Historical Books 1 Chronicles

Receiving God's Blessing

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of David 1 Chronicles 25-26 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 299 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ይህ ለማክበር ጊዜዉ ነው ፤ ይህ በአጠቃላይ በመጀመሪያዉ አመት ዉስጥ ያደረጋችሁት ክፍል 100 ጥናት ነው ፡፡ ያ የስራ ዉጤት ነው ! በታሪክ መፅሀፍት ዉስጥ ስንቀጥል 1ዜና መዋዕል ጥናት መጨረሻ ላይ እየቀረብን ነው ፡፡ 1ዜና መዋዕል 25 የሌዋዊያንን ሙዚቀኞች ይሸፍናል 1ዜና መዋዕል 26 ደግሞ በር ጠባቂዎች እና በቤተሰቦቻቸዉ ላይ ይመለከታል (ያተኩራል) ፡፡

ምዕራፍ 26 አስፈላጊ ተግባርን በተጫወቱት በር ጠባቂዎችን ይመለከታል ነገር ግን በብዛት እዉቅና አልተሰጣቸው ፡፡ አንዳንዶች ከእነርሱ የሆነ ነገር በመፈለጋቸው ምክንያት እንደ ነበሩ አስታዋሉ ፡፡ ከሌዋዊያን ከሰዎስቱ ቤተሰቦች ሁለቱ እንደ በር ጠባቂ አገልግለዋል - ቆሪያዊያን እና ሜራሪያዊያን እንጂ ጌድሶናዊያን አይደሉም ፡፡ ቁጥር 1-11 በበር ጠባቂ ቤተሰቦች ላይ ይመለከታል ቁጥር 12-19 ደግሞ ለበር ጠባቂዎች የተሰጡት ተግባራት ላይ የተመለከተ ነው ፡፡ ምዕራፍ 26 በመግለጥ በተለይም አንድ በር ጠባቂ ላይ እንመለከታለን (እናተኩራለን) ፡፡

ትምህርት

1-ዜና መዋዕል (26፡ 1-11)፡ ቆሪያዊያን በቁጥር (1-9) ተዘርዝረዋል ፡፡ በቁጥር 4 ላይ የተጠቀሰው ዖቤድኤዶም እንደ ተባረከ በ(2ሳሙ 6፡ 10-11፣ 1ዜና መዋዕል 13፡ 13-14) የተገለፅ ነበር ፤ የዚህን የሌዋዊ ቤት ዳዊት ለሰዎስት ወራት ታቦቱን አስቀምጦበት ነበር ፡፡ እግዚአብሄርን ዖቤድኤዶም በስምንት ወንድ ልጆች ባርኮት ነበር (ቁጥር 4-5) ፤ የዖቤድኤዶም የልጅ ልጆች የዚህ ትንቢት መፈፀም ማረጋጋጫዎች ነበሩ ፤ ችሎታ የነበራቸው ስልሳ ሁለት ወንዶች ከዖቤድኤዶም የመጡ ነበሩ (ቁጥር 6-8) ፡፡ ልጆች ከእግዚአብሄር በረከቶች ናቸው ፡፡ በቁጥር 10-11 የሜራሪያ ልጆች የተጠቀሱ ናቸው ፡፡ የልጆቹ ጠቅላላ ቁጥር 93 ሲሆን ከተጠቀሱት ዉስጥ ሁለት ሰዎስተኛ የሚሆኑት ከዖቤድኤዶም ነበሩ (ቁጥር 1-11) ፡፡

1-ዜና መዋዕል (26፡ 12-19)፡ ከኔልሰን ማብራሪዎች ስለ ተግባራት ክፍፍሎች እና እንደ በር ጠባቂዎች ቆሪያዊያን እና ሜራሪያዊያን ስለፈፀሟቸው ተግባራት እንማራለን፡

  • የቤተ መቅደሱን በሮች ይጠብቃሉ (1ዜና መዋዕል 26፡ 16) ፡፡
  • በመሳሪያዎች ኃላፊነት ላይ ነበሩ (1ዜና መዋዕል 9፡ 23) ፡፡
  • ለቤተ መቅደሱ ንብረት ተጠያቂ ነበሩ (1ዜና መዋዕል 9፡ 26) ፡፡
  • የቤተ መቅደሱን መዋጮዎች ተቆጣጥረዋል (2ነገ 12፡ 9፣ 22፡ 4፣ 2ዜና መዋዕል 31፡ 14) ፡፡
  • ለቤተ መቅደሱ አገልግሎቶች እቃዎችን(ፅሁፎችን) ተንከባክበዋል (1ዜና መዋዕል 9፡ 28) ፡፡
  • በቤተ መቅደሱ ዉስጥ እቃዎችን፣ ዘይትን እና ቅመሞችን ጠብቀዋል (1ዜና መዋዕል 9፡ 29) ፡፡
  • ለመስዋዕት ቅመሞችን ቀላቅለዋል (1ዜና መዋዕል 9፡ 30) ፡፡
  • ለስጦታዎች ዳቦዎችን (እንጀራዎችን) ጋግረዋል (1ዜና መዋዕል 9፡ 31) ፡፡
  • ለሰንበት እንጀራን አዘጋጁ (1ዜና መዋዕል 9፡ 32) ፡፡
  • ሙዚቃ(መዝሙር) አቀረቡ ( 9፡ 33) ፡፡
  • አዳራሾችን እና የማቅረቢያ ክፍሎችን ተቆጣጥረዋል (1ዜና መዋዕል 23፡ 28፣ 26፡ 20-29) ፡፡
  • የተጋገሩ ህብስቶችን አዘጋጁ (ዘጸ 25፡ 30) ፡፡
  • አቅርቦቶችን እና እቃዎችን ተቆጣጠሩ (1ዜና መዋዕል 28፡ 13-18) ፡፡

ዖቤድኤዶም ለደቡብ በር ሲሾም ልጆቹ ደግሞ የመጋዘን ቤቶች(የግምጃ ቤቶች) ተቆጣጣሪ ነበሩ (ቁጥር 15) ፡፡

1-ዜና መዋዕል (26፡ 20-32)፡ ከሌዋዊያን አንዳንዶች በንብረት ላይ ኃላፊ እንዲሆኑ እና በስልጣን ሌሎች ቦታዎች ላይ እንዲሆኑ የተሰየሙ(የተሾሙ) ነበሩ ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ዖቤድኤዶም ላይ እንደ ተመለከትነው “ የተባረከ “ መሆን ማለት ምን እንደሆነ አላሰስነውም ፤ ይህን ምዕራፍ ሳነበው ዖቤድኤዶም ከወንድሞቹ በላይ በኃይል የተባረከ እንደ ነበር ግልፅ ነበር ፡፡ “ የተበረከ “ መሆን ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ መመልከት እፈልጋለሁ ፡፡

“ ትርጉም “ የሚለው ቃል የአይሁድ አዋቂ ለአድማጮቹ በተለመደ ቋንቋ ብዙ ጊዜ በአረማይክ የሚሰጥበትን የአይሁዶችን መፅሀፍት በሌላ መንገድ የለመተርጎም፣ ለማብራራት እና ለማስፋት የተነገረዉን ይጠቅሳል ፡፡ ለምሳሌ አሜሽ በእያንዳንዱ ሌላ እሁድ ቤተ ክርስቲያን በሚኖራቸዉ ጊዜ በአገልግሎታቸው ፔንስልቨኒያ የጀርመንን ቋንቋ ይጠቀማሉ ፤ ነገር ግን አገልግሎቱ ሲያበቃ ሰዎች በትምህርቱ ላይ በእንግሊዘኛ አስተያየት መስጠት ይችላሉ ፡፡ ትርጉም መፅሀፍ በአንድ ቋንቋ ከተሰጠ በኋላ በራሳቸዉ ቋንቋ የተወያዩበት ነበር ፤ የመፅሀፍ ትርጉም ወይም ትንታኔ ነው ፡፡ በ 1ዜና መዋዕል (13፡ 13-14) ላይ የተባረከ መሆን ምን ማለት እንደ ሆነ የተፃፈ አንድ ትርጉም ነበር ፤ ትርጉሙ በ 1ዜና መዋዕል 13 መጨረሻ ላይ ራሱ መፅሀፍ እንዳልሆነ ይናገራል፡ “ የእግዚአብሄርም ቃል ዖቤድኤዶምን፣ ልጆቹን እና የልጅ ልጆቹን ባረከ እንዲሁም ደግሞ ሚስቱ ፀነሰች የልጆቹ ስምንት ሚስቶች (በህግ ልጆቹን) በአንድ መዉለድ እያንዳንዳቸው ስምንት ወለዱ፣ በአንድ ቀን አባቶችን እና ነጥብ ያላቸዉን ልጆች በአንድ አግኝቶ ነበር ፤ እንዲሁም የእርሱ የሆነዉን ሁሉ በመባረክ በታላቅ ጨመረው “ ፤ (መዝ 127፡ 3-5) ፡፡

ዖቤድኤዶም እዚህ ስፍራ ላይ ተገኘ ምክንያቱም ለሰዎስት ወራት በእግዚአብሄር መገኘት ተከቦ ስለ ነበር ፡፡ ታቦቱ እግዚአብሄር ከህዝቡ ጋር ያደረገዉን ኪዳን፣ በአመፃቸዉ ላይ የተመዘገበን የእግዚአብሄርን ምላሽ (ቅጣት) እና በእግዚአብሄር እና በህዝቡ መካከል የመግባቢያ ምልክት ነው ፡፡ የእግዚአብሄር መገኘት እና ፅየእግዚአብሄር የህጉ ፅላቶች በዖቤድኤዶም ቤት ነበሩ (ዘዳ 6፡ 1-9) ፡፡

መደምደሚያ

በ1ዜና መዋዕል 26 ታቦቱን ለመቀበል እና ለቤተሰቡ ያን ጊዜ ለመጠቀም በበቂ የታመነ የነበረዉ አንድ ሰው ነው ፡፡ እንደ እድል ወደ ቤተሰቦቻችሁ ለማምጣት እንዲህ አይነቱን ጊዜ እንዳታሳልፉ እንደዛ ከሆነ በብዙ የእግዚአብሄርን በረከት መቀበል ትችላላችሁ ፡፡ ሉቃስ (11፡ 28) የእግዚአብሄርን ቃል የሚሰሙ እንደ ሚባረኩ ይናገራል ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville, TN: Thomas Nelson Publishers, 1999), pp. 526–527.

  2. George Knopper, The Anchor Bible Dictionary: 1 Chronicles (New Haven, CT: Yale University Press, 2004), n. p.

  3. Adam Clark, Adam Clark’s Bible Commentary: 1 Chronicles (Nashville, TN: Abingdon Press, 2004), n. p.

ጥያቄዎች

  1. በ 1ዜና መዋዕል (25፡ 1) አሳፍና ኤማን ተጠቅሰዋል ፤ እነዚህን ሰዎች በመፅሀፍ ቅዱስ ሌላ የት ላይ ልናገኘዉ እንችላለን ? (1ዜና መዋዕል 15፡ 19፣ መዝ 50፣ 73-83፣ 88)
  2. በቤተ መቅደስ ተግባራትን ለመስጠት ዕጣን ለምን በማዘጋጀት ይጠቀሙ እንደ ነበር ምን ታስባላችሁ ? (ዘሌ 16፡ 8፣ 1ሳሙ 14፡ 41፣ ምሳ 16፡ 33)
  3. በእናንተ የግል አስተያየትበዮርዳኖስ ምዕራብ በኩል በሁለት እና በግማሽ ነገዶች ላይ ዳዊት ኬብሮዊያንን እንደ አለቃ መሾሙ አላማዉ ምን ነበር ?
  4. በ 1ዜና መዋዕል (25-26) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Chronicles 26:4–5

“Obed-edom also had sons: Shemaiah the firstborn, Jehozabad the second, Joah the third, Sachar the fourth, Nethanel the fifth, Ammiel the sixth, Issachar the seventh, and Peullethai the eighth, for God blessed him.”

ጸሀፊያኑ ዖቤድኤዶምን አስታወሱ እግዚአብሔርም እንዴት እንደ ባረከው አወሱ ፡፡ በስራው በረኛ የሆነ ዖቤድኤዶም የቃል ኪዳኑን ታቦት ወደ ኢየሩሳሌም ይዘው ሲመለሱ መዘምራኑን ተቀላቅሏል ፡፡ ይህ በረኛ እንድሁም ዘማሪ ስምንት ልጆች ነበሩት በተጨማሪም ጸህፊያኑ ከዖቤድኤም ዘር የሆኑ ስድሳ ሁለት ኃያላንን መዝግበዋል ፡፡

ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው ደግሞም ውርስና ሽልማትም ናቸው ፡፡ እግዚአብሔር በቤተሰብ አሳብ ደስ ይሰኛል እንድሁም እንደ ክርስቶስ ተከታይ ወንድ ልጄ ወይም ሴት ልጄ ብሎ ይጠራሃል/ሻል ፡፡ ምናልባት የቤተሰብ ሀሳብ ከባድ ስሜትን ይቀሰቅሳል አንተም ህመም ይሰማሃል ወይም ጉዳትህን ታስታውሳለህ ፡፡ ዛሬ ይህንን የህይወት ክፍልህን መፈወስ እንድጀምር እንድሁም እርቅን እንድያድርግልህ እግዚአብሔርን ጠይቅ ፡፡ በልላ በኩል ልጆች ካሉህ ዛሬ ቆም ልትልና ስለ ልጆች ስጦታው እግዚአብሔርን ልታመሰግን ይገባል ፡፡ ምናልባትም እነርሱን የምታሳድግበትና በእግዚአብሔር ቃል የምታሰለጥንበትን አድስ ጥበብ ይሰጥህ ዘንድ እግዚአብሔርን መለመን ያስፈልግህ ይሆናል ፡፡ በቤተሰብ ሀሳብ ደግሞም በልጆች ማግኘት በእነዚህ ስሜቶች ሁሉ ልታመስግንና ደስ ልትሰኝ ተጠርተሃል ፡፡ ለልጆችህ ፍላጎት እንድሁም በተጨማሪ ጥልቅ ለሆነው ህመምህ በእግዚአብሔር ላይ ሙሉ በሙሉ ስትታመን እግዚአብሔር ያይሃል እንድሁም ደግሞ ይባርክሃል ፡፡ አንተ ልታየው በማትችልበት ጊዜ ሳይቀር እንኳ እርሱ በስራ ላይ ነው ፡፡ ፈቅሩ ዘላለማዊ ነው ፡፡

“እግዚአብሔርም ባርኮታልና ዖቤድኤዶም ልጆች ነበሩት፤ በኵሩ ሸማያ፥ ሁለተኛው ዮዛባት፥ ሦስተኛው ኢዮአስ፥ አራተኛው ሣካር፥ አምስተኛው ናትናኤል ፥ ስድስተኛው ዓሚኤል፥ ሰባተኛው ይሳኮር፥ ስምንተኛው ፒላቲ ። “

—1ኛ ዜና 26:4–5

ተጨማሪ ጥቅስ

  • መዝሙር 127:3–5 — “እነሆ፥ ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው፥ የሆድም ፍሬ የእርሱ ዋጋ ነው ። በኃያል እጅ እንዳሉ ፍላጾች፥ የጐልማስነት ልጆች እንዲሁ ናቸው ። ከእነርሱ ዘንድ ምኞቱን የሚፈጽም ብፁዕ ሰው ነው፤ ጠላቶቻቸውን በአደባባይ በተናገሩ ጊዜ እርሱ አያፍርም ። “
  • ማቴዎስ 5:3 — “በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና ። “
  • ሮሜ 12:18 — “ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ ። “