Historical Books 1 Chronicles

David Danced Before the LORD

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of David 1 Chronicles 15-16 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 294 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በ 1ዜና መዋዕል 13 ስለ ዳዊት እና ስለ ታቦቱ ስለ አንድ ትንሽ ስህተት አዉርተናል - የእግዚአብሄር ቃል የሚለዉን ባለማድረግ የዖዝያን ሞት ሆነ ፡፡ የአቢዳራ የእግዚአብሄርን በረከትአገኘ ምክንያቱም ታቦቱ ለሰዎስት ወራት ተቀምጦ ስለ ነበር ፡፡ በ 1ዜና መዋዕል 15 ታቦቱ ከአቢዳራ ቤት ዳዊት በኢየሩሳሌም ወዳቆመዉ ድንኳን ተንቀሳቀሰ ፡፡

ትምህርት

1-ዜና መዋዕል (15፡ 27)፡ ዳዊት እና ታቦቱን ተሸክመዉት የነበሩት ሌዋዊያን ጥሩ በፍታ ለብሰዉ ነበር ፡፡ በዚህ ጊዜ ሌዋዊያን በእግዚአብሄር ትዕዛዝ በመታዘዝ ታቦቱን እየተሸከሙ ነበር ፤ በ ዘጸ (25፡ 14) እግዚአብሄር እንዴት ታቦቱን እንደ ሚሸከሙ ትዕዛዝ ሰጥቷቸው ነበር ፡፡ ዳዊት፣ ሌዋዊያን እና ዘማሪዎች እግዚአብሄርን ለማምለክ ህዝቡን ሰበሰቡ ፤ ይህ የኤፉድ ልብስ ለብሶ የነበረዉን ዳዊት የካህናትን ተግባራት እየተጫዎተ እንደ ነበር ተከስቷል ፡፡ ቃላችን ለ 1ዜና መዋዕል የዳዊት ልጅ መሆኑን አስታዉሱ ፤ ዳዊትን ለ አንድ ምክንያትም እንኳን የካህናት እና የንጉስነትን ተግባር መጫዎት መጀመሩን በምናይ ጊዜ ስለ ሚመጣዉ መሲህ ወደ ኢየሱስ እያመለከተ እንደ ነበር ታዉቃላችሁ ፡፡

1-ዜና መዋዕል (15፡ 28-29)፡ እስራኤላዊያን “ እግዚአብሄር መመለሱን “ አገኙት ማለትም ከእርሱ ጋር እንደ ገና ተዋሀድ (ህብረት ፈጠሩ) ፡፡ ዳዊት ከህዝቡ ጋር በአምልኮ በመደነስ አከባበሩን ተቀላቀላቸው የሳዖልም ልጅ ሚልኮል ተመለከተች እና በልቧ ናቀችዉ ፤ ለምን ዳዊትን ናቀችዉ ? ሚልኮል “ ከቀድሞው ጥበቃ “ ስለ መጣች ዳዊት ታቦቱን የተቀበለበትን (ያገኘበትን) መንገድ አልወደደችዉም ፡፡ “ መናቅ “ የሚለዉ ቃል በዳዊት ላይ ብስጭቷን ይገልፃል ፤ ምናልባትም በስልጣን ላይ ያለ አንድ ሰዉ እንደዚህ ሊያደርግ አይገባዉም ብላ አስባለች ፡፡ ዳዊት እንደ ተቀባ በዚህ መንገድ መሆን እንደሌለበት አምናለች ፡፡

ንጉስ ሳዖል ልጁን ሚልኮልን ዳዊት ጎልያድን ከገደለ በኋላ ለዳዊት ሰጠው ፤ በጊዜ ብዛት በዳዊት እና በእርሷ መካከል ትልቅ ርቀት ተፈጠረ ፤ ዳዊት ሌሎች ሚስቶች ነበሩት ከአባቷ ከሳዖል ሙሉ ለሙሉም የተለዩ ነበር ፡፡ የሚልኮል አስተሳሰብ ፈሪሳዊያን ለኢየሱስ ከነበራቸዉ ጋር ተመሳሳይ ነው ፤ በማቴ (23፡ 13-16, 23-32) ኢየሱስ ፈሪሳዊያንን “ መንግስተ ሰማያትን በመዝጋት “ ራሳቸዉ ስለ ማይገቡ ወይም ደግሞ ሌሎችን እንዳይገቡ ስለ ማትፈቅዱ ወዮዉላችሁ አላቸው ፤ እዚህ ጋር የፈሪሳዊያን መልስ በብሉይ ኪዳን በህዝቡ ኑሮ ዉስጥ የቀረበዉን የእግዚአብሄርን መገኘት ልምምድ በመተው በመቀዝቀዝ የራቀ የአምልኮ ቅርፅ በማድረግ የሳዖልን ድርጊት የሚመስል ነው ፡፡ በኃይማኖተኝነት መንፈስ ስር ከእግዚአብሄር ጋር ግንኙነትን መቆጣጠር ሰዎችን ወደ መገኘቱ አይጋብዝም ፤ ሚልኮል ተበሳጭታ ነበር ምክንያቱም ዳዊት በአምልኮ መሳተፍን እንዲቀላቀሉ ያደረገዉን ይህን አባቷ ህዝቡ መገኘቱን እንዳይቀምሱት ሁሉንም ነገር ከልክሎ ስለ ነበር ፡፡

1 ዜና መዋዕል 16 ስንከፍተዉ በሚልኮል ቁጥጥር ስር ስላለዉ መንፈስ እናስባለን ፤ ዳዊት ያደረገዉን አልወደደችዉም ምክንያቱም በዚያ መንገድ በፍፁም አድርገዉ ስላልነበር - ወደ እግዚአብሄር መገኘት ሲመጡ እየደነሱ እና እያጨበጨቡ መጥተዉ ስለ ማያዉቁ ፡፡ ዳዊት በእግዚአብሄር ፊት በጭፈራ ማክበሩ ለምን ነበር በጣም ያስደሰተው ? ምክንያቱም የእግዚአብሄርን መገኘት ስለ ቀመሰ ፡፡

1-ዜና መዋዕል (16፡ 1-2)፡ የእግዚአብሄርን ታቦት ወደ ድንኳኑ በማምጣት በእግዚአብሄር ፊት የሚቃጠል መስዋዕት እና የደህንነት መስዋዕት አቀረቡ ዳዊትም ህዝቡን ባረከ ፡፡ በ 1ዜና መዋዕል ስትመለሱ ለሰዎስት ወር ታቦቱ በአቢዳር ቤት በተቀመጠ ጊዜ እግዚአብሄር ቤተሰቡን እንደ ባረከ ታስታዉሳላችሁ ? በእግዚአብሄር መገኘት በሆናችሁ ጊዜ ተባርካችኋል ፡፡ በክርስቶስ ነፃነት ካላችሁ በመስኮት አትመለከቱም በመንገድ ላይ ከሚደንሱት አንዶቹ ናችሁ ፡፡

1-ዜና መዋዕል (16፡ 3)፡ ዳዊት ለእያንዳንዱ እስራኤላዊ አንድ እንጀራ፣ አንድ ቁራጭ ስጋ እና አንድ የዘቢብጥፍጥፍ አከፋፈለ ፤ ኢየሱስ በአዲስ ኪዳን ከህዝቡ ጋር በተገናኜ ጊዜ የእግዚአብሄርን መገኘት አግኝተዉታል ሁል ጊዜም በምግብ ተዓምራት እንደ ነበር ይመስላል ፡፡ 4,000 እና 5,000 ሰዎችን በመመገብ ከህዝቡ ጋር ምግብ በላ ይህም በእግዚአብሄር አቅርቦት እና መገኘት መድረስን መስሏል ፡፡ ሐዋ ( 2፡ 46-48) በምግብ እንዴት አይነት ግንኙነት እንዲኖረን እግዚአብሄር ያቀደዉን በማየት ለመረዳት በጀመርን ጊዜ ይህ ትርጉም ይሰጠናል ፡፡ እግዚአብሄር በኃይማኖት መንፈስ ያሉትን መባረክ በመፈለግ በዚያ ዉስጥ ስለ ሚሰብራቸው ከእርሱ ጋር ግንኙነቱን መልመድ ይችላሉ ፡፡

ዳዊት የእግዚአብሄርን መገኘት በሚያከብር ጊዜሰዎስት ጊዜ ምግብ ነበር ፤ በ 1ዜና መዋዕል (12፡ 39) ከዳዊት ጋር በመብላት እና በመጠጣት ሰዎስት ቀን አሳለፉ ፤ በ 1ዜና መዋዕል (16፡ 3) በዚህ ክብረ በዓል (ማክበር) ምግብ ነበር ፤ ከዚያም 1ዜና መዋዕል (29፡ 22) ላይ ስንመለከት ዳዊት ቤተ መቅደሱን ለመስራት ህዝቦቹ እንዲያዋጡ በጋበዛቸዉ ጊዜ “ በዚያም ቀን በታላቅ ደስታ በእግዚአብሄር ፊት በሉም ጠጡም “ ፡፡ የዳዊት ቤተሰብ የእግዚአብሄርን መገኘት ባገኙት ጊዜ በምግብ አድርገዉታል ፡፡

1-ዜና መዋዕል (16፡ 4-7)፡ ዳዊት ይህን ልምምድ ወደ መዝሙሩ መመለስ በመጀመሩ በጣም ደስተኛ ነበር ፡፡ በቁጥር 4-7 ዳዊት በእግዚአብሄር እንደ ታዘዘዉ ሌዋዊያንን ቀባ (ሾመ) ፤ የዚህን ጊዜ ይህን ድርጊቱን በ 1ዜና መዋዕል ጋር ካለዉ ከቀድሞዉ ጊዜ ጋር አወዳድሩት ፡፡ በእግዚአብሄር መገኘት የተነሳሳ እና ደስተኛ የሆነ ቢሆንም እንኳን ትክክለኛ ነገሮችን በቦታቸዉ አስቀመጠ ፤ ሌዋዊያንን በእግዚአብሄር ፊት እንዲያገለግሉ እና ለእግዚአብሄር ምስጋና እና ዉዳሴ እንዲሰጡ ሾማቸው (ቀባቸው) ፡፡ አሳፍን እንደ አለቃ ሰየመዉ ምክንያቱም ዳዊት ይህን በራሱ ማድረግ ስለ ማያስፈልገው ፤ በተጨማሪም ሌሎች ብዙዎች በገና እና መሰንቆ እንዲጫወቱ ሲሾሙ አሳፍ ደግሞ ፅናፅል ይጫወታል ፡፡

ህዝቡ ስለ እግዚአብሄር መገኘት በኃይል ተነቃቅተዉ ነበር ምክንያቱም ሁሉም ነገር እንደ ገና እየጀመረ እንደ ነበር ስለተሰማቸው ህያዉ እግዚአብሄር እንደ አዲስ ስላገኙት ፡፡ ወደ መጀመሪያፍቅራችሁ እንደ ተጠለፋችሁ በተረዳችሁ ጊዜ ወደ ክርስቶስ ተመልሳችሁ በመሄድ ከእርሱ ጋር በፍቅር በመዉደቅ ማን እንደ ሆነ በመያዝ ለእናንተ ባደረገዉ ነገር ምክንያት ትደሰታላችሁ ፡፡ ዳዊት ህዝቡን እነዚህን ነገሮች እንዲያደርጉ ለቀቃቸው ፡፡ የኃይማኖት መንፈስ ሁል ጊዜ ይቆጣጠራል ፤ የመንፈስ ግንኙነት ከአባት ጋር ሁል ጊዜ ያሳድጋል (ኃይል ይጨምራል) ፡፡

በቁጥር 7 መሰረት “ በዚያም ቀን ዳዊት በአሳፍና በወንድሞቹ እጅ እግዚአብሄር እንዲያመሰግኑ አስቀድሞ ትዕዛዝ ሰጠ “ ፤ ዳዊት እነዚህን ሌዋዊያንን በኃላፊነት እንዲሆኑ በመሾም በግልፅ ይህ ዝማሬ ለእግዚአብሄር አምልኮ እንዲሆን አረጋገጠ ፡፡

1-ዜና መዋዕል (16፡ 8-36)፡ በቁጥር 8-22 ዳዊት መዝ (105፡ 1-15) ላይ ዘርዝሯል ፤ ቁጥር 23-33 በመዝ (96፡ 1-13) የተንፀባረቀ ነው ፤ ቀጥሎም ዳዊት እነዚህ መዝሙሮችን ህዝቡ እግዚአብሄርን በፍፁም እንዳልረሳ እና አድርጎላቸዉ የነበረዉን እንዳልረሱ (ቁጥር 34-36) እርግጠኛ ለመሆን ለአሳፍ ሲያዝዘው መዝ (106፡ 1, 47, 48) ታያላችሁ ፡፡ ፀሀፊዉ “ ቸር ነዉና ምህረቱ ለዘላለም ነዉና እግዚአብሄርን አመስግኑት “ (ቁጥር 34) የሚለዉን ያሳስበናል ፡፡ ይህ መልዕክት ለምን አስፈላጊ ነዉ ? ከግዞት ለመጡት እግዚአብሄር አድርጎላቸዉ የነበረዉን ማስታወስ አስፈለጋችው ፤ ዳዊት እግዚአብሄር ስላደረገላቸዉ ሁሉም ነገር እንዲያመሰግኑት አበረታታቸው ፡፡

መደምደሚያ

በግላችሁ የትናችሁ ? ለመጨፈር ፈቃደኞች ናችሁ ? ወይስ መስኮት ላይ ተቀምጣችኋል ? ለመጨፈር ነፃ ሆኖ መወሰን በምትችሉ ጊዜ ምን ማለት እንደ ሆነ ትረዱታላችሁ ፡፡ በዚያ ፀጥ ማለት ካልቻላችሁ ከእግዚአብሄር ካልሆነዉ ከዚህ ባርነት ነፃ እንዲያወጣችሁ እግዚአብሄርን ጠይቁት ፡፡

ጥያቄዎች

  1. በ 1ዜና መዋዕል 15 ዳዊት እንደ ገና ታቦቱን ለማንቀሳቀስ(ለማጓጓዝ) ተዘጋጀ ፤ በዚህ ጉዞ እና በ 1ዜና መዋዕል (13፡ 6-11) ለማጓጓዝ ሞክረዉት በነበረዉ በመጀመሪያው መካከል ልዩነቶቹ ምንድን ነበሩ ?
  2. በ 1ሳሙ (18፡ 20) ዳዊትን የምትወደዉ ሚልኮል በ 1ዜና መዋዕል (15፡ 29) ላይ ስለ እርሱ ንቀት ተሰማት ፤ ስሜቷ ለምን እንደ ተቀየረ ምን ታስባላችሁ ? በ 2ሳሙ (3፡ 13-16) ዳዊት ከባሏ ወስዷት ስለ ነበር ሊሆን ይችላል ? (2ሳሙ 6፡ 20)
  3. በ 1ዜና መዋዕል (16፡ 4) ዳዊት ሌዋዊያንን በታቦቱ ፊት እንዲያመልኩ ሾማቸው ፤ ይህ በዘኁ (3፡ 6-7) መሰረት የእግዚአብሄር ትዕዛዝ ነበር ?
  4. በ 1ዜና መዋዕል (16፡ 11) ዳዊት እግዚአብሄርን በመፈለግ ሲዘምር እናየዋለን ፤ ይህን የሚመስል ጥቅስ ሌላ የት ላይ ታያላችሁ ? (ዘዳ 4፡ 29, ኤር 29፡ 13, ማቴ 7፡ 7-8)
  5. 1 ዜና መዋዕል (16፡ 34) እና መዝ (136፡ 1) በአንድ ሲነበቡ ተመሳሳይ ነው ፤ ለእናንተ ይህ ጥቅስ ምን ማለት ነው ?
  6. በ 1ዜና መዋዕል (15-16) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Chronicles 15:29

“As the ark of the covenant of the LORD was entering the city of David, Saul’s daughter Michal looked down from the window and saw King David dancing and celebrating, and she despised him in her heart.”

ከዳዊት የቃልኪዳኑን ታቦት ወደ ኢየሩሳሌም የመውሰድ የመጀመሪያ ሙከራ ሶስት ወራት በኋላ እንደገና ለመውሰድ ሞከረ ፡፡ በዚህ ጊዜ ዳዊት እግዚአብሔርን ጠየቀ እንድሁም ለታቦቱ ስፍራን አዘጋጀ ፡፡ ህዝቡም በመንገድ ሲሄዱ ይጨፍሩ ፣ ይዘፍኑና እግዚአብሔርን ያመልኩ ነበር ፡፡ በዚህ ጊዜም የዳዊት ሚስትና የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮቱ አጠገብ ተቀምጣ ታቦቱን ሲያመጡ በመንገድ ላይ ንጉሥ ዳዊት ሲጨፍር አይታ በልቧ ናቀችው ፡፡

ህዝቡ በፈለጉት ጊዜ የእግዚአብሔር መገኘት ተመለሰ ፡፡ አንተም ዘለህ በመግባት ተካፋይ ልትሆን ወይም በዳር ልትቆም ትችላለህ ፡፡ የት ነህ ? ከእግዚአብሔር ጋር በሙሉ ደስታ የሚራመዱትን ትተቻለህ ፡፡ አንተ በፍርሃትና መራራነት ውስጥ ሰምጠህ ሳለ አይተሃል ሌሎች ከኢየሱስ ጋር በእምነት እየተራመዱ ህይወታቸውን ሲያጣጥሙ ? አሁንም ወደ ኢየሱስ መምጣትንና መገኘቱን መቅመስ ምርጫ ለማድረግ ፈጽሞ አልረፈደም ፡፡ ኢየሱስ ይወድሃል ፡፡ ስርዓቱን ተወው ፣ ፍርሃትን ተወው ፣ ኩራትንም ተወው ፡፡ እነዚህን ነገሮች ስትተው እርሱ በታላቅ ፍቅሩ ፣ ሰላምና ደስታው ይሞላህ ዘንድ ታስችለዋለህ ፡፡ በትህትና ተመላለስ እንድሁም እግዚአብሔርን ፈልግ ፡፡ ስትፈልገው ታገኘዋለህ ስለዚህ በፍጹም ልብህ ፈልገው ፡፡

“የእግዚአብሔርም ቃል ኪዳን ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በደረሰ ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ተመለከተች፤ ንጉሡም ዳዊት ሲዘፍንና ሲጫወት አይታ በልቧ ናቀችው ። “

- 1ኛ ዜና 15:29

ተጨማሪ ጥቅስ

  • መዝሙር 16:11 — “ የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፤ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሐ አለ ። “
  • ኤርምያስ 29:13 — “ እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ ። “
  • ዮሐንስ 3:17 — “ ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና ፡፡ “