Shishak's Invasion, Rehoboam's Last Days
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Royal Throne 2 Chronicles 11-12 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በ 2ሳሙኤል ዳዊት መሲሁ ከእርሱ እንደሚመጣ፣ ዘላለማዊ መንግስት እና ዘላለማዊ ዙፋን እንደ ሚኖረው ተነግሮት ነበር ፡፡ የዳዊት ፍላጎት ለእግዚአብሄር ቤተ መቅደስ መስራት ነበር ነገር ግን እግዚአብሄር ለዳዊት አይሆንም በማለት ለሰለሞን እሺ አለው ፡፡ በ 2ዜና መዋዕል (1-9) ሰለሞን ቤተ መቅደሱን በመስራት ለ40 አመት በእስራኤል ላይ 40 አመት ገዛ ፡፡ ከንጉስ ሰለሞን መሞት በኋላ መንግስቱ በሮብዓም እንደ ንጉስ በአንድ በኩል (በይሁዳ) ላይ እና በኢዮሮብዓም በሌላ በኩል (በእስራኤል) ላይ እንደ ንጉስ ተከፋፈለ ፡፡
ትምህርት
2-ዜና መዋዕል 11፡ ሮብዓም ከሌሎቹ አስር ነገዶች “ (ከወንድሞቹ) “ ጋር ለመዋጋት ተስፋ ቆረጠ (ቁጥር 4) ፡፡ ሮብዓምም ይሁዳን መሸገ (ቁጥር 5) ሌዋዊያን እና ካህናቶች ከሮብዓም በኩል ወገኑ (ቁጥር 13) ፤ ነገር ግን በቁጥር 15 ሮብዓም ሕዝቡን (የእስራኤልን አስር ነገድ) ወደ ጣዖት አምልኮ እንደ መራ እንማራለን ፤ እዚህ ጋር መንግስቱ በመከፋፈሉ በሁለቱም በኩል ላይ ችግር ስለሆነ በ 2ሳሙኤል 7 ለዳዊት የተደረገዉ ተስፋ ወደ እዉነት እንዲመጣ መልካም አይመስልም ፡፡ ከጊዜ በኋላ ሮብዓም አገባ ልጁን አብያንም እንደ አለቃ ሾመው አደረገዉ ምክንያቱም ንጉስ ሊያደርገዉ ስለ ፈለገ (ቁጥር 18-22) ፡፡
2-ዜና መዋዕል (12፡ 1-4)፡ ሮብዓም በዘመኑ ህጉን በመተላለፍ ለእግዚአብሄር የታመነ አልነበረም (ቁጥር 2) ፡፡ የግብፅ ንጉስ ሺሻቅ ከይሁዳ ጋር ለመዋጋት ሄደ ፤ ከእርሱ ጋር የመጡት ጥቂቶቹ ከሊብያ፣ ሱካዊያን (በርሃ ነገዶች) እና ኩሺቲክ (ብዙ ሰዎች እነዚህኢትዮጲያዊያን ነበሩ ይላሉ) ነበሩ ፡፡ ሮብዓም በይሁዳ የተመሸጉት ከተሞችን ይዘዉ በነበሩት በግብፃዊያን የተቀደመ ሆኖ ነበር ፡፡
2-ዜና መዋዕል (12፡ 5-7)፡ ነቢዩ ሸማያ ሮብዓምን እና የኢየሩሳሌምን መሪዎችን እግዚአብሄር በሺሻቅ እጅ አሳልፎ ሰጥቶአቸዉ እንደ ነበር ነገራቸዉ ምክንያቱም መጀመሪያ እግዚአብሄርን እና ህጉን ትተዉ ስለ ነበር ፡፡ ለእግዚአብሄር እና ለህጉ የታመኑ እስካልሆኑ ድረስ እግዚአብሄር በመካከላቸዉ አያድርም ፡፡ በ 2ዜና መዋዕል (7፡ 13-14) ለዚህ ሁኔታ እግዚአብሄር ሰለሞንን መፍትሄ ሰጥቶታል ፤ ነቢዩምለሮብዓም እርሱ እና ህዝቡ ራሳቸዉን ማዋረድ፣ እግዚአብሄርን መፈለግ እና ከክፉ መንገዳቸዉ መመለስ እንደ ሚያስፈልጋቸዉ ቃልን ነገረው ፤ በ 2ዜና መዋዕል (12፡ 6) ንጉሱና ሁሉም መሪዎች ራሳቸዉን አዋረዱ ፤ ማድረግ ያለባቸዉን በሚገባ አደረጉ ፡፡ እግዚአብሄር ይህን ባዬ ጊዜ ሸማያንእንደ ማያጠፋቸዉ ነገር ግን “ በትንሽ ማዳን “ (ቁጥር 7) እንደ ሚያድናቸዉ ነገረው ፡፡ በዚህ ታሪክ ከተጓዝን በኋላ ተመልሰን በመምጣት ስለ “ በትንሽ ማዳን ” እናወራለን ፡፡ በኃጢዓት ምክንያት “ ትንሽ ማዳን “ ይኖራል ወይም ዉጤት ይኖረዋል ፤ ዉጤቱ ከልተመለሳችሁ እንደ ሚሆነዉ አይሆንም ነገር ግን የኃጢዓታችሁ ዉጤት ይሆናል ፡፡ (ይህ እንዴት እንደ ሚሆን በአንዳንድ ምሳሌዎች እንጓዛለን) ሰዎች ኃጢዓት ባደረጉ ጊዜ በፍፁም ስለ ሚይዙት ዉጤት የለም በማለት ማሳብ ይጀምራሉ ፤ ነገር ግን ሁል ጊዜ ዉጤት አለ ፤ ኃጢዓት ሁል ጊዜ በእናንተ ይያዛል ፡፡
2-ዜና መዋዕል (12፡ 8-12)፡ በዚህ ምሳሌ እግዚአብሄር ሙሉ ቁጣዉን አላፈሰሰም ነገር ግን እግዚአብሄር የሺሻቅ አገልጋዮች እንዲሆኑ ፈቀደ ስለሆነም እግዚአብሄርን በማገልገል እና ሌሎች ህዝቦችን በማገልገል መካከል ያለዉን ልዩነት ይማራሉ (ቁጥር 8) ፡፡ ንጉስ ሺሻቅ ከእነርሱ ዋጋ ያለዉን ሁሉንም ነገር ወሰደ (ቁጥር 9) ፤ የወርቅ ጋሻዎቹን ተሰረቀ ሮብዓም ከነኃስ ጋሻዎችን በመስራት ቤተ መንግስቱን እንዲጠብቅለት ለአዛዡ የሰጣቸዉን - ነገር ግን ቀድሞዉኑ በሺሻቅ ተሸንፈዉ ነበር ፡፡ ይህ ከመቶ አመታት ዘጸዓት በፊት ከግብፅ ጋር የመጀመሪያው ዋና የቶርነት ግጥሚያ ነበር ፤ አሁን እንደ ገና ባርነትን ይቀምሳሉ ፡፡ “ አይሁዶች እዉነተኛዉን የእግዚአብሄርን አምልኮ ከተው የበረከት ጠባቂ እጅንም ያጣሉ “ ፡፡ ሮብዓም ራሱን ቢያዋርድም እንኳንሁሉንም ነገር በማጣት ዉጤት ይመከራል - ንብረቱን አጣ ፤ “ ከዚያ ጎን ለጎን ሁኔታዎቹ በይሁዳ መልካም ነበሩ “ (ቁጥር 12) ፡፡
2-ዜና መዋዕል (12፡ 13-14)፡ ሮብዓም በኢየሩሳሌም እንደ ንጉስ ለ17 አመታት ገዛ ፡፡ እናቱ አሞናዊቱ ናዕማ ነበረች (ቁጥር 13) እግዚአብሄርንም ባለመፈለግ ክፉ ነገር አደረገ (ቁጥር 14) ፤ ወደ ኃላ 2ዜና መዋዕል (7፡ 14) ላይ ስንመለከት ሮብዓም ራሱን አዋርዷል ነገር ግን እግዚአብሄርን ባለመፈለግ ከክፉ መንገዱ አልተመለሰም ፡፡ ሮብዓም በኃጢዓት ሲያወሳ በከፊል ነበር የተዘዘዉ - ለማቆም በቃኝ በማለት የሚፈልገዉን ለማድረግ ቀጠለ ፡፡ እግዚአብሄር የተገለጠለትም ቢሆንም እንኳን ሮብዓም እግዚአብሄርን በመፈለግ አልቀጠለም ፡፡ ሮብዓም በዚህ ዉጊያ ዉስጥ ሚና እንደ ሚጫዎት ያዉቃል ነገር ግን ወደ ክፉ መንገዱ ተመልሶ ሄደ ፡፡ በእግዚአብሄር ይህን በምናደርግ ጊዜ በክርስቶስ ፊት ላይ ጥፊ(መማታት) ነው - ለእኛ በመስቀሉ የተደረገዉ ዋጋ የለዉም እያልን እንደ ሆነ ነዉ የሚመስለው ፡፡ ስለዚህ በዚህ እምነት ለመጓዝ እንዴት እንቀጥላለን (እንሄዳለን) ? በዚህ ታሪክ ሮብዓም ግማሽ አማኝ ይመስል ነበር ፡፡ ለፈጣን ፍላጎት ራሱን ያዋርዳል ነገር ግን እግዚአብሄር የመከተለ ኃሳብ አልነበረውም ፡፡
2-ዜና መዋዕል (12፡ 15-16)፡ በዘር ግንዱ መካከል በሮብዓም ዘመን ያሉ ክስተቶች ተመዝግበዋል ፡፡ ሮብዓም እና ኢዮሮብዓም ሁለቱም በገዙበት ዘመን በጦርነት ቆዩ ፡፡ ሮብዓም በሞተ ጊዜ መንግስቱ ወደ ልጁ አብያ ተላለፈ ፤ በ 1ነገ (15፡ 3) አቢያ እንደ ታላቅ ኃጢዓተኛ ተገልፆ ነበር ፤ ከእነርሱ ዉስጥ ለንጉሳዊ ዙፋን ዘር መሆን የሚችል የሚመጥን የለም ነገር ግን ያ የእግዚአብሄር መንገድ ዉብ ስራ ነው ፡፡ ብቃት ባይኖረንም፣ ኃጢዓተኛች ብንሆንም፣ ህጉን ብንተዉ እና ለእግዚአብሄር የምንታመን ባንሆንም እግዚአብሄር ይሰራል ፡፡ ከታላቅ ኃጢዓት የተጠራን ቢሆንም እንኳን እግዚአብሄር ለክብሩ ሊጠቀምብን ይችላል ፡፡
ወደ ዳዊት በመመለስ በኃጢዓት ዉጤት ዉስጥ እንነጋገር (እንሂድ) ፤ ሁል ጊዜ ዳዊትን እንደ ጥቂት ፍፁም ሰዎች እንስለዋለን ነገር ግን ዳዊት ከዛ የራቀ ነው ፡፡ በእርግጥዳዊት እንደ አንድ አመንዝራ የተሰየመ(በቤርሳቤህ ጉዳይ) እና እንደ አንድ ገዳይ (ከኃያላኖቹ ሰዎች አንዱ ኬጢያዊዉን ኦሪዮን በመግደሉ) የተሰየመ ነበር ፡፡ በ 2ሳሙኤል 7 ዳዊት ሰዉዬዉን ሞት እንደ ሚገባዉ አንድ ሰዉ በናታን ታሪክ ገልፆታል ፤ ነገር ግን በ 2ሳሙ (12፡ 13) ናታን እግዚአብሄር የዳዊትን ኃጢዓት ስለወሰደ አይሞትም አለ ፤ ነገር ግን ዉጤት ነበረው፡ ከቤርሳቤህ ጋር በነበረዉ ጉዳይ የሚመጣዉ ወንድ ልጅ ይሞታል (ቁጥር 14) ፡፡ ለፈፀምናቸዉ ኃጢዓቶች ዉጤት አላቸው ፡፡
ደርክ ሄል የኃጢዓትን ዉጤት ዝርዝር ሰጥቷል ፤ መጀመሪያ ኃጢዓት በምታደርጉ ጊዜ ከእግዚአብሄር ወደ መለየት ይመራችኋል ፤ ኢሳ (59፡ 2) የሚለዉ ኃጢዓታችን በእኛና በእግዚአብሄር መካከል መለያዎችን (መሰናክሎችን) እንደሚሰራ ይናገራል ፤ ሮሜ (3፡ 23) ሁሉም ኃጢዓትን ሰርተዋል ከእግዚአብሄር ክብርም ወድቀዋል ይላል ፡፡ ኃጢዓት ከእግዚአብሄር ይለየናል ፡፡
ሁለተኛ ለእናንተ በፍጥነት ጉዳት የሚያመጣባችሁ ነው ፡፡ በዘፍጥረት 19 እግዚአብሄር ሰዶም እና ገሞራ ላይ ፍርድ ባመጣ ጊዜ መለዓክቶቹ በግልፅ ሎጥንና ቤተሰቡን ከከተማዋ ሲወጡ ወደ ኃላ እንዳይመለከቱ ነገሯቸው ፤ ነገር ግን የሎጥ ሚስት ወደ ኃላ ከተማዋን ስለ ተመለከትች ወደ ጨዉ አምድ ተቀየረች (ዘፍ 19፡ 26) ፡፡
ሰዎስተኛ ኃጢዓት በሌሎች ላይ ጉዳት ሊያመጣ ይችላል ፤ በማቴ (2፡ 16) ንጉስ ሄርዶስ በሰብዓ ሰገል(በጥበበኞቹ) ሰዎች ዘዴኛ ሆኖ ስለ ነበር በቁጣ በቤቴ ልሄም ሁሉም ህፃን ወንድ ልጅ እንዲጨፈጨፍ አዘዘ ፡፡ ሌሎች ሰዎች በሄርዶስ ኃጢዓት ዉጤት ችግር ይገጥማቸዋል ፡፡ ሮብዓም የሽማግሌዎችን ምክር ለማዳመጥ እምቢ ባለ ጊዜ የእስራኤል ነገድ ተከፈለ (ተለየ) ፤ ሮብዓም ህጉን በመተዉ እና ለእግዚአብሄር ባለመታመኑ ህዝቡ ለሺሻቅ ባሪያዎች ሆኑ ፡፡
አራተኛ ኃጢዓት ለተጨማሪ ኃጢዓት እንደ አቀጣጣይነት ያገለግላል ፤ አንዱ ኃጢዓት ወደ ሌላዉ ይመራል ምክንያቱም በሌላኛዉ መንገድ በኩል የተሻለ አለ ብላችሁ ስለ ምታስቡ በፍፁም አትረኩም ፡፡ ሮሜ (6፡ 23) የኃጢዓት ደሞዝ ሞት ነዉ ይላል ፤ ኃጢዓት ትልቅ ጉዳይ(ነገርን) ይፈጥራል ፤ እግዚአብሄር ሊሸከመዉ(ሊያሸንፈዉ) የማይችል እግዚአብሄር ይቅር ሊለዋ ከሚችለዉ በላይ የሚበልጥ ኃጢዓት የለም ፡፡ ሮሜ (6፡ 23) የእግዚአብሄር ስጦታ በክርስቶስ ኢየሱስ የዘላለም ህይወት እንደ ሆነ ያረጋግጣል ፡፡ ኃጢዓት ወደ ሞት ቢመራም ኢየሱስ የኃጢዓትን ዉጤት ሁሉ አስወግዶታል(ከኛ ወስዶታል)፡ መለየትን፣ በራስ እና በሌሎች ላይ ጉዳት ማምጣትን፣ ለተጨማሪ ኃጢዓት ማነሳሳቱን(ማቀጣጠሉን)፣ ዘላለማዊ ሞትን ፡፡ በኢየሱስ በምናምን እና ባለን ነገር ሁሉ በምንከተለዉ ጊዜ ይህን ነፃ ስጦታ መቀበል እንችላለን ፡፡
መደምደሚያ
ኃጢዓት በሰራችሁ ጊዜ ምን ታደርጋላችሁ ? 2ዜና መዋዕል ( 7፡ 14) የብሉይ ኪዳንን ሃሳብ ይሰጣል ፤ የብሉይ ኪዳን አስተሳሰብ እነዚህን ነገሮች ለእግዚአብሄር በመናዘዝ ምህረት የሚደረግላችሁ ትሆናላችሁ ይላል ፡፡ ቻርለስ ስታንልይ ለዚህ ሂደቱን ይገልፃል፡
- ለኃጢዓታችሁ ኃላፊነትን መዉሰድ ፡፡
- ኃጢዓትን መናዘዝ እና ንስኃ መግባት ፡፡
- ስለ ሚያመጣዉ ዉጤት ቅሬታ አታቅርቡ(አታጉረምርሙ) ፤ ዕብ (12፡ 6) ጌታ የሚወዳቸዉን ይቀጣቸዋል፡፡
- ወደ ህይወታችሁ ዉስጥ ፍጭት የሆነዉን ድክመታችሁን እንድታገኙት እግዚአብሄር እንዲረዳችሁ መጠየቅ፡፡
- በህይወታችሁ ዉስጥ መከራዎችን እግዚአብሄር ሊጠቀምባቸዉ እንደ ሚፈልግ ማስተዋል፤ ከዚህ በመማር ተመልሳችሁ ወደ ነገሩ እንዳትሄዱ ፡፡
- ኃጢዓታችሁን ስለ ገለጠላችሁ እግዚአብሄርን ማመስገን ፡፡
ሮብዓም ግማሹን መንገድ ብቻ ሄደ ምናልባትም ሰዎስተኛዉን ብቻ ፡፡ ትግላችን ሁሉንም መንገድ መጓዝ ነው ፤ ከኃጢዓታችን በመመለስ እግዚአብሄርን ስንፈልግ በእያንዳንዱ እና በሁሉም ቀን እርሱን በብዙ እንመስላለን ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 502.
MacArthur, p. 411.
Derek Hill, “5 Biblical Consequences of Sin”; available from https://www.whatchristianswanttoknow.com/5-biblical-consequences-of-sin/.
Charles Stanley, “The Consequences of Sin,” available from https://www.intouch.org/Read/the-consequences-of-sin.
ጥያቄዎች
-
በሞኝነት ምርጫዉ ምክንያት ተከፍሎ የነበረውን መንግስቱን ለመመለስ ሮብዓም ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት ወጣ ፤ ይህ እንዳይሆን ለመጠበቅ እግዚአብሄር ምን አደረገ (2ዜና መዋዕል 11፡ 4) ? በክርስቶስ ከወንድሞቻችን እና ከህቶቻችን ጋር እንድንዋጋ ምክንያቶቹ ምንድን ናቸው (ያዕ 3፡ 16፣ 4፡ 1-2) ?ኢየሱስ ከሌሎች አማኞች ጋር ስለ ሚኖረን ግንኙነቶች ምን ይላል ? (ዮሐ 13፡ 34-35)
-
በአስሩ ነገዶች እና በይሁዳና በብንያም ነገዶች መካከል ባለዉ መከፋፈል ምክንያት ለመከላከል ንጉስ ሮብዓም ምን አደረገ (2ዜና መዋዕል 11፡ 5፣ 11-12) ? አንዱን በሌላዉ ለመከላከል ምን አይነት መከላከል አስቀምጠናል ?
-
ንጉስ ሮብዓምና ይሁዳ በዳዊት እና በሰለሞን መንገድ ለምን ያክል አመት ተጓዙ (2ዜና መዋዕል 11፡ 17) ? የእግዚአብሄርን ህግ መቼ ተዉ (2ዜና መዋዕል 12፡ 1) ? እግዚአብሄር እንዴት ምላሽ ሰጠ ?
-
2 ዜና መዋዕል (12፡ 8) አንብቡ ፤ በግል አስተያየታችሁ እግዚአብሄርን በማገልገል እና “ ነገስታትን “ በማገልገል መካከል ልዩነቱ ምንድን ነው ? (ሮሜ 7፡ 6፣ ገላ 5፡ 13፣ ቆላ 3፡ 23-24፣ 1ተሰ 1፡ 9-10)
-
ንጉስ ሮብዓም እንደ ካህናት እግዚአብሄርን ከማገልገል ሌዋዊያንን ስላላካተታቸው የግጦሽ ምድራቸዉን እና ንብረቶቻቸዉን በመስጠት ወደ ይሁዳ ተጓዙ ፤ ከነበራቸዉ ሁሉም ነገር መሄዳቸዉ ይህ ለምን አስፈላጊ ነበር ? ጥሪያችሁን ለመፈፀም መቼ እና እንዴት ነገሮችን ትሰጣላችሁ ?
-
በ 2ዜና መዋዕል (11-12) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Chronicles 12:7
“When the LORD saw that they had humbled themselves, the LORD’s message came to Shemaiah: ‘They have humbled themselves; I will not destroy them but will grant them a little deliverance. My wrath will not be poured out on Jerusalem through Shishak.’”
ንጉሥ ሮብዓምና መሳፍንቱ እግዚአብሔር የተዋቸው ለእርሱ ስላልታመኑ ፣ ህጉንም ስለተው እንደሆነ በሰሙ ጊዜ ራሳቸውን በፊቱ አዋረዱ ፡፡ ነገር ግን እነርሱ አልጸለዩም ፣ ፊቱን አልፈለጉም ወይም እግዚአብሔር ቀድሞ ለህዝቡ እንዳዘዘው ከክፉ መንገዳቸው አልተመለሱም ፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር ትንስ ደህንነትን ብቻ ሰጣቸው ፡፡ በኋላም ሮብዓም ክፉ የሆነውን እንዳደረገ ታሪክ ጸሀፊያኑ ጽፈዋል ፡፡ ረሱን በጥቂቱ አዋርዶ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ፈጽሞ ራሱን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር አሳልፎ አልሰጠም ልቡንም ከክፉ ነገር አልመለሰም ፡፡ ሰለዚህም ንጉሥ ሮብዓም የኃጢአቱን ውጤት ተቀበለ ፡፡
እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ያያል ልብህንም ያወቃል ፡፡ ሁሉንም ኃጢአትህን እንድትናዘዝ ይጠይቅሃል ፡፡ ኃጢአትህንም ሁሉ ይቅር እንደሚልህ ተናግሮሃል ፡፡ ግማሽ ነገር እንዳታደርግ አለበለዚያ ትንስ ደህንነትን ብቻ ነው ምታገኘው ወይም ወደ ቀድሞው መንገድህ ተመልሰህ መውደቅህ አይቀርም ፡፡ እግዚአብሔር በሙሉ ልብህ እንድትጸልይና እንድትፈልገው ይነግርሃል ፡፡ ለእግዚአብሔር ልብህን ፣ ፈተናዎችህን ፣ ፍርሃቶችህን ፣ ደስታህንና ህልሞችህን ስጠው ፡፡ ሁሉንም አሳልፈህ ስጠው ፤ እርሱን እመነው ፡፡ ፊትህን ከእግዚአበሔር ካልሆኑ ነገሮች መልስ ፡፡ ከኢየሱስ ጋር መራመድ ጀምር እርሱም መንገድህን ያቀናልሃል ፤ በክርስቶስም በሚሆን ሙሉ ደህንነትና ሙሉ ነጻነት ይመራሃል ፡፡
“ እግዚአብሔርም ሰውነታቸውን እንዳዋረዱ ባየ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል፦ ሰውነታቸውን አዋርደዋል፤ አላጠፋቸውም፤ ከጥቂት ቀንም በኋላ አድናቸዋለሁ፥ ቍጣዬም በሺሻቅ እጅ በኢየሩሳሌም ላይ አይፈስስም “
- 2ኛ ዜና 12፡7
ተጨማሪ ጥቅስ
2ኛ ዜና 7:14 — “በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፥ ፊቴንም ቢፈልጉ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፥ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ ። “
ምሳሌ 28:13 — “ ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል ።
ሮሜ 10:9 — “ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።