Historical Books 1 Chronicles

Passing on the Plans of the Temple

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of David 1 Chronicles 27-28 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 300 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ተስፋችን የእግዚአብሄርን ቃል እያጠናችሁ የምታሳልፊት ጊዜ ፍሬአማ እንደሚሆን ነው ለመረዳት እንኳን አስቸጋሪ ቢሆንም ፡፡ አስፈላጊዉ ነገር ጥናቱን መቀጠል ነዉ ምክንያቱም ስለ እግዚአብሄር ቃል ብዙ ስታዉቁ ከራሳችሁ ብዙ ትወጣላችሁ ፡፡ ወደ 1ዜና መዋዕል መጨረሻ ስንሄድ አሁንም ለመማር ለእኛ ብዙ ነገር አለ ፡፡

ትምህርት

1-ዜና መዋዕል (28፡ 1-10)፡ ዳዊት በአንድ ላይ የእስራኤልን መሪዎች፣ የነገዶችንም አለቆች ሁሉ፣ አዛዦችንም፣ የጭፍሮች አለቆችንም፣ ዳዊት የነበረዉን ሁሉ እንዲጠበቁ ተሸመዉ የነበሩትን ሁሉ፣ ሹመኞችን፣ ጃንደረቦችን እና ጽኑዓን ኃያላኑንም ሁሉ አመጣ (ቁጥር 1) ፡፡ ዳዊት ልቡ ለእግዚአብሄር ቤትን መስራት ቢፈልግም እግዚአብሄር የእርሱ እቅድ እንዳልነበር ነግሮት እንደ ነበር ነገራቸው (ቁጥር 2-3) ፡፡ ይልቁንም እግዚአብሄር የዳዊት ፍላጎት በልጁ በሰለሞን እንደሚፈፅመዉ ተስፋ ገባለት (ቁጥር ቁጥር 4-6) ፤ ዳዊት ከእግዚአብሄር ኪዳን አድርጎ የነበረ ሰው ነበር ፡፡ ወዲያዉኑም በእስራኤል ዙፋን ላይ እንደ ንጉስ እንዲቀመጥ እግዚአብሄር ሰለሞንን መረጠው ( ቁጥር 5) ፤ እንደ ንጉስ ሰለሞን የእግዚአብሄርን ቤተ መቅደስ ይሰራል (ቁጥር 6-7) ፡፡ እግዚአብሄር ምን እንዳቀደ ይገልጥልናል ፤ በቁጥር 7 ለዳዊት ተስፋን የእግዚአብሄር መግለጥ አሁንም በተፅዕኖ ነበር ….የዳዊት ዘር በሁሉም መንገድ በሰለሞን በኩል ወደ ክርስቶስ ያልፋል ፡፡

እግዚአብሄር ከዳዊት ጋር የመሰረተዉ የዳዊት ኪዳን በልጁ በሰለሞን በመቀጠል በኢየሱስ አገልግሎት ያበቃል (2ሳሙ 7፡ 12-16) ፤ በዘላለም ዙፋን ላይ የሚቀመጠዉ ኢየሱስ ብቻ ነው ፡፡ እግዚአብሄር መጀመሪያ ለህዝቦቹ ሳይገልጥ ምንም ነገር አያደርግም (አሞ 3፡ 7) ፤ እግዚአብሄር ዳዊትን ትዕዛዙን እንዲመለከት እና እንዲታዘዝ አዘዘዉ ይህ ከሆነ ተስፋዉ ወደ ማለፍ (መቀጠል) ይመጣል (ቁጥር 8) ፡፡ ከዚያም በቁጥር 10 እግዚአብሄር ሰለሞንን የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሄርን እንዲያዉቀዉ እና የእግዚአብሄርን ቤተ መቅደስ በመመስረት እንዲያገለግለዉ ነገረው ይህ ከሆነ በተከታዮቹ መካከል መገለጥ ይችላል (ዮሐ 3፡ 16) ፡፡ በጣም በአስፈላጊነት ሰለሞን እግዚአብሄርን እንደ አምላኩ አልተከተለውም ፡፡

1-ዜና መዋዕል (28፡ 11-19)፡ ዳዊት ሙሉዉን የቤተ መቅደሱን እቅድ(አሰራር) ለሰለሞን ሰጠው (ቁጥር 11-12) ፤ እቅዱ ካህናት እና ሌዋዊያን እንዴት ስራዉን እንደሚጨሩስት እና በቤተ መቅደሱ ዉስጥ እንዴት እንደ ሚያገለግሉ አካትቷል (ቁጥር 13) ፤ በተጨማሪም ደግሞ እቅዱ ቤተ መቅደሱን እና የዉስጥ እቃዎቹን ለመጨረሽ የሚያስፈልገዉን የወርቅ እና የብር መጠን ምን ያክል እንደ ነበር ያካትታል (ቁጥር 14-18) ፡፡ ዳዊት በእግዚአብሄር እጅ ተፅፎ የመጣለትን ሁሉንም ነገር በዝርዝር ገለፀ (ቁጥር 19) ፡፡

1-ዜና መዋዕል (28፡ 20-21)፡ ዳዊት ሰለሞንን እንዲጠነክር እና እንዲበረታ ነገረው ምክንያቱም እግዚአብሄር ከእርሱ ጋር በመሆን በአስተዳደሩ ቤተ መቅደሱን እንዲሰራ ስለ ሚመራው ፡፡

መደምደሚያ

ቤተ መቅደሱ በተለየ መልኩ የሚያምር (ያሸበረቀ) ነበር ፤ የቀድሞዉ አለም አንዱ መደነቂያ ነበር ፤ ነገር ግን ቤተ መቅደሱ ራሱ በዚያ ከሚያድረው ከእግዚአብሄር ይልቅ ለህዝቡ ጎላቸው ሆነ ፡፡ ሁሉንም ጉልበታችንን ከሰዎቹ ይልቅ በህንፃዉ ላይ ስላለማድረጋችን እርግጠኝች በመሆን ጠንቃቆች መሆን አለብን ፤ የአንድ መንግስት ካህናቶች የምንሆን እንጂ ተጠንቃቂዎች (ተንከባካቢዎች) አይደለንም ፡፡

ጥያቄዎች

  1. የሰራዊቱ እያንዳንዱ ከፍል ከአመቱ ዉስጥ ለምን አንድ ወር ብቻ ያገለግላሉ ?
  2. በናያስ የሰዎስተኛዉ ክፍል አዛዥ ነበር ፤ በእስራኤል እንደ ታላቅ ጀግና የሚታየዉ ለምን ነበር ? (2ሳሙ 23፡ 20-21)
  3. ዳዊት ትዕዛዝ ለመስጠን ማንን ሰበሰበ ? በምዕራፍ 28 ታላቅ መሪ ያደረገዉን ዳዊት ምን እያደረገ ነበር ?
  4. ዳዊት ለመላዉ እስራኤል የሰጠዉ መልዕክት ምን ነበር ? ለልጁ ለሰለሞን የሰጠዉ መልዕክት ምን ነበር ? ዳዊት ሰለሞንን ምን ያክል ጊዜ በርታ ብሎ ነገረው ? (1ዜና 22፡ 13፣ 28፡ 20)
  5. ዳዊት ሰለሞንን “የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሄር በሚገባ እንዲያዉቀዉ “ በኃይል አሳሰበው ፤ በብዙ በደንብ ኢየሱስን ወደ ማወቅ እንዴት ልንመጣ እንችላለን ? (ዮሐ 14፡ 21-24)
  6. በ 1ዜና መዋዕል (27-28) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Chronicles 28:2–3

“Then King David rose to his feet and said, ‘Listen to me, my brothers and my people. It was in my heart to build a house as a resting place for the ark of the LORD’s covenant and as a footstool for our God. I had made preparations to build, but God said to me, ‘You are not to build a house for My name because you are a man of war and have shed blood.’”

ንጉሥ ዳዊት የእስራኤልን አለቆችን ፣ የጦር አዛዦችን ፣ በንጉሥና በልጆች ሀብትና ግዛት ላይ የተሾሙትን ፣ የቤተ መንግስት ሹማምንቶችን ፣ ተዋጊዎችንና ጽኑዓን ኃይላኑን ሁሉ ሰበሰበ ። በተሰበሰቡም ጊዜ ንጉሥ ዳዊት ተነስቶ በትህትና የልቡን አሳብ አካፈላቸው ፡፡ በታማኝነት እና በግልጽ ተናገረ ፡፡ ቤተ መቅደሱን ለመስራት እንዴት በልቡ አስቦ እንደነበር ነገር ግን እግዚአብሔር የተለየ እቅድ እንዳለውና አንደነገረው አስረዳ ፡፡ ስለዚህም ዳዊት እግዚአብሔር ለቤተ መቅደሱ ያቀደውን እቅድ ተቀበለ ፡፡

በልብህ የሆነ ነገር ለመስራት ሸክም ተሰምቶህ እና ግን ከመስራትህ በፊት በድንገት እግዚአብሔር እቅድህን አስቀይሮህ ያውቃል ? ምናልባትም አንተ በወኔ በአንድ አቅጣጫ እየተጓዝክ ይሆናል እናም ከዚያ እንደ ዳዊት “ ነገር ግን እግዚአብሔር እንድህ አለኝ “ የምትልበት ሁኔታ ያጋጥምሃል ፡፡ ስለዚህም የእግዚአብሔርን አድስ አሳብ ተቀበልክ እና እሺ አልክ ፡፡ ምናልባት ምንም ትርጉም መስጠት ላይኖርበት ይችላል ፣ እንድሁም በተጨማሪ በውጭ ላሉት ቀላል ሊመስል ይችላል ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር እንደገና እየመራህ ( መንገድ እያስቀየረህ ) እንደሆነ አንተ ታውቃለህ ስለዚህም ለምሪቱ ምላሽ ከመስጠት ልትዘገይ አትችልም ፡፡ ትምከትን ጥለሃል ፤ ሌሎች ሊያስቡ ስለሚችሉት መጨነቅ ትተሃል ድምጹንም በመታዘዝ ተከትለሃል ፡፡ ምናልባትም ይሄ ዛሬ ልታደርገው የሚገባ ነገር ይሆናል ፡፡ አስታውስ እርሱን ስትከተል እርሱ አይተውህም ፡፡ በሙሉ ልብህ በእርሱ ላይ ታመን በራስህ ማስተዋል ላይ አትደገፍ ፡፡ በእግዚአብሔር ላይ በመታመን በትህትና ስትራመድ እርሱ መንገድህን ያቀናልሃል ፡፡

“ ንጉሡም ዳዊት በእግሩ ቆሞ እንዲህ አለ፦ ወንድሞቼና ሕዝቤ ሆይ፥ ስሙኝ፤ ለእግዚአብሔር ለቃል ኪዳኑ ታቦትና ለአምላካችን እግር ማረፊያ የዕረፍት ቤት ለመሥራት እኔ በልቤ አስቤአለሁ፤ ለሥራም የሚያስፈልገውን አዘጋጅቻለሁ ፤ እግዚአብሔር ግን፦ የሰልፍ ሰው ነህና፥ ደምም አፍስሰሃልና ለስሜ ቤት አትሠራም ብሎኛል ። “

  • 1ኛ ዜና 28፡2-3

ተጨማሪ ጥቅስ

ምሳሌ 3:5-6 — “በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል ። “

ምሳሌ 16:9 — “የሰው ልብ መንገዱን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቀናለታል ። “

ሮሜ 12:2 — “ እግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ ። “