Historical Books 2 Chronicles

The Fulfillment of Prophecy in Jeroboam

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Royal Throne 2 Chronicles 9-10 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 306 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

2 ዜና መዋዕል ተመሳሳይ መፀሀፍት ደግመን ደግመን እንደምናነብ ሊሰማን ይችላል ፡፡ በዚህ ቆይታችሁ ከድግግሞሽ ዉጪ እግዚአብሄር አዲስ ነገር እንዲያስተምራችሁ ለእግዚአብሄር እንድትፈቅዱለት አበረታታችኋለሁ ፡፡ 2 ዜና መዋዕል የ 1ዜና ዋዕል ቀጣይ በመሆን ለመፅሀፉ ጭብጥ ወደ ሆነዉ ንጉሳዊ ዙፋን ተጓዝ (2ዜና መዋዕል 7፡ 18) ፡፡ ለዳዊት ተስፋ ተገብቶለት የነበረዉ በልጁ በሰለሞን ተሄዶበት የነበረዉ ነው ፤ በ 2ዜና መዋዕል 9 ንግስት ሳባ ሰለሞንን ጎበኘች (ቁጥር 11-12)፣ ሰለሞን የጦር መርከቦችን ገነብቷል (ቁጥር 10-11, 12) እንዲሁም ሰለሞን ኃብትን እና ዝናን አግኝቷል (ቁጥር 13-28) ፤ ይሁን እንጂ በቁጥር 30 እና 31 ሰለሞን ሞተ ሮብዓምም እንደ ንጉስ ተካው (ቁጥር 31) ፡፡ በእስራኤል ነገስታት የተፈጠረዉ ነገር ምንም ቢሆን ንጉሳዊ ዙፋኑ ቀጠለ ፡፡ የይሁዳ(የደቡብ) ንጉሳዊ ዙፋን ከዳዊት ወደ ሰለሞን ከዚያም ወደ ዮሮብዓም የተላለፈ ነበር ፤ እዚህ ጋር የእስራኤል ነገስታቶች እስካሁን በስዕሉ አልነበሩም ፡፡

ትምህርት

2-ዜና መዋዕል (10፡ 1-7)፡ የሰለሞን ልጅ ሮብዓም በሴኬም ላይ ንጉስ ተደረገ (ዘፍ 12፡ 6-7፣ 35፡ 4፣ ኢያሱ 24) ፤ ዮሮብዓም ከሰለሞን ሸሽቶ ነበር ምክንያቱም በአንድ ትንቢታዊ ቃል (1ነገ 11፡ 26-40) ነገር ግን ከሰለሞን ሞት በኋላ ለመመለስ ተሰማዉ (ቁጥር 2) ፡፡ ሮብዓም ኢዮሮብዓምን እና ሁሉም እስራኤል ወደ ሴኬም ሰበሰባቸው (ቁጥር 3) ፡፡ ኢዮሮብዓም ለሰሜኑ ነገዶች በመናገር ዮሮብአምን ንጉስ ሰለሞን በእነርሱ ላይ አስቀምጦት የነበረዉን ከባድ ቀንበር ካቀለላቸው እንደ ንጉስ እንደ ሚቀበሉት ነገረው (ቁጥር 4) ፤ ከባዱ ቀንበር የሚያስፈልጉትን ሰራተኞች እና ግብርን ያከተተ ነው ፡፡ ይህ ለእርቅ እድል ነበር ፡፡ ሮብዓም ለመልሱ ከሰዎስት ቀን በኋላ ተመልሰዉ እንዲመጡ ነገራቸው (ቁጥር 5) ፡፡ ሮብዓም በምክራቸዉ ሰለሞንን ያገለግሉት የነበሩ አማካሪ ሽማግሌዎችን አማከረ (ቁጥር 6-7) ፤ ነገሮችን ለማድረግ አማካሪዎችን መፈለግ ጥሩ ነገር ነበር ፤ ሌሎች ነገስታቶች አማካሪዎችን የተመለከቱ፡ ዳዊት (1ዜና መዋዕል 13፡ 1-9), ኢዮሳፍጥ (2ዜና መዋዕል 20፡ 21) እና ሕዝቅያስ (2ዜና መዋዕል 30፡ 2፣ 32፡ 3) ፡፡

2-ዜና መዋዕል (10፡ 8-15)፡ ነገር ግን ሮብዓም ለሰሜኖቹ ነገዶች መልካም የሚሆነዉን ምክር ለመስማት አልመረጠም ይልቁንም ከእርሱ ጋር አድገዉ ወደ ነበሩት ወጣት ሰዎች ምናልባትም የሱ “ ተመሳሳይ ሰዎች “ 40 አመት ወደ ሚሞላቸው ተመለሱ (ቁጥር 8-9) ፡፡ እነዚህ ልምድ የሌላቸዉ ወጣቶች ሮብዓምንበሰሜን ነገዶች ላይ ጫናዉን በመጨመር በከባድ ጫና እንዲቀጣቸዉ እና በሹል ጅራፍ እንዲቀጣቸዉ ነገራቸው (ቁጥር 10-11) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ የሮብዓምን ጅራፍ ከተቀጣ ሰዉነት ላይ ስጋን በማንሳት ለከፍተኛ ህመም ምክንያት የሚሆን በቆዳ ዘለላ ዉስጥ ትንሽዬ ብረት እንደ ነበረዉ አንድ አልንጋ ይገልፃዋል ፡፡ በሰዎስት ቀን የእስራኤል ሰዎች በተመለሱ ጊዜ ሮብዓም ዉሳኔዉን ነገራቸው (ቁጥር 12-14) ፡፡ ቁጥር 15 ሰለሞን ዮሮብዓምን ሊገድለዉ እንደ ሞከረ ይገልፃል ምክንያቱም ትንቢታዊ ቃሉ ሁሉም ዮሮብዓም ወስኖት የነበረው በፊት ተነግሮ የነበር እንደ ነበር ስለ ሚናገር (ቁጥር 15) ፡፡ ትንቢቱእግዚአብሄር ከሰለሞን ልጅ አስሩን ነገድ በመዉሰድ እንደ ንጉስ እንዲአስተዳድራቸዉ ለኢዮሮብዓም እንደሚሰጠው ተናግሯል (1ነገ 11፡ 28-38) ፡፡ ማክአርቱር “ እግዚአብሄርበሙሉነት የሮብዓምን ሞኝነት የኤልያስን ትንቢት ለመፈፀም እንደ ተጠቀመበት “ ይናገራል ፡፡ ይሁዳ ወደ አዲሱ እስራኤል 10 ነገዶችን በማጣቱ ተዋረደ ነገር ግንእግዚአብሄር ዉርደታቸዉ ለዘላለም እንደማይቆይ ተስፋን ሰጣቸው (1ነገ 11፡ 39) ፡፡

2-ዜና መዋዕል (10፡ 16-19)፡ የእስራኤል ሰዎች (አስሩ ነገዶች) ከሮብዓም መልስ ከዳዊት ርስት እንደሌላቸዉ እና በራሳቸዉ መንገድ መሄድ እንዳለባቸው ተረዱ (ቁጥር 16-17) ፡፡ ሁሉም በአንድ ድምፅ ስለ መዘመራቸዉ ያወራንበትን ጊዜ እናስታዉስ ? በአጭር ጊዜ ያ አንድነት ጠፋ መንግስቱም የተከፋፈለ ሆነ ፡፡ ሮብዓም በእስራኤል ህዝብ ላይ በማስፈራራት እንዲከተሉት በመሞከር ወደ ሰሜን ተገደዉ የሚሰሩትን (የጉልበት) ሰራተኞችን የሚያስገብራቸዉን አዶራምን ላከው ፤ የእስራኤል ሰዎች አዶራምን እስኪሞት ድረስ ወግረዉ በገደሉት ጊዜ ሮብዓም በመሸሽ በሰላም ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ (ቁጥር 18) ፡፡ የእስራኤል ህዝቦች በሮብዓም እና ይሁዳ ላይ አምፀዉ ቀሩ (ቁጥር 19) ፡፡ ሮብዓም በመንግስቱ አንድነትን የመጠበቅ እድል ነበረዉ ነገር ግን በድርጊቱ ተፅኖ እንዲያደርጉ ለስግብግብነትና ለትዕቢት ፈቀደ ፡፡

ማርቲን ሰልማን ይህ መከፋፈል ምን እንደሚመስል ይገልፃል፡

  1. ሮብዓም መንግስቱን እንዲለቁ ለፈቀደላቸዉ ለአብዛኞቹ ነገዶች “ ለመላው እስራኤል “ በይሁዳ ዉስጥ ባሉት ላይ በጣም ያተኮረ ነበር (ቁጥር 16) ፡፡
  2. “ እስራኤላዊያን “ የሚለዉ ሐረግ የህዝቡን አንድነት በአንድ ላይ የጠበቀ ሁሉንም አይሁዶችን እና እስራኤልን ለመጥቀስ የተጠቀመ ነበር (ቁጥር 17) ፡፡
  3. ወደ ሁለት ህዝብ መከፋፈላቸው የእስራኤልን ህዝብ እና የዳዊትን ቤት ይጠቅሳል (ቁጥር 16, 19) ፡፡
  4. አዲስ ህዝብ ለመሆን የእስራኤል ሰዎች ጥሪ ለንጉስ ዳዊት ተሰጥተዉ ከነበሩት የእስራኤል ህዝቦች ሙሉ የተቃረነ ነበር (ቁጥር 16) ፡፡
  5. “ በየድንኳኖቻቸው በፊት እያንዳንዳቸው በተጨማሪ ከዳዊት መንግስት ለመለየት እያንዳንዳቸዉን ጋበዛቸው “ ፡፡

በዚህም ሮብዓም መዋቅሩን እና መስመሩን አጥቶ ነበር ፡፡ ራሱንም በመጥፎ ባልንጀርነት አስከበበ “ ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል “ (1ቆሮ 15፡ 33) ፤ ሮብዓም የእግዚአብሄርን ምሪት በመስማት አልቀጠለም ይልቁንም የወጣት “ ሞኞች” ቡድንን ተማመነ (ምሳ 13፡ 20) ፡፡ ምሳ (18፡ 24) የሚለው “ ብዙ ወዳጆች ያሉት ሰዉ ይጠፋል ፤ ነገር ግን ከወንድም አብልጦ የሚጠጋጋ ወዳጅ አለ “ ፡፡

መደምደሚያ

ምክር ለእናንተ በተሰጣችሁ ጊዜ ከእግዚአብሄር መሆኑን እና አለመሆኑን እንዴት ታዉቁታላችሁ ? ደባይማክዳንኤል “ በበጎች ልብስ የሆነን አንድ ተኩላን መለያ አምስት መንገዶችን ያስቀምጣል(ያመለክታል) “፡

መጠንቀቅ ( ማቴ 7፡ 15፣ 1ቆሮ 16፡ 13)፡ በዙሪያችሁ ስላሉት (ባሉት) የተጠነቀቃችሁ ሁኑ ፡፡

እዉነቱን እወቁ ከዚያም ዉሸቱን ታዉቁታላችሁ (ማቴ 7፡ 16፣ 1ቆሮ 4፡ 5)፡ ማን እዉነተ ማን ደግሞ ዉሸት እንደ ሆነ በፍሬአቸዉ ታዉቋቸዋላችሁ ፡፡

የእግዚአብሄርን ቃል እወቁ (ማወቅ) ከዚያም የተጠመዘዘ ወይም የተጣመመ ሲሆን ታዉቁታላችሁ (መዝ 199፡ 11, 2ቆሮ 11፡ 14-15)፡ የእግዚአብሄር ቃል ምን እንደሚል ካላወቃችሁ አንድ ሰዉ እግዚአብሄር እንደ ማይፈልገዉ አይነት ነገር ለማለት ቀላል ይሆናል ፡፡

በእናንተ ዉስጥ በሚኖረው የእግዚአብሄር መንፈስ መለየትን እና ጥበብን እመኑ (ማቴ 24፡ 23-25፣ ዮሐ 16፡ 13)፡ የእግዚአብሄር የሆነዉን እና ያልሆነዉን ለመለየት እንዲረዳን በመንፈስ ቅዱስ ላይ መደገፍ እንችላለን ፡፡

በምታምኑዓቸዉ እና በምታዉቋቸው በሌሎች አማኞች ራሳችሁን አስከብቡ (ምሳ 11፡ 14, 2ጴጥ 3፡ 3)፡ ልታደምጧቸዉ ፍቃደኛ የምትሆኑት ሰዎች መፅኀፍ ቅዱሳዊ መመሪያ በማቅረብ በህይወታችሁ የሚናገሩ ስለ መሆናቸዉ እርግጠኞች መሆን አለባችሁ ፡፡

መጥፎ ወዳጅነትሁል ጊዜ በሚባል ደረጃ መልካሙን ፀባይ እና ባህሪይ ያበላሻል ፡፡ ሮብዓም እግዚአብሄር የመሰረተዉን የማየት ዘዴን አጣ ፤ ምክንያቱም በእስራኤል ላይ ያለ አግባብ ስልጣን ለመያዝ የፈለጉትንወጣት ወንዶች በድን ስለሰማ ነገዶቹ በመለያየት አንድነታቸዉን አጡ ፡፡ በአሁኑ ጊዜም እንኳን በዚህ እንመካከራለን (እንነጋገራለን ) ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 411.

  2. MacArthur, p. 411.

  3. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds. Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 545.

  4. MacArthur, p. 411,

  5. Martin J. Selman, Tyndale Old Testament Commentary: 2 Chronicles (Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 1994), p. 364.

  6. Debbie McDaniel, “Five Ways to Recognize a Wolf in Sheep’s Clothing”; available at https://www.crosswalk.com/faith/spiritual-life/5-ways-to-recognize-a-wolf-in-sheep-s-clothing.html.

ጥያቄዎች

  1. ወደ እምነታችሁ ስታመጡት ራሳችሁን በምን መንገድ እንደ ንግስት ሳባ ታገኙታላችሁ ? (2ዜና መዋዕል 9፡ 5-6)
  2. በንጉስ ሰለሞን እና በንጉሱ ኢየሱስ መካከል ሌሎች ጥቂት አንድነቶች ምንድን ናቸው ?
  3. 666 የሚለዉ ቁጥር በአንድ አመት ለሰለሞን በመጣ በወርቅ ክብደት የተጠቀሰ ነው ፤ ይህ ቁጥር በመፅሀፍ ቅዱስ ሌላ የት ላይ የተጠቀሰ ነው በሁለቱ ጥቅሶችስ መካከል ዝምድና አለዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? (ራዕ 13፡ 16-18)
  4. 2ዜና መዋዕል (10፡ 15) ለአሒያ የነገራቸዉን ከእግዚአብሄር ስላዞሮ ክስተቶች ያወራል ፤ ይህ ጥቅስ ምን እየገለፀ ነበር ? (1ነገ 11፡ 9-13)
  5. በ 2ዜና መዋዕል (9-10) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Chronicles 10:13–14

“Then the king answered harshly. King Rehoboam rejected the elders’ advice and spoke to them according to the young men’s advice, saying, ‘My father made your yoke heavy, but I will add to it; my father disciplined you with whips, but I, with barbed whips.”

ከሰሎሞን የአርባ አመት ንግሥና በኋላ ሮብዓም በእስራኤል ላይ ነገሠ ፡፡ ህዝቡም ጽኑው አገዛዝና የከበደው ቀንበር ይቀልላቸው ዘንድ ለነገሠው ለአድሱ ንጉሥ ጠየቁ ፡፡ ንጉሥ ሮብዓምም ውሳኔውን ለመወሰን እንድረዳው ምክርን ለመቀበል ሶስት ቀን ወሰደ ፡፡ መጀመሪያ አባቱን ያገለግሉ ከነበሩ አባቶች ጋር ተማከረ እናም ከዚያ ከአቻዎቹ ከአብሮ አደግ ጓደኞቹ ጋር ተማከረ ፡፡ በመጨረሻም የብላቴኖቹን ምክር ሰምቶ የእስራኤልን ህዝብ ለሁለት የከፈለ የተሳሳተ ውሳኔን አደረገ ፡፡

ውሳኔን መስጠት በሚያስፈልግህ ጊዜ ምንድን ነው ምታደርገው ? አስተውል ፣ ተረጋጋ ፣ ጊዜ ውሰድ እናም እግዚአብሔርን ፈልግ ፡፡ በቀንና በማታ በእርሱ ደስ ሲልህ እርሱ ረዳትህ እንደሚሆን ተናግሯል ፡፡ ብዙ ጊዜ እግዚአብሔር ምክር እንድትሰማ ይመራሃል ፡፡ ሆኖም ግን ለምክር ፊትህን ወደ ማን እንደምትመለስ ተጠንቀቅ ፡፡ ንጹህ ልብ ያለው እግዚአብሔርን በመታመን የሚያገለግል ሰው ፈልግ ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ምክር ሊሰጡህ ይችላሉ ነገር ግን እነርሱ ራስ ወዳድ ወይም ትምክህተኛ የሆነ ፍላጎት ይኖራቸው ይሆናል ፡፡ አንዳንዶች አንተ ከምትለው የተለየ ነገር የላቸውም ጥሩ ምክር አይሰጡህም ፡፡ ምክርን ስትሰማ እግዚአብሔር እንድረዳህ ጸልይ እናም ወስን ፡፡ በሁሉም ነገር በእርሱ ለሚታመኑ ነገር ሁሉ ተያይዞ ለበጎ እንደሚደረግ እግዚአብሔር ተናግሯል ፡፡ እርዳታን ለማግኘት ስትጮህ ይሰማሃል ፈጽሞ አይተውህም ፡፡

“ ንጉሡም ጽኑ ምላሽ መለሰላቸው፤ ንጉሡም ሮብዓም የሽማግሌዎቹን ምክር ትቶ ፦ አባቴ ቀንበር አክብዶባችሁ ነበር፥ እኔ ግን እጨምርበታለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገርፎአችሁ ነበር፥ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ ብሎ እንደ ብላቴኖቹ ምክር ተናገራቸው ። “

—2ኛ ዜና 10:13–14

ተጨማሪ ጥቅስ

  • መዝሙር 1:1-2 — “ ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል ። “
  • ምሳሌ11:14 — “መልካም ምክር ከሌለ ዘንድ ሕዝብ ይወድቃል፤ በመካሮች ብዛት ግን ደኅንነት ይሆናል ። “
  • 1ኛ ዮሐንስ 4:1 — “ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና ። “