Historical Books 1 Chronicles

Being a Mighty Man

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of David 1 Chronicles 11-12 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 292 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የመፅሀፉን ይህን ምዕራፍ እወደዋለሁ ምክንያቱም የዳዊት ኃያላን ሰዎች ላይ በመመልከት ለእግዚአብሄር ኃያላን መሆን ለእኛ ምን ማለት እንደ ሆነ እንድንማር ይፈቅድልናል ፡፡ የዳዊት ህያዉ (የሚኖር) ድንጋይ አንድ አገልጋይ እና የሚያስደንቅ አንድ የእግዚአብሄር ሰዉ ነበር ፡፡ ሰዎች በእርሱ አካባቢ ህያዉ ድንጋይ በአንድ ጥሩ መንገድ ላይ ተገኝቶ እንደ ነበር ሲጠይቁትበስሩ የሚሰሩ እና ከእርሱ የሚማሩ ሰዎች ይልኩለታል የሚኖረው ድንጋይ “ ጥሩ መንገድ እንዳለ በማወቅ ብቻ የሚመጡ ሰዎች ካሉህ አልፈልጋቸዉም ይላል “ ፡፡ የእግዚአብሄር አንድ ኃያል ሰዉ የተደላደለ መንገድ ወይም የሚስብ መንገድ አይመለከትም ፤ ይልቁንም የእግዚአብሄር ፅኑ ሰዉ የራሱን የተደላደለ መንገድ ይፈጥራል፣ ለራሱ ደህንነት አይጨነቅም ምክንያቱም ለመንገዱ እግዚአብሄር እንደ ጠራው ያውቃል ፡፡

ትምህርት

1-ዜና መዋዕል (11፡ 1-3)፡የዳዊት መቀባት ፡፡ ሁሉም እስራኤል (የቀሩት) ወደ ዳዊት ኬብሮን ላይ መጡ ፤ በዉጊያ እንዴት መርቷቸዉ እንደ ነበር እና እንዲያስተዳድር በእስራኤል ላይ እግዚአብሄር ቀብቶት እንደ ነበር ያውቃሉ ( ቁጥር 1-2፣ መዝ 78፡ 70-72) ፡፡ የቀሩት ነገዶች ተወካዮች በአንድ ላይ በመምጣት በእግዚአብሄር ፊት ከዳዊት ጋር ኪዳን በማድረግ በይሁዳ ላይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም በእስራኤል ላይ ንዳዊትን ጉስ አደረጉት (ቁጥር 3) ፤ እነዚህ ጥቅሶች በ 1ሳሙኤል 16 ( 2ሳሙኤል 5፡ 1-3) የሚገኘዉን የእግዚአብሄርን ቅባት በዳዊት ላይ መፈፀሙን ይገልፃሉ፡፡

1-ዜና መዋዕል (11፡ 4-9)፡ የዳዊት ኢየሩሳሌምን መያዝ ፡፡ ዳዊት እስራኤልን በኢየሩሳሌም ከተማ(ኢያቡስ ተብላ ትጠራለች) ላይ ለዘመቻ መራ ፡፡ በዚያ የነበሩት ነዋሪዎች ዳዊት ወደ ኢየሩሳሌም በፍፁም መግባት እንደ ማይችል ቢያስቡም ከተማዋን ያዘ (ቁጥር 4-5) ፤ ከተማዋ እንደ ገቡ ዳዊት ፅኑ ከሆኑት ከከተማዋ ነዋሪዎች መጀመሪያ አንድ የሚገድል የእርሱ አለቃ አዛዥ እንደ ሚሆን ተናገረ ፡፡ ኢዮአብ የመጀመሪያዉ ስለ ነበር አለቃ ሆነ (ቁጥር 6) ፤ በዚህ ሂደት ዳዊት በህይወቱ ቅባት እና ሽፋን ስለ ተናገረ ሰዎች በዚያ መጓዝ ችለዋል ፡፡ ኢዮአብ ዳዊት እንዲያደርጉት ጠርቶ በነበረዉ ተጓዘ ፤ ኢዮአብ ከዳዊት አጠገብ በመሄድ በዚያ ቅባት እራሱን አገናኘ ፡፡ ለኢዮአብ የነበረዉ ያ መነቃቃት እንዴት በሌሎች ላይ ማለፉ ያስገርመናል ፡፡ በሚያስደንቅ ሁኔታ ኢዮአብ የዳዊት እህት (1 ዜና መዋዕል 2፡ 16) የጽሩያ ልጅ ነበር ስለዚህ ኢዮአብ የዳዊት እህት ልጅ ነበር ፡፡ የዳዊት ከተማ ቆይቶ ቤተ መቅደሱ ከተገነባበት ስፍራ ከሞሪያ ተራራ ስር ከቄድሮን ሸለቆ በላይ የምትገኝ ነበረች (1ዜና መዋዕል 3፡ 1) ፡፡ ፂዎን የኢየሩሳሌምን መላዉ አካባቢ - የዳዊትን ከተማ፣ የቤተ መቅደሱን ተራራ፣ የኢየሩሳሌምን ጠቅላላ ከተማ (ኢሳ 28፡ 16) ያመለክታል ፤ በደቡብ ምስራቅ ተራራ ላይ የምትገኝ የኢያቡስ የምሽግም ስፍራ ነበረች (ቁጥር 7) ፡፡ እነዚህን ቃሎች አስታዉሉ፡ የዳዊት ከተማ፣ ኢየሩሳሌም እና ፂዎን በመቀያየር ይጠቀሙባቸዉ ነበር ፡፡ ዳዊት በከተማዋ ዙሪያ ገነባ ኢዮአብ ደግሞ የቀረዉን አደሰ (ቁጥር 8) ፡፡ ዳዊት በኃይል ሲያድግ እግዚአብሄር ከእርሱ ጋር ነበር (ቁጥር 9) ፡፡

1-ዜና መዋዕል (11፡ 10-47)፡የዳዊት ኃያላን ሰዎች ፡፡ የዕብራዊ ቃል “ ኃያላን “ ለሚለው ጠንካራ ወይም ኃይለኛ ማለት ሲሆን ከፍተኛ ችሎታን ወይም ያልተለመደ ጥራትን ይገልፃል ፡፡ በቁጥር 10 የዳዊት ኃያላን ሰዎች ቀርበዋል (ተዋዉቀዋል) ፤ በአጠቃላይ በብሉይ ኪዳን ዉስጥ “ ኃያል “ የሚለው ቃል ችሎታን ለመግለፅ ጥቅም ላይ ዉሎ ነበር፡ የአንበሳን ጥንካሬ ለመግለፅ (ምሳ 30፡ 30)፣ ለጡሩ እና ለመጥፎ ሰዎች (1ዜና መዋዕል 19፡ 8)፣ “ ለግዙፎች “ (ዘፍ 6፡ 4)፣ ለመለዓክት ( መዝ 103፡ 20) እና ለእግዚአብሄር (ዘዳ 10፡ 17) ፡፡ በቁጥር 11 መጀመሪያ ላይ ኃያላን ሰዎች ቀርበዋል ስራቸዉም ተመዝግቧል - ኢዮአብ አዛዥ ነበር እንዲሁም በአንድ ጊዜ 300 ሰዎችን የገደለዉ ያሾብዓም የ30 ኃያላን ሰዎች አለቃ ነበር (ቁጥር 11) ፡፡ ሰዎስት የተለዩ ተዋጊዎች በአንድ ላይ ለዳዊት ሰርተዋል - አልዓዛር (ቁጥር 12)፣ ኢያቡስቴ (2ሳሙ 23፡ 8) እና ሳማ (2ሳሙ 23፡ 11-12) ፡፡ ቁጥር 13-14 ዳዊት እና አልዓዛር በፍልስጤማዊያን ላይ በአንድ ላይ በመዋጋት ድል አድርገዉ እንደ ነበር ይገልፃል ፡፡ ዳዊት ኃያላን ሰዎች ተሰጥተዉት እንደ ነበር አስባለሁ ምክንያቱም ከጎናቸዉ በጦር ሜዳ ስለ ተዋጋ ፡፡ መሪዎች አሸናፊዎች ለመሆን የሚወስደዉን ማንኛዉንም ነገር በመዝለል ለማድረግ ፍቃደኞች መሆን አለባቸው ፡፡ በፍልስጤም ጦር ላይ በአንድ ላይ ከተዋጉ በኋላ በዳዊት እና በአልዓዛር መካካል ያለዉን ግንኙነት ማሰብ ትችላላችሁ ?

እነዚህ ሰዎስት የ30 አለቃ ሰዎች ፍልስጤማዊያን በቤተልሄም እንደ ነበሩ ወደ ዳዊት ወደ አዶላ ዋሻ አለት ላይ ሄዱ (ቁጥር 13-16) ፤ ከቤቴ ልሄም ምንጭ ዳዊት ዉኃ ተጠምቶ ስለ ነበር ሰዎስቱ ኃያላን ሰዎች ለእርሱ ዉሃ ለማምጣት ሰርገዉ(ቀድደው) ወደ ቤቴ ልሄም ገቡ (ቁጥር 17-18) ፤ ነገር ግን ዳዊት ለመጠጣት እምቢ አለ በዚያም ፋንታ ለእግዚአብሄር አፈሰሰው (ቁጥር 18) ፡፡ ይህን ያደረገበት የዳዊት ምክንያት በቁጥር 19 ላይ ይገኛል ፤ ያንን መታደስ(ዉሃ መጠጣት) መቀበል አልቻለም ምክንያቱም የእርሱ ሰዎች ለእርሱ ምቾት ሲሉ ለብቻቸዉ ህይወታቸዉን አደጋላይ ጥለዉ ስለ ነበር ፡፡

የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የ 30 ኃያላን ሰዎች እንደ አዛዥ የተዘረዘረ ነበር (ቁጥር 20-21) ፤ በናያስም ከእርሱ ኃያላን ጅግኖች ጋር ተዘርዝሮ ነበር (ቁጥር 22-24) ፡፡ በናያስ በዳዊት ጠባቂ ልጆች ላይ ተቀምጦ የነበረ ከ30ዎቹ በጣም እንደ ተከበረ ተደርጎ ተለይቷል (ቁጥር 25) ፡፡ በቁጥር 26-47 የቀሩት ኃያላን ሰዎች የቤርሳቤህን ባል ኬጢያዊዉን ኦሪዮን አካትቶ የተዘረዘረ ነበር (ቁጥር 41) ፡፡

መደምደሚያ

ለእግዚአብሄር ኃያል (ፅኑ) ወንድ ወይም ሴት ለመሆን ምን ይወስዳል (ይፈልጋል) ? ስቴፈን ኮል የዳዊት ኃያላን ሰዎች ያጋሩትን አምስት ባህሪያት ያመለክታል ፡፡ እነዚህ መርሆች በአሁኑም ጊዜ ለሁላችንም መተግበር ይቻላል - ለወንድም ለሴትም ፡፡

  1. ለእግዚአብሄር ቁርጠኝነት በእምነት ላይ የተለየ የሆነዉን ለመቋቋም የሚችል ጠንካራ ያደርጋል (2ሳሙ 23፡ 9-12, 18, 21) ፡፡
  2. ለእግዚአብሄር ቁርጠኝነት ድካምን ለመቋቋም የሚችል ጠንካራ ያደርጋል (2ሳሙ 23፡ 8, 10) ፡፡
  3. ለእግዚአብሄር ቁርጠኝነት የብዙሀኑን የግል አስተያየት በመተዉ እግዚአብሄር የሰጠዉ ተግባር እንዲፈፀም ለብቻ መቆም የሚችል ጠንካራ ያደርጋል (2ሳሙ 23፡ 10) ፡፡
  4. ለእግዚአብሄር ቁርጠኝነት መነቃቃት ለመዉሰድ ጥበብ እና ጥንካሬ እንዲኖር ጠንካራ ያደርጋል (2ሳሙ 23፡ 9-12) ፡፡
  5. ለእግዚአብሄር ቁረጠኝነት ለምክንያቱ የራስን አንድ ህይወት አደጋ ላይ መጣል እስኪቻል ጠንካራ (ማቴ 10፡ 38-39) ፡፡

የዳዊት ኃያላን ሰዎች ከብበዉት ነበር፣ ጠብቀዉት ነበር፣ ከእርሱ ጋር ተዋግተዉ ነበር እናም ጥሪዉን እንዲፈፀም አግዘዉታል ፡፡ ኢየሱስም የራሱ ፅኑ (ኃያላን ሰዎች) ነበሩት - ከእነርሱም ዉስጥ አንዱን ከመንገዱ ቢያጣዉም እንኳን 12 ደቀ መዛሙርት ነበሩት ፤ ሐዋሪያዉ ጳዉሎስም ነበሩት - ጢሞቲዎስ፣ ዮሐንስ ማርቆስ፣ ሲላስ እና ሉቃስ፡፡

ለእኛ ጥያቄው በማንኛዉም የተለዬ ነገር ለመወሰድ፣ በአለፈዉ ድካም ለመቀጠል፣ እግዚአብሄርን ለመከተል የሌሎችን የግል አስተያየት ላለመቀበል፣ መነሳሳት ለማድረግ ጥበብ እና ጥንካሬ እንዲኖረን እና ለእግዚአብሄር ጥሪ ራሳችንን አደጋ ዉስጥ ለመጣል ፍቃደኞች ለመሆን (ማቴ 10፡ 38) በመዘጋጀት ቆርጠኞች ነን የሚል ነው ፡፡

  1. Stephen Cole, “God’s Mighty Men (2 Samuel 28:8-39)”; available at www.bible.org.

ጥያቄዎች

  1. ኢዮአብ የዳዊት ሰራዊት አዛዥ ለመሆን ምንድን አደረገ ? ጥሪያችንን እንድንፈፅም ስለ እኛ ይህ ምን ይለናል ?
  2. የመላዉ እስራኤል ንጉስ ከመሆኑ በፊት ዳዊት ለምን ያክል ጊዜ የይሁዳ ንጉስ ነበር (2ሳሙ 5፡ 4-5) ? የእስራኤል ሰዎች ስለ ዳዊት የእኛ ንጉስ ለምን አይሆንም ብለዉ ስለ ዳዊት የተናገሩዓቸዉ አንዳንድ ነገሮች ምንድን ነበሩ ? በዳዊት ህይወት ላይ በግልፅ ስለ ተነገረዉ ትንቢት ያውቃሉ ፤ ይህን በመዉሰድ ለማረጋገጥ ለምን እንደ ቆዩ ምን ታስባላችሁ ?
  3. ከዳዊት ሰዎች መካከል ሰዎስቱ ኃያላን እነማን ነበሩ ? ኃያላን ተብለዉ የተወሰዱት(የታሰቡት) ለምን ነበር ?
  4. ጥቂት እንደፈለገ ከገለፀ በኋላ ዳዊት ከጉድጓድ የሆነዉን ዉሃዉን ለመጠጣት ለምን እምቢ አለ ? ስትቀበሉ እንደ መስዋዕት ለእግዚአብሄር ለማቅረብ የምትናፍቁት አላችሁ ?
  5. በ 1ዜና መዋዕል 12 እንደ ንጉስ የዳዊትን በዓል ይገልፃል ፤ እንደ አማኞች የምናደርጋቸዉ ምን ድግሶች አሉ ምንስ ይሆናል ? (ኢሳ 51፡ 11, ራዕ 7፡ 17, 19፡ 7-10, 21፡ 4, 22፡ 3-5)
  6. በ 1ዜና መዋዕል (11-12) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Chronicles 11:10

“The following were the chiefs of David’s warriors who, together with all Israel, strongly supported him in his reign to make him king according to the LORD’s word about Israel.”

ዳዊት ንጉሥ ሁኖ በሚመራበት ጊዜ ተቀብቶ ብቻ አልነበረም ነገር ግን በዙሪያው ሰላሳ ኃያላን ሰዎችም ነበሩ ፡፡ እነዚህ ሰዎች ዳዊትን በንግሥና ጥሪው ውስጥ በጣም ኃያል ሁኖ እንድያድግ አስችለውታል ፡፡ እነዚህ ኃያል ሰዎች ከሌሎቹ ከፍ ባለ ጦረኝነት ተለይተው ይቀመጣሉ ፡፡ ዕድሎችን በእምነት ያልፋሉ እንድሁም ድካምን ለመሸከም ዝግጁነት አላቸው ፡፡ ለምሳሌ ፡- በናያስ በበረዶ ውስጥ አንበሳ ገደለ እንድሁም አቢሳ ጦሩን በሶስት መቶው ላይ አነሳ በአንድ ጊዜም ገደላቸው ፡፡ እነዚህ ጽኑዓን ሰዎች እርመጃን ለመውሰድ ዝግጁ ነበሩ ፣ ታማኞች እና ደግሞ የሚከፈለው ዋጋ ምንም ቢሆን ለራሳቸው ምንም ሳይፈልጉ ንጉሡን አገለገሉ ፡፡ ለምሳሌ ውኃ ለጠማው ለንጉሥ ዳዊት ሲሉ ሶስቱ ሰዎች ወደ ጦር ግንባር ሄደዋል ለእርሱ ፍላጎት ሲሉ ህይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለዋል ፡፡

ልክ እንደ እነዚህ ኃያል ሰዎች እናንተም ለነገሥታት ንጉሥ ለሆነው ለእግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ ለመሰጠት ተጠርታችኋል ፡፡ ስለ ልማድ ወይም የሆነ ነገር ሰለሚሰጣችሁ እንድትከተሉት እግዚአብሔር አይፈልግም ፡፡ ይልቁንም ለእርሱ ከሆነ ከሙሉ ልብ ከሚመነጭ ፍቅር እንድትከተሉት እንጅ ፡፡ እርሱ ራሳችሁን እንድትክዱና መስቀሉን በመሸከም እንድትከተሉት ይጠይቃችኋል ፡፡ ኢየሱስን በሙሉ ልባችሁ ፣ ነፍሳችሁና አሳባችሁ ውደዱት ፡፡ ከብዙሃኑ የተለያችሁ ሊመስል ይችላል ፣ ብቻችሁን ልትሆኑም ትችላላችሁ ፣ ትልልቅ እድሎችን ልትተው ትችላላችሁ ፣ ልትዝሉም ትችላላችሁ ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር እንድህ ይላችኋል ኃይልን በሚሰጣችሁ በክርስቶስ በእርሱ ሁሉን ትችላላችሁ ፡፡

“ለዳዊትም የነበሩት የኃያላን አለቆች እነዚህ ናቸው፤ ስለ እስራኤል እንደ ተናገረው የእግዚአብሔር ቃል ያነግሡት ዘንድ ከእስራኤል ሁሉ ጋር በመንግሥቱ ላይ አጸኑት ። “

  • 1ኛ ዜና 11፡10

ተጨማሪ ጥቅስ

1ኛ ነገሥት8:61 — “ ንደ ዛሬው ቀን በሥርዓቱ ትሄዱ ዘንድ፥ ትእዛዙንም ትጠብቁ ዘንድ፥ ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ጋር ልባችሁ ፍጹም ይሁን ። “

ማቴዎስ 16:24 — “ በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ ። “

ፊልጵስዩስ 4:13 — “ ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ ። ”