The Descendants of Levi
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of David 1 Chronicles 6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በ 1ዜና መዋዕል የእስራኤልን ነገዶች የዘር ግንድ አጥንተናል ፤ ምዕራፍ 6 በሌዊ ነገድ ላይ ያተኩራል - ወደ ህያዉ አምላክ ወደ ክርስቶስ የሚያመለክተዉ ነገድ ፡፡ ስለ ሌዋዊያን አገልግሎት ሁሉም ነገር ወደ ህያዉ አምላክ ያመለክታሉ ፡፡
ትምህርት
1-ዜና መዋዕል (6፡ 1)፡ ሌዊ ሰዎስት ልጆች ነበሩት፡ ጌድሶን፣ ቀዓት እና ሜራሪ ፡፡ ይህ ነገድ ሰፊ መጠን ያላቸዉ ሰዎች ልክ እንደ ሙሴና ሳሙኤል ነበሩት ፤ በተጨማሪም ታላቅ ያልሆኑ ሰዎች ልክ እንደ አሮን ልጆች፣ ልክ እንደ ኤሊ ልጆች እና እንደ ሳሙኤል ልጆች አይነትም ነበሩ ፡፡ የሌዊ ሰዎስቱ ልጆች የሰዎስቱ ጎሳ አለቃ ሆኑ ፡፡ አሮን ከቀዓት ወገን ነበር የመጀመሪያዉም ታላቅ ካህን ሆነ ፡፡ ሁሉም ሰዎስቱም ወገኖች ጠቅላላ የቤተ መቅደስ ተግባራት ነበራቸው ፤ ከእነዚህ ከሰዎስቱ ወገኖች ሙዚቀኞች መጥተዋል ፡፡ በድንኳኑ ማደሪያ አገልግሎት እና ለሌዋዊያን በተመደበዉ ተግባራት ምክንያት ይህን ነገድ መረዳት አስፈላጊ ነው ፡፡
1-ዜና መዋዕል (6፡ 2-15)፡ በዚህ ፅሁፍ የቀዓት ልጆች የካህናትን ዘር መስመር ሰጥቷል ፡፡ ከቀዓት መጀመሪያ የድንኳኑ ማደሪያ በቆመ ጊዜ ልጁ አሮን ታላቅ ካህን ተደርጎ የተሸመዉ እንበረም መጣ ፡፡ የመጀመሪያዉ ቤተ መቅደስ በቆመ ጊዜ ሳዶቅ ካህን ነበር ፡፡ ቤተ መቅደሱም ሲጠፋ ያዬ ካህንም አለን -ኢዮሴዴቅ ፡፡ የእንበረም ልጆች ሙሴ፣ አሮን እና ማሪያም ነበሩ ፤ የአሮን ልጆች ብቻ እንደ ካህናት እንዲያገለግሉ ተፈቀደላቸው ፡፡ አሮን የናዳብ፣ የአብዮድ፣ የአልዓዛር እና የኢታምር አባት ነበር ፡፡ ናዳብና አብዮድ ለእግዚአብሄር እንግዳ እሳት ባቀረቡ ጊዜ ያለምንም ልጆች ሞቱ ፡፡ የአልዓዛር ልጆች ታላቅ ካህናት ሆኑ ነገር ግን ተግባሮቹ በሆነ ጊዜ ላይ በጊዜዉ ወደ ኢታምር ልጆች ተላለፈ ፡፡ በሚታወቅ ሁኔታ በአጠቃላይ ሳሙኤልን ያሳደገዉ እና ያሰለጠነው ታላቁ ካህን ኤሊ በዚህ የዘር ግንድ አልተጠቀሰም ፤ ከአገልግሎቱ በኋላ የታላቅ ካህን መስመር ወደ ኢታምር ልጆች አለፈ በዚህም ምክንያት በንጉስ ዳዊት ዘመን ጊዜ ሳዶቅ እና ኢያታር በጋር እንደ ታላቅ ካህን አገለገሉ ፡፡ ሳዶቅ ለዳዊት እና ለሰለሞን ታማኝ ሆኖ እንዳለ አቢያተር በዋጋው ለንግስና ከአዶኒያስ በኩል ወገነ ፤ በምላሹም ሰለሞን እንደ ታላቅ ካህን ከስልጣኑ አወረደው ሳዶቅንም ብቻዉን እንደ ታላቅ በመተው የካህናትን ቤተሰብነት በአልዓዛር ዘር እንደ ገና አቋቋመ ፡፡ የክህነት አገልግሎት በፍፁም ከአሮን ቤት አልጠፋም ፡፡
በቁጥር 10 ፀሀፊዉ አዛርያስ የሰለሞን ቤተ መቅደስ ታላቅ ካህን እንደ ነበር ገልፃል ፡፡ በ 2ዜና መዋዕል (26፡ 16-21) አዛርያስ ንጉሱ የክህነትን ተግባር ለማድረግ እና እጣኑን ለማጠን በቤተ መቅደሱ ባሰበ ጊዜ ንጉስ ኦዝያን የከለከለዉ ክህን ነበር ፡፡ ንጉስ ዖዝያንም በለምፅ ተመታ በፍፁምም ወደ ቤተ መቅደሱ አልገባም ፤ ፀሀፊዉም አዛርያስን ቤተ መቅደሱን እና የክህነት አገልግሎቱን ንፅህና ስለ ተከላከለ አከበረው ፡፡
በቁጥር 13 የተለየው ሌለኛዉ ካህን ኬልቅያስ ነው ፤ የህጉን መፅሀፍ አግኝቶ ለንጉስ ኢዮስያስ የሰጠዉ ታላቅ ካህንም ነው ፡፡ ንጉስ ኢዮስያስ በህጉ ላይ እየተገበረ ሳለ ኬልቅያስ ያገኘዉ ካህን ነበር ፡፡ ቁጥር 14 በነገስታቶች መጨረሻዉ በንጉስ ሴዴቅያስ ዘመን ጊዜ ታላቅ ካህን እንደ ነበር ሰራያምን ይጠቅሳል ፤ እንደ እስራኛ ወደ ባቢሎን በመላክ በንጉስ ናቡከደነፆር ተገደለ ፤ ልጁም ኢዮሴዴቅ ባቢሎን ይሁዳን እና ኢየሩሳሌምን በያዘች ጊዜ በምርኮ ተወሰደ ፡፡ ይህ የክህነት አገልግሎት ዘር (መስመር) የጊዜአዊነት ማብቂያ ነበር ፡፡ የእስራኤል ድርጎቶች ዉጤት ነበራቸው ፀሀፊዉም እንኳን እግዚአብሄር ወደ ግዞት አስገብቷቸዉ እንደ ነበር አብራርቷል ፡፡
በአሁኑም ጊዜም እንኳን ይህ የዘር ግንድ መሰረታዊ ነገር ያስፈልጋል ፤ ሳይንቲስቶች ወደ አሮን የሚመልስ ናሙና የዘረ መልን አግኝተዋል ስለሆነም አሁንም ከክሀነት መስመር የሆኑትን ሰዎች መለየት ይችላሉ ፡፡ የዘር ግንድ ያስፈልጋል ምክንያቱም ወደ እግዚአብሄር ቅዱስነት፣ ወደ እግዚአብሄር ፅናት እና ወደ እግዚአብሄር ተስፋ ያመለክታል ፡፡
1-ዜና መዋዕል (6፡ 17-28)፡ እነዚህ ጥቅሶች ብዙ የተደበቁ ስሞችን ዘርዝሯል ነገር ግን የሕልቃና ስም ብዙ ጊዜ ተከስቷል ፤ በቁጥር 27 ይህ ሕልቃና የነቢዩ የሳሙኤል አባት ነበር ፡፡ ሳሙኤል እንደ ልጁ ባይጠቀሰም ቁጥር 28 የሳሙኤልን ልጆች ኢዩኤል እና አብያን ዘርዝሯቸዋል ፤ በ 1ሳሙኤል 8 መሰረት የሳሙኤል ልጆች ለእግዚአብሄር የታመኑ አልነበሩም ፤ የተበላሹ እና ጉቦ የተቀበሉ ነበሩ ፤ ለእስራኤልም ሰዎች ምድራዊ ንጉስ ለመፈለግ እንደ ምክንያት የሚጠቀሙዓቸዉ ሆኑ ፤ እነዚህ ሰዎች ያልታመኑ ቢሆኑም ቆይቶ የኢዩኤል ልጆች አስፈላጊ ተግባር ይጫወታሉ ፡፡
1-ዜና መዋዕል (6፡ 31-43)፡ ይህ ፅሁፍ ዳዊት በእግዚአብሄር ቤተ መቅደሱ ላይ በዜማ ተግባራት ያስቀመጣቸዉን ሰዎች ይዘረዝራል ፤ በዜና መዋዕል የተመዘገበዉ አንዱ የተነዬ ዋና ነገር ይህ ነው ፡፡ ዳዊት ወደ እግዚአብሄር ቅዱስነት ለማመልከት እንደ አስፈላጊ አካል ሙዚቀኞችን(ዘማሪዎችን) አካተተ ፤ ዘማሪዉ ኤማን አንዱ አለቃ ሙዘቀኛ(ቁጥር 33) የሳሙኤል የልጅ ልጅ የኢዩኤል ልጅ ነበር ፡፡ መዝሙር 88 ለእርሱ መለያ ነበር ፤ ቁጥር 39 የኤማንን ዘመድ (አንዳንድ ትርጉሞች ወንድሙ ነዉ ይላሉ) “ እንደ ቀኝ እጁ “ አሳፍን ጠቅሷል ፡፡ አሳፍ መዝሙር 50 እና 73-83 ፅፏል ፤ አሳፍ ዳዊት የኪዳኑን ታቦት ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ማደሪያዉ ድንኳን ለማምጣት እስራኤልን በመራ ጊዜ አለቃ አስመላኪ ነበር (1ዜና 16፡ 1-6) ፡፡
1-ዜና መዋዕል 6፡ 44-47)፡ እነዚህ ጥቅሶች በቀዓት ልጆች አጠገብ እንደ ሙዚቀኛ ያገለገሉትን የሜራሪን ልጆች ይዘረዝራሉ ፡፡ ኤታን (ቁጥር 44) እንዲሁም ኤዶታም ተብሎ ይታወቅ ነበር ፤ ከመዝሙሮች አንድም ባይፅፍም ሰዎስቱን መዝሙራት (39, 62,77) ለመዘምራን አለቃ ለኤዶታም የተፃፉ ነበሩ ፡፡ ሁለቱ በዳዊት አንዱ ደግሞ በአሳፍ የተፃፉ ነበሩ ፡፡ ይህ የአለቃ መዘምራን አደረጃጀት ስርዓት ከሌዊ ነገዶች ከእያንዳንዳቸዉ አንድ እስከ ኢዮስያስ ዘመን ድረስ አልተሰበረም (2ዜና መዋዕል 35፡ 15) ፡፡
1-ዜና መዋዕል (6፡ 48-53)፡ የአሮን ዘመዶች ሌዋዊያን ለድንኳኑ ማደሪያ አገልግሎት የተሸሙ ነበር ፤ ስራቸዉ የካህናቱን ስራ ይደግፋል ጥረታቸዉ ደግሞ ወደ እግዚአብሄር ቅዱስነት እና ወደ ዳዊት ልጅ ኢየሱስ አመልክቷል ፡፡
1-ዜና መዋዕል (6፡ 54-81)፡ ኃላፊነታቸዉን ለመፈፀም ሌዋዊያን ህዝቡን ለማገልገል እና ወደ እግዚአብሄር ቅዱስነት ለማመልከት በምድሪቱ ሁሏ ተበተኑ ፤ ይህ ወደ ኋላ የስምዖን እና የሌዊ ነገዶች በሴኬም ያሉትን ወንዶች ስለ ጨፈጨፉ ተረግመዋል ወደ ሚለዉ ወደ ዘፍጥረት 34 ይመልሳል ፡፡ ባላመታመናቸዉ ምክንያት የስምዖን ነገድ በሚገባ ወደ ይሁዳ ነገድ ተስበዉ በመግባት ተዋጡ ፤ ሌዋዊያን በወርቅ ጥጃ አመፅ ጊዜ በመታመናቸዉ ምክንያት በሁሉም በእስራኤል ህዝብ ዉስጥ እንደ በረከት ተበተኑ ፡፡ ስምዖን እንደ እርግማን ተበተነ ፤ ሌዊ ደግሞ እንደ በረከት ተበትኖ ነበር ፡፡
ሌዋዊያን በተለያዩ ስፍራዎች ተመድበዉ ነበር ፤ ቀዓትያዊያን በደቡብ በኩል የይሁዳን፣ የቢኒያምን እና የኤፍሬም ነገዶች የሚሸፍኑትን ከተሞችን ተቀበሉ ፡፡ ጌድሶዋዊያን በሰሜን የይሳኮር፣ የአሴር፣ የንፍታሌም እና የምናሴ ነገዶችን በመሸፈን ነበሩ (ቁጥር 62) ፡፡ ሜራሪያዊያን በዮርዳኖስ ወንዝ በምስራቅ በኩል የሮቤልን፣ የጋድን እና የዛብሎንን ነገድ በመሸፈን ነበሩ (ቁጥር 63) ፡፡ በድንኳኑ ማደሪያ በኢየሩሳሌም አልነበሩም አገልግሎታቸዉ እና ተልዕኳቸዉም ተመሳሳይ ነበር - እርግጠኛ ለመሆን በእነዚያ አካባቢዎች የእግዚአብሄር ህግ የነበረ ይከበር ነበር ፡፡ 2ዜና መዋዕል 17 ከሌዋዊያን አንዳንዶች የተለዬ የማስተማር አገልግሎት እንደ ነበራቸዉ ይገልፃል - በመሰረቱ ተመሳሳይ ሰዎችን አስተምረዋል ፡፡
መደምደሚያ
ይህ የሌዊ ነገድ ነበር በመላዉ ምድሪቷ ተቀምጠዉባቸዉ የነበሩሰ በጣም ብዙ ስሞች እና ስፍራዎች አሉ ፡፡ አስታዉሉ ይህ ከተመረጡት ህዝቦች መካከል የተቀደሰዉ ነገድ ነበር ፡፡ የአሮን ቤተሰብ የክህነት አገልጋይነትን መሰረተ ፤ ጠቅላላ ነገዱ ወደ መሲሁ አመልክተዋል ፡፡ ለአምልኮ እና ለመስዋዕት ከመጀመሪያዉ እስከ መጨረሻ ስጦታ ተደርጎ ነበር ፡፡ ለእግዚአብሄር መሰጠትን ሞደል ሆነዉናል ፤ አንዳንዶች በጥሩ አድርገዉታል ሌሎች ደግሞ አላደረጉትም ፤ ነገር ግን በዚህ ጠቅላላ ቤተስብ ላይ ስንመለከት የዕዝራ የልብ ምቱ በሚያስፈልጉበት ስፍራ እንደ ገና ማቋቋም ነበር ምክንያቱም የእግዚአብሄር አምልኮ እግዚአብሄር ወደ ሆነዉ ሁሉም ስለሚያመለክት በሚያስደንቅ ሁኔታ አስፈላጊ ስለ ነበር ፡፡ አስታዉሉ የቤተ መቅደሱን ተግባር የሚሰሩ ካህናቶች፣ ሙዚቀኞች እና በምድሪቱ ዉስጥ የሚያስተምሩ ነበሩዓቸው ፡፡ ለእኛ ምሳሌ ሞደል የሆኑበት በጥሪያቸዉ ዉስጥ መለያየት ነበር ፤ ሌዋዊያን የእግዚአብሄርን ክብር ለማመልከት በንጉሱ አጠገብ መጡ ፡፡ ስተነዉ ከሆነ ለእኛ የሆነ ነገር ስተናል ፤ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እጆች፣ እግሮች እና አፎች ነን ፤ ሌዋዊያን አንሆን ይሆናል ነገር ግን ተቀበለዉ በነበረዉ ተመሳሳይ ጥሪ ተጠርተናል - ለኃያሉ ንጉስ ክብር ለመስጠት - ለዳዊት ልጅ ለኢየሱስ ምስጋና ለመስጠት ፡፡
Ralph F. Wilson, “The Genealogy of the Priesthood in David’s Time,” available from http://www.jesuswalk.com/david/genealogy_of_the_priesthood_in_davids_time.htm.
Adam Eliyahu Berkowitz, “DNA Studies Trace Jewish Priestly Lineage from Biblical Times,” available from https://www.breakingisraelnews.com/49932/dna-studies-prove-existence-of-bib-lical-priestly-class-health-and-science/.
ጥያቄዎች
-
ሌዋዊያን የተለየ ተግባር ምን ተሰጥቷቸዉ ነበር ? ሁሉም ሌዋዊያን ካህናት ነበሩ ?
-
የሌዊ እና የስምዖን ነገድ ሁለቱም የተበተኑ እንዲሆኑ ተረግመዉ የነበረዉ ለምን ነበር (ዘፍ 34፡ 24-30, 49፡ 5-7) ? የሌዊ ነገድ ለእስራኤል እንደ በረከት ተበትኖ የነበረዉ ለምን ነበር ? (ዘጸ 32፡ 26-29)
-
እግዚአብሄርን በሙዚቃ ማምለክ አስፈላጊ ሆኖ የታየው እንዴት ነበር ? (2ሳሙ 6፡ 5, 1ዜና መዋዕል 15፡ 16-17, 2ዜና መዋዕል 5፡ 11-14, 7፡ 6)
-
በመዝሙር 88የሚታየዉ ሄማን ምን አይነት ሰዉ ነበር ?
-
በ 1ዜና መዋዕል (6፡ 48) ሁሉም አገልግሎት ለእግዚአብሄር አስፈላጊ እንደሆነ እንዴት ማወቅ እንችላለን ? ከሌሎች የተሸለ በማድረግ ወደ እግዚአብሄር ወደ ሆነ አገልግሎት ታዘነብላላችሁ ?
-
በ 1ዜና መዋዕል 6 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Chronicles 6:48–49a, 54
“Their relatives, the Levites, were assigned to all the service of the tabernacle, God’s temple. But Aaron and his sons did all the work of the most holy place. These were the places assigned to Aaron’s sons from the Kohathite family for their settlements in their territory, because the first lot was for them.”
ታሪክ ጸሀፊው የእስራኤላውያንን የኋላ ታሪክ ማስታወሱን ሲቀጥል የተለያዩ የሌዋውያን ሚናዎች እና የአሮን ዘሮች ተዳስሰዋል ፡፡ አንዳንዶቹ የእግዚአብሔር ቤት ማደሪያ አገልግሎት ሰጭዎች ፣ ሌሎቹ ካህናት ፣ ሌሎቹም መዘምራን ነበሩ እያንዳንዳቸውም የራሳቸው ስራ አላቸው ፡፡ ጸሀፊው ለእስራኤላውያን ሌዋውያኑ ስለሚሰፍሩባቸው የተለያዩ ቦታወች እንድሁም እነርሱን በተለያዩ ግዛቶች ስለ መሾም እንደገና መመሪያን ሰጠ ፡፡
የእግዚአብሔር ልብ ወደ ሚመጣው መሲህ እንደሚያመለክት ማስታወስ አስፈላጊ ነው ፡፡ ዛሬ እያንዳንዱ የክርስቶስ ተወካይ በተለያዩ ግዛቶች ውስጥ የተለየ ሚና አለው ፡፡ እግዚአብሔር ግዛት ፣ ቤት ፣ የስራ ቦታ ፣ ማህበረሰብ ፣ ድርጅት ሰጥቶሃል ፡፡ በግዛትህ ውስጥ የክርስቶስን ብርሃንና ፍቅር በዙሪያህ ላሉት እንድታንጸባርቅ ፡፡ በተጨማሪም እርሱ ለተለየ ስራ ጠርቶሃል ፡፡ ስለዚህ ተቀኝ መዝሙርም ዘምር ፣ መጸዳጃ ቤቱን አጽዳ ፣ ቃሉን አስተምር ፣ ምግብ አበስል ፣ የንግድ አቅድ ጻፍ ፣ ልጆችህን እስከመጨረሻው የሚሄዱበትን መንገድ አሰልጥናቸው ፣ ሌሎች አንዱንና እወነተኛን የእግዚአብሔርን ልጅ ኢየሱስን እንድያመልኩ ምራ ፡፡
ኢየሱስ እንድህ ይላል “ እኔን በቻ አምልክ “ ፡፡ የምታደርገውን ሁሉ በምታደርግበት ቦታ ለእግዚአብሔር ክብር አድርገው ፡፡
“ ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን ለእግዚአብሔር ቤት ማደሪያ አገልግሎት ሁሉ ተሰጡ ። አሮንና ልጆቹ ግን የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ እንዳዘዘው ሁሉ ለቅድስተ ቅዱሳን ሥራ ፡፡ ማደሪያዎቻቸውም በየሰፈራቸው በየዳርቻቸው እነዚህ ናቸው፤ ለአሮን ልጆች ለቀዓት ወገኖች አንደኛው ዕጣ ነበረ። “
—1ኛ ዜና 6:48–49, 54
ተጨማሪ ጥቅስ
- መዝሙር 100:2–3 — “በደስታም ለእግዚአብሔር ተገዙ፥ በሐሤትም ወደ ፊቱ ግቡ። እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ እወቁ፤ እርሱ ሠራን እኛም አይደለንም፤ እኛስ ሕዝቡ የማሰማርያውም በጎች ነን። “
- ሮሜ 12:4 — “በአንድ አካል ብዙ ብልቶች እንዳሉን፥ የብልቶቹም ሁሉ ሥራ አንድ እንዳይደለ፥ ”
- ኤፌሶን2:10 — “እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።