Reasons to Fast
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of David 1 Chronicles 10 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በሁል ጊዜ ህይወታችሁን ለማስገባት በሪቫይቭ ት/ቤት መፍቀዳችሁ ትህትና እንደ ሆኖ አገኘዋለሁ ፡፡ አሁን የዚህ ጥናት የአንድ አመት ሰዎስት አራተኛዉ ጉዞ ላይ ነን ፡፡ ለእናንተ ጥያቄ አለኝ ፤ የት እንደምታጠኑ፣ ምስሎችን የት እንደ ምትመለከቱ ወይም ድምፆችን የት እንደ ምትሰሙ ምስል በማንሳት በ info@reviveSchool.org ላይ ለእኛ ላኩልን ? ቡድናችን ያን ማየት ይወዳል ፡፡ ምንም ነገር እንዳትሉ ፤ ሁል ጊዜ ሰዎች ከእግዚአብሄር ጋር ጊዜ አቸዉን የት እንደሚያሳልፉ በማየት እሳባለሁ ፡፡ ለእኛ ዜና መዋዕልም ኃይለኛ ጥናት ሆኗል ስለዚህ የእናንተም ምስልም ያበረታታናል ፡፡
በግልፅ እንከልስ ፤ የይሁዳ ሰዎች በእግዚአብሄር ላይ ኃጢዓት አድርገዉ ነበር ፤ ህዝቡም በመያዝ ሰዎቹ ወደ ባቢሎን ተሰደዱ ፡፡ በዜና መዋዕል ህዝቦቹ በመጨረሻም ከምርኮ ነፃ በመዉጣት ወደ ይሁዳና ኢየሩሳሌም እየተመለሱ ነበር፡፡ በ 1ዜና መዋዕል በመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ምዕራፎች የአስራ ሁለቱ ነገዶች የዘር ግንድ ተመዝግቧል - ሰዎቹን ኃጢዓታቸዉን በማስታወስ አሁንም የእግዚአብሄር እቅድ ሳይሰበር እንደ ነበር እና የሚፈፀም እንደ ሆን ለማሳየት ፡፡ ትናትና ሰዎቹን በእግዚአብሄር የት እንደ ነበሩ እንደ ገና ወደ ቦታቸዉ ለመመለስ እንዴት በቡድን ( እስራኤላዊያን፣ ካህናት፣ ሌዋዊያን እና የቤተ መቅደስ አገልጋዮች) ተመልሰዉ እንደ ነበር ተመልክተናል ፡፡
ትምህርት
1-ዜና መዋዕል (10፡ 1-6)፡ ቁጥር 1 በጊልቦአ ተራራ የእስራኤል ሰዎች ስለ መጨፍጨፋቸው ይገልፃል ፤ በግድያዉ ሳዖል እና ልጆቹ ዮናታን፣ አሚናዳብ እና ሜልኪሳን ሁሉም ተገደሉ (ቁጥር 2) ፡፡ በ 1ዜና መዋዕል 8 ሳዖል አራት ልጆች እንደ ነበሩት አንብበናል ፤ አራተኛዉ ልጅ (አስበኣል) በ 1ዜና መዋዕል (9፡ 39) የተዘረዘረ ነው ፡፡ በ 2ሳሙ (2፡ 8) አረተኛዉ ልጅ ኢያቡስቴ ተብሎ የተጠራ ነው ትርጉሙም “ የእፍረት ሰው “ በዉጊያዉ አስበኣል ስላልሞተ ምናልባት ተቀይሮ የነበረው ፡፡
ሳዖል በኃይል በቀስት ቆስሎ ስለ ነበር ጋሻ አጃግሬዉን ፍልስጤማዉያን ሞቱን መጨረስ ከመቻላቸዉ በፊት የእርሱን ሰይፍ በመጠቀም እንዲገድለዉ ጠየቀው (ቁጥር 3-4) ፤ ይሁን እንጂ ጋሻ አጃግሬዉ እምቢ ባለዉ ጊዜ ሳዖል በሰይፉ ላይ በመዉደቅ ራሱን ገደለ (ቁጥር 4) ፡፡ ጋሻ አጃግሬዉ ሳዖል ሲሞት ባዬ ጊዜ በተመሳሳይ ሰይፍ ራሱን ገደለ (ቁጥር 5) ፡፡ በቁጥር 6 ፀሀፊዉ የሳዖል ሙሉ ቤቱ እንደ ሞተ ተናግሯል ፡፡
የራሱን ህይወት መዉሰድ ሲሰማዉ ሳዖል በእዉነት እግዚአብሄርን ታምኗል ?ማክአርቱር “ የሳዖል ራስን ማጥፋት በህይወቱ በዚህ ክስተት ላይ በእግዚአብሄር እምነት ማጣት የመጨረሻዉ መግለጫ እንደሆነ ተናግሯል “ ፡፡ ራስን ማጥፋት በብሉይ ኪዳን ያልተለመደ ክስተት ነበር (2ሳሙ 17፡ 23፣ 1ነገ 16፡ 18) ፡፡ ከደረሰብን ማንኛዉም ነገር ሁል ጊዜ እግዚአብሄር ሊዋጀን ይችላል ፤ ራስን ማጥፋት የእግዚአብሄር አይደለም ፡፡ ሁል ጊዜ ተስፋ አለን !
1-ዜና መዋዕል (10፡ 7-10)፡ ከዉጊያዉ ስር በሸለቆዉ ዉስጥ የነበሩት ሳዖል እና ልጆቹ እንደ ሞተ በሰሙ ጊዜ ከከተሞቻቸዉ ሸሹ ፡፡ ፍልስጤማዉያንም ወደ ከተሞቹ በመሄድ በዚያ ተቀመጡ (ቁጥር 7) ፡፡ ፍልስጤማዉያን የሳዖልን እና የልጆቹን አካል አገኙት (ቁጥር 8) ፤ ሳዖልን ቆራረጡት ራሱንም በመቆራረጥ እስራኤላዊያንን አሸነፍዉባቸዉ በነበሩት ምድር ሁሉ ዜናዉን ላኩ (ቁጥር 9) ፡፡ በጣዖቶቻቸዉ አምላኮች ቤተ መቅደስ መሳሪያዉን አስቀመጡ ራሱንም በዳጎን አማልክት መቅደስ ላይ ሰቀሉት (ቁጥር 10) ፡፡ የዳጎን መቅደስ ፍልስጤማዉያን ከ100 አመት በፊት ከእስራኤላዊያን ሰርቀዉት የነበሩትን የኪዳኑን ታቦት ያስቀምጡበት በነበረበት ስፍራ ነበር ፡፡
1-ዜና መዋዕል (10፡ 11-12)፡ የኢያቢስ ገለዓድ ፅኑ ሰዎች በሳዖል እና በልጆቹ አካል ላይ ሆኖ የነበረዉን ሲሰሙ በመሄድ ሰዉነታቸዉንመለሱት ፡፡ አጥንታቸዉን በአንድ አጣጥ ዛፍ ስር በመቅበር ስለ ሞታቸዉ ለማዘን ለሰባት ቀን ፆሙ (1ሳሙ 31፡ 12-13) ፡፡
1-ዜና መዋዕል (10፡ 13-14)፡ ሳዖል ሞተ ምክንያቱም ለእግዚአብሄር የታመነ ስላልነበረ ፤ በሞት ያስቀጣ የነበረዉን መናፍስት ጠሪዎችንም ማማከር አማክሮ(ዘሌ 20፡ 27) ነበር እግዚአብሄርን አላማከረም ነበር ፡፡ በሞቱ የሳዖል መንግስት ወደ ዳዊት ዞረ ፡፡ እግዚአብሄር ሳዖልን ስለ አለመታዘዙ እና ስለ አለመታመኑ እራሱን እንዲገድል ፈቀደለት ፡፡ በሳዖል ድርጊት ምክንያትእግዚአብሄር ጆሮዉን በማዞር ወደ ሳዖል ጩኸት አላዳመጠም (ኤር 7፡ 13-16)፡፡ ሳዖል በቀድሞዉ ኪዳን ስር እንደ ነበር አስታዉሱ ነገር ግን እግዚአብሄር ይመስገን በአዲሱ ኪዳን ስር ነን ፡፡ መናፍስት ጠሪዎችን ማማከራችን ወይም ያልታዘዘን መሆናችን ምንም አይደለም ምክንያቱም ንስሃ መግባት እንችላለን በክርስቶስም በኩል የኃጢዓት ይቅርታ እናገኛለን ፡፡
መደምደሚያ
ብሎገር ክርስቲን ፊዖል አማኞች ለምን እንደማይፆሙ ሰዎስት ምክንያቶችን ትሰጣለች፡ 1) ፍርሀት፣ 2) አላዋቂነት እና 3) አመፅ ፤ ነገር ግን “ ፆም እግዚአብሄር ለእናንተ ላዘጋጀዉ ስራ እንደ ሚያዘጋጃችሁ “ ትገልፃለች ፡፡ ለመፆም ምክንያቶቹ ምንድን ናቸው ?
- ለአገልግሎት ለመዘጋጀት (ማቴ 4፡ 1-17፣ ማር 1፡ 12-13)
- የእግዚአብሄርን ጥበብ ለመፈለግ (ሐዋ 14፡ 23)
- ሀዘንን ለመግለፅ (ነህ 1፡ 1-4)
- ጥበቃ ወይም ነፃ መዉጣትን ለመፈለግ ((ዕዝ 8፡ 21-23)
- ለንስሃ (ዮና 3፡ 6-10)
- ድል ለማግኘት (መሳ 20፡ 26)
- እግዚአብሄርን ለማምለክ (ሉቃ 2፡ 36-38)
ቢል ብራይት (የካምፓስ ክሩሰድ አገልግሎት መስራች) በህይወቱ ብዙ ጊዜ ፆሟል ፤ ፆም ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ የመጀመሪያ ፍቅሩን እንዳደሰዉ እንዲሁም ትሁት በማድረግ እዉነተኛ መንፈሳዊ ሁኔታዉን እንዳነቃቃዉ ይናገራል ፤ በህይወቱ የእግዚአብሄርን ቃል እንዳፈጠነው፣ የፀሎት ህይወቱን እንደ ጨመረዉ እና የግል መነቃቃትን እንዳመጣለት ይናገራል ፡፡ ፆም ምንም ነገር አያስወጣም ይሁን እንጂ ሁሉንም ነገር ያስወጣል(ይጠይቃል) ፡፡ እስራኤላዊያን ለአዲስ ንጉሳቸዉ በሚጠብቁ ጊዜ ይፆማሉ ፤ ለእኛም ይህ ትንቢታዊ ቃል እንደ ሆነ አምናለሁ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 347.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 506.
Kristen Feole, Why Should I Fast? Seven Examples of Fasting in the Bible; available at https://www.faithgateway.com/why-should-i-fast-7-examples-fasting-bible/#.W6qPW34pBPM.
Bill Bright, 7 Basic Steps to Successful Fasting & Prayer (Wayne, NJ: New Life Publications, 1995), n.p..
ጥያቄዎች
-
ከሞንድሞቻቸዉ ጋር ያልተገደሉት የሳዖል ልጆች ስማቸዉ ማን ነበር (1ዜና መዋዕል 8፡ 33) ? እንዴት ነበር የገደለቸው ? (2ሳሙ 4፡ 5-7)
-
ንጉስ ሳዖል በተገደለ ጊዜ በእስራኤላዊያን መካከል ምን ተፈጠረ ? በዚህ ድርጊት እና ኢየሱስ በታሰረ እና በተገደለ ጊዜ ባለዉ ንፅፅር ታያላችሁ ? (ማር 14፡ 27)
-
የሳዖል ጥቂት ኃጢዓቶች ምን ነበሩ ? ካለ ምን ያክል ሰው በሳዖል ኃጢዓት ተጠቅቶ(ተጎድቶ) ነበር ? የኃጢዓታችሁ ጉዳት ከእናንተ ስለ ማለፉ አስባችሁ ታውቃላችሁ ?
-
የኢያቢስ ገለዓድ ኃያላን ሰዎች የሳዖልን ሰዉነት ለምን በክብር ቀበሩት (ተቀበሉት/ቀበሩት) ? (2ሳሙ 11፡ 1-11)
-
በ 1ዜና መዋዕል 10 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Chronicles 10:13–14
“Saul died for his unfaithfulness to the LORD because he did not keep the LORD’s word. He even consulted a medium for guidance, but he did not inquire of the LORD. So the LORD put him to death and turned the kingdom over to David son of Jesse.”
ታሪክ ጸሀፊያኑ የንጉሥ ሳኦልን ህይወት በአጫጭር አረፍተ ነገሮች ለእስራኤላውያን ጠቀለሉላቸው በቃ የሳኦልን ህይወት ታሪክ የጻፉ በሚመስል መልኩ አድርገው ፡፡
ይህንን የሳኦልን ህይወት ማጠቃልያ ስታነብ የአንተ የህይወት ታሪክ ምን ሊሆን እንደሚችል አስብ ፡፡ ህይወትህ ነገ ቢያበቃ ሰዎች እንዴት ይሆን በአጭር አረፍተ ነገር የሚገልጹህ ? የምትኖረው እንደምትታወስ ተስፋ በምታደርግበት መንገድ ነው ? ህይወትህን ያለ ቁጭት ኑር ፡፡ ወደ ኋላ እንዳትል ፡፡ ነገ እስኪመጣ እንዳትጠብቅ ፡፡ እግዚአብሔር እንድትሆን የፈጠረህን ያንን ሁን ፡፡ ተነስና በልብህ ያለውን ማድረግ የምትፈልገውን ነገር ግን እስካሁን ያላደረከውን አድርግ ፡፡ ያን ጓደኛህን አግኘው ፣ ይቅርታ አድርግለት ፣ ግብዣውን ተቀበል ፡፡ የስራ ለውጥ አድርግ ፣ የተጨናነቀውን ቀጠሮ ቀይር እና ብቻህን ከኢየሱስ ጋር ቀንህን አሳልፍ ፡፡ በቃ ይህን አድርገው ! ስታደርገውም በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ላይ ታመን ደግሞም ተከተለው ፡፡ ፍርሃቱን ተውና በእምነት ኑር ፡፡ ከአምላክህ ጋር በትህትና ተመላለስ ፡፡ ኢየሱስ በፍቅር እጆቹ ይይዝሃል ፡፡ አድርገው !
“ እንዲሁ ሳኦል በእግዚአብሔር ላይ ስላደረገው ኃጢአት፥ የእግዚአብሔርንም ቃል ስላልጠበቀ ሞተ። ደግሞም መናፍስት ጠሪ ስለ ጠየቀ እግዚአብሔርንም ስላልጠየቀ፥ ስለዚህ ገደለው፥ መንግሥቱንም ወደ እሴይ ልጅ ወደ ዳዊት አሳለፈው ። “
- 1ኛ ዜና 10፡13-14
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 118:24 — “እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ ሐሤትን እናድርግ፥ በእርስዋም ደስ ይበለን ። “
መዝሙር 119:73–74 — “እጆችህ ሠሩኝ አበጃጁኝም፤ እንዳስተውል አድርገኝ፥ ትእዛዛትህንም እማራለሁ ። በቃልህ ታምኛለሁና የሚፈሩህ እኔን አይተው ደስ ይላቸዋል ። “
ሚክያስ 6:8 — “ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን ? “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።