"If My People..."
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Royal Throne 2 Chronicles 7-8 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ትናትና ቤተ መቅደሱ በሰለሞን ከተጠናቀቀ በኋላ መለየቱን (መቀደሱን) ተመልክተናል ፡፡ ህዝቡ እናመሪዎቹ በአንድ ላይ በበምጣት በአንድ ድምፅ ቤተ መቅደሱን ቀደሱት ፡፡ ለአንድ ምክንያት ህዝቡ - ሁሉም የእስራኤል ነገድ በአንድ ድምፅ አንድ ሆኑ ፡፡ ምዕራፍ 6 በመቀደሱ ላይ የሰለሞንን ፀሎት ይይዛል ፡፡ ምዕራፍ 7 በመቀደሱ ጊዜ የተካሄዱትን አከባበሮች(ስርዓቶች) ላይ ይሰራል ፡፡ በጣም የሚታወቀዉ ጥቅስ በ 2ዜና መዋዕል ከምዕራፍ 7 ይመጣል፡ “ በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰዉነታቸውንአዋርደው ቢጸልዩ ፊቴንም ቢፈልጉ ከክፉ መንገዳቸዉም ቢመለሱ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ ኃጢዓታቸዉንም ይቅር እላለሁ ምድራቸዉንም እፈዉሳለሁ “ (ቁጥር 14) ፡፡ በምዕራፍ 7 በጥናታችን ላይ እንቀጥላለን (ሉቃ 2፡ 25) ፡፡
ትምህርት
2-ዜና መዋዕል (7፡ 1-7)፡ ከሰለሞን ፀሎት በኋላ እሳት ከሰማይ በመምጣት መስዋዕቱን እና ቁርባኑን በላች ቤተ መቅደሱንም የእግዚአብሄር ክብር ሞላዉ (ቁጥር 1) ፡፡ ይህ እሳት ከሰማይ የመጣበት የመጀመሪያዉ ጊዜ አልነበረም (ዘሌ 9፡ 23-24፣ መሳ 6፡ 21፣ 1ነገ 18፡ 38) ፤ እግዚአብሄር በእሳት እና በጥብቅ ፀሎታችን ራሱን ሊገልጥ ይችላል (ያዕ 5፡ 16-18) ፡፡ ኤልያስና ሰለሞን ሁለቱም እንዴት መፀለይ እንዳለብን ሞደላችን ናቸው ፤ ይህ አስፈላጊ ነው ፡፡ እንዴት እንደሚፀለይ እና በ 2ዜና መዋዕል (7፡ 14) ምን እንደሚመስል ንብርብሮሽ አሉ ፡፡ እናንተ እና እኔ በዙፋኑ ፊት የመምጣት እና ልክ እንደዚህ የመፀለይ ሁሉም መብት አለን ፡፡
የእግዚአብሄር ቤተ መቅደሱን በኃይል ስለሞላው ካህናቱ ወደ ዉስጥ መግባት አልቻሉም ነበር (ቁጥር 2) ፡፡ የተሰበሰቡት ሁሉም እስራኤላዊያን እሳቱን እና የእግዚአብሄርን ክብር አዩ በማክበርም ምላሽ ሰጡ (ቁጥር 3) ፤ ህዝቡ በመስዋዕት ምላሽ ሰጡ ሰለሞንም 22,000 ከብቶች እና 120,000 በጎችን አቀረበ (ቁጥር 4-5) ፡፡ ሰልማን ይህን ለመፈፀም አንድ እንስሳ ለ12 ቀናት ለ10 ሰዓት በእያንዳንዱ ሰዎስት ሴኮንድ እንደሚሰዋ ያመለክታል ፤ እነዚህ የደህንነት መስዋዕት ነበሩ (ዘሌ 3፡ 1-17፣ 11-12፣ 1ነገ 8፡ 62) ፡፡
ሰለሞን ሌዋዊያንን እና የሙዚቃ መሳሪያቸዉን፣ ካህናቱንና መለከቶቻቸዉን “ ምህረቱም ለዘላለም ነዉና “ (ቁጥር 6) በሚለዉ ዝማሬ አመጣቸው ፡፡ “ ምህረቱ ለዘላለም ነዉና “ የሚለዉ ሀረግ በ 1 እና 2 ዜና መዋዕል ኃላ ያለዉ ምክንያት ነው ፡፡ ተመልሰዉ የነበሩትን ስደተኞች ስለ ገጠማቸዉ ነገር ችግር የለዉም የእግዚአብሄርን ዘላለማዊ ምህረት እንደሚሆንላቸዉ እርግጠኞች መሆን ይችላሉ ፡፡ መሰዊያዉ ሊይዛቸዉ የማይችሉ ብዙ መስዋዕቶች ስለ ነበሩ ሰለሞን መስዋዕት እንደ ማቅረቢያና መሰዊያ ስፍራ አደባባዩን ቀደሰው (ቁጥር 7) ፡፡
2-ዜና መዋዕል (7፡ 8-11)፡ ከሐማት ሰሜን ድንበር እስከ በደቡብ ድንበሮች ግብፅ ወንዝ ላይ ድረስ ያለ ሁሉም እስራኤል ለሰባት ቀናት በአንድ ላይ አመለኩ (ቁጥር 8) ፡፡ የዳስ ድግስ ለሰባት ቀናት የሚቆይ እንደ ነበር እንዲሁ የቤተ መቅደሱ መቀደስ ለሰባት ቀናት ቆየ ፡፡ በስምንተኛዉ ቀን ላይ እስራኤላዊያን መሰዊያዉን ለመቀደስ የተቀደሰ ገባኤ አደረጉ ከዚያም ህዝቡ “ እግዚአብሄር ለዳዊትና ለሰለሞን ለሕዝቡም ለእስራኤል ስላደረገዉ ቸርነት ደስ ብሎአቸው ሐሴት እያደረጉ “ (ቁጥር 9-10) ወደ ድንኳኖቻቸዉ ተመልሰዉ ሄዱ ፡፡ ሰለሞን ለመጨረስ 22 አመታትን የወሰደዉን ቤተ መቅደሱን እና የንጉሳዊ ቤተ መንግስቱን ጨረሰ (ቁጥር 11) ፡፡ ይህ ጥቅስ ሁሉንም የሰለሞንን ዘመን እንደ ግማሽ ጊዜ ጎዞ ያስቀምጠዋል ፡፡
2-ዜና መዋዕል (7፡ 12-22)፡ ከዚህ ሁሉ በኋላ ይህ ተፈፀመ እግዚአብሄርም ለሰለሞን “ ተገለጠለት “ ምክንያቱም የሰለሞንን ፀሎት ሰምቶ ስለ ነበር (ቁጥር 12) ፡፡ መገለጡ (መከሰቱ) በመለዓክት፣ በህልም ወይስ በራዕይ ነበር ? ይህ ከግዞት ለተመለሱት እግዚአብሄር በቤተ መቅደሱ በዚህ ስፍራ ለማደር እንደ መረጠዉ ለማሳሰብ (ለማሳወቅ) አስፈላጊ ነበር (ቁጥር 12-13) ፡፡ እግዚአብሄር ኃይሉን በምድር ላይ ሁሉ በደንብ በመሳየት እስራኤላዊያንን ከእነርሱ ጋር የሚያደርጉትን የኪዳን ሁኔታ አሳሰባቸው - በመፀለይ እና እርሱን በመፈለግ ከክፉ መንገዳቸዉ እንደሚመለሱ (ቁጥር 14) ፡፡
ይህ ጥቅስ ለእስራኤል ሰዎች ወደ እግዚአብሄር በመመለስ እንዲነቃቁ አነሳሽ ነበር (ዳን 9፡ 3-19) ፤ ይህ ለተዋሀደ መንግስት (ስርዓት) ማለት ነበር ? አይደለም ነገር ግን እነዚህን ሁኔታዎች፣ መርሆች በመዉሰድ በራሳችን ኑሮ መተግበር እንችላለን ፡፡ እስራኤል ከእግዚአብሄር ጋር በኪዳን ትስስር ዉስጥ ስትሆን አሜሪካ አይደለችም ፤ ይህ ሁሉንም የተለየ ያደርገዋል ፡፡
በቁጥር 15-18 እግዚአብሄር ከእስራኤል ትዉልድ ጋር የነበረዉን ኪዳኑን ለዘላለም ተመስርቶ በነበረዉ አስተዳደር በአንድ ንጉሳዊ ዙፉን ያረጋግጣል ፡፡ እግዚአብሄር በቁጥር 14 እንዳዘዛቸዉ እንዲኖሩ ጠራቸው ፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሄር በዚያ መንገድ ካልኖሩ፣ እንደ ገና ከእርሱ ከተመለሱ ህዝቡን እንደሚነቅል፣ ቤተ መቅደሱን እንደ ሚያጠፋና ህዝቦቹን እንደሚቀጣ ተናገረ (ቁጥር 19-22) ፡፡ ይህ እስራኤል ወደ ባቢሎን ተሰዶ በነበረበት ጊዜ ተፈጥሮ የነበረዉ ነገር ነበር ፡፡
መደምደሚያ
ቁጥር 14 ከግዞት ለተመለሰዉ ህዝብ እንደ ማርከሻ (ማቆሚያ) የተሰጠ ነበር ፡፡ በእግዚአብሄር መንገድ መጓዝን መምረጥ ይችላሉ ወይም ደግሞ በእስራኤል ላይ በባብሎናዊያንቅጣት በደረሰባቸዉ ጊዜ ተፈጥሮ የነበረዉን መጋፈጥ መምረጥ ይችላሉ ፡፡ ዋልተር ሲ.ካሲየር ጅር በ 2ዜና መዋዕል (7፡ 14) ላይ ለመነቃቃት የተካሄዱ አራት ነገሮችን ለይቷል፡
- ህዝቤ ራሳቸዉን ቢያዋርዱ፡ ኢየሱስ ራሱን አዋርዶ እንደ ነበረዉ እና ስለ እኛ እንደ ሞተ እንዲሁ የእግዚአብሄር ሰዎች ራሳቸዉን እንዲያዋርዱ እና እንዲክዱ ተጠርተዋል (ማቴ 16፡ 24፣ ፊል 2፡ 8) ፡፡
- ህዝቤ ቢፀልዩ፡ የእግዚአብሄር ሰዎች በፀሎት ወደ እግዚአብሄር ይማልዳሉ (1ሳሙ 12፡ 23) ፤ በፀሎት ከእግዚአብሄር ጋር እንሳተፋለን - በልመና፣ በቁርባን (በመተሳሰር) እና በምልጃ - በእርሱ እና በሰይጣን መካከል ባለዉም ግጭት ፡፡ ለዉጊያ እግዚአብሄር መሳሪያን ሰጥቶናል - የመንፈስን ሰይፍ እና የምልጃ ፀሎት ኃይልን (ኤፌ 6፡ 17-18) ፡፡
- ህዝቤ ፊቴን ቢፈልጉ፡ የእግዚአብሄርን “ ፊት “ መፈለግ “ ከመገኘቱ፣ ከማፅደቁ እናልክ እንደ ሰበዓዊነት በመተሳሰር በመልመድ የሚመጣዉን ደስታና ጥቅም መፈለግ ማለት ነው “ ፡፡ ወደ እርሱ በመቅረብ፣ እርሱን በማወቅ እና እርሱን በመቅመስ(በመለማመድ) ፊቱን እንፈልጋለን ፡፡
- ህዝቤ ከክፉ መንገዳቸዉ ከተመለሱ፡ የእግዚአብሄር ሰዎች በኑሮአቸዉ ከክፉ መንገዳቸዉ በንስኃ መመለስ አለባቸው ፡፡
ኤፌ (4፡ 27) በኑሮአችን ለሰይጣን እድልፋንታ መስጠት እንዴለለብን ይናገራል ፤ እነዚህን ነገሮች ካደረግን ሰይጣን በኑሮአችን እድልፋንታ ሊያገኝ አይችልም ፡፡ በሂደቱ በእግዚአብሄር ላይ ብቻ መመልከት አለብን ፡፡
3 Kaiser.
Martin J. Selman, Tyndale Old Testament Commentaries: 2 Chronicles (Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 1994), p. 351.
Walter C. Kaiser, Jr., “Revival on God’s Terms”; available at https://verticallivingministries.com/tag/an-exposition-of-2-chronicles-714-by-dr-walter-kaiser/.
ጥያቄዎች
-
በግል አስተያየታችሁ የእግዚአብሄር ክብር ቤቱን በሞላዉ ጊዜ ካህናቱን ወደ ቤተ መቅደሱ እንዳይገቡ ምን ከለከላቸው (2ዜና መዋዕል 7፡ 1-3) ? ይህ የእግዚአብሄር መገኘት በአሁኑ ጊዜ ብዙዉን ጊዜይጠቅሳል ምንስ ማለት ነው ?
-
22,000 በሬዎችን እና 120,000 በጎችን የመሰዋት ሂደት ምን ያክል ጊዜ ወስዷል ብላችሁ ታስባላችሁ (2ዜና መዋዕል 7፡ 5) ? የእንስሳቶቹ አይነት እና ቁጥር እንዴት ነበር የተወሰነው ? (ዘሌዋዊያን 11)
-
ቤተ መቅደሱ የተቀደሰ (የተለየ) በሆነበት ጊዜ ምን ድግስን እያከበሩ ነበር (ዘሌ 23፡ 33-34) ?
-
ለህዝቡ እና ለግሉ ለሰለሞን የእግዚአብሄር ማስጠንቀቂያ እና ተስፋ ምን ነበር ? (2ዜና 7፡ 12-14, 17-20)
-
በ 2ዜና መዋዕል (7፡ 14) እግዚአብሄር ለሰለሞን “ በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰዉነታቸዉን አዋርደዉ ቢጸልዩ ፊቴንም ቢፈልጉ ከክፉ መንገዳቸዉም ቢመለሱ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ ኃጢዓታቸዉንም ይቅር እላለሁ ምድራቸዉንም እፈዉሳለሁ “ አለው ፤ በአሁኑም ጊዜ ይህ ተጋባራዊ ነዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ?
-
በ 2ዜና መዋዕል (7-8) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Chronicles 7:14
“And My people who are called by My name humble themselves, pray and seek My face, and turn from their evil ways, then I will hear from heaven, forgive their sin, and heal their land.”
ንጉሥ ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ቤትና በራሱ ቤት ይሠራው ዘንድ በልቡ ያሰበውን ሁሉ አከናወነ ። ከምረቃ በዓሉ በኋላም እግዚአብሔር ለሰሎሞን በሌሊት ተገልጦ ሰሎሞን የጸለየውን ሁሉ አጸደቀለት ፡፡ እንድህም አለው የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ህዝቦች ፊታቸውን ከእርሱ ቢመልሱ እና ግን ከዚያ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፥ ፊቴንም ቢፈልጉ ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፥ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ ።
ይህ ከእግዚአብሔር በተገባው ኪዳን ውስጥ ያለው መርህ ዛሬም እውነት ነው ፡፡ እግዚአብሔር አሁንም ራሱን ዝቅ ለሚያደርግ ሰው ፣ ንስሀ ለሚገባና ፊቱን ለሚፈልግ ልብ እነድሁም ከአመጻ መንገዳቸው ለሚመለሱ ይቅር ባይና ፈዋሽ አምላክ ነው ፡፡ አለም ያለ ልዩነት የእግዚአብሔርን ታላቅና አዳኝ ፍቅር ይፈልጋል ፡፡ ይህን እያሰብክ ለመጸለይ ጊዜ ውሰድ ፡፡ “ ምናልባት እኛ አንደ እግዚአብሔር ህዝብ ራሳችንን ብናዋርድ ፣ ብንጸልይ ፊቱንም ብንፈልግ ፣ ከክፉ መነገዳችንም ብንመለስ እግዚአብሔርም ከሰማይ ጸሎታችንን ሰምቶ ኃጢአታችንን ይቅር ይላል ምድራችንንም ይፈውሳል “ ፡፡ እስኪ ራስህን ዝቅ በማድረግ ፣ በጸሎት ፣ ፊቱን በመፈለግ ፣ ከክፉ መንገድም በመመለስ ጀምር ፡፡ ጊዜው አሁን ፡፡
“በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፥ ፊቴንም ቢፈልጉ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፥ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ ።
- 2ኛ ነገሥት 7፡14
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 34:14 — “ ከክፉ ሽሽ መልካምንም አድርግ፤ ሰላምን እሻ ተከተላትም ። “
ምሳሌ 8:17 — “ እኔ የሚወድዱኝን እወድዳለሁ፥ ተግተው የሚሹኝም ያገኙኛል ። “
1ኛ ጴጥሮስ 5:6 — “እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ ”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።