The Tribe of Benjamin
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of David 1 Chronicles 8 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የስም ስምንተኛዉ ምዕራፍ ላይ እንሄዳለን ፤ በ 1ዜና መዋዕል 7 ስለ ስድስት ነገዶች አዉርተናል ቢኒያምን ጨምሮ፡፡ እንደ ገና ስለ ቢንያም የምናወራዉ ለምንድን ነው ? ተስፋ አስቆራጭ እና ድግግሞሽ ሊመስል ይችላል ነገር ግን ትልቅ ስዕል አለ ፡፡ ቀስ በማለት በምናጠናበት ጊዜ እንድናይ የሚፈልገዉን ነገር እንዲያሳየን እግዚአብሄርን መጠየቅ አለብን (1ዮሐ 2፡ 20, 27) ፡፡ ወደ ቃሉ በጥልቀት ለመሄድ ራሳችንን ማስቀመጥ ያስፈልገናል ፤ ከወተት ወደ ስጋ መንቀሳቀስ (ዕብ 5፡ 13-6፡ 12) ፡፡ ይህን ትምህርት ለመማር የምንችል መሆን አለብን ! በግልፅ በእነዚህ ስሞች ላይ ለሆነ ምክንያት ሲባል ደግመን ደግመን ሄደንባቸዋል ፀሀፊዉም የጠለቀ ነገር እንድንማር ፈልጓል ፡፡
የብንያም ነገድ ወደ ሁለት ቡድን የተከፈለ ነበር ፡፡ የሰሜኑ ነገድ ከይሁዳ በተገነጠለ ጊዜ (922 ከክርስቶስ ልደት በፊት) የብንያም ነገድ ህብረቱን ተለዬ ፤ ከሮብዓም ሞኝነት በኋላ ሰለሞን ከእግዚአብሄር በመለሱ አኪያ የእስራኤልን መንግስት እንደሚከፍል ትንቢት ተናገረ፡ “ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሄር እንዲህ ይላልና ፡፡ እነሆ ከሰለሞን እጅ መንግስቱን እቀድዳለሁ አስሩንም ነገዶች እሰጥኃለሁ ፤ ስለ ባሪያዬ ስለ ዳዊት ከእስራኤልም ነገድ ስለ መረጥኋት ከተማ ስለ ኢየሩሳሌም ግን አንድ ነገድ ይቀርላታል “ (1 ነገ 11፡ 31-32) ፤ ነገር ግን መንግስቱ በተከፈለ ጊዜ ጥቂት ብንያማዊያን ለይሁዳ ታማኞች ሆነዉ ቀርተዋል፡ “ ሮብዓምም ወደ ኢየሩሳሌም መጣ የእስራኤልም ቤት ወግተው መንግስቱን ወደ ሰለሞን ልጅ ወደ ሮብዓም ይመልሱ ዘንድ ከይሁዳ ቤት ሁሉና ከብንያም ነገድ የተመረጡት አንድ መቶ ሰማንያ ሺህ ሰልፈኞች ሰዎች ሰበሰበ “ (1 ነገ 12፡ 21) ፡፡
ትምህርት
1-ዜና መዋዕል (8፡ 1-7)፡ ብንያማዊያን በይሁዳ እና በሌዊ ደረጃ ላይ ነበሩ ፡፡ ወደ መኖርያ ስፍራ ከተመለሱት ዉስጥ የቀሩ አካል ነበሩ ፡፡ ኤሁድ በሞዓባዊያን ንጉስ ላይ ድል እንዲመጣ የረዳ በጣም ይታወቅ የነበረ የእስራኤላዊያን መሳፍንት ነበር (መሳ 3፡ 12-30) ፡፡ ጌባ (ቁጥር 6) በብንያማዊያን ደቡብ ድንበር ከኢየሩሳሌም ሰሜን -ሰሜን ምስራቅ ስድስት ማይል ያክል ላይየምትገኝ የሌዋዊያን ከተማ ነበረች ፡፡ ንጉስ አሳ በዘመኑ ጊዜ ጌባን መሸገ ነገር ግን ከተማዋን እስራኤላዊያን ከግዞት ቀደም ባለ ጊዜ ተቆጣጠሩአት (ዕዝ 2፡ 26) ፡፡
1-ዜና መዋዕል (8፡ 8-13)፡ ሌሎች ብዙ ስፍራዎች ተጠቅሰዉ ነበር፡ ሞዓብ (ቁጥር 8)፣ ኦኖንና ሎድን (ቁጥር 12) እና ጌት (ቁጥር 13) ፡፡
1-ዜና መዋዕል (8፡ 14-28)፡ የቤተሰቦች አለቆች እና የቢንያማዊያን አለቆች ቤታቸዉን በኢየሩሳሌም አደረጉ (አስቀመጡ) ፤ ማንነታቸዉ በቤተሰባቸዉ ስም እና በመጡበት ስፍራ ነበር ፡፡ አንዳንድ የቀሩት ብንያማዊያን ሰሜን ሄዱ ሌሎቹ ደግሞ ደቡብ ሄዱ ፤ የቤተሰብ መስመራቸዉን ስላቆሸሹ ማንነታቸዉን ለቀቁ ፡፡ ማንነታችንን በዳዊት ልጅ በኢየሱስ ዘር ዉስጥ ልናስቀምጥ ያስፈልገናል - በራሳችን ስም ወይም ዘር አይደለም ፡፡
1-ዜና መዋዕል (8፡ 29-40)፡ ይህ ቤተሰብ በኢየሩሳሌም ቅርብ በነበረች በገባዖን ኖረ ፤ ኮንስታብል “ ገባዖን ሳዖል የጀመረባት የድንኳኑ ማደሪያ መዓከላዊ እንደ ሆነች “ ይገልፃል ፡፡ ለድንኳን ማደሪያ ገባዖን የእግዚአብሄር ምርጫ አልነበረችም ፤ የእግዚአብሄር ምርጫ ኢየሩሳሌም ነበረች ፡፡ ሳዖል የተመረጠ መሪ አልነበረም ፤ ዳዊት ግን ነበር ፡፡
የብንያም ነገድ በስጋ እና በመንፈስ መካከል የመታገል መወከያ ነው ፤ ጥቂቶች ወደ ደቡብ ሄዱ ጥቂቶቹ ደግሞ ወደ ሰሜን ሄዱ ፤ አንዳንዶች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ አንዳንዶች ደግሞ በገባዖን ተቀመጡ ፡፡ ለማድረግ የፈለጉትን መወሰን አልቻሉም ፤ ብንያማዊያን ሁል ጊዜ በአጥሩ ላይ ነበሩ ፡፡ በብንያማዊያን ምክንያት በእስራኤል የእርስ በእርስ ጦርነት ተጀመረ ፤ መሳፍንት 19-21 የአንድ የሌዋዊ ቁባት አስደንጋጭ ሞትን መግለጫ ይገልፃል ፡፡ በዚያ ዉስጥ የነበረዉን ችግር ያላዩ ብንያማዊያን ነገዶች ብቻ ነበሩ ፤ ሌሎቹ ነገዶች በብንያማዊያን ላይ አንድነት በመፍጠር በብንያማዉያን እምቢ በማለት በወንጀለኞቻቸው ምክንያት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ አጠፋዓቸው፡፡ ከትንሽ የእርስ በእርስ ጦርነት በኋላ ስድስት መቶ ብንያማዊያን ብቻ ቀሩ ፡፡ ብንያማዉያን ለስጋቸዉ ተላልፈዉ በመሰጠት በአይናቸዉ ትክክል ነዉ በማለት ማንኛዉንም ነገር የሚያደርጉት ምሳሌዎች ናቸዉ ፡፡ የብንያም የያዕቆብ ትንቢት በፍፁም ወደ እዉነት መጣ፡ “ ብንያም ነጣቂ ተኩላ ነው ፤ የበዘበዘዉን በጥዋት ይበላል የማረከዉንም በማታ ይካፈላል “ (ዘፍ 49፡ 27) ፡፡ ይህ ቁጥር የሁለት ነገሮችን ሰዎስት ስብስቦች ይገልፃል፡
- የጊዜ መዋቅሮች፡ ጥዋት እና ምሽት
- ድርጊቶች፡ መካፈል እና መብላት
- ዉጤቶቹ፡ ማደን እና መበዝበዝ
ብንያማዉያን ምን እንደ ነበሩ አያዉቁም ፤ ከደቡብ ወይም ከሰሜን አልነበሩም ፤ ከኢየሩሳሌም ወይ ከገባዖን አልነበሩም ፡፡ ያዕ (1፡ 5-8) ብንያማዉያንን፡ “ ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠዉን እግዚአብሄርንይለምን ለእርሱም ይሰጠዋል ፡፡ ነገር ግንበምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን ፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበልን ይመስላልና ፡፡ ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላዉል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለዉ “ በማለት ሊገልፃቸው ይችላል ፡፡ በይሁዳ የቀሩት ብንያማዉያን የወደፊት ተስፋ አይተዋል ፡፡
መደምደሚያ
ከአልተረጋጋ ቤተሰብ መጥታችኋል ማለት ማንነታችሁ በዚያ ይገኛል ማለት አይደለም ፡፡ የሚበልጥ ነገር አካል መሆን ትችላላችሁ ፡፡ ራዕ (7፡ 4-8) ሁሉም በአንድ ላይ የሚመጡትን 144,000 ባሪያዎች (አገልጋዮችን) ይገልፃል “ ሁሉም የእስራኤል ነገድ “ ይህ ፅሁፍ ከተጠቀሰ ጀምሮ ብንያምም የዚህ አካል መሆን ይችላል ፡፡ ብንያማዉያንም በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም ስማቸዉ ከበሮቹ በአንዱ ላይ ይቀመጣል (ራዕ 21፡ 12-13) ፡፡ ለእግዚአብሄር ታማኝ ሆነዉ በቀሩት እና ሌሎችን ወደ ዳዊት ልጅ ባመለከቱት ቅሪቶች ምክንያት ይህ ብቻ ቀላል ይሆናል ፡፡
Thomas Constable, Dr. Constable’s Notes on 1 Chronicles, p. 18; available at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/1chronicles.pdf.
“What Should We Learn from the Tribe of Benjamin?””, Gotquestions.org; https://www.gotquestions.org/tribe-of-Benjamin.html.
ጥያቄዎች
-
በ 1ዜና መዋዕል (1-9) በሁሉም የዘር ግንድ መዝገብ ከዳዊት ቤት ከተለዩ በኋላ ከእስራኤል ነገስታቶች የተጠቀሰ ምንም የለም ፤ ለምን እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ?
-
እግዚአብሄር ሳዕልን እንደ ንጉስ ያልተቀበለዉም ቢሆን በ 1ዜና መዋዕል 8 የሳዖልን ቤተሰበ ዝርዝር መግለጫ እናነባለን ፤ በቁጥር (33-40) የሳዖልን ልጆች ይመዘግባል ከዚያም የዮናታንን ዘር ብቻ ፤ ለምን ሆነ ?
-
በ 1ዜና መዋዕል 8 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Chronicles 8:33
“Ner fathered Kish, Kish fathered Saul, and Saul fathered Jonathan, Malchishua, Abinadab, and Esh-baal.”
ስለ ብንያም ዘሮች ስታነቡ እነማን እንደነበሩ ፣ አባታቸው ማን እንደነበር እና ከየት እንደተገኙ ታያላችሁ ፡፡ የብንያም ነገድ የመጀመሪያውን በእስራኤል የተቀባ ንጉስ ሳኦልን ያካትታል ፡፡ ሆኖም ግን ከይሁዳ ነገድ የተቀባው ንጉስ ዳዊት ነበር በመጨረሻ ወደ ኢየሱስ ንግስና የመራው ፡፡ ለደቂቃ ቁሙና በብንያምና ነገድና በይሁዳ ነገድ መካከል ያለውን ልዩነት አስቡ ፡፡ ስለ ዳዊትና ስለ ሳኦል አስቡ ሁለቱም በእግዚአብሔር ህዝብ ላይ ተቀብተዋል ፡፡ ነጉሥ ሳኦል በክፉ መንገድ መሄድን ሲመርጥ ንጉሥ ዳዊት በበኩሉ በእግዚአብሔር መንገድ መሄድን መረጠ ፡፡
እንደ ተቀቡ የእግዚአብሔር ልጆች በመንፈስ ወይም ደግሞ በስጋ ልትመላለሱ ምርጫ አላችሁ ፡፡ በመንፈስ መመላለስ የመንፈሰ ፈሬዎችን ያስገኛል እነዚህም ፡- ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ፡፡ በስጋ መመላለስ ደግሞ ወደ ስጋ ስራ ይመራል እነዚህም ፡- ዝሙት ፣ ትዕቢት ፣ ጣዖትን ማምለክ ፣ ቁጣ ፣ ራስ ወዳድነት ፣ ቅንዓት እና ስካር ፡፡ እንዴት ነው የምትመላለሱት ? እግዚአብሔር በእኔ ኑሩ ይላል ፡፡ ከክርስቶስ ጋር ጊዜን ስታሳልፉ ፣ ስትጸልዩ እንድሁም ደግሞ ቃሉን ስታነቡ የመንፈስን ፍሬ ማፍራት ትጀምራላችሁ ፡፡ ከዚያም አለም በክርስቶስ ስትኖሩ ፍቅራችሁን አይቶ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት መሆናችሁን ያውቃል ፡፡ በመንፈስ በምትመላለሱበት ጊዜ ለሰጋ ምኞት እንደማትመቹ እግዚአብሔር ያስታውቃችኋል ፡፡
“ ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፥ ሚልኪሳን፥ አሚናዳብን፥ አስባኣልን ወለደ ። “
- 1ኛ ዜና 8፡33
ተጨማሪ ጥቅስ
ገላትያ 5:19–21a — “የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥ መዳራት፥ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥ መለያየት፥ መናፍቅነት፥ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው ። “
ገላትያ 5:22–23a — “የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።
1 ዮሐንስ 2:6 — “በእርሱ እኖራለሁ የሚል እርሱ እንደ ተመላለሰ ራሱ ደግሞ ሊመላለስ ይገባዋል። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።