታምነናልና እርዳን ፡፡ “ እግዚአብሔርም ለንጉሥ አሳ ጦር ፍጹም ድልን እንድሁም በተጨማሪ ለተቸገሩት ምርኮን ሰጠ ፡፡
ዛሬ እግዚአብሔር እንድዋጋልህ የምትፈልገው የምን ውጊያ ነው ? ደካማ እንደሆንክ ይሰማሃል ወይስ ዛሬ እንዴት እንደሚቀየር እርግጠኛ አይደለህም ? ትንስ ጊዜ ውሰድና በእግዚአብሔር ላይ በደንብ ታመን ፡፡ ራስህን ዝቅ አድርግ መንገዱንም ተከተል እናም ከክፉ ተመለስ ፡፡ በድካምህ እንኳ እግዚአብሔር ካንተ ጋር ጠንካራ እንደሆነ እመን ፡፡ ውጊያህን ይዋጋልሃል ፡፡ በእምነት መውጣት ወደ ውጊያ ሰልፉም መግባት እግዚአብሔርም እንደሚገኝ ማመን ያስፈልግ ይሆናል ፡፡ በእግዚአብሔር ድልን ታገኛለህ ፤ በእግዚአብሔር አሸናፊ ነህ ፤ በእግዚአብሔር ብቻህን አይደለህም ፡፡ እግዚአብሔር ጠላቶችህን ረምርሞ እንደገና ህይወትህን የተትረፈረፈ ያደርገዋል ፡፡ ዛሬ በፊትህ ያለውን ውጊያ አትፍራ ፤ በውስጥህ ያለው እግዚአብሔር ኃያል ነውና በእምነት ተዋጋ ፡፡
“ አሳም፦ አቤቱ፥ በብዙም ሆነ በጥቂቱ ማዳን አይሳንህም፤ አቤቱ አምላካችን ሆይ፥ በአንተ ታምነናልና፥ በስምህም በዚህ ታላቅ ወገን ላይ መጥተናልና እርዳን፤ አቤቱ፥ አምላካችን አንተ ነህ፤ ሰውም አያሸንፍህ ብሎ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ ። “
- 2ኛ ዜና 14፡11
ተጨማሪ ጥቅስ
- ዘዳግም 20:4 — “ ከእናንተ ጋር የሚሄድ፥ ያድናችሁም ዘንድ ጠላቶቻችሁን ስለ እናንተ የሚወጋ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነውና።
- መዝሙር 44:5 — “ በአንተ ጠላቶቻችንን እንወጋቸዋለን፥ በስምህም በላያችን የቆሙትን እናዋርዳቸዋለን ። “
- 1ኛ ቆሮንቶስ 15:57 — “ ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድል መንሣትን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።