The Service of the Nethinim
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of David 1 Chronicles 9 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የብንያም ነገድ የእርስ በእርስ ጦርነት እንደፈጠሩ እና ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ እንደ ጠፉ አይተናል ፤ ከነገዱ ስድስት መቶ ብቻ ተረፉ ፡፡ ሚስቶችን ለጋብቻ ተሰጥተዉበት የነበረዉን ጊዜ የሚያስገርም ፅሁፍ ታሳታዉሳላችሁ ነገዱስ መቀጠል ይችላልን ? አንዳንድ ብንያማዉያን በሰሜን መንግስት ሲኖሩ ጥቂቶቹ ደግሞ በደቡብ ፡፡ ማክአርቱር “ የእስራኤል ሰሜኑ መንግስት በ 722 ከክርስቶስ ልደት በፊት በፍፁም ባይመለሱም እንኳን በ 931 ከክርስቶስ ልደት በፊት ከተከፈሉ በኋላ ከአስሮቹ ነገዶች የሆኑት ብዙዎቹ ደቡብ መንግስት መፍለሳቸዉን “ አመልክቷል ፤ ያ ማለት ሁሉም የእስራኤል አስራ ሁለት ነገዶች በመጀመሪያ በይሁዳ ነገዶች ተወክለዉ ነበር ፡፡ ይሁን እንጂ ይሁዳ ለእግዚአብሄር ባለመታመኑ ምክንያት ያን ሊሆን አልቻለም ነበር ፡፡
ትምህርት
1-ዜና መዋዕል (9፡ 1-34)፡ “ ሁሉም እስራኤል “ ወደ ይሁዳ የተመለሱት የእያንዳንዳቸዉ ቅሬቶች ያመለክታል (ቁጥር 1) ፤ ቀጥሎም ፀሀፊዉም ወደ ይሁዳ የተመለሱት ላይ ቀጠለ ፡፡ ሰዎቹም ወደ ኢየሩሳሌም እና ይሁዳ በመመለስ እንደ ገና በዚያ ተቀመጡ ፡፡ ቁጥር 2 አራት ቡድኖችን ይለያል፡
- እስራኤላዊያን (ሁሉንም አይደለም)፡ ከአራቱ ነገዶች የሆኑ ሰዎች - ከይሁዳ፣ ከብንያም፣ ከኤፍሬም እና ከምናሴ እንደ ገና በኢየሩሳሌም ተቀመጡ 956 ብንያማዊያን ነበሩ (ቁጥር 3-9) ፡፡
- ካህናቱ፡ ካህናቱ በስም የተጠቀሱ እና በ 1,760 ዘመዶች የተጠቃለሉ ነበሩ (ቁጥር 10-12) ፤ “ ለእግዚአብሄር ቤት ማገልገል ስራ እጅግ ብልሃተኞች ሰዎች እንደ ነበሩ “ ገልጧቸዋል (ቁጥር 13) ፡፡ እነዚህ ካህናቶች በአዲስ ኪዳን ለአንድ ፓስተር ተሰጥቶ ከምናየው ይበልጥ የአንድ ስራ ዝርዝር ነበራቸው ፡፡
- ሌዋዊያን፡ ሌዋዊያን የካህናቱን ስራ ረድተዋል በብዙም በስም ተዘርዝረዋል (ቁጥር 13-16) ፤ በእርግጥ ካህናትን እና ሌዋዊያንን እንደ ገና ለመስፈር ከመጀመሪያዎቹ ቡድኖች መካከል መሆናቸዉ አስፈላጊ ነው ፡፡ ይሁዳ ባለመታመኑ ምክንያት ተቀጥቶ ነበር ፤ ለእስራኤል እንደ ታማኝ ህዝብ እንደ ገና ለመጀመመር አምልኮ የሚመሩ፣ መስዋዕት የሚሰዉ እና ቤተ መቅደሱን የሚጠብቁት አስፈላጊዎች ነበሩ ፤ ህዝቡን መልሰዉ ወደ እግዚአብሄር አመልክተዋል ፡፡
- የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፡ በቁጥር 17 ይህ ቡድን በይበልጥ እንደ በር ጠባቂዎች በመባል ተለይተዋል ፤ በር ጠባቂዎች በተግባራቸዉ መሰረት በስማቸው ተለይተዋል፡
የመግቢያዎቹ ጠባቂዎች (ቁጥር 19-25)፡ በሮቹን ይጠብቃሉ፣ በማታ እና በጥዋት በሮቹን ይከፍታሉ ይዘጋሉ እንዲሁም ከተማዋ ደህና እንደ ነበርች እርግጠኛ ያደርጋሉ ፡፡ በር ጠባቂዎች ከከተማዋ በሚወጣዉ እና በሚገባዉ ላይ ስልጣን ተሰጥቷቸወ ነበር ፡፡
የንብረቱ ጠባቂዎች (ቁጥር 26-27)፡ ሌዋዊ የነበሩ አራት የበር ጠባቂዎች አለቆች በቤተ መቅደሱ ዉስጥ ያለዉን ንብረት እና ክፍሎች የማየት ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል ፤ በቤተ መቅደሱ ዉስጥ ላለዉ ገንዘብ ተጠያቄዎች ነበሩ ፡፡
በቤተ መቅደሱ አገልግሎት (ቁጥር 28-32)፡ ለቤተ መቅደሱ እጣን፣ እቃዎች እና በአምልኮ ለተጠቀሙባቸው አቅርቦቶች ኃላፊነት ነበረባቸው ፡፡
በቤተ መቅደሱ ዉስጥ ዝማሬን መምራት (ቁጥር 33-34)፡ አንዳንዶች ከእነዚህ ተግባራት የሚበልጡ ነበሩ ኃላፊነታቸው በቤተ መቅደስ ዉስጥ ለመዘመር እና ለማምለክ መገኘት ነበር ፡፡
የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች በቁጥር 2 ሲገለፁ ሌላ ስም ነበራቸዉ -የተሰጡ የሚል ትርጉም ያለው ናታኔም የሚል ነበር (ዘኁ 31፡ 30) ፡፡ ከእያንዳንዱ 50 ሰዎች አንድ በሚያስፈልግ በማንኛዉም አቅም እንዲያገለግል ለሌዋዉያን የተሰጠ ነበር (ዕዝ 8፡ 20) ፤ በቤተ መቅደሱ ዉስጥ የሚነድድ እንጨት እንደ መሸከም እና እንደ ማፅዳት ያሉትን ትንንሽ ተግባራት ተሰጥቷቸዉ ነበር ፡፡ ናታኔም የሚለዉ አሕዛቦች በእስራኤላዉያን ተይዘዉ የነበሩትን ለማመልከት እንጂ የእስራኤላዉያን ስም አልነበረም ፤ ይሁን እንጂ አይሁዶችን እና ሌዋዊያንን እንዲያገለግሉ በዳዊት እና በሌሎች መሪዎች የተሸሙ ነበሩ (ዕዝ 8፡ 20) ፡፡ ዳዊት እና መሪዎቹ ናታኒሞች የማገልገል ተግባር እንደ ነበራቸዉ ያዉቃሉ ያም ይመጣ የነበረው ቀጥተኛ ጥላ ነበር (ሮሜ 15፡ 25-27) ፤ የህያዉ እግዚአብሄርን ዬሹዋ (የኢየሱስን) መገኘት ስለለመድን “ አይሁዶችን በስጋዊ ነገር በሚያስፈልጋቸዉ እንድናገለግላቸው “ ታዘናል (ሮሜ 15፡ 27) ፡፡ ነህ (3፡ 26) መጀመሪያ ወደ ኢየሩሳሌም ናታኒሞች በተመለሱ ጊዜ ግንቡን እና በከተማዋ ቅጥር በዉሃ በር አጠገብ ህንፃዉን ለማደስ እንደ ሰሩ ፅፏል ፡፡ እንደ ቤተ መቅደስ አገልጋይ መስራት ስላልቻሉ የሚሰሩት ሌላ ነገር አገኙ ምክንያቱም የሚበልጠዉን ስዕል ስለተረዱ ፡፡ ነህ (10፡ 28-29) አይናቸዉን በእግዚአብሄር እና በህጉ ላይ በማድረጋቸዉ ምክንያት ናታኒሞች ለጥሪያቸዉ የታመኑ እንደ ነበሩ ያሳያል ፡፡
መደምደሚያ
የሚያስፈልገንን እንድናደርግ እንደ አገልጋይ ለማድረግ ሁላችንምበተጠራንበት እዉነት በመጣን ጊዜ ሰዎች በስራችን እግዚአብሄርን መቅመስ (ማወቅ) ይችላሉ ፡፡ አገልጋይ መሆን ሁሉም የሚፈፅሙት ተግባር ላይ በመደገፍ የሚበልጥ ስዕል እንዳለ እንድናዉቅ ይረዳናል ፤ በናታኒም ምላሽ በምሰጥ ጊዜ ወዲያዉኑ ወደ ትልቅ ስዕል እሄዳለሁ፡፡ እንደ ክርስቶስ ተከታይ መንፈሳዊ ስጦታዎችን እና ጥቅሞችን በመቀበል እግዚአብሄር እንደ ተመረጡ ህዝቦቹ የመረጣቸዉን የማገልገል ኃላፊነት አለብን ፡፡
ኤፌ (4፡ 11-13) “ እርሱም አንዳንዶችን ሐዋሪያት፣ ሌሎቹም ነቢያት፣ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፣ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ ፤ ሁላችን የእግዚአብሄርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት ሙሉ ሰዉም ወደ መሆን የክርስቶስንም ሙላት ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመስራትና ለክርስቶስ አካል ሕንፃ ፍፁማን ይሆኑ ዘንድ “ ፡፡ ሁሉም አገልጋዮች ተግባራቸዉን በመያዝ በአንድነት በአንድ ላይ በሚሰሩ ጊዜ ሰዎችን ወደ ዳዊት ልጅ ያመለክታል ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 483.
ጥያቄዎች
-
1 ዜና መዋዕል (9፡ 1) አንባቢዎችን ይሁዳ ለምን ወደ ግዞት እንደ ተወሰደ ያስታዉሳል ፤ ፀሀፊዉ ይህን ለምን ጠቀሰ ?
-
የተተከለ ድንኳን ነበር ስለሆነም ከግዞት የተመለሱት እግዚአብሄርን ማምለክ ይችላሉ ፤ ሌዋዊያን በእያንዳንዱ ተግባር እንዲያገለግሉ እንዴት ተመደቡ (ተወሰኑ) ? ( 1ዜና መዋዕል 9፡ 22)
-
በዚህ ጊዜ ለእስራኤላዊያን የዘማሪዎች ተግባር የነበረው እንዴት ሲከሰት ያስፈልጋል (1ዜና መዋዕል 9፡ 33)? በዚህ ጥቅስ እና በራዕ (4፡ 8) መካከል ያለዉን ትይዩነት(አንድነት) ግለፁ ፤ የእግዚአብሄር አምልኮአችሁ አካል በመሆን ሙዚቃ ለእናንተ እንዴት ያስፈልጋችኋል (ይጠቅማችኋል) ?
-
የ 1ዜና መዋዕል (8፡ 29-38) በ (9፡ 35-44) መደገም አለ ፤ አንዳንዶች ይህን የፁሁፊ ገልባጭ ስህተት እንደ ነበር ያስባሉ ፤ ምን ታስባላችሁ ? በእናንተ አስተያየት አዎ ከሆነ ይህ ከእግዚአብሄር ቃል ቀነሰበት ወይስ የማይታመን ነው ?
-
በ 1ዜና መዋዕል (9፡ 2) የተጠቀሰዉ አንዱ ቡድን የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች ናታኒሞች ተብለዉ የሚጠሩት ነበሩ ፤ እነማን ነበሩ (ዘኁ 31፡ 30, ኢያ 9፡ 27, ዕዝ 2፡ 43-58) ? ለእግዚአብሄር አገልግሎት በዚህ ተግባር ራሳችሁን እንዴት ታዩታላችሁ ?
-
በ 1ዜና መዋዕል 9 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Chronicles 9:2
“The first to live in their towns on their own property again were Israelites, priests, Levites, and temple servants.”
የይሁዳና የእስራኤል መንግስታት ተከፍለው አልቀጠሉም ፡፡ ከሰባ ዓመት የባቢሎን ግዞት በኋላ ቤተ መቅደሱን ለመገንባት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ፡፡ በአውራጃዎቻቸውና በከተሞቻቸው መጀመሪያ የተቀመጡ እስራኤል ፣ ካህናት ፣ ሌዋውያን እና ናታኒምም ነበሩ ። የታሪክ ጸሀፊውም በታሪክ ውስጥ ለዚህ ግዜ ቤተ መቅደሱን እንደገና ለመስራት የሚጠቅሙ ሚናዎችን ለየ እነርሱም ፡- ልዩ ጥሪና መታዘዝ ናቸው ፡፡
በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ እንደ ክርስቶስ ተከታይ አናንተ የተለየ ሚና አላችህ ፡፡ በእርሱ አካል ውስጥ ቅዱሳንን ለአገልግሎቱ ስራ ያሰለጥኑ ዘንድ እርሱ አንዳንዶችን ሐዋርያት ፣ ሌሎችን መምህራን ፣ ሌሎችን ወንጌላውያን ፣ ሌሎችን እረኞች ሌሎችን ደግሞ ነቢያት አድርጎ መርጧል ፡፡ እያንዳንዱ አገልግሎት እየተደጋገፈ የክርስቶስን አካል ለመገንባት በአንድነት ይሰራል ፡፡ ዛሬ በትህትና እንድታደርጉት የተሰጣችሁን ሚና ተቀበሉ ፡፡ ስራው ወይም ሚናው ምንም ይሁን አንዱ ሌላውን ያገልግል ፡፡ ብትታዩም ባትታዩም ለሰው ሳይሆን ለእግዚአብሔር እንደምታደርጉ በሙሉ ልባችሁ አድርጉ ፡፡ ለእግዚአብሔር ከራስ ወዳድነት በፀዳ መልኩ እንድታደርጉት የተጠየቃችሁትን ስራ ስትቀበሉ በህይወታችሁ የእግዚአብሔርን መገኘት ታያላችሁ እንድሁም የተትረፈረፈ ደስታና ሰላም ይሆንላችሁ ፡፡
“ በአውራጃዎቻቸውና በከተሞቻቸው መጀመሪያ የተቀመጡ እስራኤልና ካህናት ሌዋውያንም ናታኒምም ነበሩ ። “
- 1ኛ ዜና 9፡2
ተጨማሪ ጥቅስ
ሮሜ 15፡25 — “ አሁን ግን ቅዱሳንን ለማገልገል ወደ ኢየሩሳሌም እሄዳለሁ ። “
ኤፌሶን 4፡11-12 — “ እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ ፤ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ። “
ቆላስይስ 3:23 — “ ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ፥ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት ፥ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።