Historical Books 2 Chronicles

"Then He Made"

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Royal Throne 2 Chronicles 3-4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 303 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለ 2ዜና መዋዕል ጭብጣችን ንጉሳዊ ዙፋን ነው ፡፡ በ 2ዜና መዋዕል የዳዊት ልጅ (ሰለሞን) ቃል ገብቶት በነበረዉ መጓዝ ችሎ ነበር -በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሄር ቤተ መቅደስን በመስራት ፡፡ በምዕራፍ (1-2) ሰለሞን ቤተ መቅደሱን በአንድ ላይ ለመስራት ከጢሮስ ንጉስ ከኪራም እርዳታን ጠየቀ ፤ ቀድሞ ተፈጥሮ የነበረዉን ከባቢሎን ምርኮ ለተመለሱት ለመግለፅ የተፃፈ እንደ ነበር እናስታዉሳለን ፡፡ ከስደት ከተመለሱት ዉስጥ አንዱ ዘሩባቤል ከተመለሰ በኋላ ቤተ መቅደሱን እንደ ገና ሰርቷል ስለሆነም እነዚህ ዝርዝሮች ለእርሱ አስፈላጊዎች ይሆናሉ (ዘካ 4፡ 10) ፡፡

ትምህርት

2-ዜና መዋዕል (3፡ 1-4)፡የቤተ መቅደሱ መሰረት ፡፡ ሰለሞን ቤተ መቅደሱን መስራት በኦርናን የመዉቂያ አዉድማ ዳዊት አዘጋጅቶት በነበረዉ ስፍራ በሞሪያ ተራራ (አሁን ከደብረ ዘይት ተራራ በቃዴስ ሸለቆ ላይ በሚገኝ እንደ ቤተ መቅደስ ተራራ ይታወቃል) መስራት ጀመረ (ቁጥር 1) ፤ አብርሃም መልከፀድቅን ካገኘበት ስፍራ ጋር (ዘፍጥረት 14) እና አብርሃም ልጁን ይስሐቅን ለመሰዋት መጥቶበት ከነበረዉ ስፍራ ጋር ተመሳሳይ ነበር (ዘፍጥረት 22) ፡፡ ምድር በእስራኤል ሁል ጊዜ አስፈላጊ ነው ፡፡ ይህ እግዚአብሄር ለዳዊት እና ኦርናን የተገለጠበት ስፍራ ነበር ፡፡ ስራዉ በሰለሞን ዘመን በአራተኛዉ አመት በሁለተኛዉ ወር በሁለተኛዉ ቀን እንደ ማክአርቱር አገላለፅ በማዚያ ወይም ግንቦት 966 ከክርስቶስ ልደት በፊት ጀመረ ፡፡ ፕሮጀክቱ (ስራዉ) በሰባት አመት ከግማሽ ተጠናቀቀ ፡፡ ቤተ መቅደሱ 90ጫማ ርዝመት እና 30ጫማ ስፋት (ቁጥር 3) እና ሌላ 30ጫማ የሚጨምር በንፁህ ወርቅ የተሸፈነ አንድ ኮሪደር ያለዉ ነበር (ቁጥር 4) ፡፡ ትልቅ ህንፃ አልነበረም ከአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ህንፃዎች ያንሳል ፡፡ ስራዉን የሚመራው ብልሀተኛ ሰዉ ከጢሮስ ኪራምአቢ ነበር (2ዜና 2፡ 13) ፡፡

2-ዜና መዋዕል (3፡ 5-7)፡ዋናዉ ቤተ መቅደስ፡ ፀሀፊው እነዚህን የቤተ መቅደሱ አራት ዋና ክፍሎችን በዝርዝር መግለጫ ይቀጥላል ፡፡ ምናልባትም እንደ ዛፍ ህይወት ስዕል እና ምናልባትም የኤደን ገነትን ለመወከል እንቡጥ እና አበባዎችን በመጠቀም የተፈጠረን ሰንሰለትን የሚያመለክት የፅድ ዛፎችን አካትቷል (ቁጥር 5) ፡፡ “ የጠራ ወርቅ ( የወርቅ ኃብት) “ የሚለዉ ቃል በምሁራን የተረዳ(የተገነዘቡት) አይደለም ነገር ግንግምቶች በጣም የጠራ እና ዉድ የሆነ ወርቅ እንደ ነበር ነው (ቁጥር 6) ፡፡ አብዛኛዉ ሁሉም ነገር በቤተ መቅደሱ ዉስጥ በወርቅ የተሸፈነ ነበር ኪሩቤል ደግሞ ከእንጨት የተቀረፁ ነበሩ (ቁጥር 7) ፡፡

2-ዜና መዋዕል (8-14)፡ቅድስተ ቅዱሳን፡ የታቦቱ እና የእግዚአብሄር መገኘት ቋሚ ማደሪያ ይሆናል ፡፡ የቅድስተ ቅዱሳን ዉድነት (ቅዱስነትን) ተጠቅመዉት በነበረው 45,000 ፓዉንድ (23ቶን) ወርቅየታየ ነው ፡፡ የሰለሞን ትኩረት ለዝርዝሩ የሚያስደነግጥ ነው ፡፡

“ ሰራዉ “ የሚለዉ ፅሁፍ በዚህ ምዕራፍ ዉስጥ ስራዉ በሰለሞን እንደ ተፈፀመ ያንፀባርቃል (ቁጥር 8) ፡፡ ማርቲንሰልማን ሰለሞን እግዚአብሄር ለሰጠዉ እቅድ የታመነ እንደ ነበር ይገልፃል ፤ እቅዱ ወደ ፍሬአማነት መጣ ምክንያቱም ሰለሞን በእቅዱ ላይ ስለተጓዘ ፡፡ ጋርይ ሊንተን “ እግዚአብሄር ፍፁም ሰዎችን አይመለከትም ለእርሱ በመሰጠት የሚሆኑትን ብቻ በቀላሉ እንደ ሚፈልግ “ ይፅፋል ፡፡ ለመነቃቃት የምትፀልዩ ከሆነ በዚያዉ መጓዝ አለባችሁ !

መፅኀፍ ቅዱስ ስለ መታመን ምን ይላል ?

  • 1ሳሙ (26፡ 23)፡ ዳዊት ለእግዚአብሄር የታመነ በመሆን ንጉስ ለመሆን ጥሪዉን ለመፈፀም በእግዚአብሄር ላይ ጠበቀ ፡፡
  • 2ዜና መዋዕል (16፡ 9)፡ እግዚአብሄር ልባቸዉ ሙሉ ለሙሉ ወደ እርሱ ወደ ሆነዉ ይመለከታል ፡፡
  • መዝ (12፡ 1)፡ እግዚአብሄር ስለ መታመን የሚመለከት ነው ፡፡
  • ምሳ (20፡ 6)፡ የታመነዉን ሰዉ ማን ያገኘዋል ?
  • ምሳ (28፡ 20)፡ የታመነ ሰው ብዙ በረከቶች ይኖሩታል ፡፡
  • ማቴ (25፡ 21)፡ መልካም አንተ በጎ ታማኝ ባሪያ ፡፡
  • ሉቃ (16፡ 10, 12)፡ በጥቂቱ የታመኑ በብዙ ይታመናሉ ያልታመኑት ደግሞ ያላቸዉን ያጣሉ ፡፡
  • 1ቆሮ (4፡ 1-2)፡ የእግዚአብሄር ሚስጢር መጋቢዎች ነን ፡፡
  • ራዕ (2፡ 10)፡ እስከሞት ድረስ የታመነ መሆን ፡፡

አብዛኞቻችን ለእግዚአብሄር እቅድ ማሳያነት የተሰጠን መሆናችንን አናስተዉልም ምክንያቱም በኑሮአችን የታመንን ስላልሆንን ፡፡ የሰለሞንን የመታመን ደረጃ እናያለን ምክንያቱም በረንዳዊን እና ቤተ መቅደሱን በአሪፍ ስለ ገነባ ፤ የተቀደሰ ቦታዉን በሚገባ ገነባ ፤ ቅድስተ ቅዱሳኑን በኃይለኛዉ በአሪፍ ገነባ ፡፡ እግዚአብሄር እንዲሰራቸው የሰጠዉን ተግባራት በትክክል አደረገ ፤ በሚገባ ሰራ ፡፡

2-ዜና መዋዕል (3፡ 14)፡የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ፡፡ ሰለሞን ሰለሞን ለድንኳኑ ማደሪያ ተጠቅመዉበት የነበረዉን የመጋረጃ መልክ ተመሳሳይ ለቤተ መቅደሱ ተጠቀመ ፤ ኪሩቤልንም ተጠለፈበት ፡፡

2-ዜና መዋዕል (3፡ 15-17)፡የመግቢያዎቹ አምዶች ፡፡ 27ጫማ ከፍታ የነበራቸው ሁለቱ የቆሙት አምዶች ወደ ቤተ መቅደሱ መግቢያ ላይ የተቀመጡ ነበሩ ፡፡ በተቀደሰዉ ስፍራ ዉስጥ ላይ ተሰርቶ የነበረ ብዙ የሰንሰለት ስራ በአምዶቹ ላይ ተቀምጠዋል (1ነገ 7፡ 17-20) ፡፡

2-ዜና መዋዕል 4፡ የዉስጥ እቃዎቹ እና መብራቶቹ በምዕራፍ አራት የተገለፁ ናቸው ፡፡

መደምደሚያ

ሰልማን ለቤተ መቅደሱ ምላሾቹ የሚጋጩ እንደ ነበሩ ይመዘግባል ፤ አንዳንዶች ቤተ መቅደሱ እግዚአብሄርን ወደ ህዝቡ አቅርቦ በማምጣት ታላቅ ደስታን እንደ ሚሰጣቸዉ (መዝ 27፡ 4-6) እና ቤተ መቅደስ መገኘት ወደ እግዚአብሄር መገኘት ለመምጣት መንገዱን እንደ ሚሰጥ ተረድተዋል (2ሳሙ 22፡ 7፣ ዮና 2፡ 7) ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ትክክለኛዉ ንድፉ እናአቀማመጥ እግዚአብሄርንለማግኘት እንዴት አስቸጋሪ እንደ ነበር ያብራራል ፡፡ ወደ መግደሱ እንዲገቡ የተፈቀደላቸዉ ብቸኞቹ እስራኤላዊያን ሌዋዊያን እና ካህናቱ ነበሩ ፤ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ ታላቁ ካህን በእያንዳንዱም አመት አንድ ጊዜ ብቻ መግባት ይችላል ፡፡ ስለሆነም ህዝቡ በዚህ ምዕራፍ የተገለፀዉን ምንም አይተዉ አያዉቁም ፡፡ “ ለአብዛኞቹ እስራኤላዊያን ቤተ መቅደሱ የማይታይ አለም ነበር ፤ እግዚአብሄር ሊቀርባቸዉ ተስቦ ነበር ነገር ግን ወደ እርሱ መንገዱ በብዙ ገደቦችዙሪያዉ የታጠረ ነበር “ ፡፡

የእግዚአብሄር መገኘት በብዙኃኑ ሰዎች የማይታይ እና የማይነካ ነበር ፡፡ ቤተ መቅደሱ በሚያምር ሁኔታ የተገነባ ነበር ነገር ግን ወደ እግዚአብሄር ለመምጣት ማንም አልቻለም ፤ ነገር ግን በክርስቶስ ሞት በቤተ መቅደሱ የነበረዉ መጋረጃ ከላይ ወደታች ስለ ተቀደደ ሁሉም ተራ የሆነዉ እኛም እንኳን ወደ እግዚአብሄር እድሉን ማግኘት ቻልን (ማቴ 27፡ 51፣ ዕብ 10፡ 19-20) ፡፡ ቤተ መቅደሱን በመገንባት የሰለሞን መታመን በሰማይ ለሚሆነዉ ጥላ ነው (ዕብ 8፡ 5) ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville, TN: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 496.

  2. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville, TN: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 538.

  3. Martin Selman, 2 Chronicles (Tyndale Old Testament Commentary) (Downers Grove, IL: InterVarsity Press, USA, 1994), p. 304.

  4. Gary Linten, “Scriptures on Being Faithful to God”; available at https://www.ministrymaker.com/mm/preach/.

  5. Selman, p. 304.

ጥያቄዎች

  1. ሌላ የት ላይ ሞሪያ ተራራ ተጠቅሶ እናያለን (ዘፍጥረት 22) ? በዚያ ምን አስፈላጊ ክስተት ተከሰተ ? ዉጤቱ ምን ነበር ?
  2. ሰለሞን የእግዚአብሄር ቤተ መቅደስን በኢያቡሳዊዉ በኦርና መዉቂያ ዉድማ ላይ መስራት ጀመረ ፤ ለምን ይህ ስፍራ ? በዚህ ስፍራ በአባቱ በዳዊት ምን ተካሂዷል (2ሳሙ 24፡ 16) ? ይህ እንዲሆን ምን መራው ? (2ሳሙኤል 24)
  3. በ 2ዜና መዋዕል (3-4) ቤተ መቅደሱ የተገነባ ነበር ፤ ሌላ የት ላይ የእነዚህን አንዳንድ ዝርዝሮች እናገኛለን (ዘጸዓት 36-38) ? በሁለቱ መካከል ጥቂት ልዩነቶቹ ምንድን ናቸው ?
  4. በ 2ዜና መዋዕል (3-4) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Chronicles 3:1–3a

“Then Solomon began to build the LORD’s temple in Jerusalem on Mount Moriah where the LORD had appeared to his father David, at the site David had prepared on the threshing floor of Ornan the Jebusite. He began to build on the second day of the second month in the fourth year of his reign. These are Solomon’s foundations for building God’s temple.”

ሰሎሞን ንጉሥ ሆኖ ከተሾመ በኋላ ቤተ መቅደሱን መገንባት ለመጀመር ምንም ጊዜ አላቃጠለም ነበር ፡፡ ገና በንግሥና አራተኛ አመቱ ላይ የግንባታውን የመጀመሪያ ምዕራፍ የመሰረቱን ስራ አጠናቀቀ ፡፡ ንጉሥ ሰሎሞንም እግዚአብሔር እቅዱን እንደሚያጸናና እቅዱንም በእምነት ለማከናወን የሚያስፈልገውን ኃይል እንደሚሰጥ አመነ ፡፡ እግዚአብሔርም ታመኝነቱን ቀጠለ ሰሎሞንም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለተሰጠው እቅድ ታዛዠ ሆኖ ቀጠለ ፡፡

የምንነግርህ ለእርሱ ምሪት እንድትታዘዝ ነው ፡፡ የምታውቀው ነገር አለ እግዚአብሔር እንድታደርገው ያዘዘህ ነገር ግን አንተ የተውከው ( ያልታዘዝከው ) ? ደብዳቤ መጻፍ ሊሆን ይችላል ፤ ለተቸገረ ሰው መስጠት ፤ እርቅን ወይም መስማማትን መሻት ወይም ደግሞ ቤትህን ወይም መኪናህን ማጽዳትም እንድሁ ፡፡ እግዚአብሔር ታማኚነታችሁን ማየት ይፈልጋል ለአንተ አደራ በተሰጡ ትንንስ ነገሮች ጭምር ፡፡ ስለዚህ ዛሬ ፡- ነገ ዛሬ ማለትሀን አቁም ፣ ወደ መሬት አውርደው ፣ እግዚአብሔርን ጥበብ ለምነው እና አድርገው ! ልክ ሰሎሞን ከቤተ መቅደሱ መሰረት እንደጀመረ እግዚአብሔር እንድታደርግ ባዘዘህ ነገር ላይ የመጀመሪያውን እርምጃ ውሰድ ፡፡ በመታዘዝ ስትራመድ እግዚአብሔር ይታመንልሃል ፡፡ በቃ ጀምር !

“ ሰሎሞንም እግዚአብሔር ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠበት በሞሪያ ተራራ ዳዊት ባዘጋጀው ስፍራ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ ። በነገሠም በአራተኛው ዓመት በሁለተኛው ወር መሥራት ጀመረ ። ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤት ይሠራ ዘንድ የጣለው መሠረት ይህ ነው ፡፡ “

-2ኛ ዜና 3፡1-3

ተጨማሪ ጥቅስ

  • መዝሙር 119:60 — “ትእዛዝህን ለመጠበቅ ጨከንሁ አልዘገየሁምም ። “
  • ማቴዎስ 25:21 — “ጌታውም፦ መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው ። “
  • ሮሜ 1:5 — “ በእርሱም ስለ ስሙ በአሕዛብ ሁሉ መካከል ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንዲገኝ ጸጋንና ሐዋርያነትን ተቀበልን “