Historical Books 1 Chronicles

The Power of a Plan

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of David 1 Chronicles 23-24 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 298 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለዚህ ምዕራፍ ሜንዲ ስዕል ላይ እንዲትመለከቱ በኃይለኛዉ እመክራለሁ ፤ ከምርጫዎቼ አንዱ ነው ፡፡ ለዚህ ስዕል ብዙ የተለያዩ ሁኔታዎች አሉ ፤ የወይራ ዘይት ስዕል ነው ፡፡ መሰረት ላይ (ታች ላይ) የሚያድገዉን ኃጢዓት ለመወከል ስሩን ተጠቅማለች ፤ በተጨማሪም ሜንዲ 12ቱን ነገዶች የሚወክሉ 12 ቅርንጫፎችን፣ የክህነት አገልግሎትን የሚወክሉ ሰባት መለከቶችን የዳዊትን የአምልኮ የኑሮ ስርዓት፣ ለክብር አክሊል ለእግዚአብሄር የአንድ ሙሽራን መዝሙር የሚወክል በገናን እና ለእግዚአብሄር ሰዎች የታቀደ እቅዱን የሚወክል በታች ላይ ጥቅሎችን ተጠቅማለች፡፡ ዛሬ በሌዊ ነገድ ላይ ማትኮር እፈልጋለሁ ፡፡

ትምህርት

1-ዜና መዋዕል (23፡ 1)፡ “ በሸመገለ ጊዜ እና እድሜዉን በጠገበ ጊዜ “ የሚለዉ ሐረግ ዳዊትን እንደ ፃድቅ ሰዉ ይገልፀዋል ፤ በዚያ መንገድ የተገለፁ ሌሎች ሰዎች አብርሃም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ እና ሙሴ ነበሩ ፡፡ ዳዊት ከመሞቱ በፊት ሰለሞን እንደ ንጉስ ተቀብቶ ነበር ፤ 1ነገ (3፡ 13-14) ከዳዊት ወደ ንጉስ ሰለሞን ተላልፎ የነበረዉን ተስፋ ይይዛል ፤ ይህ ዉርስ ነበር፣ በረከት ነበር፣ ይህ የንጉስ ዳዊት ፅድቅ ዉጤት ነበር (ዘዳ 5፡ 33) እንዲሁም የረጅም እድሜም መኖር ምሳሌ ነበር ፡፡

1-ዜና መዋዕል (23፡ 2)፡ የእስራኤል መሪዎች የእስራኤል ልዑላን የዳዊት ልጆች ነበሩ ፡፡ 1ዜና መዋዕል (3፡ 1-9) የዳዊትን ዘር ያሳያል ፡፡ ዳዊት ስለመጨረሻዉ ዘመን ሊነጋራቸዉ በህይወት የነበሩትን ልጆቹን በአንድ ላይ ጠራቸው፡፡

1-ዜና መዋዕል (23፡ 3-4)፡ እዚህ ጋር የሌዋዊያን ጠቅላላ 38,000 ተቆጠሩ ፡፡ 30 አመት እና በላይ የነበሩትን ወንዶች ለምን ቆጠሩ (ዘኁ 4፡ 3) ? በተግባር ደረጃ ላይ እነዚህ ወንዶች የሰለጠኑ እና የበሰሉ ነበሩ ፤ ከ 38,000 ወንዶች 24,000 ቤተ መቅደሱን የመገንባት ኃላፊነት ተሰጥቷቸው ነበር ሌሎቹ ባለስልጣኖች እና ዳኞች እንዲሆኑ የተመረጡ ነበር ፡፡

1-ዜና መዋዕል (23፡ 5)፡ እንዲሁም 4,000 ወንዶች በር ጠባቂዎች እንዲሆኑና 4,000 ደግሞ ሙዙቃ መሳሪያ ተጫዋች እንዲሆኑ የተመረጡ ነበሩ ፡፡ ንጉስ ዳዊት አንድ የተረጋጋ ፈጣሪ(ፈልሳፊ) ነበር ፤ ልክ እንደ በገና ብዙ የሙዚቃ መሳሪያዎችን ሰርቷል ፡፡ በጣም የሚናበበዉን በ ኤፌ (4፡ 11) በብሉይ ኪዳን እና በአዲስ ኪዳን መካከል ማየት ትችላላችሁ (1ቆሮ 12፡ 27-31) ፤ ታዋቂ ሓዊሪያ ወይም ፓስተር ስለ መሆን አይደለም የክርስቶስ አካል ስለ መሆን ነዉ እንጂ !

በዚህ ምዕራፍ ላይ ስመለከት ወደ ጫወታዉ ሲመጣ የማየዉ 24,000 ገንቢዎች እንዳስፈለጉ ነው ፤ ዳኞች እና ሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋቾች አስፈለጉአቸው ፤ ሁሉም ያስፈልጉ ነበር ፡፡ በክርስቶስ አካል ዉስጥ ሁላችንም እኩል ነን ፤ አዎ የስልጣን መዋቅር አለ ነገር ግን ሁላችንም እኩል ነን ፡፡ ንጉስ ዳዊት እያደረገ የነበረው የኃይል እቅድ የተገለጠ ነበር - የሚሆነዉን እቅድ በመጣል ፤ እቅዱ የትኛዉ የትኛዉን ስራ እና አሳይመንት እንደሚሰራ መወሰን ነበር ፡፡ በጊዜዉ በምድሪቱ ባለዉ አለመረጋጋት ምክንያት ዳዊት ተግባራቸዉን ሙሉ በሙሉ እንዲረዱ እርግጠኞች ለማድረግ ልጆቹን በአንድ ጠራቸው ፡፡

1-ዜና መዋዕል (23፡ 6)፡ ዳዊት በሌዊ ልጆች መሰረት 38,000 ወንዶቹን ወደ ክፍፍሎች ከፋፈላቸው ፡፡ ከየትኛው ከሌዊ ልጅ ከየትኛዉ ዘር እንደ ነበር የዳዊት ወንዶቹን መከፋፈል እዉነት ነበር ምክንያቱም የቤተሰቡ ማሰሪያ በጣም ጠንካራ እንደ ነበር ተረድቷል ፡፡

1-ዜና መዋዕል (23፡ 7-12)፡ ዳዊት እቅዱን እንዳስቀመጠ ቤተሰብ በቤተሰብ፣ ደረጃ በደረጃ እና ስም በስም ዉስጥ ሰራ ፡፡

1-ዜና መዋዕል (23፡ 13)፡ ይህ የሙሴና የአሮን ማብቂያ የሌለው የመለየት ማስረጃ ነበር (1ጴጥ 2፡ 4-10) ፤ ከአመታት በፊት ሙሴ ዘርቶት የነበረው በ 1ጴጥሮስ ወደ ፍሬማነት እየመጣ ነበር ፡፡ የዘራችሁት የምትሰበስቡት ነው ፤ አሁን የምታደርጉት ወደፊቱን ትዉልድ ላይ ተፅዕኖ ያደርጋል ፡፡ በዚህ በንጉሳዊ ክህነት ሀሳብ ቴርስተገን የፃፈው፡

“ የእግዚአብሄር የተቀቡ ካህናት ዘር

በፍፁም አይጠፉም

በክብሩ ፊቱ በመቆም

ቀን እና ማታ ያገለግሉታል ፡፡

በነዚህ ምክንያቶች ይደሰታሉ አለማመንም

በፅኑ ቆብ ላይ ይፈስሳሉ

የተደበቁትም የእግዚአብሄር ካህናት

እስከ መጨረሻዉ በዚያ ይሆናሉ ፡፡

የመረጣቸዉ ነፍሶች ምድራዊ ቆሻሻቸው

በሚያስፈራዉ እስታ ተበልቷል

ወደ እግዚአብሄር ወደ ራሱ ልብ

በሚቀጣጠል በጠለቀ ፍላጎት

ልባቸዉ ከፍ ይላል ፤

የአምልኳቸው እጣን ቅዱስ

የሆነዉን ቦታ ቤተ መቅደሱን ይሞላል ፤

በሚያስደስት በአዲስ የፃጋ መዝሙር

ከመደነቅ ጋር በመዘመር ሰማያትን ይሞላል ፡፡ “

በንጉሳዊ ክህነት ላይ ለመሳተፍ እናገኛለን ፤ ጴጥሮስ እንዳለው በአንድ ላይ የምንሰራ ህያዋን ድንጋዮች ነን - የክርስቶስ አካላቾ ነን ፤ ማሳያዎች (ድዛይኖች) ነን ፤ የመንፈስ ቅዱስ ህያዉ ድንጋዮች የእቅዱ አካላት ነን ፡፡

1-ዜና መዋዕል (23፡ 25-26)፡ የመሳፍንት መፅሀፍት በትንሹም ቢሆን እብደት እንደ ነበር አስታዉሱ ! እስራኤል በቀድሞዉ ጠላቶቿ ላይ የሰላምን ደረጃ እየተዝናናችበት ነበር ፡፡ አሁን የኪዳኑ ታቦት ደህንነቱ በተጠበቀ ቤተ መንግስት በሚመስል ቤት ይቀመጣል ፤ የዳዊት የድንኳን ማደሪያ ቋሚ ማረፊያ እናለሁሉም እስራኤል እና ያለፈ የማምለኪያ መካከል ላይ ይሆናል ፡፡ ይህ ቅዱስ ቤት ከወርቅ ወይም ከከበረ ድንጋይ የተሰራ አልነበረም ፤ ይህን ቅደሱ የነበረ ስፍራ ስለ ነበር ስፍራውን ቅዱስ አደረገው ፡፡

1-ዜና መዋዕል (23፡ 27)፡ በአጋጣሚሁል ጊዜ ቅዱስ ስፍራዎች ቅዱስ ሆነዉ አይቆዩም ፡፡ ቅርፆችን እና ህንፃዎችን ከእግዚአብሄር በላይ ማምለክ በምንጀምር ጊዜ መገኘቱን ያስወግደዋል ፡፡ የእግዚአብሄር መገኘት በዚህ አዲስ ቤተ መቅደስ ለዘላለም አይቀመጥም ፤ በዚህ የሚነገረዉ ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም በቀጣይነት እንደማይኖር ነው ይህም የሚሆነዉ እግዚአብሄርን ከቤተ መቅደሱ መትተን ስናስወጣዉ ይሆናል ፡፡

መደምደሚያ

ዳዊት በእግዚአብሄር በራሱ ቅባት ስር ለሚገነባዉ ነገር እርምጃ አስቀመጠ ፤ እቅዱን ለእግዚአብሄር አሳልፎ ሰጠ (አስገዛ) ፡፡ በሚመጡት ምዕራፎች ይህን እቅድ እንዴት እንደ ተጫወተዉ እናያለን ፤ ስፖይለር እንደ ሚሳካ ያሳዉቃል (ያነቃል) ! ይህ የእቅድ ደረጃ በምዕራፍ 24 ላይ ይጠፋል (ይቃጠላል) ፡፡ ክምር በክምር ላይ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ንጉስ ዳዊት የህይወቱን ረጅም ህልም እየገነቡ ነበር - ለእግዚአብሄር ቤትን መስራት ለእርሱ ጥቅም ነው ፤ ዳዊት ጉዳዮቹን በስርዓት ስላስቀመጠ ወደ ሰለሞን አገዛዝ ሽግግሩ የተገጣጠመ እና የበቃ ነበር ፤ ማሳያው እቅድ በቦታዉ ስለ ነበር የዚህን እቅድ ኃይል ማየት ጀመርናል ፡፡

  1. Gerhard Tersteegen (1697–1769); quoted in A. W. Tozer, The Christian Book of Mystical Verse (Chicago: Moody Publishing, 2016) pp. 78–79.

ጥያቄዎች

  1. በ 1ዜና መዋዕል (23፡ 3) ህዝብ ቆጠራዊ በሌዋዊያን ብቻ ላይ 30 አመት እና ከዚያ በላይ በነበሩት ላይ የተወሰደዉ ለምን ነበር? (ዘኁ 4፡ 1-4)
  2. ሌዋዊያን ቤተ መቅደሱን እንዲከባከቡ በእግዚአብሄር የታዘዙ ነበሩ ፤ ለተለየ ተግባር ኃላፊነት የተለየን ቤተሰብ የማስቀመጥን ሀሳብ ዳዊት ከየት እንዳገኘዉ ምን ታስባላችሁ ? አነቃቅቶ እንደ ነበር ታስባላችሁ ?
  3. በ 1ዜና መዋዕል (24፡ 2) ናዳብና አብዩድ ከአባታቸዉ በፊት ሞቱ ፤ እንዴት እና ለምን ሞቱ ? (ዘሌ 10፡ 1-2)
  4. በ 1ዜና መዋዕል (23-24) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Chronicles 23:30

“They are also to stand every morning to give thanks and praise to the LORD, and likewise in the evening.”

ንጉሥ ዳዊት ለእግዚአብሔር መገኘት መኖሪያ በሆነው በቤተ መቅደሱ ውስጥ ሌዋውያኑ የሚሰሩዋቸውን ልዩ ተግባራት አስቀመጠ ፡፡ ማደሪያውን መሸከም ከዚያ በኋላ አስፈላጊ ስላልነበር ሌዋውያኑ አድስ የስራ ድርሻን ተቀበሉ ፡፡ በእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት የአሮንን ልጆች እንድያግዙ ተደረገ ፡፡ በተለይም ሁልጊዜ የቤተ መቅደስ መዝሙር አስፈላጊ ነበር ስለዚህ በየጥዋቱና በየማታው ቆመው እግዚአብሔርን ለማመስገንና ለማክበር ይታዘዙ ነበር ፡፡

እንደ አድስ ኪዳን አማኞች የእግዚአብሔር መገኘት ሁልጊዜም ከእናንተ ጋር ነው ፡፡ እርሱ ፈጽሞ ላይተዋችሁ ምሏል ፡፡ ስታወድሱትና ምስጋናን ስታቀርቡለት እግዚአብሔር ደስ ይለዋል ፡፡ እርሱ “ በነገር ሁሉ አመስግኑ “ ይላችኋል ፡፡ ዛሬ አስተዋይ ሁኑ ! በጠዋት መነሳትና እግዚአብሔርን ማመስገንና ማክበር ቃዳሚ ተግባር አድርጉት ! ይህንንም ደግማችሁ በማታ አድርጉት ፡፡ ምናልባትም እራት ከመብላታችሁ በፊት ቆማችሁ ስለ ቀናችሁ እግዚአብሔርን ለምን እንደምታመሰግኑ ለመናገርና ለእርሱ ክብርን ለመስጠት አምስት ደቂቃ ወሰዱ ! አንዳንድ ጊዜ ሀይወት ተራ የተለመደ ይሆናል ፤ አንዳንድ ጊዜም ህይወት የሚያስጠላ ይሆናል ፡፡ በዚህ ሁሉ ግን የእግዚአብሔር መገኘት ከእናንተ ጋር ነው ፡፡ ስለዚህም ቁሙ ተነስታችሁም አመስግኑት ! ዛሬ በእግዚአብሔር መገኘት ትልቅ ቀን ይሆናል ፡፡

“ ሥራቸውም በየጥዋቱና በየማታው ቆመው እግዚአብሔርን ለማመስገንና ለማክበር “

  • 1ኛ ዜና 23፡30

ተጨማሪ ጥቅሰ

መዝሙር 9:1 — “አቤቱ፥ በልቤ ሁሉ አመሰግንሃለሁ፥ ተአምራትህንም ሁሉ እነግራለሁ ። “

መዝሙር 95:2–3 — “በምስጋና ወደ ፊቱ እንድረስ፥ በዝማሬም ለእርሱ እልል እንበል ፤ እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ ነውና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ ታላቅ ንጉሥ ነውና ። “

ማቴዎስ 28:20b — “እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።