Historical Books 1 Chronicles

David Expands and Establishes His Kingdom

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of David 1 Chronicles 19-20 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 296 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በ 1ዜና መዋዕል 18 ዳዊት ፍልስጤማዊያንን በመቆጣጠር ጋዛን ወሰደ ፤ ሞዓባዊያንን በመቆጣጠር በሞዓብ መንግስቱን መሰረተ ፤ ከዚያም በመላዉ ምድሪቱ መንግስቱን ወደ ሚመሰርትባት ወደ ያዛቸዉ ሌሎች ህዝቦች ቦታ ከኤፍራጠስ ወንዝ በታች ወረደ ፡፡ በዘፍጥረት እግዚአብሄር አብርሃምን ዘሩ ምድረቲቱን እንደ ሚይዝ ቃል ገባለት ፤ አሁን ዳዊት የምድሪቱን ንብረት ሲወስድ እናያለን ፡፡ ዳዊት በመላዉ እስራኤል ላይ ገዛ ለሁሉም ህዝቡም ፍትህን አደረገ (1 ዜና መዋዕል 18፡ 14) ፡፡

ትምህርት

1-ዜና መዋዕል (19፡ 1)፡ የአሞናዊያን ንጉስ ናዖስ ሞተ ልጁም በአሞን ላይ ንጉስ ሆነ ፡፡ በ 1ሳሙ (11፡ 1-6) ከናዖስ ጋር ስምምነት ለማድረግ እስከ ጠየቁት ድረስ ናዖስ በኢያቢስ ገለዓድ እስራኤልን አጥቅቶ ነበር ፡፡ ናዖስ በስምምነቱ ላይ አንድ ሁኔታን አስቀመጠ - እስራኤልን ለማዋረድ የሁሉንም ቀኝ አይን ማዉጣት ፤ ናዖስ እስራኤልን መያዝ ብቻ አልነበረም የፈለገው ነገር ግን እነርሱንም እንደ ሞኝ ማድረግ ፈለገ ፡፡ የኢቢስ ሽማግሌዎች በሁሉም እስራኤል መልዕክተኞችን ለመላክ ሰባት ቀን ጠየቁ ፤ ሳዖል ስለ ስምምነቱ በሰማ ጊዜ የእግዚአብሄር መንፈስ በእርሱ ላይ ወረደ ናዖስንም ፈራዉ ፡፡ ሳዕል ከኢያቢስ ገለአድ ጋር በነበረዉ ስምምነት ለምን ተበሳጨ ? መልሱ እስራኤል የኢያቢስ ገለዓድ ከተማ በማጥቃት ከቢንያም ለነበሩት ወንዶች ከተዉአቸዉ አራት መቶ ድንግል ሴቶች ዉጪ ሁሉንም ነዋሪዎች ሲገድሉ በ መሳፍንት 21 መልሱ ይገኛል ፡፡ ሳዖል ከቢንያም ነገድ ስለ ነበር ናዖስ ከተማዋን በአስፋራራ ጊዜ ተበሳጨ ፤ ሳዕል እጆቹን በማንሳት አሞናዊያንን አጠቃ ጥቂት የተረፉ ሰዎች ብቻ አመለጡ ፡፡

1-ዜና መዋዕል (19፡ 2)፡ ዳዊት ለናዖስ ልጅ ለሐኖን ቸርነት ለማሳየት ወሰነ ምክንያቱም ናዖስ ለዳዊት ቸርነትን አሳይቶት ስለ ነበር ፤ ሐዋ (13፡ 21) ሳዕል ለ 40 አመታት ንጉስ እንደ ነበር ነገር ግን ትክክለኛ ስልጣኑ የትም ቦታ ከ 12-20 አመታት እንደ ነበር ለማመልከት የአገዛዙን መግለጫ ለማንበብ አንዳንድ ምሁራን ይተዋሉ ፡፡ በሳዖል እና በናዖስ መካከል ግጭቱ በስልጣኑ መጀመሪያ ላይ ተፈጠረ ፤ ዳዊት በሁኔታዉ ላይ በመጣ ጊዜ በግዞት ኖረ ምክንያቱም ሳዖል ዳዊትን በማሳደድ ሊገድለዉ ሞከረ ፡፡ በጊዜዉ ዳዊት ከሳዖል እየሮጠ በነበር ጊዜ ናዖስ ለዳዊት ርህራሄ አደረገለት ፤ አሞናዊያን የእስራኤል ጠላት ቢሆኑም የዳዊት ልብ የሰላም አስፋኝ ልብ ነበር ፤ ስለሆነም ናዖስ በሞተ ጊዜ ዳዊት ስለ ሞቱ ለማዘን አፅናኞችን ላከ ፡፡

1-ዜና መዋዕል (19፡ 3-5)፡ የዳዊት የርህራሄ ድርጊትን ሳይቀበል ሐኖን መልዕክተኞቹን ፂማቸዉን እንዲላጩአቸው እና ልብሳቸዉን እወገባቸዉ ላይ እንዲቀድዱት አዘዛቸው ፡፡ በቀደሙት ጊዜያት ፂም የወንድነት ምልክት በመሆን በእስራኤላዊያን ባህል እና ኃይማኖት አስፈላጊ ነገር ነበር ፡፡ ዳዊት ርህራሄን ቢያሳይም እንኳን ሐኖን በክፉ መለሰለት ፤ የሐኖን ድርጊት በዙ ወንዶችን ህይወታቸዉን በማሳጣት ጀመረ ፡፡ ዳዊት በእርሱ ሰዎች ላይ የሆነዉን በሰማ ጊዜ ፂማቸዉ ተመልሶ እስኪያድግ ድረስ በኢያሪኮ እንዲቀመጡ አበረታታቸው ፡፡

1-ዜና መዋዕል (19፡ 6-7)፡ አሞናዊያን የዚህን ድርጊት ዉጤት ስላወቁ ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት እንዲያግዟቸው ሶሪያዊያንን ከሰለገሎቻቸዉ እና ከፈረሶቻቸዉ ጋር በብራቸዉ ቀጠሩዓቸው ፡፡ አሞናዊያን እና ሶሪያዊያን ለጦርነት በሜዳብ ሸለቆ ላይ ተሰበሰቡ ፡፡

1-ዜና መዋዕል (19፡ 8-13)፡ ዳዊት የአሞናዊያንን ጦር እንዲገናኙ ኢዮአብን እና ሁሉንም ጦሩን ላከ ፤ ኢዮአብ ጦሩ በእርሱ ላይ እንደ ከበበዉ ባዬ ጊዜ ብዙ ቁጥር እንደ ነበር አወቀ ፡፡ ኢዮአብ ኃይሉን በእርሱ እና በወንድሙ በአቢሳ መካከል ዉጊያዉን ለማሸነፍ ባስፈለጋቸዉ ጊዜ እያንዳንዳቸዉ ሌለኛዉን እንዲረዱ በማድረግ ከፋፈላቸዉ ፡፡ ኢዮአብ ጦሩን “ እንዲጠነክሩ ! “ አሳሰባቸዉ ንግግሩም የሙሴን ንግግር ለኢያሱ ያለዉን ያስተጋባል ፡፡ ወታደሮቹንም በእግዚአብሄርን እና ብሏቸዉ በነበረዉ እንዲታመኑ አበረታቸው ፡፡ ኢዮአብ ጠላቶቻቸዉን እንዲዋጉ (እንዲከፋፍሉ እና እንዲይዙአቸው) ጦሩን የከፋፈለ ቢሆንም አንዱ ቡድን በትግል ላይ በሚሆን ጊዜ እርስ በእርስ እርዳታ እንዲሰጣጡ አዘዛቸው ፡፡

የክርስቶስም አካል በተመሳሳይ ቡድን ላይ ነው ፡፡ ሁላችንም የራሳችንን ዉጊያ እየተዋጋን ነዉ ነገር ግን በዉጊያ መሸነፍ የጀመሩትን ለመርዳት ፍቃደኞች ልንሆን ያስፈልገናል ፤ ባስፈለግናቸዉ ጊዜ ወደ ሌሎች መፍሰስ እንዲሁም ባስፈለጉን ጊዜ ወደ እኛ እንዲፈሱ ፍቃደኞች መሆን ያስፈልገናል ፡፡

1-ዜና መዋዕል (19፡ 14-16)፡ ሶሪያዊያን ከኢዮአብ ሸሹ አሞናዊያን ደግሞ ከአቢሳ ሸሹ ፡፡ ኢዮአብ እና አቢሳ ኢየሩሳሌም ከተማ ገቡ ፡፡ ሶሪያዊያን ሽንፈታቸዉን በማያት ለማጠናከር በኤፍራጠስ ዙሪያ እንዲጣሩ መልዕክተኞችን ላኩ ፡፡

1-ዜና መዋዕል (19፡ 17-19)፡ ዳዊት እያደረጉ የነበረዉን ባዬ ጊዜ እስራኤልን በመሰብሰብ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻገረ ፤ ሙሉ የእስራኤል ጦርም በእነርሱ ላይ ተሰለፉ ሶሪያዊያንም ከእስራኤል ፊት ሸሹ ፡፡ ዳዊት 7,000 ሰረገለኞች፣ 40,000 እግረኞችን እና የጦራቸዉ አዛዦችን ገደለ ፤ በደንብ ስላሸነፋቸው ሶሪያዊያን ከእስራኤል ጋር ሰላም በማድረግ የዳዊትም ገባሪ ሆኑ ፤ ደግመዉ በፍፁምም አሞናዊያንን አልረዱም ፡፡

ዳዊት የጠላቶቹን ምድር ወስዶ ስለ ነበር ጠላቶቹ ሁል ጊዜ በመበቀል መልሰዉ ለመዉሰድ ሞከሩ ፤ ይህን በአሞናዊያን በኖዖስ ልጅ እና በሶሪያዊያን አይተነዋል ፡፡ በአሁኑ ጊዜ እስራኤል አሁንም በትርምስ ነች ምክንያቱም እግዚአብሄር የእስራኤል ነዉ ያለዉን መልሰዉ ለመዉሰድ እየሞከሩ ስለሆነ ፡፡ ጠላቶቿ አሁንም እየተዋጉ ነዉ ነገር ግን እስራኤል እና ኢየሩሳሌም አሁንም አሉ ፡፡

1-ዜና መዋዕል (20፡ 1-3)፡ ሶሪያዊያን ተስፋ የቆረጡ ቢሆንም አሞኒያን ግን አልቆረጡም ነበር ፡፡ በዘመን መለወጫ ላይ ኢዮአብ የእስራኤልን ሰራዊት በረባት ላይ በአሞናዊያን ላይ በመዝመት አጠፋት ፤ ነገር ግን ዳዊት በኢየሩሳሌም ቀረ ፡፡ ዳዊት በኢየሩሳሌም በተቀመጠ ጊዜ ምን እንደሆነ ታስታዉሳላችሁ ? ዳዊት ከቤርሳቤህ ጋር ኃጢዓት ያደረገበት ጊዜ (2ሳሙኤል 11) እና ኦሪዮን ከጦር ሜዳ ያስጠራበት ጊዜ ነበር ፡፡ ኢዮአብ በረባት ላይ በመዋጋት የዉሃ አቅርቦቷንም ያዘ (2ሳሙ 12፡ 26) ፤ በታሪክ በዚህ ዘመን የከተማዋን ዉሃ አቅርቦት መያዝ ማለት በእርግጠኝነት ማሸነፍ ማለት ነው ፤ ያለ ዉሃ መኖር ስለ ማይችሉ ፡፡ ኢዮአብ ለዳዊት “ ለመታየት እና ከተማዋን ለመያዝ ጊዜዉ እንደ ሆነ “ አንድ መልዕክት ላከ ፡፡ ኢዮአብ ለዳዊት በኢየሩሳሌም ከተማ በመቀመጡ ፋንታ በጦርነቱ ትክክለኛ ስፍራ ቦታዉን እንዲወስድ እየጠራዉ ነበር ፤ ዳዊት ወደ ጦር ሜዳ በመጣ ጊዜ እስራኤል አሞንን ተቆጣጥራለች ፡፡ በዳዊት ኃጢዓት ከቤርሳቤህ እና ከኦሪዮ ጋር በሂደት ዉስጥ እንኳን ቢሆንም እግዚአብሄር ዳዊትን እና ስልጣኑን መለሰለት ፡፡

አንዳንድ ጊዜ እነዚህን ታሪኮች ሁሉንም ነገር ሳናሰላስል አንብበናል ፤ በ ሪቫይቭ ት/ቤት መፅሀፍትን በአንድ ላይ በማምጣት ሁሉም እንዴት በትልቅ ስዕል እንደሚጣጣሙ ለማየት እየሞከርን ነው ፡፡

1-ዜና መዋዕል (20፡ 4-8)፡ ይህን ምዕራፍ ስናጠናቅቅ ዳዊት የቀሩትን የፍልስጤም ኃያላን ለመግደል እስራኤልን መራ ፤ ጠላት ምንም ቢያደርግ ችግር የለም የእግዚአብሄርን ሉዓላዊ እቅድ እናያለን ፡፡ ዳዊት እና ኃያላን ሰዎቹ ሁሉንም ነገር በትክክል ባያደርጉም እንኳን የዳዊት ልብ እግዚአብሄርን ማገልገል ነበር ፤ እግዚአብሄር በመገለጥ ነፃ አወጣቸው ፡፡ ጠላቶቻቸዉ በፊታቸዉ ሸሹ ምድሪቱን በማሸነፍ እና መያዝ ቀጠሉ ፡፡

መደምደሚያ

በአሁኑ ጊዜ በህይወታችሁ እየሆነ ባለዉ ችግር የለዉም እግዚአብሄርን መታን መቀጠል ትችላላችሁ ፤ ጠላቶቻችሁ ምንም ይሁኑ ወይም በአሁኑ ጊዜ በእናንተ ላይ ይምጡም ችግር የለዉም ልክ እንደ ዳዊት እግዚአብሄር ለተስፋዉ የታመነ እንደ ሆነ ማመን ትችላላችሁ ፡፡

ጥያቄዎች

  1. በ 1ዜና መዋዕል (19፡ 1-5) ሐኖን የዳዊትን ሰዎች ለምን በመጥፎ ተቀበላቸዉ ? ለምን በጣም ያፈሩ እንደ ነበር ምን ታስባላችሁ ? ፂማቸው እስኪያድግ ድረስ ዳዊት ወደ ኢያሪኮ ሲልካቸው ቅጣት ነበር ? ለምን ወይስ ለምን አልነበረም ?
  2. በ 1ዜና መዋዕል (19፡ 14) ሶሪያዊያን ከኢዮአብ እና ከሰዎቹ በፊት ሸሹ ፤ ጠላቶች ሲሸሹ ሌላ የት ላይ አይተናል ? (ዘዳ 32፡ 30, ያዕ 4፡ 7)
  3. በ 1ዜና መዋዕል (20፡ 4-8) ብዙ የአስፈሪዎቹ ሰዎች ልጆች(ዘሮች) በዳዊት ሰራዊት ተገደሉ ፤ ከግዙፎቹ (ከኃያላኖቹ) ጋር ሲገናኙ ያየነዉ ይህ የመጀመሪያ አይደለም ፤ ሌላ የት ነበር ተሸንፈዉ የነበረው ? (1ሳሙ 17፡ 32-50)
  4. በ 1ዜና መዋዕል (19-20) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Chronicles 19:12-13

“‘If the Arameans are too strong for me,’ Joab said, ‘then you’ll be my help. However, if the Ammonites are too strong for you, I’ll help you. Be strong! We must prove ourselves strong for our people and for the cities of our God. May the LORD’s will be done.’”

ሶርያውያን በእስራኤል ጦር አዛዥ በኢዮአብ ፊት ለጦርነት ተሰለፉ ፡፡ ከዚያም ኢዮአብ አሞናውያንም ከኋላው ለጦር እንደተሰለፉ አወቀ ፡፡ እርሱም ሶርያውያንን በግንባር ይፋለሙ ዘንድ ሰዎችን ለየ ፡፡ የቀረውንም ህዝብ ከጦሩ ጀርባ የተሰለፉትን አሞናውያንን ይዋጉ ዘንድ ለወንድሙ ሰጠው ፡፡ ወንድሙንም “ አይዞህ ! ጦርነቱ ከከበደኝ አንተ ትረዳኛለህ እንድሁም ጦርነቱ አንተን ከከበደህ እኔ እረዳሃለሁ ! “ አለው ፡፡ እግዚአብሔር በዚህ ውጊያ ድልን ሰጣቸው ፡፡

እንደ ክርስቶስ አማኝ እግዚአብሔር መንፈሳዊ ውጊያዎች እንደሚገጥሙህ ይናገራል ፡፡ በእነዚህ ውጊያዎች ድካም ይሰማህ ይሆናል ወይም በእግዚአብሔር ላይ ትናደድ ይሆናል እንድሁም ጉዞህን ለመቀጠል አቅም እንደሌለህ ታስብ ይሆናል ፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ፈጽሞ ብቻህን እንዳልሆንክ አስታውስ ፡፡ እግዚአብሔር ሁልጊዜም ከአንተ ጋር ነው እንድሁም ጦርነቱን እንድትዋጋ ይረዱህ ዘንድ ፣ ይጸልዩልህ ዘንድ ፣ በሚያበረቱ ቃላት የበረቱህ ዘንድ እንድሁም እውነቱን ያስታውሱህ ዘንድ በክርስቶስ ወንድሞችና እኅቶች አሉህ ፡፡ ዛሬ የገጠመህ ምንም ይሁን ራስህን ትሁት አድርገህ ወደ ጓደኞችህ ሂድ ፡፡ ውጊያው ለብቻህ ከበዛብህ ለእነርሱ ንገራቸውና እርዳታን ጠይቅ ፡፡ በጌታ ላይ ጠንክር እርሱም ድልን እንደሚሰጥህ እመን ፡፡

“ እርሱም፦ ሶርያውያን ቢበረቱብኝ እርዳኝ የአሞንም ልጆች ቢበረቱብህ እረዳሃለሁ ። አይዞህ፥ ስለ ሕዝባችንና ስለ አምላካችንም ከተሞች እንበርታ እግዚአብሔርም ደስ ያሰኘውን ያድርግ አለ ። “

  • 1ኛ ዜና 19፡12-13

ተጨማሪ ጥቅስ

ኢሳይያስ 43:2 — “ በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም ። “

ገላትያ 6:10 — “ እንግዲያስ ጊዜ ካገኘን ዘንድ ለሰው ሁሉ ይልቁንም ለሃይማኖት ቤተ ሰዎች መልካም እናድርግ ። ”

ፊልጵስዩስ 2:4 — “ እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ ። “