The Lord's Covenant With David
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of David 1 Chronicles 17-18 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
1 ዜና መዋዕል 17 2ሳሙኤል 7 እየደገምን ነዉ የሚመስለው ፤ የሁለቱን ምዕራፎች ፅሁፍ በምናወዳድር ጊዜ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ አንድ አይነት ናቸው ፡፡ ለ 1ዜና መዋዕል ቃላችን የዳዊት ልጅ የሚል መሆኑን አስታዉሱ ፤ ይህ በብሉይ ኪዳን ቁልፍ ምዕራፍ ነው ፡፡ ይህን መግለጫ በፊት የተመለከትነዉም ቢሆንም እንኳን ዛሬ ከተለያየ አስተሳሰብ አንፃር እንመለከተዋለን ፡፡ በዳዊት ኪዳን ላይ እናተኩራለን ፡፡
ትምህርት
1-ዜና መዋዕል (17፡ 1-3)፡ ወልፍጋንግ ሮዝ “ ዳዊት ኢያሱ ጀምሮት የነበረዉን ከነዓንን መዉሰድ እንደ ጨረሰ ይናገራል “ ፡፡ በእንዲህ አይነት አስደናቂ ቤት መኖር ዳዊት በኃብት እና በምቾት እየኖረ እንደ ነበር ይገልፃል ፤ ዳዊት ናታንን ችግር ዉስጥ እንደ ነበር ነገረው ምክንያቱም እግዚአብሄር በድንኳን ዉስጥ እየኖረ እሱ በምቾት ስለሚኖር፡፡ መዝ (132፡ 1-5) “ ለያዕቆብ አምላክ “ ማደሪያ ስፍራ ለማግኘት የዳዊትን ፍላጎት እና ቁርጠኝነት መዝግቧል ፡፡ ናታን ወዲያዉኑ ዳዊትን በልቡ የነበረዉን እንዲያደርግ ነገረው ፤ ነገር ግን እንደ አንድ ኃያል የእግዚአብሄር ሰዉ እንደ ነቢይ አንድ ሰዉ ለምክር በሚጠይቃችሁ ጊዜ ሁል ጊዜ ትንቢታዊ ቃል ለመናገር የዘገያችሁ መሆንን አስታዉሱ ፤ በዚህ ጊዜ ናታን እግዚአብሄርን ሳያማክር በፍጥነት ተናገረ ፡፡ ቆይቶም በዚያን ምሽት እግዚአብሄር ናታንን ሊያስተካክለዉ (ሊያርመዉ) መጣ ፡፡ ያዕ (1፡ 19) አማኞችን ለመስማት የፈጠኑ ለመናገር ደግሞ የዘገዩ እንዲሆን ያሳስባል ፤ ይህ ትዕዛዝ እንድንናገር የሚፈልገዉን መጀመሪያ እግዚአብሄር ሳንጠይቅ መልስ የምንናገርበትን ተፈጥሮአዊ አዝማሚያችንን ይቆጣጠራል ፤ አንዳንድ ጊዜ ይህ ችግር ዉስጥ ያስገባናል ፡፡ ሰዎችን ከእግዚአብሄር ቃልን ሲናገሩ በምንሰማ ጊዜ አንዳንድ ጊዜ ከመናገራቸዉ በፊት በእዉነት ከእግዚአብሄር ከጠየቁ ማድነቅ አለብን ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሰዎች ትንቢታዊ ቃሎችን የማያምኑት ለዚያ ነው ፡፡
1-ዜና መዋዕል (17፡ 3)፡ ምስጋና ይሁንለትና ናታን ለእግዚአብሄር ማስተካከያ ክፍት ነበር ፡፡ ወደ እግዚአብሄር ማስተካከያ ቃላት ከመጣ በኋላ ናታን ራሱን ትሁት በማድረግ በእግዚአብሄር ትዕዛዝ ወደ ዳዊት ተመለሰ ፡፡ ይህ “ ተሳስቻለሁ ይህን ማስተካከል እፈልጋለሁ ምክንያቱም እግዚአብሄር ይህን ስላሳየኝ “ ማለት በሚችል መሪ በሆነ ሰው ስር የመሪነት አይነት ሰዎች የሚፈልጉት ነው ፡፡
1-ዜና መዋዕል (17፡ 4-6)፡ እግዚአብሄር ናታንን የጊዜ ሰሌዳ በመስጠት እስራኤልን ከግብፅ ካወጣ ጀምሮ ከድንኳን ወደ ድንኳን ከድንኳን ማደሪያ ወደ ታቦቱ ማደሪያ ሲንቀሳቀስ እንደ ነበር አመለከተው ፤ እግዚአብሄር ከመገናኛዉ ድንኳን ወደ ሙሴ ታቦቱ ማደሪያ ተጓዘ በመጨረሻም ወደ ዳዊት ታቦት ማደሪያ ተንቀሳቀሰ ፡፡ በእነዚያ ሁሉ እንቅስቃሴዎች እግዚአብሄር የት ማደር እንዳለበት ለማንም አልተናገረም ፤ በተመሳሳይ ኢየሱስ በአዲስ ኪዳን ምን አደረገ ? የሚጠራበት ቤት እንደ ለለዉ አንድ ሰዉ እንደ ዘላን ኖረ ፡፡ ይህን ስለ እግዚአብሄር መረዳት ለምን አስፈለገ ? እግዚአብሄርን በሳጥን ዉስጥ ማስቀመጥ እንደ ማንችል እንድንረዳ ፤ እግዚአብሄር በፍፁም አንድ ስፍራ አልነበረም ነገር ግን ሀሳባችን ቤተ መቅደስ ዉስጥ ወይም ቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ያስቀምጠዋል ስለዚህ መጫዎት ያለብንን ተግባር እንረዳለን ፡፡ እግዚአብሄር ያለማቋረጥ በመንቀሳቀስ በምንሄድበት ሁሉም ቦታ ላይ ስለ ሚገኝ በዚህ ልክ መተግበር አለበን ፤ እግዚአብሄርን ለመከተል በጣም አስቸጋሪ የሚያደርገዉ ይህ ነው ፡፡ እግዚአብሄር ለእርሱ ቤት መስራት የሚለዉን የዳዊትን ፍላጎት ማክበር ፈለገ ነገር ግን ዳዊት በፈለገበት መንገድ አይሆንም ፡፡
1-ዜና መዋዕል (17፡ 7-10)፡ እግዚአብሄር ዳዊትን ከረኝነት በመዉሰድ በእስራኤል ላይ ንጉስ እንዳደረገው ተናገረ ፤ ይህን ቃል እግዚአብሄር ሰጠ ምክንያቱም ለመስማት ናታን ዝቅ ማለቱን አስታዉሱ ፤ ትህትና ወደ መነቃቃት ሊመራ ይችላል ፡፡ እግዚአብሄር ከዳዊት ጋር በመሆን ጠላቶቹን አጠፋለት ፤ እግዚአብሄር ለእስራኤል ሲኖሩ የማይረበሹበት ቦት እንደሚመሰርትላቸዉ ተስፋ ሰጥቷል ፤ እንደ ገና እግዚአብሄር ሁል ጊዜ ህዝቡን እየቀጣ እያስተካከለ እና እየመራ መቆጣጠሩን ያሳያል ፡፡
1-ዜና መዋዕል (17፡ 10-15)፡ ይህ ያዙ ቤት ይገነባል ፤ እግዚአብሄር ለዳዊት ቤት እንደሚሰራለት ተስፋን ሰጠው፡፡ እግዚአብሄር ዳዊት በሞተ ጊዜ ከልጆቹ አንዱን ዘሩን ወደፊት በማምጣት መንግስቱን እንደሚመሰረት ቃል ገባለት (ቁጥር 11) ፡፡ በዚህ ትንቢታዊ ቃል ብዙ ነገሮችን ማየት እንችላለን ፤ አንድ እግዚአብሄር ከዳዊት አንድ ልጅ ያስነሳል -ሰለሞንን ፡፡ በ 1ዜና መዋዕል (22፡ 6-10) ዳዊት ልጁን ሰለሞንንለእግዚአብሄር ቤት እንዲሰራ ይነግረዋል ፤ ዳዊት ይህ ሊያደርግ ፈለገ ነገር ግን እግዚአብሄር ይህን አይፈቅድም ምክንያቱምዳዊት እንደ አንድ ጦረኛ ሰዉ ብዙ ደም አፍስሶ ስለ ነበር ፡፡ እነዚህን ፅሁፎች ስናወዳድር እግዚአብሄር ናታንን የዳዊት ልጅ ለእርሱ ቤት እንደሚሰራለት እንደ ነገረው እንማራለን ( 1ዜና መዋዕል 22፡ 11-13) ፡፡ እግዚአብሄር ለዳዊት ልጅ መንግስትን ብቻ አይደለም የሚመሰርተው ነገር ግን ልጁ ለእግዚአብሄር ቤትም ይሰራል ፡፡ “ ቤት “ ለሚለዉ ቃል “ ስረዉ መንግስት “ ማለት ይቻላል ፡፡ እግዚአብሄር መንግስቱን ለዘላለም እንደሚያቋቋም ቃል ገባለት ፤ ለ 2ሳሙኤል ቃላችን የዘላለም ዙፋን ነው ፡፡ የዘላለም ዙፋን ከዳዊት ልጅ በኩል ይመጣል - ከኢየሱስ ፡፡ ይህን ተስፋ ከ 2ሳሙ (7፡ 16) ተመሳሳይ ጥቅስ ታነባላችሁ ፤ ይህ የእግዚአብሄርን ቤት በመመስረት ሁሉንም ለዘላለም የሚገዛዉ የዳዊት ልጅ አስደናቂ ስዕል ነው ፡፡ እግዚአብሄር ከዚህ ልጅ የሚታመን ፍቅሩን በፍፁም እንደ ማይወስድ ተስፋን ሰጥቷል ፡፡
የዳዊት ዘር ያለማቋረጥ ወደ ሚመጣዉ ንጉስ ያመለክታል - ወደ ዳዊት ልጅ ራሱ የነግስታት ንጉስ ወደ ሆነዉ ወደ ኢየሱስ ! ይህ እንደሚሆን እግዚአብሄር ቃል ገባ - ለወድቅ (ሊፈርስ) አይችልም ! ዳዊት ባደረገዉ በማንኛዉም ነገር ላይ የሚቀየር አልነበረም በእግዚአብሄር ተስፋ ላይ ሙሉ በመሉ ከመደገፍ በቀር ፡፡
ይህ ዳዊታዊዉ ኪዳን በ 1እና 2 ዜና መዋዕል ሰባት ጊዜ ተገልፃል ፡፡
- እግዚአብሄር ለናታን ነገረው ናታን ደግሞ ለዳዊት ነገረው (1 ዜና መዋዕል 17) ፡፡
- ዳዊት ለሰለሞን ነገረው (1 ዜና መዋዕል 22) ፡፡
- ዳዊት እንደ ገና ለሰለሞን ነገረው (1 ዜና መዋዕል 28) ፡፡
- ሰለሞን ለእስራኤል ህዝብ ነገረው (2 ዜና መዋዕል 6) ፡፡
- እግዚአብሄር ለሰለሞን ነገረው (2 ዜና መዋዕል 7) ፡፡
- አብያ ኢዮርብዓምን ነገረው (2ዜና መዋዕል 13) ፡፡
- የዜና መፅሀፍ ፀሀፊዉ በዳዊት ኪዳን ላይ ተናገረ (አስተያየት) ሰጠ (2 ዜና መዋዕል 21) ፡፡
እግዚአብሄር አንድ ቃል በተናገረ ጊዜ ይሰራል ፡፡
6 Jeffrey Hardwick, “What Do You Do When You Receive A Prophecy,” at ATransformingWord.com.
1-ዜና መዋዕል (17፡ 16-19)፡ ዳዊት ይህን ከሰማ በኋላ በእግዚአብሄር ፊት በመቀመጥ እግዚአብሄር ይህን ያደርግለት ዘንድ ማን እንደ ነበር ተደነቀ ፡፡ ዋረን ዋይርስቤ እንዳለው ለሰዓቱ ሞገስ የዳዊት እግዚአብሄርን በማመስገን ይህ ሆነ ፤ ዳዊት እግዚአብሄር ስለ ቤቱ በሩቅ ወደፊት ተናግሮ እንደ ነበር (ቁጥር 17) እና እነዚህን ሁሉ ታላቅ ተስፋዎች በፍቃዱ አድርጓቸዉ እንደ ነበር ተረድቷል ፡፡ ናታን ትንቢታዊ ቃል እንደ ተናገረ ዳዊት ተቀበለዉ ምክንያቱም በእግዚአብሄር ፍቃድ መሰረት እንደ ሚሆን ስለተረዳ ፡፡ እግዚአብሄር ከይሁዳ አንፃር ብዙ ተስፋዎችን አድርጓል ፤ በዘፍ (49፡ 10) “ በትረ መንግስት ከይሁዳ አይጠፋም የገዥም ዘንግ ከእግሮቹ መካከል “ በማለት ያዕቆብ ልጁን ይሁዳን ባረከው ፤ ይህ ማለት የይሁዳ አስተዳደር (ሞገስ) ለዘላለም ይቆያል - በዳዊት ልጅ - በሰለሞን እና በመጨረሻም በኢየሱስ በመሲሁ ምክንያት ከይሁዳ አይለይም ፡፡
1-ዜና መዋዕል (17፡ 20-22)፡ ዳዊት እግዚአብሄርን ማመስገን ቀጠለ፡ “ አቤቱ እንደ አንተ ያለ የለም በጆሮአችንም እንደ ሰማን ሁሉ ከአንተ በቀር አምላክ የለም “ (ቁጥር 20) ፡፡ ዋይርስቤ ዳዊት በሰዓቱ አምላክን ከማመስገን ቀድሞ አድርጎለት ስለ ነበረው እግዚአብሄርን ወደ ማመስገን ዞረ ፡፡
1-ዜና መዋዕል (17፡ 23-27)፡ ዳዊት እንደ ገና በመዞር አሁን እግዚአብሄር ወደ ፊት ተስፋዉን እንዲፈፅመው ልመና አደረገ ፤ ዳዊት በእግዚአብሄር ተስፋ የገባቸዉ ነገሮች ወደ እዉነት እንዲመጡ ዳዊት ለመነ ፡፡ አንዴ ዳዊቱ ቃሉን ሲሰማ በፀሎት ወደ እግዚአብሄር ሄደ ፤ የኔልሰን ማብራሪያ የዳዊት ቤት ሁል ጊዜ በንጉሳዊ መስመር ይሆናል የማስተዳደርምመብት ሁል ጊዜ የዳዊት ዘር ስር ይሆናል ፡፡ ይህ ተስፋ ለዘላለም ይቆያል ቢቆሹሹም እንኳን ፡፡
መደምደሚያ
ከእግዚአብሄር አንድ ቃል እንዴት ትቀበላላችሁ ? ከዳዊት ምን ልንማር እንችላለን ? በመጀመሪያ መዝግባችሁ አዳምጡት ፤ በአሁኑ ጊዜ ትንቢታዊ ቃሎችን በምናወራ ጊዜ ስለ አዲስ መፅሀፍት ያወራን አይደለም ነገር ግን አማኞች እርስ በእርስ ስለ ሚነጋገሩአቸዉ ቃላቶች እንጂ (1 ዜና መዋዕል 14፡ 3) ፡፡ በዚያ ትንቢታዊ ቃል ምን ለማለት እንደ ሆነ እግዚአብሄርን ጠይቁት ፤ የእናንተ ድርሻ ምን እንደ ሆነ እና የእግዚአብሄርስ ምን እንደ ሆነ ጠይቁ ፡፡ ቁልፉ እርምጃ ትንቢታዊ ቃሉን ከመፅሀፍ ጋር የተገናኘ መሆንን ለማየት መፈተን ነው ፤ 2ጢሞ (3፡ 16) ነገሮችን በመፅሀፍ ለምን መፈጠን እንዳለብን ይገልፅልናል ፡፡ 1 ተሰ (5፡ 19-21) እግዚአብሄር ወደ ኑሮአችን እንዲናገረን ክፍት እንድንሆን ይነግረናል ነገር ግን ሁሉንም ነገርም ለመፈተን ፡፡ ስራችን ከመፅሀፍት ጋር በማገናኘት እርግጠኛ በመሆን ወደ ህይወታችን የመጣዉን የእግዚአብሄርን ቃል በመፈተን መልካም በሆነዉ ላይ በመፅናት ከክፉ መራቅ ነው (1ተሰ 5፡ 21-22) ፡፡
በፊል (4፡ 8) አይኖቻችንን ትክክል፣ የተከበረ እና እዉነት እሆነ ነገር ላይ እንድናደርግ ተነግረናል ፡፡ ትንቢታዊ ቃሎች ከእግዚአብሄር ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ ዳዊት የሰማዉ ቃል ትክክል እንደ ሆነ እናዉቃለን ምክንያቱም ሉቃ (1፡ 31-33) ኢየሱስ የአባቱ የዳዊት ዙፋን እንደ ተሰጠዉ ስለ ሚያወራ ፡፡ ኢየሱስ የዳዊት ልጅ ነበር ፤ በኢየሱስ ምክንያትም መንፈሳዊ በረከቶችን መቀበል እንችላለን ፡፡ ኢየሱስ መንፈሳዊ መንግስት ከእርሱ እየመጣ እንደ ነበር ተሰፋን ሰጥቷል ፤ እነዚህ ሁሉ ነገሮች በ 2ሳሙኤል 7 እና በ1 ዜና መዋዕል 17 ዳዊት ከሰማዉ ጋር የተገናኘ ነው ፡፡ ዋናዉ ጭብጥ እዚህ የዳዊት ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የሚፈፀም ነዉ ፡፡
Wolfgang Roth, The Deuteronomic Rest Theology, p. 8; quoted in The Expositor’s Bible Commentary: 1 Samuel—2 Kings, ed. Tremper Longman III and David E. Garland (Grand Rapids: Zondervan, 2005), p. 381.
Warren Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2007), p. 566.
Wiersbe, p. 566.
Wiersbe, p. 566.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 517.
ጥያቄዎች
-
ዳዊት ለኪዳኑ ታቦት ቤት ለመስራት ፈለገ ነገር ግን እግዚአብሄር አይሆንም ብሎ ነገረው ፤ ዳዊት ከመስመር ዉጪ ነበር ወይስ ንፁህ አሳብ ነበረዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን አሰባችሁ ወይስ ለምን አላሰባችሁም ? ለእግዚአብሄር በደንብ ቀንታችሁ አይሆንም ብሎ ነግሯችሁ ወይስ ሳይነግሯችሁ ያውቃል ? በምን አይነት መንገድ ?
-
1ዜና መዋዕል (17፡ 26-27) በሚገባ አንብቡ ፤ ዳዊት በእግዚአብሄር ፊት በአክብሮት እና በሙሉ ምስጋና ሰጪነት ተቀመጠ ፡፡ በሙሉ ማህበረሰቡ ለእግዚአብሄር ምስጋና መስጠትን ሲተዉ ማሰብ ትችላላችሁ ? ልክ እንደ ዳዊት ለመሆን ተጨማሪ በጊዜአችሁ በእግዚአብሄር ማድረግ ወይም ማለት የምትችሉት ምንድነው ? በምትፀልዩ/በምታመሰግኑ ጊዜ እግዚአብሄር ሁሉንም እንደሚሰጣችሁ ይሰማችኋል ? ለምን ወይስ ለምን አይሰማችሁም ?
-
እግዚአብሄር ከሆኑ ሰዎች በፊት በመሄድ በጣላቶቻቸዉ ላይ ድልን ሲሰጣቸዉ ሌላ የት ላይ አይተናል ? (ኢያ 8፡ 1-2, 2ዜና መዋዕል 20፡ 27)
-
በ 1ዜና መዋዕል (17-18) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Chronicles 17:16
“Then King David went in, sat in the LORD’s presence, and said, ‘Who am I, LORD God, and what is my house that You have brought me this far?’”
ዳዊት ለእግዚአብሔር መኖሪያ ይሆን ዘንድ ቤትን ለመስራት ፈለገ ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ለነቢዩ ናታን በሰጠው ቃል ለዳዊት የተለየ እቅዱን አካፈለው እንድሁም ማን ቤቱን ይሰራለት ዘንድ እንደሚገባ ነገረው ፡፡ ንጉሥ ዳዊትም ቃሉን ከሰማ በኋላ እግዚአብሔርን በሚያመሰግንበትና በሚያመልክበት ስፍራ በእግዚአብሔር ፊት ሄዶ ተቀመጠ ፡፡ ከዚያም ዳዊት እግዚአብሔር የተናገረውን ሁሉ እንድፈጽም ጸለየ ፡፡
ከእግዚአብሔር ስትሰማ ለአንተ የሚናገረው ማንም ይሁን ወደ ፊቱ ለመቅረብና በፊቱ ለመሆን ጊዜን ውሰድ ፡፡ የምትወደው ወንበር ወይም የጸሎት ስፍራ ይኖርህ ይሆናል ፡፡ ወደ ቤትህ ወይም ወደ ቢሮህ ከመሄድህ በፊት ትንስ ጊዜ መኪናህ ውስጥ መቆየት ያስፈልግህ ይሆናል ፡፡ ምናልባትም ብቻህን መሄድም ያስፈልግህ ይሆናል ፡፡ ቦታው የትም ይሁን ከእርሱ ጋር ተጣበቅ በእርሱም እረፍ ፡፡ ዛሬ ሀላፊነት ካለብህ ፣ መወሰን ካለብህ ወይም እግዚአብሔር የልብህን መሻት ሲያስቀይርህ ሄደህ በፊቱ ሁን ፡፡ በፊቱ ስትሆንም ምስጋናን ለእግዚአብሔር አቅርብ ፣ ስሙንም አወድሰው ከዚያም በኋላ በህይወትህ የገባውን ቃል ይፈጽም ዘንድ ጸልይ ፡፡
“ ንጉሡም ዳዊት ገባ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ተቀምጦ እንዲህ አለ፦ አቤቱ አምላክ ሆይ፥ እስከዚህ ያደረስኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምንድር ነው ? “
- 1ኛ ዜና 17፡16
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 103:1-2 — “ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ አጥንቶቼም ሁሉ፥ የተቀደሰ ስሙን። ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ ምስጋናውንም ሁሉ አትርሺ፤
ማርቆስ 6:31 — “እናንት ራሳችሁ ብቻችሁን ወደ ምድረ በዳ ኑና ጥቂት ዕረፉ አላቸው፤ የሚመጡና የሚሄዱ ብዙዎች ነበሩና፥ ለመብላት እንኳ ጊዜ አጡ ።
ዮሐንስ 15:5 — “እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል ።
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።