Historical Books 2 Chronicles

Praising God in One Voice

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Royal Throne 2 Chronicles 5-6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 304 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በዚህ ጥናት ተዝናንቻለሁ ነገር ግን አልጠበኩም ፡፡ ከዚህ ሁሉ በኋላ በታሪክ መፅሀፍት ዉስጥ አልፈናል 2ዜና መዋዕል እንደ ትልቅ ግራ መጋባት መስሏል ፤ ነገር ግንየእግዚአብሄር ቃል ህያዉ እና የሚሰራ ነው ፡፡ ስንከፍተው በዉስጡ ያለዉን ኃይለኛ ነገር እግዚአብሄር ሊያሳየን ይችላል ፡፡ እስካሁን በ 2ዜና መዋዕልለእግዚአብሄር ቤተ መቅደስ በመስራት የዳዊትን ፍላጎት ሰለሞን እንዴት እንደ ፈፀመ ተመልክተናል ፡፡

ማክአርቱር ቤተ መቅደሱን ገንብቶ (ሰርቶ) ለማጠናቀቅ ሰባት አመት ከግማሽ እንደ ወሰደ እና በሰለሞን ዘመን በአስራ አንደኛዉ አመት እንደ ተጠናቀቅ ይገልፃል ፡፡ መቀደሱ (መለየቱ) 11 ወር ቆይቶ ስለ ተካሄደ በዳስ በዓል ድግስ አከባበር መካከል ላይ ሊካሄድ ይችላል ፡፡ ቤተ መቅደሱ ወደ መሲሁ መምጣት በማመልከት ለእስራኤል ሰዎች አምስት አስፈላጊ ጥቅሞችን አገልግሏል፡

  1. በብዙ ትዉልድ ላይ ቅዱስ እምነትን እና አምልኮን በመወከል እንደ አምልኮ ማዕከላዊነት አገለገለ ፡፡
  2. በህዝቡ መካከል የእግዚአብሄርን መገኘት ይወክላል ፡፡
  3. የኃጢዓትን ከባድነት በማብራራት የእግዚአብሄርን ይቅርታ፣ ፀጋ እና ምህረት ይወክላል ፡፡
  4. ኃጢዓት የሚያስወግደዉ ለእግዚአብሄር ልጅ ለመሲሁን መምጣት መንገድን አዘጋጀ ፡፡
  5. እንደ ፀሎት ቦታ ጠቀመ (2ዜና መዋዕል 7፡ 12-17) ፡፡

ትምህርት

2-ዜና መዋዕል (5፡ 1-3)፡ ሰለሞን ዳዊት ከድንኳኑ ማደሪያ ለይቶት የነበረዉን ሁሉንም ነገር በማምጣት በግምጃ ቤቱ አስቀመጠው (ቁጥር 1) ፡፡ ከዚያም ሰለሞንየእስራኤልን ሽማግሌዎች በአንድ ላይ አመጣቸዉ በጊዜዉ በኢየሩሳሌም በጊዜአዊ መኖሪያ ዉስጥ የነበረዉን ታቦቱን ማምጣት ቻሉ (2ሳሙ6፡ 17) ፡፡ ሰዎቹም በበዓሉ ጊዜ ተሰብስበዋል - በዳስ በዓል (ድግስ) ጊዜ (ቁጥር 3) ፡፡ ድግሱ በድንኳኑ ማደሪያ (ድንኳን በነበረው) ዉስጥ በማምለክ የመንከራተት አመታቸዉን ያከብራሉ ስለሆነም ወደ እግዚአብሄር ቋሚ ማደሪያ ቦታ ዉስጥ ታቦቱን እንደ ገና ለማስቀመጥ ትክክለኛዉ ክስተት (አጋጣሚ) ነበር (ዘሌ 23፡ 39-43) ፡፡

2-ዜና መዋዕል (5፡ 4-6)፡ በዚህ ጊዜ እስራኤላዊያን የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ተከተሉ ፡፡ ሌዋዊያን ታቦቱን ተሸከሙ (ቁጥር 4)፣ ሌዋዊያን እና ካህናቱ በድንኳኑ የነበረውን የተቀደሰዉን እቃ አመጡ (ቁጥር 5) ፡፡ ሰለሞን እና የእስራኤል ጉባኤ ብዙ ቁጥር(ለመቁጠር የሚያስቸግር) ከብቶችንና በጎችን ለመሰዋት ተሰበሰቡ (ቁጥር 6) ፡፡ አስታዉሉ ሰለሞን እንደ ካህን እና እንደ ንጉስ በመሆን ሁለቱንም ተግባራት በማድረግ መስዋዕቱን በማቅረብ በነፃነት መናገርን ስራዉን ተለማመደ (1ዜና መዋዕል 16፡ 1-3) ፡፡

2-ዜና መዋዕል (5፡ 7-10)፡ ታቦቱ በጣም በተቀደሰዉ ስፍራ ወይም በቅድስተ ቅዱስ ስፍራ ተቀመጠ ፤ በዚያ የኪሩቤል ክንፎች ከታቦቱ በላይ ለመሸፈን ተዘጋጅተዋል (ቁጥር 7-8) ፡፡ ቁጥር 9 ካህናቱ እንዲያገለግለ ስለሚፈቅዱላቸው(በመስመሩ ታላቁ ካህን በእግዚአብሄር ፊት እንዲቆዩ እንደ ጠባቂ ሀዲድ ) 30ጫማ ስለሚረዝሙት አምዶች ይናገራል (ዘጸ 25፡ 12-15፣ 1ነገ 8፡ 8) ፡፡ አምዶቹ ሌዋዊያንን ታቦቱን ወደ ቦታዉ እንዲያንቀሳሱት ረድተዋቸዋል ፡፡ የተመለሱት ስደተኞቹ ምንም አምዶች አላዩም ምክንያቱምሁሉም ጠፍቶ ነበር ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ንጉስ ናቡክነደፆር ቤተ መቅደሱን እና በዉስጡ የነበረዉን ሁሉንም ነገር ካጠፋዉ ጀምሮ የተመለሱት አይሁዶች ስራቸዉን በስሜት አምዶቹን እየረሱኣቸዉ እንደ ነበር በማስተዋል ይጠቅሳል ፤ እግዚአብሄር ለሙሴ ሰጥቷቸዉ የነበረው ፅላቶች ብቻ በታቦቱ ዉስጥ ነበሩ (ቁጥር 10) ፡፡

ዛሬም የምንጠብቃቸዉ መስመሮች “ አምዶች አሉን “ ቃሉ እና መንፈስ ቅዱስ ፤ ከእነዚህ አምዶች ዉጪ ሰዎች የሚመረጠዉን እና የሚገፋዉን ይመርጣሉ ፡፡ በእነዚህ አምዶች በማንሰራ ጊዜ ኑሮአችን ምስቅልቅል ይሆናል ፡፡

2-ዜና መዋዕል (5፡ 11-14)፡ ተቀድሰዉ የነበሩት ካህናቶችከቅዱሱ ስፍራ በመዉጣትበሌዋዊያን ዘማሪዎች፣ ሙዚቀኞች እና መለከትን የሚነፉት 120 ካህናቶች ተገናኝተዉ ነበር ፡፡ ከዚህ በፊት ህዝቡ በፍፁም ቤተ መቅደስ ስላልነበራቸው የቤተ መቅደሱን መለየት ማክበርን ቀጠሉ (ቁጥር 11-12) ፡፡ የሌዋዊያን ዋና ቤተሰብ እንደ ወንድ ልጆቻቸዉ እና እንደ ቀረቡ ዘመዶቻቸዉ የተወከሉ ነበሩ ( ቁጥር 12) ፡፡ ሁሉም በአንድ ድምፅ እግዚአብሄርን ለመመስገን እና ለማክበር በአንድ ተጣመሩ (ሆኑ) (ቁጥር 13) ፡፡ ቤተ መቅደሱ በእግዚአብሄር መገኘት ደመና ተሞላየእግዚአብሄርምክብር ቤተ መቅደሱን ሞላው (ቁጥር 14) ፡፡

መደምደሚያ

በምስጋናና በአንድ ድምፅ በአንድ ድምፅ አብረን እንድንመጣ ተጠርተናል፡

መዝ (133፡ 1-3)፡ በአንድ ድምፅ በአንድ ላይ መምጣት መልካም እና የሚያስደስት ነው ፡፡

2ዜና መዋዕል (30፡ 12)፡ በኃንሳብ አንድነት መኖሩ መልካም ነው ፡፡

ኤፌ (4፡ 1-6)፡ በአንድነትአንድ እንሆናለን ፡፡

ኤፌ (4፡ 11-13)፡ አንድነት ላይ እስክንደርስ ድረስ በአንድነት ለመቀጠል ተጠርተናል ፡፡

1ቆሮ (1፡ 10)፡ ሁላችንም በአንድ ላይ በፍፁም በአንድነት ኃሳብ እንጂ በመከፋፈል አልተጠራንም ፡፡

ቆላ (3፡ 12-14)፡ በአንድነት አብረን እንያያዛለን ፡፡

1ቆሮ (12፡ 4-6)፡ የተለያዩ ስጦታዎች ሲሰጡን መንፈስ ግን አንድ ብቻ ነዉ የተሰጠን ፡፡

ሮሜ (15፡ 4-6)፡ በኃሳብ እና በድምፅ አንድ እንሆናለን፡፡

ሮሜ (15፡ 7-13)፡ እግዚአብሄርን በአንድነትእንድናከብረው ተጠርተናል ፡፡

2ዜና መዋዕል (5፡ 14) የእግዚአብሄር ክብር ቤተ መቅደሱን እንደ ሞላው ይናገራል ፡፡ አንድ ድምፅ ባለን ጊዜ የእግዚአብሄርን ክብር እንቀምሰዋለን (እንለማመደዋለን) ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville, TN: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 497.

  2. MacArthur, p. 497.

  3. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville, TN: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 539.

  4. Nelson’s Commentary, p. 540.

  5. Nelson’s Commentary, p. 540.

ጥያቄዎች

  1. 2ዜና መዋዕል (5፡ 10) በታቦቱ ዉስጥ የነበረዉን አስዕርቱን ትዕዛዞች ብቻ ይገልፃል ፤ ነገር ግን ዕብ (9፡ 4) ጳዉሎስ የመናዉ ማድጋ እና የአሮን ብትርም በታቦቱ ዉስጥ እንደ ነበር ፅፏል ፡፡ ለእነርሱ በሆነዉ ምን ታስባላችሁ ? ማን እንደሚወስዳቸዉ ወይም ለምን በሚለዉ ላይ ኃሳብ አለ ?
  2. በ 2ዜና መዋዕል (5፡ 14) ህዝቡ በመሰብሰብ በአንድ ድምፅ እግዚአብሄርን አመሰገኑ ፤ ቤቱ በደመና ተሞላ ፡፡ ይህ ሌላ የት ላይ ሲሆን እናየዋለን ? (ዘጸ 40፡ 34-35)
  3. በጊዜ ብዛት የእግዚአብሄር ሰዎች “ እንደ አንድ ህዝብ “ እና እንደ “ አንድ ድምፅ “ በተሰበሰቡ ጊዜ ኃያላን ነገሮች መሆን ሲችሉ አይተናል ፤ አንዱ ምሳሌ ምንድን ነው (ዘፍ 11፡ 1-9) ? በኢየሱስ ጊዜስ (ሐዋ 2፡ 1-4) ? በአንድ ድምፅ እንደ አንድ ህዝብ ስንመጣ ምን ልንፈፅም እንችላለን ? አንድ ህዝብን መቀየር እንችላለን ?
  4. በ 2ዜና መዋዕል (6፡ 2) ሰለሞን ለእግዚአብሄር ለዘላለም እንዲኖርበት ቤት እንደ ሰራ ተናገረ ፤ እስካሁን ይህ እዉነት ነው ? ለምን ወይስ ለምን እዉነት አይደለም (ሐዋ 17፡ 24-25) ? አሁን እግዚአብሄር የሚኖረዉ የት ነው ? (ዮሐ 14፡ 23፣ 1ቆሮ 3፡ 16)
  5. በ 2ዜና መዋዕል (5-6) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Chronicles 5:13

“The trumpeters and singers joined together to praise and thanks the LORD with one voice. They raised their voices, accompanied by trumpets, cymbals, and musical instruments, in praise to the LORD: For He is good; His faithful love endures forever. The temple, the LORD’s temple, was filled with a cloud.”

የቤተ መቅደሱ ግንባታ ተጠናቀቀ ፡፡ ካህናቱም የቃልኪዳኑን ታቦት ወደ ስፍራው ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ወሰዱት ፡፡ በቦታውም ከተቀመጠ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን ፣ ከካህናቱና ከሌዋውያን መዘምራኑ ጋር ፣ በስራ ድርሻቸው ሳይከፋፈሉ በአንድ ድምጽ እግዚአብሔርን ለማምለክ ተሰበሰቡ ፡፡ በዚህ ጊዜም የእግዚአብሔር ክብር መጣ ቤተ መቅደሱንም በታላቅ ደመና ሞላው ፡፡ ህዝቡም አንድ ሆኑ ትኩረታቸውንም በአግዚአብሔር ላይ ብቻ አደረጉ ፡፡

እነዚህ ተከፋፍለው የነበሩት አንድ ላይ በአንድ ድምጽ መጡ ፡፡ አንድነት ሆነ ፤ የአግዚአብሔርም ክብር መጣ ፡፡ አግኝታችሁታል ? አይታችኋል የእግዚአብሔርን ክብር ምን እንደሚያመጣው ? በክርስቶሰ አካል ወሰጥ ያለ አነድነት ነው ፡፡ ቤተከርስትያን በልዩነት ላይ መከራከርን አቁማ ወደ አንድነት ለመምጣት ምን ይሆን የሚያስፈልጋት ? እግዚአብሔር አማኞችን በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም ፤ እርስ በርሳቸውም በፍቅር በመታገስ ፤ በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ በመትጋት እንድመላለሱ ያዛል ፡፡ ያ ሰላም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፡፡ ከክርስቶስ ፍቅር የተነሳ እግዚአብሔርን በአንድነት አምልኩ ፡፡ ሰውን ሳይሆን ጌታን ተመልከቱ ፡፡ አንድ ድምጽ ( አሳብ ) ሲኖራችሁ እግዚአብሔር ክብሩን ይገልጣል ፡፡ እናም ከዚያ ሌሎች አንድ አድርጎ ያስተሳሰራችሁን ፍቅር ማወቅ ይፈልጋሉ ፡፡ በአንድ ድምጽ ሆናችሁ ተሰብሰቡ እናም የእግዚአብሔርን ክብር ጠብቁ !

“ መለከቱንም የሚነፉ መዘምራኑም በአንድነት ሆነው እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እያከበሩ፦ እግዚአብሔር ቸር ነውና፥ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ እያሉ በአንድ ቃል ድምፃቸውን ወደ ላይ ከፍ አድገው በመለከትና በጸናጽል በዜማም ዕቃ ሁሉ እግዚአብሔርን ባመሰገኑ ጊዜ፥ ደመናው የእግዚአብሔርን ቤት ሞላው ። “

  • 2ኛ ዜና 5፡13

ተጨማሪ ጥቅስ

ዮሐንስ 17:23 — “ እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ፥ የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ፤ እንዲሁም ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል ። “

ሮሜ 15:6–7 — “በአንድ ልብ ሆናችሁ በአንድ አፍ እግዚአብሔርን፥ እርሱም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት፥ ታከብሩ ዘንድ ፥ ስለዚህ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ክብር እንደ ተቀበላችሁ እንዲሁ እርስ በርሳችሁ ተቀባበሉ ። “

ኤፌሶን 4:1–3 — “ እንግዲህ በጌታ እስር የሆንሁ እኔ በተጠራችሁበት መጠራታችሁ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እለምናችኋለሁ ፤ በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም፤ እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሡ ፤ በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ ። “