The Price of Pride
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of David 1 Chronicles 21-22 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ይህ ክፍል ለ 1ዜና መዋዕል ጭብጣችን የዳዊት ልጅ ላይ ለመገንባት ይቀጥላል ፤ ብዙ ሰዎች የዳዊት “ ዋና ኃጢዓት “ ከቤርሳቤህ ጋር የነበረዉ ኃጢዓቱ እንደ ነበር ያምናሉ ምዕራፍ 21 ግን የዳዊትን ሌላ ኃጢዓት ይገልፃል ፡፡ ሰዎች ስለ ዚህ ኃጢዓት ብዙ ጊዜ ባያወሩም የኢየሩሳሌም ከተማ አጥፍቷል ፤ ይህ ታሪክ በ 2ሳሙኤል 24 ተነግሯል ነገር ግን እንደገና (ደግመን) እናወራበታለን ፡፡
ትምህርት
1-ዜና መዋዕል (21፡ 1)፡ “ ሰይጣን “ ለሚለው ቃል “ጠላት “ ማለትም ነው ፡፡ በዘካ (3፡ 1-2) ዘካሪያስ ታላቁ ካህንን ኢያሱን ለመክሰስ በእግዚአብሄር መልዓክ ፊት ሰይጣንን ቆሞ አየው ፡፡ ሰይጣን ዳዊትን አነሳሳዉ - በመከታተል ዳዊትን አሳመነው - የእስራኤልን ህዝብ እንዲቆጥር ፤ እግዚአብሄር በሆነ ጊዜ የእስራኤልን ህዝብ ቁጥር እንዲቆጥር አዞት ነበር ለመቁጠር የዳዊት ዉሳኔ ግን በኩራቱ ላይ የተመሰረተ ነበር ፡፡ በዮሐንስ ማክአርቱር መሰረት እስራኤልን በመቁጠር አድርጎት ለነበረዉ ነገር ዋጋ በመዉሰድ ከእግዚአብሄር ይልቅ በራሱ ስራ እና ሰዎች ላይ ብዙ መተማመንን በመመስረት ዳዊት ጅማሬ ላይ ነበር ፡፡ ሰይጣን ወደ ዳዊት ኩራት ላይ ማጥመድ ከቻለ ለመዉደቅ ለዳዊት ምክንያት ሊሆን ቻለ ፡፡
2ሳሙ ( 24፡ 1) ግን የሚለው “ ደግሞም የእግዚአብሄር ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ ዳዊትንም ሂድ እስራኤልንና ቁጠር ብሎ በላያቸው አስነሳዉ “ ፡፡ እግዚአብሄር ወይስ ሰይጣን ዳዊት ህዝቡን እንዲቆጥር የነገረው ? ማንኛዉንም ሰይጣን የሚያደርገዉን እግዚአብሄር እንዲያደርግ እንደሚፈቅድለት አስታዉስ ፤ ሰይጣን ይህን ከእግዚአብሄር ፍቃድ ዉጭ አላደረገም ፤ ይህ እግዚአብሄር ሰይጣንን ለአስቸጋሪ ስራ ከመፍቀዱ ጋር የሚወዳደር ሊሆን ይችላል ፡፡ ስለዚህም እግዚአብሄር ዳዊትን እንዲፈትነዉ ሰይጣንን ፈቀደለት ፡፡
ዮሐንስ ማክአርቱር አንዳንድ የሰይጣን ተግባራትን በግልፅ አስቀምጧል ፡፡ አንዱ የሰይጣን ስራ ኃጢዓተኞችን ይዳኛል (ማር 4፡ 15) ፤ ( ሰይጣን ኃጢዓተኞችን ይዳኛል የሚለዉን ንግግሩን ለመግለፅ፡ በመጨረሻ ኢየሱስ ኃጢዓተኞችን ይዳኛል ነገር ግን ኢየሱስ (ጌታ) ሰይጣን በመምጣት ኃጢዓተኞችን ሰብስቦ እንዲወስድ ይፈቅድለታል) ፤ ሌለኛዉ የሰይጣን ስራ ቅዱሳንን ማጥራት(ማንጠር) ነው (ሉቃ 22፡ 31-32) ፡፡ ሰይጣን እግዚአብሄርን “ ስምዖንን ላበጥረዉ ? “ ብሎ መጠየቁን አስታዉሉ የሰይጣን ስራ ድርሻ አማኞችን ማንጠር ነው ፡፡ እግዚአብሄር በትክክል በእርሱ ጠንካሮች ሊያደርገን ሰይጣንን ሊጠቀም ይችላል ፡፡ በዳዊት ጊዜ እምነቱ ስለ ወደቀ በዚህ ቅፅበት መጥራት አልነበረም ፡፡ ሰይጣን በቤተ ክርስቲያን ያሉትንም ለመቅጣት(ለማስተካከል) ይጠቀማል ፤ በ 1ቆሮ (5፡ 1-5) ጳዉሎስ አንድ ከአይምሮ ዉጪ የሆነ ስራን የሰራን ሰዉ ስጋዉን ለማጥፋት ለሰይጣን አዞሮ ሰጠው መንፈሱ ግን ይድናል ፤ በ 2ቆሮ (12፡ 7) ጳዉሎስ ሰይጣን ስለሚጎስመዉ አልታበይም አለኝ ፡፡ በዚህ መገናኘት ከዳዊት ጋር የሰይጣን የመጨረሻዉ ግብ ለመስረቅ፣ ለመግደል እና ለማጥፋት ነበር ፡፡
1-ዜና መዋዕል (21፡ 2-4)፡ ዳዊት ኢዮአብን ከደቡብ ከቤርሳቤህ እስከ ሰሜን ዳን ድረስ እንዲቆጥር አዘዘው ፤ ነገር ግን ኢዮአብ ይህን በማድረግ ለምን በእስራኤል ላይ ጥፋት ታመጣለህ ብሎ ዳዊትን በመጠየቅ ተቃወመው ፤ ነገር ግን የዳዊት ትዕዛዝ አሸነፈ ፡፡ ኢዮአብ ሁሉም ጊዜ በእግዚአብሄር ፍቃድ ላይ በተቃራኒ መሄድ እንደ ሆነ እያወቀ ወታደሮቹን እየቆጠረ በእስራኤል ዉስጥ ተጓዘ ፡፡
1-ዜና መዋዕል (21፡ 5-7)፡ በዚህ ታሪክ ያለዉን ቆጠራ በ 2ሳሙኤል 24 ላይ ካለዉ ቆጠራ ጋር አወዳድሩ ፡፡ ዮሐንስ ማክአርቱር በዚህ ላይ ጥሩ የሆነ እይታን ይሰጣል ፡፡ የሰለጠኑ 800,000 ወታደሮች እያሉ በጦር ተጠባባቂነት እድሜአቸዉ የደረሰ 300,000 ነበሩ ፡፡ በይሁዳ በ470,000 እና በ500,000 ወንዶች መካከል የነበረዉ ልዩነት ከብንያም ወገን የነበሩት 30,000 ሰዎች ነበሩ ፡፡ አስታዉሉ በ 1ዜና መዋዕል (21፡ 6) ኢዮአብ ሌዋዊያንን ወይም ከቢኒያም የሆኑትን ሰዎች አልቆጠረም ፡፡ ዳዊት አድርጎት የነበረው በእግዚአብሄር ፊት እንደ ክፉ የሚታይ ስለ ነበር እስራኤልን አስቀሰፈ ፤ ኃጢዓት ሁል ጊዜ ቁጣን ያመጣል ፡፡
1-ዜና መዋዕል (21፡ 8-13)፡ ዳዊት ኃጢዓት በሰራ ጊዜ ሁል ጊዜ የሚያስደንቅ ንስሀ መግባት ነበር ፡፡ ዳዊት ኃጢዓት እንደ ሰራ በማወቁ ንስኃ ገባ ፤ የእግዚአብሄር ታላቅ ወንዶች እና ሴቶች ሁል ጊዜ ኃጢዓት ማድረጋቸዉን እዉቅና ይሰጣሉ ፡፡ የኃጢዓት ጥፋተኝነት በህዝብ ላይ ይከብዳል ፡፡ እግዚአብሄር ለቅጣቱ ከሰዎስቱ ምርጫዎች እንዲመርጥ ለዳዊት እንዲነግረው ባለ ራዕዩን ጋድን ላከው ፤ እግዚአብሄር ይህን ያደረገበት በመፅሀፍት ብቸኛዉ ጊዜ ነው ፡፡ ከሰዎስቱ ምርጫዎች ዳዊት በእግዚአብሄር እጅ መዉደቅን መረጠ ምክንያቱም ከሰዉ እጅ ዉስጥ ከመዉደቅ ይልቅ ምህረቱ ስለሚሻል ፡፡ ዳዊት ቅጣቱ መልካም እንደ ማይሆን ያዉቃል ነገር ግን በቁጣ መሀከል እንኳን ሆኖ በእግዚአብሄር ምህረት መታመን መረጠ ፤ የእግዚአብሄር ምህረት በየማለዳዊ አድስ እንደ ሆነ ተረድቷል፡፡
1-ዜና መዋዕል (21፡ 14-15)፡ እግዚአብሄር በእስራኤል ላይ አንድ መቅሰፍት በመላኩ 70,000 ሰዎች ሞቱ ፤ ከዚያም እግዚአብሄር ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት አንድ መለዓክ ላከ ፤ ነገር ግን በጥፋቱ ሂደት ላይ እግዚአብሄር መልዓኩን እጁን እንዲያስወጣ(እንዲመልስ) አዘዘው ፡፡ ይህ አብርሃምን፣ ጌዲዎንን እና የሳምሶንን ቤተሰቦች የጎበኘዉ መለዓክ ሊሆን ይችላል ፤ እንዲሁም በፋሲካ ላይ በሞት መንፈስ ተገልጦ የነበረዉ መለዓክ ሊሆን ይችላል ፤ ይህ በኢየሩሳሌም ሰይፉን በመምዘዝ የታየው ራሱ ክርስቶስ ሊሆን ይችላል ፡፡ ኦርናን በዳዊት ኃጢዓት ምክንያት የእግዚአብሄርን ቁጣ የምትቀበል ነበረች ፡፡ ተመሳሳይ ነገር ተመሳሳይ ነገር ሆኗል ፤ በአንድ ሰዉ በአዳም ኃጢዓት ምክንያት የእግዚአብሄርን ቁጣ እኛም መቋቋም አለብን ፡፡
1-ዜና መዋዕል (21፡ 16-22)፡ ዳዊት የእግዚአብሄርን መለዓክ እጁን በኢየሩሳሌም ላይ ዘርግቶ ባየዉ ጊዜ እርሱና ሽማግሌዎች በእግዚአብሄር ፊት ተደፉ ፤ ዳዊት በኃጢዓቱ ምክንያት እስራኤል የእግዚአብሄር መዓት እንደ ገጠመዉ አዉቋል ፡፡ ዳዊት ኃጢዓተኛዉ እርሱ እንደ ሆን በመናዘዝ ስለ እርሱ ኃጢዓት “ እነዚህ በጎች “ ምንም የማያዉቁ ሰዎች ችግር እንዳይገጥማቸዉ ለመነ ፡፡ የእግዚአብሄር መለዓክ ጋድን ዳዊትን በኢያቡሳዊዉ ኦራን አዉድማ መሰዊያ እንዲሰራ እንዲነግረዉ አዘዘው ፤ ኦርና ዞሮ መልዓኩን ባዬ ጊዜ ስንዴ እየወቃ ነበር (ቁጥር 20) ፤ ዳዊት ኦርናን የመዉቂያ አዉድማዉን ለመግዛት ሙሉ ዋጋዉን አቀረበ ፡፡ ይህ ቦታ አብርሃም ልጁን ይስሐቅን ለመሰዋት ፍቃደኛ ሆኖበት የነበረዉ ሞሪያ ተራራ ጋር ተመሳሳይ ነበር ፡፡
1-ዜና መዋዕል (21፡ 23-30)፡ ኦርና መሬቱን ለመስጠት ለዳዊት አቀረበ እንዲሁም ደግሞ ለመስዋዕት በሬዎችን እና ስንዴዉንም ለመስጠት አቀረበ ፡፡ ኦርና ለመስዋዕት የሚያስፈልገዉን ሁሉ በመስጠት ስለ ህዝቡ ጣልቃ ገባ ፤ ነገር ግን ዳዊት ሙሉ በመክፈል ላይ ሙጭጭ አለ ፡፡ ይህ በአጠቃላይ በመስዋዕቱ የተጠቀመዉ የሁሉም ነገር ጠቅላላ ዋጋ 15 ፓዉንድ ወርቅ እንደመዘገበ ይናገራል ፤ ከዚያም ዳዊት መሰዊያዉን በመስራት የሚቃጠል መስዋዕት እና የደህንነት መስዋዕት አቀረበ ፡፡ ይህ ስፍራ በኢየሩሳሌም በአሁኑ ጊዜ የቆመው የዶም አለት አላስካ መስጊድ ነው ፤ በሌለኛዉ በኩል ወደ ደብረ ዘይት ተራራ የሚመራዉ ታላቁ በር (ወርቃማዉ በር ) ነው ፡፡ አንድ ቀን ኢየሱስ በዚያ በር ይመጣል በዚህ ምድር ላይ ራሱን እንደ ንጉስ ደግሞ ያቋቁማል ፤ እግዚአብሄር ለዚች ምድር አላማ እንዳለዉ የሚመስል ነው ፤ ህዝቡን ለማዳን እና ለመዋጀት እቅድ አለው ፡፡ ዳዊት መስዋዕቱን በማድረግ እግዚአብሄርን በተጣራ ጊዜ እግዚአብሄር ከሰማይ በእሳት መለሰለት ፡፡ በቀርሜሌዎስ ተራራ ላይ በኤልሳዕ መዝገብ ላይ ከሰማይ የሆነዉን እሳት በተለየም እናስባለን ፤ ይህ በብዙ በኦርና መዉቂያ አዉድማ ላይ ሆነ ፤ በምህረቱ ምክንያት እግዚአብሄር ከተማዋን አዳነ …. ዳዊትም ያን እንደሚያደርግ በእግዚአብሄር ታመነ ፡፡ ዳዊት በእግዚአብሄር መገኘት በዚያዉ ቆየ(ተቀመጠ) ፡፡
መደምደሚያ
ሌሎችን በማስወገድ በኃይል የምንቆሽሽበት ጊዜያት ይገጥሙናል ፤ ነገር ግን በንስሃ ልብ በእግዚአብሄር ፊት በምንመጣ ጊዜ (2ዜና መዋዕል 7፡ 14) እግዚአብሄር ይመልሳል ፡፡ ንስሃ በመግባት ወደ እግዚአብሄር በምንመለስ ጊዜ እግዚአብሄር እንደ ሚመልስልን ማወቅ እንችላለን ፤ ቁጣ እንኳን የሚገባን ቢሆንም ክርስቶስ በመስቀል ላይ ባደረገው ምክንያት ይቅርታ ማግኘት እንችላለን ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 487.
MacArthur, p. 487.
MacArthur, p. 487.
MacArthur, p. 487.
MacArthur, p. 487.
ጥያቄዎች
-
በ 1ዜና መዋዕል (21፡ 1) ሰይጣን የተዋጊ ሰዎቹን እንዲቆጥር ከዳዊት ጀርባ ነበር ፤ 2ሳሙ (24፡ 1) ይህን እንዲያደርግ እግዚአብሄር በመልካም ለምን እንዳነሳሳዉ ምን ታስባላችሁ ?
-
የህዝብ መቁጠር የዳዊት ኃጢዓት ታሪክእና እግዚአብሄር በእስራኤል ላይ ባመጣው ቅጣት በእግዚአብሄር ህዝብ ላይ መሪዎች ስለ ሆኑት የሆነ ነገር ያስተምረናል (ያዕ 3፡ 1) ? በአዳም ኃጢዓት በሁሉም ሰብዓዊ ላይ የመጣዉን ዉጤት ምክንያቱን እና ጉዳቱን እንዴት ታዩታላችሁ ?
-
ለእግዚአብሄር ለሚሰራዉ ቤት ብዙ ነገር ሚሰጡ እንግዶች ዳዊት መኖሩ አስፈላጊ ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ ? አዎ ከሆነ እንዴት ነበር አስፈላጊ የነበረው ?
-
በ 1ዜና መዋዕል (22፡ 9) መሰረት ለዳዊት ልጅ “ ሰለሞን “ የሚለዉን ስም ማን ነበር የመረጠው ? ይህ ስም ምን ማለት ነው ? ኢየሱስም ሰላም የሚል ትርጉም ያለዉን ስም የተሸከመዉ እንዴት ነው ? (ኢሳ 9፡ 6)
-
1ዜና መዋዕል (22፡ 10) ፤ ከሰለሞን ቀጥሎ ብዙ ጊዜ እንደ ዳዊት ልጅ ይጠቀስ የነበረው ማን ነበር (ማቴ 1፡ 1፣ ማር 10፡ 47፣ ሉቃ 18፡ 38) ? ይህን ጥቅስ ኢየሱስ እንዴት ፈፀመው ?
-
በ 1ዜና መዋዕል (21-22) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Chronicles 21:1–2, 8
“Satan stood up against Israel and incited David to count the people of Israel. So David said to Joab and the commanders of the troops, ‘Go and count Israel from Beer-sheba to Dan and bring a report to me so I can know their number.’ . . . David said to God, ‘I have sinned greatly because I have done this thing. Now, please take away Your servant’s guilt, for I’ve been very foolish.’”
ዳዊት በውጊያ ድል አድራጊ ነበር እንድሁም ብዙ ወታደሮችን አከማችቶ ነበር ፡፡ በዚህ የስኬት ጊዜ ሰይጣን የእስራኤልን ህዝብ እንድቆጥር በማነሳሳት ዳዊትን ፈተነው ፡፡ እግዚአብሔር ፈጽሞ ህዝቡን ይቆጥር ዘንድ ዳዊትን አላዘዘውም ደግሞም ይህ በእርሱ ፊት ጸያፍ ነበር ፡፡ ምንም እንኳ የእግዚአብሔር ታላቅ ምህረት በመጨረሻ እስራኤልን ቢያተርፍም የትዕቢት ኃጢአት አሁንም ትወልዱን ጎዳ በተጨማሪም ሰባ ሽህ የእስራኤል ሰዎች ሞቱ ፡፡ ከዚህ በኋላ ዳዊት በእግዚአብሔር ይቅር ባይ ፍቅርና ምህረት የተነሳ እግዚአብሔርን በትህትና እና በመታዘዝ መገልገሉን ቀጠለ ፡፡
ብዙውን ጊዜ ትዕቢት ራሱን የተደበቀና የግል ኃጢአት አድርጎ ነው የሚገልጠው ፡፡ በተለያዩ መንገዶችም ሊታይ ይችላል ፡- እርዳታን ከመጠየቅ መኩራት ፣ የተወሰኑ ስራዎችን ለመስራት በጣም ጥሩ መሆን ፣ ሌሎችን መተቸት ፣ የሌሎችን ምክር አለመቀበል ወይም ቀድመህ በሰውነት አቋምህ መመካት ፡፡ ልክ የዳዊት ትዕቢት ህዝቡን እንደጎዳና ከሞላ ጎደልም ህዘቡን እንዳጠፋ ፤ የአንተም ትዕቢት የሌሎችን ህይወት በከባዱ ይጎዳ ዘንድ ይችላል ፡፡ ሆኖም ግን ተስፋ አለ ፡፡ ከኢየሱስ ጋር ስትራመድ እርሱ ለአንተ የሚሻው ሁሉንም ጥረትህን በትህትና እና ከራሰ ወዳድነት በነጻ መንገድ ለመኖር እንድታደርገው ነው ፡፡ በልብህ የታበይክባቸው ነገሮች ካሉ እግዚአብሔርን ጠይቅ ፡፡ ከዚያም ይህን ኃጢአት ተናዘዝ ይቅርታንም ለምን ፡፡ ጸጋውና ምህረቱ ህይወትህን እንድያጥለቀልቅ ስትፈቅድ እግዚአብሔር በጸጋና ሌሎችን በመውደድ የተሞላ ንጹህን ልብ ይፈጥርልሃል ፡፡
“ ሰይጣንም በእስራኤል ላይ ተነሣ፥ እስራኤልንም ይቈጥር ዘንድ ዳዊትን አንቀሳቀሰው ። ዳዊትም ኢዮአብንና የሕዝቡን አለቆች፦ ሂዱ፥ ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ዳን ድረስ እስራኤልን ቍጠሩ፥ ድምራቸውንም አውቅ ዘንድ አስታውቁኝ አላቸው ። …. ዳዊትም እግዚአብሔርን፦ ይህን በማድረግ እጅግ በድያለሁ፤ አሁን ግን ታላቅ ስንፍና አድርጌአለሁና የባሪያህን ኃጢአት ታስወግድ ዘንድ እለምንሃለሁ አለው ። “
-1ኛ ዜና 21፡1-2 ፣ 21፡8
ተጨማሪ ጥቅስ
- ፊልጵስዩስ 2፡3 – “ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ “
- ያዕቆብ 4:6 — “ ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ፦ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ይላል ። “
- 1ኛ ዮሐንስ 1:9 — “በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።