Historical Books 2 Chronicles

Preparing to Build the Temple

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Royal Throne 2 Chronicles 1-2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 302 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዛሬ የ 2ዜና መዋዕል ጥናታችንን እንጀምራለን ፤ ከመጀመሪያው ዜና መዋዕል እንደ አንድ መፅሀፍት ነበር የተፃፈው ቆይቶ ወደ 1 እና 2ዜና መዋዕል እስከ መደረጉ ድረስ ሁለት መፅሀፍት አልነበረም ፡፡ ለ 1ዜና መዋዕል ሐረጋችን የዳዊት ልጅ ነው ምክንያቱም ያለማቋረጥ ወደ ሚመጣዉ መሲህ ወደ ዳዊት ልጅ ስለ ሚያመለክት ፤ ለ 2ዜና መዋዕል ቃላችን ንጉሳዊ ዙፋን የሚል ነው ምክንያቱም ከዳዊት ጋር ተሳስረዉ በነበሩት በእስራኤል ሳይሆን በይሁዳ ነገስታት ላይ በብዛት ስላተኮረ ፡፡ የሜንዲ ስዕል ለ 1 እና 2 ዜና መዋዕል እንደ አንድ ፅሁፍ ስለ ሆነ (ሁለት የተለያዩ ስዕሎች በአንድ ላይ በተቀመጡ ጊዜ አንድ ስዕል ይፈጥራሉ ) ከመጀመሪያዉ ስዕል የሆነው መልዕክት ወደ ሁለተኛው ያደርሳል ፡፡

ዜና መዋዕል ማለት “ ታሪክ ወይም የዘመናት ክስተት “ ማለት ሲሆን በባቢሎን ከምርኮ ከተመለሱ በኋላ ለአይሁዶች የተፃፈ ነበር ፡፡ አንድ ቦታ ላይ መፅሀፉ “ የተሰወሩ ነገሮች “ በሚል ተሰይሞ ነበር ምክንያቱም በመፅሀፍት የትም ስፍራ ላይ ያልተካተቱ ብዙ ነገሮችን ስለያዘ ፡፡ ልምዱ ዕዝራ ፀኃፊዉ እንደ ነበር ይዟል (አምኗል) (ዕዝ 7፡ 1-6) ፡፡ ስደተኞቹ ከ 70 አመት ግዞት በኋላ በሰዎስት ደረጃ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፡ 1) ዘሩባቤል (ዕዝራ 1-6)፣ 2) ዕዝራ (ዕዝ 7-10) እና 3) ነህምያ (ነህ 1-13) ፡፡

ማክአርቱር ስደተኞቹ ወደ ከተማ ያለ ዕብራዊ ንጉስ፣ ያለ ጠባቂ፣ ያለ ቤተ መቅደስ፣ ለማደሪያ ከሚሆን ገዢ ስፍራ ዉጪ፣ በጥቂት መለኮታዊ በረከት፣ በጥቂት የቀድሞ መንግስት ብልፅግና እና በኢየሩሳሌም ያለ እግዚአብሄር መገኘት እንደ ተመለሱ ያብራራል ፡፡ የዜና መዋዕል አምሳ አምስት ፐርሰንት አዲስ እቃ (ነገር ) ነው ፡፡

2 ዜና መዋዕል 1 ዳዊት ዙፋን ላይ የሰለሞንን መዉጣት ይመዘግባል ፡፡ እግዚአብሄር ሰለሞንን የፈለገዉን እንዲጠይቀዉ ነገረዉ ጥበብንም ጠየቀው ፤ ዳዊትም በብዙ ስለ ጥበብ ጠይቋል (1ዜና መዋዕል 22፤ 12) ፡፡ እግዚአብሄር የሰለሞንን ጥያቄ ታላቅ ጥበብ እን ብልፅግና በመስጠት መለሰለት ፡፡

ምዕራፍ 2-9 የሰለሞንን ዘመን ሲሸፍን ምዕራፍ 10 ደግሞ መንግስቱ የተከፋፈለ እንዲሆን የአስሩ ነገዶችን አመፅ ይመዘግባል ፡፡ ምዕራፍ 11-36 የይሁዳን ነገስታት ይሸፍናል፡ የአሳን ቤተ መቅደሱን ማደስ (2ዜና መዋዕል 15)፣ ኢዮሳፍጥ ያቋቋማቸው ተልዕኮዎች (ምዕራፍ 18)፣ የኢዮአስ ቤተ መቅደሱን መጠገን (2ዜና መዋዕል 23-24)፣ የሕዝቅያስን ቤተ መቅደሱን መክፈት (ምዕራፍ 29-31) እና የኢዮስያስን “ የህጉን መፅሀፍት “ ማግኘትን (2ዜና መዋዕል 34-35) ፡፡ በእነዚህ ምዕራፎች መታደስን፣ መነቃቃት እና መሻሻል ተካሄደዋል ፤ በ 2ዜና መዋዕል (36፡ 15-23) ምሮኮኝነትን ይሸፍናል ፡፡ በዚህ ሁሉ መሀከል ላይ ንጉሳዊ ዙፋን የተመሰረተ ነው ፡፡

ትምህርት

2-ዜና መዋዕል (2፡ 1-10)፡ በአባቱ በዳዊት ፍላጎት በመሄድ ሰለሞን ለያህዌ ስም(በዕብራዊ ስም ለእግዚአብሄር ትርጉሙ ጌታ ማለት ለሆነው) ቤተ መቅደሱን እና ለራሱ ቤተ መንግስትን ለመስራት ዝግጁ ነበር (ቁጥር 1) ፡፡ ለእግዚአብሄር ጎጆ አልሰራም ነገር ግን እርሱን ለማክበር በእግዚአብሄር ስም ቤተ መቅደስን ሰራ እንጂ ፡፡ ሰለሞን ለሰራተኞች ስራዎችንእንደ ተሸካሚዎች፣ ጠራቢዎች እና ተቆጣጣሪዎች በማድረግ ሰየመ (ቁጥር 2) ፤ ከዚያም ሰሎሞን ከኪራም ንጉስ ከጢሮስ ያህዌን ለማምለክ ቤተ መቅደሱን ለመስራት በዝግባ እንጨት እንዲረዳዊ ጠየቀው (ቁጥር 3-4) ፡፡ ቤተ መቅደሱ በሰማይ ወይም በምድር ሊያዝ የማይችለዉንለአንዱ ታላቅ አምላክ ይሆናል (ቁጥር 5-6) ፡፡ ሰለሞንመጥረብ የሚችሉ እና ከይሁዳ በዳዊት ከተቀቡት ከጥበበኞች ጋር ለመስራት ሱፍ እንዲሰሩ ጠየቃቸው (ቁጥር 7) ፤ በተጨማሪም ንጉስ ሰለሞን ከሊባኖስ ግንዶችን በመጠየቅ እና ጥበበኛ ሰዎቹ የኪራምን ሰራተኞች በመቁረጥ እና ግንዶችን በማዘጋጀት እንደ ሚረዱዓቸው ተስፋን ሰጣቸው (ቁጥር 8-9) ፤ ከዚያም በብዙ ምግብ አቅርቦት ሰራተኞቹን እንደ ሚከፍላቸው ቃል ገባላቸው (ቁጥር 10) ፡፡

2-ዜና መዋዕል (2፡ 11-16)፡ ኪራምም ለሰለሞን ጥያቄ ለንጉስ ዳዊት ልጅ እንዲአይነት ጥበብ የሰጠዉን የእስራኤልን አምላክ በማመስገን መለሰለት (ቁጥር 11-12) ፡፡ ለቤተ መቅደሱ በተመረጡ ብረቶች እና ድንጋዮች ላይ ከሰለሞን አስተዋይ ሰዎች ጋር የሚሰራ ጠራቢን ኪራምአቢን ላከለት (ቁጥር 13-14) ፡፡ ኪራምም ንጉሱን ቃል ገብቶ የነበረዉን የምግብ አቅርቦት ለመላክ ጠየቀ የኪራምም ሰዎች የፅድ ዛፎችን መቁረጥ በመጀመር በእስራኤል ወደ ኢዮጴ ወደብ ያጓጉዙታል (ቁጥር 15-16) ፡፡ ሰለሞን ስለ ጠየቀዉ ሁሉም ነገር ተሰጥቶት ነበር ፡፡

2-ዜና መዋዕል (2፡ 17-18)፡ ሰለሞን በምድሪቱ እስራኤላዊ ያልሆኑት ላይ ህዝብ ቆጠራ በማካሄድ 153,000 አገኘ ፤ ከዚያም ወንዶቹን ለስራ አስቀመጣቸው፡ 70,000 እንደ ተሸካሚዎች፣ 80,000 እንደ ድንጋይ ቆራጮች እና 3,600 እንደ ተቆጣጣሪዎች አደረገ ፡፡

መደምደሚያ

የሰለሞን ቤተ መቅደስ በመፅሀፍ ከተገለፁት ሰዎስት ቤተ መቅደሶች የመጀመሪያዉ ነበር ፡፡ የሰለሞን ቤተ መቅደስ ለመገንባት ሰባት አመት እና ግማሽ ወስዷል ፤ ይሁን እንጂ የሰለሞን ቤተ መቅደስ በ586 ከክርስቶስ ልደት በፊት ፈርሶ ነበር ፡፡ ዘሩባቤል በእስራኤል ከግዞት መመለስ በኋላ በብዙ የተሸሻለ ቤተ መቅደስ ሁለተኛዉን ቤተ መቅደስ እንደ ገና ሰራ ፤ ከዚያም ንጉስ ሄሮድስ በ20 ከክርስቶስ ልደት በፊት ይህን ቤተ መቅደስ ተስፋፍቷል ፤ ያም በ70 ከሞት በኋላ በሮማዊያን ፈርሶ ነበር ፡፡ የሄሮድስ ቤተ መቅደስ በኢየሱስ የተጎበኘ ነበር ፡፡ በአሁኑ ጊዜ አካላዊ ቤተ መቅደስ የለም ፡፡

ሆኖም ግን ሆሴ (3፡ 4-5) “ የእስራኤል ልጆች ያለ ንጉስና ያለ አለቃ ያለ መስዋዕትና ያለ ዓምድ ያለ ኤፉድና ያለ ተራፊም ብዙ ወራት ይቀመጣሉና ፤ ከዚያም በኋላ የእስራኤል ልጆች ተመልሰው አምላካቸዉን እግዚአብሄርንና ንጉሳቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ ፤ በኋለኛውም ዘመን ፈርተው ወደ እግዚአብሄርና ወደ በረከቱ ይመጣሉና “ በማለት ይገልፃል ፡፡

ሕዝ (37፡ 27-28) እግዚአብሄር በመካከላቸዉ እንደ ሚያድር እናመቅደሱም ከእስራኤል እንደ ገና መዋኃድ በኋላ ለዘላለም ከእነርሱ ጋር እንደ ሚሆን ይናገራል ፡፡ ኢየሱስ ስለ ሰዎስተኛዉ ቤተ መቅደስ አወራ (ማቴ 24፡ 15-21) ፤ በዘመኑ መጨረሻ ላይ በቅደሱ ስፍራ ክፉ ቆሞ እናየዋለን (2ተሰ 2፡ 1-4) ስለዚህም በዚያ ቤተ መቅደስ ይኖራል ፡፡

በአሁኑ ጊዜ በኢየሩሳሌም በቤተ መቅደሱ ተራራ ሁለት የሙስሊም ቅዱስ ስፍራዎች ናቸው ፤ አብርሃም መልከፀድቅን ያገኘበት (ዘፍጥረት 14)፣ አብርሃም ልጁን ይስሐቅን ለመሰዋት የመጣበት (ዘፍጥረት 22)፣ ዳዊት ለእግዚአብሄር መሰዊያን ለመስራት የኦርናን የመዉቂያ አዉድማ የገዛበት (1ዜና መዋዕል 21) እና ሰለሞን የመጀመሪያዉን ቤተ መቅደስ የሰራበት ስፍራ ነው ፤ በመጨረሻዉም ዘመን ሰዎስተኛዉ ቤተ መቅደስም ይገነባበታል የሚል ሀሳብ (ዉይይት) አለ ፡፡ በራዕ (11፡ 1-2) የእግዚአብሄር ቤተ መቅደስ የተለካ ነው ፡፡

ይህ ሁሉ በኢየሩሳሌም በአካል የሚገነባ ሰዎስተኛ ቤተ መቅደስ እንደ ሚኖር እየተናገረ እንደ ሆነ አምናለሁ ፤ በበቃ ጊዜ ወደ ክርስቶስ መመለስ በደንብ የቀረበ ይሆናል ፡፡

  1. John MacArthur, MacArthur’s Bible Commentary: 2 Chronicles (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 478.

ጥያቄዎች

  1. ሰለሞን እንደ ንጉስ እንደ እግዚአብሄራዊ በመገለጥ ለመጀመር የሚያስደንቀዉ መንገድምን ነበር ?
  2. ወደ መገናኛዉ ድንኳን የመሄድ አላማዉ ምን ነበር ? ቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ስትሄዱ አንዳንድ ጊዜ በይበልጥ ከሰዎች ጋር ለመገናኘት ወይስ ከእግዚአብሄር ጋር ለመገናኘት ስትፈልጉ ራሳችሁን ታገኙታላችሁ ?
  3. ሰለሞን ሀብት፣ ጤንነት እና ዝና እያለው ቢሆንም በሚገባ አልረካም ወይም ፍሬ ነገር አላገኘም ያልሆነዉ ለምንድን ነው (መክ 2፡ 1-9፣ 11) ? አማኞች በእግዚአብሄር ደስታን እንዴት ያገኙታል (ይለማመዱታል) ? (መዝ 16፡ 11፣ ዮሐ 15፡ 9-11፣ ፊል 4፡ 4)
  4. ንጉስ ሰለሞን ቤተ መቅደሱን ለመስራት እንዲረዳዉ ንጉስ ኪራምንየጠየቀዉ አንዳንድ ነገሮች ምን ነበሩ ? ለጥያቄዉ የንጉስ የኪራም ምላሽ ምን ነበር ?
  5. እግዚአብሄር ከህዝቡ ጋር የሚገናኝበት የተቀደሰ ስፍራ ሀሳብ ወደ ኢየሱስ፣ ወደ መንፈስ ቅዱስ እና ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ያመለክታል ? (ዮሐ 1፡ 14፣ 1ቆሮ 6፡ 19፣ ኤፌ 2፡ 21)
  6. በ 2ዜና መዋዕል (1-2) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ መን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Chronicles 1:10

“Now grant me wisdom and knowledge so that I may lead these people, for who can judge this great people of Yours?”

ቤተ መቅደሱን ለመስራት እግዚአብሔር መጀመርያ ሰሎሞንን ማዘጋጀት ነበረበት ፡፡ ጸሀፊያኑ ሰሎሞንን የገለጹት እንደ መሪ ፣ እንደ ንጉሥ ፣ በራሱ ኃይል ብቁ እንዳልሆነ ሰው ይልቁንም እግዚአብሔር በጣም ደስ እንደተሰኘበትና አብሮት እንዳለ ሰው ነው ፡፡ እግዚአብሔር ለሰሎሞን አንድ ነገር ይጠይቅ ዘንድ እድልን በሰጠው ጊዜ ሰሎሞን ጥበብን ይሰጠው ዘንድ ለመነ ፡፡ ከዚያም ከእግዚአብሔር ከሆነ ጥበብ በተጨማሪ ሰሎሞን ባለጠግነትን ፣ ሀብትንና ክብርን ተቀበለ ፡፡

አድሱ ኪዳን ከእግዚአብሔር የሆነ ጥበብን እንደ ንጽሕ ፥ ሰላም ወዳድ (ታራቂ) ፥ ገር፥ እሺ ባይ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለበት አድርጎ ይገልጸዋል ። እንደ ክርስቶስ ተከታይ ጻውሎስ እንዴት እንድትመላለሱ ትጠነቀቁ ዘንድ ደግሞም ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና እንደ ሞኝ ሳይሆን እንደ ብልሆች እንድትመላለሱ ጽፏል ፡፡ እንዴት ይሆን ዛሬ ከትላንት የሚለየው በእያንዳንዱ ሁኔታ ብትቆሙና እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣችሁ ዘንድ ብትለምኑ ? ቃል ተገብቶላችኋል ወደ እርሱ በተጣራችሁ ጊዜ ሊመልስላችሁና የማታውቋቸውን ታላላቅ ነገሮች ሊነግራችሁ ፡፡ ዛሬ በሁሉም ሁኔታ ቆም ብላችሁ እግዚአብሔር ጥበብን አንድሰጣችሁ ጠየቁ ፤ እንደሚሰማችሁም እመኑ የእርሱንም መልስ ጠብቁ ፡፡ እግዚአብሔርን ፍሩ ምክንያቱም እርሱ በህይወታችሁ ዛሬ ታላላቅ ነገሮችን ማድረግ ይፈልጋልና ፡፡

“ አሁንም በዚህ ሕዝብ ፊት እወጣና እገባ ዘንድ ጥበብንና እውቀትን ስጠኝ፤ ይህን በሚያህል በዚህ በታላቅ ሕዝብ ላይ ይፈርድ ዘንድ የሚችል የለምና ። “

—2ኛ ዜና 1:10

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ኤርምያስ 33:3 — “ወደ እኔ ጩኽ፥ እኔም እመልስልሃለሁ፤ አንተም የማታውቀውን ታላቅና ኃይለኛ ነገርን አሳይሃለሁ ። “
  • ኤፌሶን 5:15–16 — “እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ ፤ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ ። “
  • ያዕቆብ 3:17 — “ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፥ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት ። “