Historical Books 1 Chronicles

Finding Delight in the Lord

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of David 1 Chronicles 29 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 301 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በ 1ዜና መዋዕል ይህ የመጨረሻ ጥናት ነው ፡፡ ይህ ለሁሉም ፍላጎቶች እና አላማዎች በመጨረሻም ለህዝቡ የንጉስ ዳዊት ማድረስ(ማቅረብ) ነው ፤ በቀደሙት ጥቂት ምዕራፎች እግዚአብሄር ዳዊትን ቤተ መቅደሱ በተለዬ ምን መምሰል እንዳለበት ዝርዝር ሰጥቶታል ፡፡ በዚህ ምዕራፍ ለቤተ መቅደሱ ግንባታ ኃላፊነት ወደ ሰለሞን የተላለፈ ነበር ፡፡

በዚህ በሙሉ ምዕራፉ ዋና ጭብጡ በእግዚአብሄር ደስታን ማግኘት ነው (መዝ 119፡ 16፣ 47) ፡፡ “ ደስታ “ የሚለዉ ቃል በሆነ ነገር እንደ ታላቅ ደስታ መዉስድ ወይም መፈንጠዝን ወይም በሆነ ነገር እንደ ምስጋና መረዳት ይቻላል ፡፡ ዳዊት በጠቅላላ ህይወቱ የታየ ለአምልኮ ልብ ነበረው ፡፡

ትምህርት

1-ዜና መዋዕል (29፡ 1-9)፡ የዳዊትን ዙፋን ለመዉሰድ ግጭት ስለ ነበር በግጭቱ ሁለት የዳዊት ልጆችም ሞቱ ፤ ስለሆነም ዳዊት ህዝቡን እግዚአብሄር እንደ ቀጣይ ንጉስ ሰለሞንን እንደ መረጠው መረዳታቸዉን እርግጠኛ ለማድረግ በአንድ ላይ ጠራቸው (ቁጥር 1) ፡፡ ሰለሞን 20 አመት አካባቢ ነበር ነገር ግን እንደ ወጣት እና በልምድ ላይ እንደ ነበር ይትይ ነበር ፤ ስለሆነም ሰለሞን በሚደግፉት እና በሚረዱት አባቶች እና መምህሮች የተከበበ ይሆናል ( 1ቆሮ 4፡ 15) ፡፡ በተጨማሪም ዳዊት ቤተ መቅደሱን ለመስራት አቅርቦቶችን ወርቅን፣ ብርን፣ ነሐስን፣ ዉድ ድንጋዮችን እና እምነበረዶችን ሰብስቦ ነበር (ቁጥር 2) ፡፡

እነዚህ እቃዎች በቤተ መቅደሱ ዉስጥ ታላቅ ቅርፅ በመፍጠር በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም የሚመጣዉን መንፈሳዊ መንግስት ሌላ ጥላን ይሰጣል (ራዕ 21፡ 1-2፣ 10-12፣ 18-20) ፡፡ በራዕይ የተጠቀሱት 12 ድንጋዮች በእኛ ዉስጥ ስለሚኖረዉ ህያዉ የድንጋይ ቅርፅ ወደ ፊት ስለሚመጣዉ አዲስ ቤተ መቅደስ ያመለክታል (1ቆሮ 3፡ 16-17፣ 6፡ 17) ፡፡ ለህያዉ እግዚአብሄር ማደሪያዎች ነን የራሳችን አይደለንም (1ጴጥ 2፡ 4-5) ፡፡

በተጨማሪም ዳዊት ለቤተ መቅደሱ መስሪያ የራሱን የወርቅ እና የብር ንብረት ሰጥቷል ( ቁጥር 3-4) ፡፡ የብሪቴን ሙዚየም አንድ ሰቅል 66.5 ፓዉንድ እንደ ሚመዝን አቋቁሟል ፤ ስለሆነም በዛሬዉ ኢኮኖሚ መሰረት የዳዊት የግል ስጦታ 1.26ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያክል ይሆናል ፡፡ ዳዊት ምንም የማያስወጣዉን ለእግዚአብሄር ለመስጠት ፍቃደኝ እንዳልነበር እናስታወሳለን (1ዜና መዋዕል 21፡ 24) ፡፡ የሰጠዉን ከተናገረ በኋላ ዳዊት የተሰበሰቡትንም ለቤተ መቅደሱ ስራ እንዲሰጡ ጠየቃቸው (ቁጥር 5) ፤ እንደ ኃይማኖት ትዕዛዝ የነበራቸውን እና ለመለኮታዊ አላማ የሚጠቀሙበትን በመናገር ራሳቸዉን እንዲቀድሱ ጠየቃቸው ፡፡ መሪዎቹ እና ሰራተኞቹ (ባለስልጣኖቹ) በደስታ በፈቃደኝነት ሰጡ (2ቆሮ 9፡ 7) ፤ በለጋስነት እና በሙሉነት ሰጡ ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሲጠጋጋ 2.268 ቢሊዮን ዶላር የሚሆን ወርቅ፣ ብር፣ ነሐስ እና ብረት አላቸው - ዳዊት በግሉ ከሰጠዉ ሁለት እጥፍ ይሆናል (ቁጥር 7) ፡፡ ከዳዊት ጋር የነበረዉ ህዝብ መሪዎቹ በሰጡት ተደሰቱ በደስታም ተወሰዱ ዳዊትም በታላቅ ተደሰተ (ቁጥር 8-9) ፡፡

1-ዜና መዋዕል (29፡ 10-18)፡ ዳዊት ህዝቡን በፀሎት፣ እግዚአብሄርን በዘላለማዊነቱ በማመስገን (ቁጥር 10)፣ በትዝታ በማቴዎስ ላይ ተጨምሮ በነበረዉ በጌታ ፀሎት፡ “ ምን ግዜም ለዘላለም መንግስት፣ ኃይል ክብር ያንተ ነው “ መራ ፡፡ ዳዊት በደስታ አመሰገነ ፤ የዳዊት ፀሎት የእግዚአብሄርን ታላቅነት እና ኃይል፣ ክብሩን ዉበቱን እና ግርማዉን እንደ ሁሉም ነገር ፈጣሪ የሁሉም ነገር ሰጪ እና ባለቤትነቱን ገልጧል (ቁጥር 11-13) ፡፡ ዳዊት በደስታ አመለከ (መዝ 100፡ 4) ፡፡ ዳዊት ቀድሞዉኑ እግዚአብሄር የነበረዉን ነገር ለእግዚአብሄር ሰጠው (መዝ 24፡ 1-2፣ ሐጌ 2፡ 8) ፤ ሁሉም ነገር የእግዚአብሄር ነው (ቁጥር 14, 18) ፡፡

በቁጥር 15 ዳዊት ትንቢታዊ ቃል በመስጠት “ በምድር ላይ ዘመናችን ከተስፋ ዉጪ ጨለማ “ እንደ ሆነ እዉቅና ሰጠ ፡፡ በእግዚአብሄር ምክንያት እና በነበረው ምክንያት ዳዊት ህዝቡ በደስታ የሚያስደስት ነገር ተሰጥቷቸዉ ነበር ጠቀሰ (ቁጥር 17-18) ፡፡

1-ዜና መዋዕል (29፡ 19-25)፡ ከዚያም ዳዊት እግዚአብሄርን ሰለሞን ትዕዛዙን በመጠበቅ በሙሉ ልቡ በእርሱ ላይ ትኩረት እንዲያደርግ እንዲረዳው ጠየቀው (ቁጥር 19) ፡፡ የዳዊት ፀሎት ሰለሞንን ለስኬት አመቻቸው(አበቃዉ) ፤ ይህ የአባት ፀሎት እና ባርኮት በብዙ ለልጆቻችን መስጠት እንደ ምንችል ያሳያል ፡፡ ዳዊት ህዝቡን በአምልኮ መራ ለእግዚአብሄርም በደስታ በመስገድ አክብሮት ሰጡት (ቁጥር 20) ፡፡ በቀጣዩም ቀን ለእግዚአብሄር መስዋዕትን በማድረግ በእግዚአብሄር ፊት በታላቅ ደስታና መፈንደቅ በሉም ጠጡም (ቁጥር 21-22) ፤ ከዚያ ቀጥሎም በግልፅ በሚገባ ዙፋኑን ለመዉረስ ሰለሞን የእግዚአብሄር ምርጫ እንደ ነበር ለሁለተኛ ጊዜ ሰለሞንን እንደ ንጉስ ቀቡት (ሾሙት) (ቁጥር 22) ፡፡ ሰለሞን ዙፋኑን ወሰደ ሁሉም መሪዎች፣ የዳዊት ኃያላን ወንዶች እና የቀሩት ሁሉም የዳዊት ልጆች ከንጉስ ሰለሞን ጋር ጥምረታቸዉን አጠነከሩ (ቁጥር 23-24) ፡፡ እግዚአብሄር ሰለሞንን አስበለጠው ዘመኑም አበለፀገው (ቁጥር 25) ፡፡

1-ዜና መዋዕል (29፡ 26-30)፡ የቀሩት ጥቅሶች የዳዊትን ዘመን ማጠቃለያ ይሰጣል ፡፡ በእስራኤል ላይ እንደ ንጉስ ዳዊት 40 አመት ገዛ ፤ በኬብሮን ለሰባት አመት እና በኢየሩሳሌም ደግሞ ለ33 አመት ገዛ (ቁጥር 26-27) ፡፡ ዳዊት “ ዕድሜም፣ ባለጠግነትም፣ ክብርም ጠግቦበመልካም ሽምግልና ሞተ “ (ቁጥር 28) ፤ ይህ በደህና የመኖር ምልክት፣ የአንድ ሰዉ የሙሉ እምነት ምልክት ነው ከእርሱ በፊት አርፈዉ እንደ ነበሩት እንደ ሙሴ፣ አብርሃም እና ይስሐቅ (ቁጥር 28-30) ፡፡

መደምደሚያ

ቁጥር 25 እግዚአብሄር በሰለሞን ላይ “ ከእርሱ በፊትም ለነበሩት ለእስራኤል ነገስታት ያልሆነዉን የመንግስትን ክብር ሰጠው “ ፤ ለምን? ምክንያቱም ሰለሞን የአባቱ የዳዊት በረከት ስለሆነ ፡፡ ሰለሞን አባቱ ዳዊት እንደ ነበረው በእግዚአብሄር በመደሰቱ ምክንያትመጀመሪያ ዳዊት የፈለገዉን ሁሉንም ነገር ተቀበለ ፡፡ በእግዚአብሄር በምንደሰት ጊዜ የልባችንን ፍላጎት ይሰጠናል ፡፡

ጥያቄዎች

  1. ዳዊት ሁሉንም የግል ንብረቱን ለቤተ መቅደሱ መስሪያ ለምን ሰጠ ? ለሁኔታዉ ሁሉንም ነገር ስለ መስጠት ምን ያነሳሳችኋል(ማቴ 6፡ 21) ? ፍላጎታችሁ ለአለማዊ ነገር ላይ ነው ወይስ ለእግዚአብሄር ነገር ነው ?
  2. ለእግዚአብሄር ቤተ መቅደስ ለመስጠት ለዳዊት ልመና መሪዎቹ እንዴት ነበር ምላሻቸው (2ቆሮ 9፡ 7) ? በዚህ መፅሀፍ አገላለፅ “ አስደሳች “ የሚለዉ ቃል ምን ማለት ነው ? ለእግዚአብሄር ወይም ለስራዉ ለመጨረሻ ጊዜ በዚያ ሁኔታ የሰጣችሁት መቼ ነበር?
  3. በቁጥር 10 ዳዊት በምስጋና ፀሎቱን እንዴት እንደ ጀመረዉ እና በጌታ ፀሎት መካከል አንድነቶቹን እንዴት ታዩታላችሁ ? (ማቴ 6፡ 9-13)
  4. ሰለሞንን በተመለከተ የዳዊትን አስፈላጊ የፀሎት ጥያቄ በምን ታዩታላችሁ ? (1ዜና መዋዕል 29፡ 19፣ መዝ 72፡ 1)
  5. በሰለሞን መጀመሪያ ጊዜ ቅባት በ 1ነገ (1፡ 38-39) እና 1ዜና መዋዕል (29፡ 21-25) መካከል ልዩነቱ ምን እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ?
  6. በ 1ዜና መዋዕል 29 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Chronicles 29:3, 5b

“Moreover, because of my delight in the house of my God, I now give my personal treasures of gold and silver for the house of my God over and above all that I’ve provided for the holy house . . . Now who will volunteer to consecrate himself to the LORD today?”

የቤተ መቅደሱ ግንባታ ሳይጀመር ንጉሥ ዳዊት ለስብሰባው ተናገረ በተጨማሪም ስራው ለሰው ሳይሆን ለአምላክ በመሆኑ ታላቅ እንደሆነ ገለጸ ፡፡ ንጉሥ ዳዊት ለስራው አቅሙ የቻለውን ሁሉ ሰጠ ደግሞም በተጨማሪ መሪዎቹን ቀርቦ እነርሱም ገንዘብ ይሰጡ ዘነድ ጠየቀ ፡፡ እግዚአብሔርን እንደሚያመልክና በእግዚአብሔር ደስ እንደተሰኘ ህዝብ ለዳዊት ልመና ምላሽ ሰጡ ፡፡ ሕዝቡም ፈቅደው ሰጥተዋልና ደስ አላቸው እግዚአብሔርንም በህብረት አመለኩ ፡፡

ሁሉም መልካምና ፍጹም ስጦታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው የሚገኘው ፡፡ አግዚአብሔር እናንተን የጠራችሁ አንድኛው ገንዘባችሁን በመስጠት እንድታመልኩት ነው ፡፡ ነገር ግን አስታውሱ ለእግዚአብሔር መስጠት በግድ መሆን የለበትም ፡፡ እግዚአብሔር በልማድ ፣ በግዴታ ወይም በጓደኛ ግፊት እንድትሰጡት አይፈልግም ፡፡ እግዚአብሔር ደስ በተሰኘ ልብ እንድትሰጡ ይፈልጋል ፡፡ በግሪኩ ይሄ ማለት “ የደስታ ስጦታ “ በሌላ አባባል መግለጽ ከሚቻለው በላይ ራስን መሥጠት ከዚህም አልፎ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ መስጠት ፡፡ መንፈሳችሁ የሆነ ያክል እንድትሰጡ ካሳሰባችሁ ይህ ደስ የሚል ነው ፡፡ እግዚአብሔርንም እመኑት ይህንን ለቤቱ ስራ ይጠቀምበታል ፡፡ እግዚአብሔር የተትረፈረፈ ጸጋን ይሰጣችኋል እናንተም እርሱ እንድትሰሩት ለሰጣችሁ ሰራ የሚያስፈልጋችሁ ነገር ሁሉ ይኖራችኋል ! እግዚአብሔር ዛሬ ለስራው በደስታ እንድትሰጡ እየተየቃችሁ ነውን ? እንደ አምልኮ በመቁጠር በመታዘዝ ምላሽ ስጡ ፡፡

“ ከዚህም በላይ ደግሞ የአምላኬን ቤት ስለወደድሁ፥ ለመቅደሱ ካዘጋጀሁት ሁሉ ሌላ የግል ገንዘቤ የሚሆን ወርቅና ብር አለኝና ለአምላኬ ቤት ሰጥቼዋለሁ ……… ዛሬ በፈቃዱ ራሱን ለእግዚአብሔር የሚቀድስ ማነው ? “

  • 1ኛ ዜና 29፡3 ፣ 29፡5

ተጨማሪ ጥቅስ

1ኛ ዜና 29:6, 9 — “የአባቶችም ቤቶች አለቆች፥ የእስራኤልም ነገዶች አለቆች፥ ሻለቆችም፥ የመቶ አለቆችም፥ በንጉሡም ሥራ ላይ የተሾሙት በፈቃዳቸው አቀረቡ ። ……… ሕዝቡም ፈቅደው ሰጥተዋልና፥ በፍጹም ልባቸውም ለእግዚአብሔር በፈቃዳቸው አቅርበዋልና ደስ አላቸው፤ ንጉሡም ዳዊት ደግሞ ታላቅ ደስታ ደስ አለው ። “

መዝሙር 37:4 – “ በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል ። “

2ኛ ቆሮንቶሰ 9:7–8 – “ እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም ። እግዚአብሔር፥ ሁልጊዜ በነገር ሁሉ ብቃትን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ፥ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል ። “