Recognizing the Importance of Unity
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of David 1 Chronicles 7 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በመፅሀፍ ቅዱስ በታሪካዊ መፅሀፍት ዉስጥ እየሰራን ነው ፤ ዜና መዋዕል እንደ ሌሎች ጥቂት የታሪክ መፅሀፍት እንደ ጥናት ያለ(የሆነ) አይደለም ነገር ግን አስፈላጊነቱ የዳዊትን ዘር ከመጀመሪያው በመሲሁ ተስፋዉ እስከመፈፀሙ በመከታተል የተገኘ ነው ፡፡ ለ 1ዜና መዋዕል ጭብጣችንን - የዳዊትን ልጅ ይገልፃል ፤ የእስራኤል ሰዎች በአሶራዊያን እና የይሁዳ ሰዎች በባቢሎን በምርኮ ዉስጥ ነበሩ ፡፡ ከ 70 አመታት በኋላ የይሁዳ ሰዎች ከምርኮ ተለቀቁ (ነፃ ወጡ) 1 ዜና መዋዕልም ወደ ምርኮ መመራታቸዉን እና ከራሳቸዉ አገር በስደት በመወሰዳቸዉ ዉስጥ ሆኖ የነበረዉን ሁሉ ይገልፃል ፡፡ የመጨረሻዉ የእስራኤል ነገዶች በአንድ ወደ አንድነት መምጣታቸዉ ነው (ሕዝ 37፡ 15-28) ፡፡
ትምህርት
1-ዜና መዋዕል (7፡ 1-5)፡ የይሳኮር ልጆች ፡፡ እነዚህ ቁጥሮች ዘፍ (46፡ 13) እና ዘኁ (26፡ 23-24) የይሳኮርን አራት ልጆች ቶላ፣ ፉዋ፣ ያሱብ እና ሺምሮን ብሎ በመዘርዘር ይደግፋሉ (ቁጥር 1) ፡፡ ቁጥር 2 የቤተሰቦቹን አያቶች አለቆችን ይጠቅሳል ፡፡ ቶላ ከመሳፍንት ዘመናት አንዱ ፈራጅ ነበር ፤ ከቶላ ብቻ 22,600 ተዋጊዎች መጥተዋል ፡፡ የቶላ ልጅ የኢዚ ልጆች 36,000 ተዋጊ ወታደሮች እና ከነገደ አለቆች ሰዎቿቸው 87,000 ተዋጊ ወታደሮች መጥተዋል (ቁጥር 4-5) ፤ ይህ ቁጥር ከዳዊት የጦር ቆጠራ የመጣ ነበር ፡፡ እነዚህ ልጆች የዳዊት ዘር አካል ባይሆኑም ህዝቡን ለመከላከል በንቃት በዉጊያ ላይ ተሳትፈዉ ነበር ፡፡ ከግዞት ከተመለሱ በኋላ ጦርነትን እና ማስፈራራትን ለመጋፈጥ በመቀጠል ለህዝቡ ወደፊት አስፈላጊ ነበሩ (ዕዝ 4፡ 1-6፣ 5፡ 3፣ ነህ 2፡ 7፣ 9-10፣ 19) ፡፡ ነፃ የወጡ ቢሆኑም እንኳን የሚመጣዉ ጦርነት እዉነት ነዉ የሚሆነው ፤ ህዝቡም ተዋጊ ጦራቸዉን እንደ ገና መገንባት አስፈልጓቸዋል ፡፡ በመንፈሳዊ ግዛት ነፃ መሆናችንን ማወቅ አስፈላጊ ነዉ ያማለት ግን ዉጊያችን አልቋል ወይም ጠላቶቻችን ተመልሰዉ አይመጡም ማለት አይደለም ፡፡
1-ዜና መዋዕል (7፡ 6-12)፡ የብንያም ልጆች ፡፡ በመጀመሪያዎቹ አምስት ቁጥሮች ላይ የምንመለከታቸዉ ሂደቶች ለብንያም ነገዶች በመቀጠል እንደ ገና ነገዱ ወልደዋቸው የነበሩት ተዋጊ ሰዎች ቁጥር ላይ ያተኩራል ፡፡
1-ዜና መዋዕል (7፡ 13)፡ የንፍታሌም ልጆች ፡፡ የንፍታሌም ልጆች ተዘርዝረዋል ነገር ግን በፊት ስለ ተዋጊ ሰዎቻቸዉ የተዘረዘረ ዝርዝር አልነበረም ፤ ተካተዋል ምክንያቱም ለህዝቡ አንድነት አስፈላጊ ስለ ነበሩ ፡፡
1-ዜና መዋዕል (7፡ 14-19)፡ የምናሴ ልጆች ፡፡ የምናሴ ዝርዝር ወንዶችን እና ሴቶችን አካትቷል ፡፡ በዚህ ክፍል ላይ በሴቶች ላይ በሚያስደንቅ እናተኩራለን በተለይም በምናሴ ሴት ልጅ ሰለጰዓድ ላይ ፤ ዘኁ (27፡ 1-11) ስለ እነዚህ አምስት ሴቶች ዝርዝር መግለጫ ይሰጣል ፡፡
1-ዜና መዋዕል (7፡ 20-29)፡ የኤፍሬም ልጆች ፡፡ እነዚህ ዝርዝሮች ሲቀጥሉ ፀሀፊዉ ደግሞ ደግሞ አንድ ንግግር ያደርጋል - መሲሁ በዳዊት በኩል ከይሁዳ ነገድ ቢመጣም ሁሉም የይሁዳ እና የእስራኤል ነገድ በወደፊቱ ሀገር አስፈላጊ ነበሩ ፡፡ ሴቶች በኤፍሬም ዘር ዉስጥ በማካተት በወደፊቱ አገር ሴት እና ወንድ ሁለቱም አስፈላጊ እንደ ነበሩ ያመለክታል (ቁጥር 24) ፤ ዘሩ ህዝቡን ወደ ተስፋይቱ ምድር የመራው የነኔዉን ኢያሱን ያካትታል (ቁጥር 27) ፡፡
1-ዜና መዋዕል (7፡ 30-40)፡ የአሴር ልጆች ፡፡ የአሴር የዘር ግንድ “ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፣ የተመረጡ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች እና የመኳንንቶች አለቆች “ ያካትታል (ቁጥር 40) ፡፡ በጦርነት አገልግለዉ የነበሩት ቁጥራቸው 26,000 ነበር ፡፡
መደምደሚያ
በዚህ ማስረጃ ምን ማድረግ እንዳለብን እግዚአብሄርን ጠይቄዋለሁ ፤ አንድ ደረጃ ላይ ምዕራፍ 7 ለመናገር የሚያስቸግሩትን ረጅም የስም ዝርዝሮችን ያቀርባል ፡፡ በሌላ ደረጃ ላይ ምዕራፍ 7 ጦርነቱ በአንድ ላይ መዋጋት እንደ ሚሆን ማስታወሻ ነው ፡፡ በአሁኑ ጊዜ እየሆነ ባለዉ ነገር እፈራለሁ ጦርነቱን በራሳችሁ ለመዋጋት እየሞከራችሁ ነው - ለብቻችን ያለ አጋዥ ፤ በአሜሪካ ቤተ ክርስቲያን የጋራ ግንባር ያልሆነዉን ወደ ጦርነት ለመሄድ ፍቃደኞች የምንሆንበትን የራሳችንን ጎራዎች ለመምረጥ አዘንብለናል ፡፡ ከራሳችን ሀሳብ በላይ እና ጦርነት በላይ በመሆን ጦርነት በመንፈሳዊ ደረጃ እንደ ሆነ መረዳት አለብን ፡፡ የሰይጣን መርሆች እኛን ማሸነፍ መመከር ናቸው በእርሱ ላይ ድል አድራጊዎች የምንሆንበት ብቸኛዉ መንገድ በአንድ ላይ በመምጣት በጋራ ጠላታችን ላይ አንድ መሆን ነው ፡፡ ሮሜ (8፡ 38-39) የሚለው “ ሞት ቢሆን ሕይወትም ቢሆን መላዕክትም ቢሆን ግዛትም ቢሆን ያለዉም ቢሆን የሚመጣዉም ቢሆን ኃይላትም ቢሆኑ ፤ ከፍታም ቢሆን ዝቅታም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሄር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ “ ፡፡
ጥያቄዎች
-
በ 1ዜና መዋዕል 7 ፀሀፊዉ በዘር ግንድ መዝገቡ ላይ የተዋጊ ወንዶችን ቁጥር መዝግቧል ፤ በቀደሙት ምዕራፎች ሳይካተት ይህ በምዕራፍ 7 በዝርዝር ያካተተበት ምክንያቱ ምን ሊሆን ይችላል ?
-
በ 1ዜና መዋዕል 7 ስለ ምን ያክል ነገዶች ተፅፏል ? እነዚህ አጭር መግለጫዎች ለምን እንደሆኑ ነገር ግን ሌሎቹ ደግሞ በደንብ ዝርዝር መሆናቸዉን ምን ታስባላችሁ ?
-
በ 1ዜና መዋዕል 7 በትምህርት ወይም በትናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Chronicles 7:2b
“During David’s reign, 22,600 descendants of Tola were recorded as warriors in their genealogies.”
የታሪክ ጸሀፊያኑ የዘር ሀረግ በልዩነት መዘርዘራቸውን ሲቀጥሉ ለይሳኮር ፣ ለብንያምና ለአሴር ጽኑዓን ኃያላን ሰዎችም ትኩረትን ሰጥተዋል ፡፡ ነገዶቹ ለጦርነት በርካታ ተዋጊዎችን አሰልጥነዋል ፡፡
እግዚአብሔር የጠራህ በየቀኑ በሚገጥምህ ፈተና ውስጥ እንደ ክርስቶስ ተከታይ እንደ ተዋጊ እንድትኖር ነው ፡፡ ጦረኛ ማለት “ በጦርነት የሚሰታፍ ፣ ወታደር ፣ ኃይለኛ ፣ ጅግና ወይም ጠባ አጫሪ ፣ ደፋር የሆነ ፡፡ “ በየቀኑ ከእንቅልፍህ ስትነቃ እንድህ በል “ እኔ የእግዚአብሔር ተዋጊ ነኝ ! ለውጊያ ዝግጁ ነኝ ፡፡ “ በአንተ ውስጥ ያለው በአለም ካለው እንደሚበልጥ አስታውስ ፡፡ የእግዚአብሔርን ጦር ፣ የእግዚአብሔርን ኃይል ፣ የእግዚአብሔርን ጸጋ ስለታጠቅ ቀኖችህ ይዘው ስለሚመጡት ነገር አትፍራ ፡፡ እግዚአብሔር ብርታትን ያስታጥቅሃል ጣላቶችህንም ከአንተ በታች ያስገዛቸዋል ፡፡ አንተ ኃያል ተዋጊ አስተውል ! በአንተ ላይ የተሰራ መሳሪያ አይከናወንም ፡፡ ዛሬ በዚህ እውነት ውስጥ ተመላለስ ፡፡ በክርስቶስም ስም ድልን ትቀዳጃለህ ፡፡
“በትውልዳቸው ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ፤ በዳዊት ዘመን ቍጥራቸው ሀያ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ነበረ። “
- 1ኛ ዜና 7፡2
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 18:39 — “ለሰልፍም ኃይልን ታስታጥቀኛለህ፤ በበላዬ የቆሙትን ሁሉ በበታቼ ታስገዛቸዋለህ። “
ኢሳይያስ 54:17 — “በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም፤ በፍርድም በሚነሣብሽ ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፥ ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ “
1ኛ ዮሐንስ 4:4 — “ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።