Taking God Lightly
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of David 1 Chronicles 13-14 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በ 1ዜና መዋዕል ዉስጥ ስንጓዝ ዳዊት እግዚአብሄርን ስለ መገናኘቱ ሽግግር ለማየት ጀምረናል ፤ ኮንስታብል ፀሀፊዉ “ ያህዌ ቅዱስ መሆኑን እና የእግዚአብሄርን መገኘት በመካከላቸዉ እንዳያቀሉ “ አንባቢዎቹን እርግጠኞች ለማድረግ እንደ ፈለገ ይገልፃል ፡፡ በመጥፎ መንገድ እስራኤላዊያን በሰዓቱ በነበሩበት ሁኔታ ለምን እንደ ሆኑ ያን ንግግር መጠቀም እንደ ምንችል አስባለሁ ፤ የአምላክን መገኘትአልተረዱትም እንዲሁም ማን እንደሆነ ዋጋ፣ ክብር እና አክብሮት አልሰጡም ፡፡ እርሱን አቅልለዉ ወሰዱት ፤ ዳዊት፣ እስራኤላዊያን እና የዳዊት ኃያላን ሰዎች በዚህ መንገድ ለመስራት ሁሉም በአዲስ መንገድ እየተማሩ ነበር ፤ ነገር ግን ሁሉም ዳዊት እንደ ነበረው ተመሳሳይ አክብሮት አላደረጉም ፡፡
ትምህርት
1-ዜና መዋዕል (13፡ 1-4)፡ ዳዊት ታቦቱን ለማንቀሳቀስ እየተዘጋጀ እንደ ነበር ከመሪዎቹ እና ከአዛዦቹ ጋር ተመካከረ (ቁጥር 1) ፤ ንጉስ ኢዮሳፍጥ (2ዜና መዋዕል 20፡ 17) እና ንጉስ ሕዝቅያስ (2ዜና መዋዕል 30፡ 2, 4, 12, 23) ሁለቱም ከሰዎቻቸዉ ምክርን ተመልክተዋል ፡፡ ጥበበኝ ምክርን መፈለግ ጡሩ ነው (ምሳ 11፡ 14, 12፡ 15, 15፡ 31-33) ፡፡ ዳዊት መልዕክቱ ከእግዚአብሄር መሆኑን በደንብ ከተረዳው ሁሉንም ህዝብ በአንድ ላይ ይጠሩዓቸዋል (ቁጥር 2) የእግዚአብሄርንም ታቦት መልሰዉ ማምጣት እንደሚችሉ ተናገሩ (ቁጥር 3) ፡፡ ሙሉ ጉባኤዉም ወደ ታቦቱ ለመሄድ ተስማሙ (ቁጥር4) ፡፡
አስዕርቱን ትዕዛዝ የያዘዉ ታቦት በጦርነት ይዘዉት ከነበሩት ከፍልስጤማዉያን ሰርቀዉት እንደ ነበር እናስታዉሳለን ፤ ታቦቱ ወደ እስራኤል በተመለሰ ጊዜ ሳዖል እግዚአብሄር ምን እንዲያደርጉበት እንደ ሚፈልግ አልጠየቀዉም ፡፡ ዳዊት ኢየሩሳሌምን እንደ ዋና ከተማዉ በመመስረት እና መጀመሪያ በፍቅሩ ወድቀዉ የነበሩትን (እስራኤልን) ከእግዚአብሄር ጋን ግንኙነታቸዉን እንደ ገና በማቋቋም ህዝቡን አንድ ማድረግ ፈለገ ፤ ይህ የመነቃቃት ጊዜ በመባል ሊከፈል ይችላል ፡፡ በዘጸዓት (35-40) የእግዚአብሄር መገኘት በድንኳኑ ማደሪያ ነበር ፤ በ 2ዜና መዋዕል (7፡ 14-16) እግዚአብሄር የሰለሞን ቤተ መቅደስ የመኖሪያ ስፍራዉ እንደሚሆን አወጀ ፡፡ ሳዖል በገባዖን የሰዉ እቅድ ነበር ፤ ዳዊት በኢየሩሳሌም የእግዚአብሄር እቅድ ነበር ፡፡ ዳዊት ህዝቡን እግዚአብሄርን እንዲፈልጉ መራቸው ( ኢሳ 55፡ 6-7, ኤር 29፡ 13-14) ፤ አዳም እና ሒዋን ቀምሰዉት እንደ ነበረዉ የእግዚአብሄር ፍቅር፣ ምህረት እና የግል ስጦታቸዉን (ዘፍ 3፡ 15, 21, 4፡ 26, 5፡ 24) ዳዊት ህዝቡን የእግዚአብሄርን ፍቅር፣ ምህረት የግል ስጦታን ቀርበዉ እንዲስቡ መምራት ፈለገ ፡፡ በአዲስ ኪዳን ወደ እግዚአብሄር ተሰበን በመጠጋት ላይ ለማተኮር (ያዕ 4፡ 8-10)፣ እግዚአብሄርን መጀመሪያ የምንፈልግበት (ማቴ 6፡ 33)፣ ወደ አባታችን ወደ እግዚአብሄር የምንመለስበት (ሉቃ 15፡ 11-32) እና ከእግዚአብሄር ጋርህብረት እንዲኖረን ሌሎች ፅሁፎች አሉ ፡፡
1-ዜና መዋዕል (13፡ 5-8)፡ ዳዊት ሁሉንም ህዝብ ወደ ሜዴትራሊያን ባር ከሚፈሰዉ ከግብፅ ወንዝ ከሺሖር የእስራኤል ደቡብ ድንበር እስከ በሰሜን ድንበር እስከ ምትገኘው ሐማት ድረስ ያሉትን ሰበሰበ ፤ ዳዊት በይሁዳ ወደ ቂርያትይዓሪም ታቦቱን በማግኘት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲያመጡትሁሉንም ሰዎች ጠራቸው (ቁጥር 5-6) ፡፡ ለማጓጓዝም ታቦቱን በአዲስ ሰረገላ ላይ አስቀመጡት (ቁጥር 7) ፡፡ ፍልስጤማዉያንም ታቦቱን ለማጓጓዝ ሰረገላ ተጠቅመዉ ነበር ነገር ግን የብሉይ ኪዳን ህግ ታቦቱ በቀዓት ልጆች መሸከም እንዳለበት ይጠይቅ ነበር (ዘኁ 3፡ 3-31) ፡፡ ምናልባትም ዖዛና አሒዮም (ሰረገላዉን የነዱት) የቀዓት የልጅ ልጆች ነበሩ ፤ በመንገዱ ላይ ሲሄዱ ዳዊት እና ህዝቡ መዝሙሮችን እየዘመሩ እና መሳሪያዎቹን እየተጫወቱ እግዚአብሄር ስለሚቀርብ አከበሩት (ቁጥር 8) ፡፡
1-ዜና መዋዕል (13፡ 9-10)፡ ሲጓዙ በሮቹ በአልተስተካከለ የአዉድማ ወለል ላይ ሲያደናቅፉት ዖዛን ታቦቱን ለመያዝ እና እንዳይወድቅ ለመጠበቅ እጁን ዘረጋ (ቁጥር 9) ፤ እግዚአብሄር በዖዛን አለመታዘዝ በመበሳጨቱ በሞትም ቀሰፈው (ቁጥር 10) ፡፡ ታቦቱን መንካት ብቻ ሳይሆን ለመሸከምም ምሰሶዎቹን ይጠቀሙ ነበር እንጂ (ዘጸ 25፡ 12-15) ፤ ድርጊቱ በየዋህነት መፈፀሙ ችግር የለዉም ታቦት መንካት የእግዚአብሄርን ህግ በቀጥታ መጣስ እና ሞት የሚያመጣ ነው (ዘኁ 4፡ 15) ፡፡ የሆነ ነገር ለማድረግ የእግዚአብሄር ማረጋገጫ ማግኘት አንድ ነገር ነው ነገር ግን እንዴት ማድረግ የሚኖርብን ሌላ ነገር ነው ፡፡ እንዴት ታቦቱን እንደሚያንቀሳቅሱ እግዚአብሄር ትዕዛዝ ሰጥቷቸው ነበር ነገር ግን እዚህ ትዕዛዞቹን ላለመከተል በግልፅ መረጡ ፡፡
1-ዜና መዋዕል (13፡ 11-14)፡ ዖዝያ ሞተ ምክንያቱም ዳዊት የእግዚአብሄር ትዕዛዝ አቅልሎ ስለ ወሰደ ፡፡ በምላሹ ዳዊት በእግዚአብሄር ድርጊት ስላዘነ ስፍራዉን “ የዖዝ ስብራት “ አለው (ቁጥር 11) ፡፡ ዳዊትም እግዚአብሄርን በመፍራት ታቦቱን ወደ ኢየሩሳሌም ለመዉሰድ መቀጠልን ፈራ ፤ በዚያም ፋንታ ለሰዎስት ወራት ወደ ተቀመጠበት ወደ ጌት ሰዉ አቢዳራ ቤት ወሰደው (ቁጥር 13-14) ፡፡ እግዚአብሄር አቢዳራን፣ ቤተሰቡን እና የነበረውን ሁሉ ባረከ (ቁጥር 14) ፡፡ እንደ ጌት አቢዳራ ከሌዋዊያን ከተማ ከጋትሪሞንን አንድ ሌዋዊ ነበር ( ኢያ 21፡ 24-25) ፡፡ ታቦቱ የእግዚአብሄር መገኘትን በማያቀልል አንድ ሌዋዊ መገኘት (ፊት) ነበር ፡፡
መደምደሚያ
በአሁኑ ሰዓት ከእግዚአብሄር ጋር በጉዞአችሁ የት እንዳላችሁ አላዉቅም ፤ በህይወታችሁ የእግዚአብሄርን መገኘት አቅልላችሁ ወስዳችሁታል ? ወይስ እግዚአብሄር በክርስቶስ በኩል ያደረገላችሁን ተገንዝብችሁታል ? በምትረዱት ጊዜ ትባረካላችሁ ምክንያቱም መገኘቱን ማግኘት(መቅመስ) ስለ ምትችሉ ፡፡
Thomas Constable, Dr. Constable’s Notes on 1 Chronicles, p. 25; available at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/1chronicles.pdf.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 484.
ጥያቄዎች
-
በ 1ዜና መዋዕል( 13፡ 10) እግዚአብሄር ለምን ዕዚያን ገደለው ? ታቦቱን ከመዉደቅ በመጠበቁ ምን ነበር ስህተቱ ? (ዘኁ 4፡ 15)
-
በ 1ዜና መዋዕል (13፡ 7) የኪዳኑ ታቦት በአንድ ሰረገላ ላይ ተቀመጠ ፤ በመንቀሳቀሱ ይህ ድርጊት የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ጥሷል (ዘጸ 25፡ 12-15, ዘኁ 7፡ 9) ? ለምን ?
-
ከታቦቱ ጋር እንዴት እንዲቀሳቀሱ ነበር የታዘዙት ?
-
ታቦቱ መጓዝ ያቆመዉ የት ነበር ? ለምን (1ዜና መዋዕል 13፡ 12-13) ? ለአቢዳር ዉጤቶቹ ምን ነበሩ ?
-
በ 1ዜና መዋዕል 14 ዳዊት የሆነ ነገር ሊያደርግ ሲል እግዚአብሄርን ብዙ ጊዜ ጠይቋል ፤ በራሳችሁ ህይወት ዉስጥ ወደ ፊት ከመቀጠላችሁ በፊት ወይም ከሆነ በኋላ እራሳችሁን እግዚአብሄርን ስትጠይቁ አግኝታችሁታል ? ችግሮቹ ተመሳሳይ ሆነዉ እንኳን እግዚአብሄር ሁል ጊዜ ተመሳሳይ መልስ ሳይሰጥ በህይወታችሁ አስታዉላችሁታል ? እንድናደርገው ይህ እንዴት ይፈርድብናል ?
-
በ 1ዜና መዋዕል (13-14) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Chronicles 14:8
“When the Philistines heard that David had been anointed king over all Israel, they all went in search of David; when David heard of this, he went out to face them.”
እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ነጉሥ አድርጎ አጽንቶታልና ዳዊት ጠላቶቹን ፍልስጥኤማውያንን በድፍረት ገጠማቸው ፡፡ ምንም እንኳ ዳዊት ፍልስጥኤማውያን እየፈለጉት እንደሆነ ቢሰማም እርሱ ግን በድፍረት ገጠማቸው ፡፡ ከዚያም ዳዊት ከፍልስጤኤማውያን ጋር ጦርነት ለመግጠም ስለመውጣት እግዚአብሔርን ጠየቀ ፡፡ እግዚአብሔርም “በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጣ ። “ አለው ፡፡
ልክ እንደ ዳዊት እግዚአብሔር አጽንቶሃል ፡፡ ጣላትህን እንድትገጥም እርሱ ሰርቶሃል ፣ ጠርቶሃል ፣ አሰታጥቆሃል ደግሞም ስልጣን ሰጥቶሃል ፡፡ ምናልባት ፍርሃት ከኋላ ሁን ፣ ሂድ ተደበቅ ወይም ሌላ ሰው እንድጋፈጠው አድርግ ይል ይሆናል ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ ያለ ጽኑ እምነት እውነቱን ለነፍስህ ይናገራል ፡፡ እንደ እግዚአብሔር ልጅ ጠላትህን ከመግጠም በላይ ትችላለህ ፡፡ እያንዳንዱን ውሸት በቃሉ እውነት እንድቀይርልህ እግዚአብሔርን ጠይቅ ፡፡ ከመቻል በላይ ነህ ምክንያቱም እርሱ ያለ ገደብ ከምታልመውና ከምታስበው በላይ መስራት ስለሚችል ፡፡ ኢየሱስን ከሞት ያስነሳው ኃይል በአንተም ውስጥ አለ ፡፡ ውብና ድንቅ ተደርገህ ተፈጥረሃል ፡፡ በክርስቶስ ድል አለ ፡፡ በእግዚአብሔር ላይ ታምነህ ይህንን ስታደርግ ሁልጊዜም ጸልይ ፡፡ እርሱም በኢየሱስ ስም ጣላቶችህን አሳልፎ በእጅህ ይሰጥሃል ፡፡
“ፍልስጥኤማውያንም ዳዊት በእስራኤል ሁሉ ላይ ንጉሥ ሆኖ እንደተቀባ ሰሙ፥ ፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ዳዊትን ሊፈልጉ ወጡ፤ ዳዊትም በሰማ ጊዜ ሊጋጠማቸው ወጣ ። “
—1ኛ ዜና14:8
ተጨማሪ ጥቅስ
- ምሳሌ 16:7 — “የሰው አካሄድ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘው እንደ ሆነ በእርሱና በጠላቶቹ መካከል ስንኳ ሰላምን ያደርጋል ። “
- ሐዋርያት ሥራ 4:13 — “ ጴጥሮስና ዮሐንስም በግልጥ እንደ ተናገሩ ባዩ ጊዜ፥ መጽሐፍን የማያውቁና ያልተማሩ ሰዎች እንደ ሆኑ አስተውለው አደነቁ፥ ከኢየሱስም ጋር እንደ ነበሩ አወቁአቸው “
- ሮሜ 8:11 — “ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ፥ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።