Historical Books 1 Chronicles

The Descendants of Rueben, Gad and Manasseh

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of David 1 Chronicles 5 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 286 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ይህ ምዕራፍ በብዙ መንገድ የሚያስደንቅ ነው ፡፡ እስራኤል የተባለዉን የያዕቆብን 12 ልጆች እንወያያለን ፤ በሮቤል ዘር እንጀምራለን ፡፡ ነገር ግን መጀመሪያ በትልቁ ስዕል ላይ ስንመለከት - እቅዱን - ከአዳም ወደ ኖህ ወደ አብርሃም ወደ ያዕቆብ ከዚያም ወደ አስራ ሁለቱ ልጆች ሁሉም መንገዶች ወደ እስራኤል እና ይሁዳ ነገስታቶች ያመጣሉ ፡፡ ዘሩ በእስራኤል ታሪክ ዉስጥ ሙሉ የእግዚአብሄርን እቅድ ታሪክ ይናገራል ፤ ሁሉም ነገር ወደ ዳዊት ልጅ ወደ ኢየሱስ ያመለክታል ፡፡ ይህ ምዕራፍ የሮቤልን፣ የጋድንእና የምናሴን ግማሽ ጎሳ ታሪክ ይናገራል ፡፡

ትምህርት

1-ዜና መዋዕል (5፡ 1)፡ ሮቤል ለልያ የተወለደ የያዕቆብ የበኩር ልጅ ነበር ነገር ግን የአባቱን አልጋ ስላረከሰ የብኩርና መብቱ ለዮሴፍ ልጆች ተሰጠ ፡፡ ዘዳ (21፡ 15-17) እናቱ በያዕቆብ የተወደደች ባትሆንም እንኳን ሮቤል የበኩር ልጅ እንደ ነበር ይገልፃል ፤ እንደ በኩር የበኩርነቱን ይቀበላል - እጥፍ ድርሻዉን ፤ ያዕቆብ 12 ልጅች ስለነበሩት ሀብቱን ወደ 13ድርሻ ይከፋፍላል እንደ ልምድቻዉም ከእነዚህ ድርሻዎች ዉስጥ 2 ድርሻ የበኩር ልጅ ይቀበላል ሌሎቹ ልጆች ደግሞ እያንዳንዳቸዉ አንድ ድርሻ ይቀበላሉ ፡፡ ይሁን እንጂ ሮቤል የብኩርናዉን መብት አጣዉ ያልተወደደችዉ ሚስት ስለ ሆነ ሳይሆን የአባቱን አልጋ በማርከሱ ፡፡ ዘፍ (35፡ 19-22) የራሄልን መቃብር ይገልጻል ፤ ራሄል ቢኒያምን የያዕቆብን አስራ ሁለተኛ እና የመጨረሻ ልጁን ስትወልድ ሞተች ፡፡ የያዕቆብ ቤተሰብ በጋዴር እያሉ ሮቤል ከያዕቆብ ቁባት ከባላን ጋር ተኛ ያዕቆብ (እስራኤልም) ሰማ ፡፡ ባላ በሰዓቱ የያዕቆብ የሆነች የራሄል አገልጋይ ነበረች ፤ ስለሆነም ከ12 እስራኤል ልጆች እናት ከአንዷ ጋር ሮቤል ተኛ ፤ ይህ ድርጊት የእግዚአብሄርን ህግ ጣሰ ፤ ሮቤልም ከባላን ጋር በመተኛት የእግዚአብሄርን እቅድ አረከሰ የበኩርነት መብቱንም አጣ ፡፡

1-ዜና መዋዕል (5፡ 2-6)፡ እነዚህ ጥቅሶች የሮቤል የዘር ግንድ ድርሻን ዘርዝረዋል ነገር ግን በኢዩኤል እና በሮቤል መካከል ያለዉን ግንኙነት አይሰጡም ፡፡ ትንሽ ጥናቶች “ ኢዩኤል “ በዜና መዋዕል አራት ወይም አምስት ጊዜ እንደተጠቀሰ ያሳያል ፤ ስለዚህ ይህነ ቀጥታ እንዴት እንጠብቀዋለን ? የኢዩኤል ግንኙነት ከሮቤል ጋር አልተጠቀሰም፡፡ ምክረ ሀሳቦች ኢዩኤል የከርሚ ልጅ እንደ ነበር ወይም ሄሆኅ መጀመሪያ ስለተጠቀሰ የሄኖኅ ልጅ እንደ ነበር ያካትታሉ፡፡ መፅሀፍ የኢዩኤልን ግንኙነት ከሮቤል ጋር ስለ ማይሰጥ የምንደርስበት ማንኛዉም ድምዳሜ ግምት ይሆንብናል ፡፡ ልናዉቀዉ የምንችለዉ ብቸኛዉ ነገር ወደ ታች በትውልዱ ነው ፤ ብኤራ በአሶር ንጉስ በቴልጌልቴፍፌልሶር ምርኮ ተወስዶ የነበረዉ የኢዩኤል ዘር ነበር ፡፡

1-ዜና መዋዕል (5፡ 7-10)፡ የሮቤል ልጆች(ዘሮች) (ሄኖኅ፣ ፈሉሶ፣ አስሮን እና የኢዩኤል ልጆች) በአሮዔር እና እስከ ኤትራጠስ ምስራቅ ምድረበዳ ድረስ ተቀመጡ ፡፡ በሳዖል ዘመን ጊዜ ከአጋራዊያን ጋር በመዋጋት በገልዓድ ክልል ሁሉ ተቀመጡ ፡፡ ሮቤል፣ ገልዓድ እና የምናሴ ግማሹ ነገድ ሌላዉ የእስራኤል ነገዶች ወደ ከነዓን ዮርዳኖስን ሲሻገሩ እነርሱ በገልዓድ ተቀመጡ ፡፡ እነዚህ ሁለቱ እና ግማሹ ነገዶች ከምስራቅ እና ከሰሜን ብዙ ጠላት በገጠማቸዉ በሰፊዉ ግዛት ኖሩ ፡፡

1-ዜና መዋዕል (5፡ 11-17)፡ የእስራኤል ሌሎቹ ልጆች የጋድ ልጆች በዘመኑ ጊዜ ሶሪያ እና ጎላን ከፍታ ላይ በባሳን ኖሩ ፡፡ የጋድ ትዉልድ በኢዩኤል (ቀድሞ በተጠቀሰዉ በሮቤል ኢዩኤል ሳይሆን በጋድ ዘር) እንደ አለቃ የተዘረዘረ ነበር ፤ በዚህ የዘር ግንድ ብዙ ሰዎች በመፅሀፍ ከዚህ ዉጪ የትም አልተዘረዘሩም ፡፡ በጊዜዉ እሆነ ስፍራ ላይ የይሁዳ ንጉስ በኢዩአታም እነዚህን የእስራኤልን ዘር ስሞች የዘር ግንድ አቆያቸው ፤ የእስራኤል ንጉስ ኢዮርብዓም የሁሉንም የእስራኤል ነገድ ዘር የዘር ግንድ ተቆጠሩ ፡፡

1-ዜና መዋዕል (5፡ 18-22)፡ የሮቤል፣ የጋድ እና የምናሴ ግማሹ ነገድ ሰዎች 44,760 ነበሩ ፤ እነዚህ ሰዎች በእስራኤል ጠላቶች ላይ የዘመቱ እና ለጦርነት የሰለጠኑ ነበሩ ፡፡ አጋራዊያን የአጋር(የአብርሃም ሚስት የሳራ ሰራተኛ) ዘር ነበሩ ፤ ኢጡር፣ ናፌስና ናዳብ የእስማኤል ልጆች ነበሩ ፤ ይህ በእስራኤላዊያን እና በእስማኤላዊያን መካከል ግጭቱን ይገልፃል ፡፡ በጦርነት እስራኤላዊያን ወደ እግዚአብሄር ጮኹ አጋራዊያንንም በማሸነፍ ከብቶቻቸዉን ወሰዱ(መረኩ) ፤ ምክንያቱም የእግዚአብሄር ጦርነት ስለ ነበር አጋራዊያን ተሸነፉ የሮቤል እና የጋድ ነገዶችም እስከ ግዞት ድረስ በዚህ ምድር ኖሩ ፡፡

1-ዜና መዋዕል (5፡ 23-26)፡ የምናሴ የግማሹ ነገድ ዘር ከዮርዳኖስ ምስራቅ ከባሳን ጀምሮ እስከ አርሞንዔም ተራራ ተቀመጡ ፡፡ በተዋጊነታቸዉ የሚታወቁና በዘመናቸዉ ታዋቂዎች ቢሆኑም ስለ እነርሱ ሌላ ምንም አናዉቅም ምክንያቱም በእግዚአብሄር ላይ በማመፅ የሌሎች አማልዕክቶችን ስለ ተከተሉ ፡፡ በዚህም ምክንያት እግዚአብሄር ወደ ምርኮ ወደ ወሰዳቸው ወደ አሶር ንጉስ ቴልጌልቴልፌልሶርን እጅ አሳልፎ ሰጣቸው ፡፡ 2ነገስት (15-16) በእስራኤል ላይ ስለ ቴልጌልቴልፌልሶርን ዘመቻ ብዙ ዝርዝር ይሰጣል ፡፡

የአባቱን አልጋ በማርከሱ ምክንያት ሮቤል የብኩርናዉን መብት ባይወርስም ይህ ፅሁፍ ዘሮቹ ወደ እግዚአብሄር በጮኹ ጊዜ ጠላቶቻቸዉን ማሸነፋቸዉን ይገልፃል (1ዜና መዋዕል 5፡ 18-20) ፤ ነገር ግን ከእግዚአብሄር ዞር ባሉ ጊዜ በአሶር ንጉስ ተሸንፈዉ ነበር (1ዜና መዋዕል 5፡ 25-26) ፡፡

በህይወታችን በእግዚአብሄር ፊት የማያስደስቱ ነገሮች እንዳሉን የምናዉቅበት ጊዜያት ይኖራሉ ፤ የእግዚአብሄር ተስፋ በኑሮአችን ከተቋቋመ ተቃዉሞ ከእግዚአብሄር በረከት አያስወግደንም ፡፡ በኑሮአችን ንስሀ ያስፈልገናል ፤ ለእግዚአብሄር ነገሮች እና ለእቅዱ በጉዞአችን ፀንተን መቆም ያስፈልገናል ፡፡

ሮቤል ወደ አባቱ እና ወደ እግዚአብሄር እፍረት ባመጣዉ በህይወቱ ዋና ኃጢዓት ምክንያት ትልቅ ነገር አጣ ፡፡ የብኩርና መብቱም ለዮሴፍ ሁለት ልጆች ለኤፍሬም እና ለምናሴ ተሰጠ ፤ ነገር ግን ምድሪቱን የሚወስዱባት ጊዜ በመጣ ጊዜ - እግዚአብሄር በሙሴና በኢያሱ በኩል ለእስራኤላዊያን አዘጋጆቷት የነበረችዉን የተስፋይቱን ምድር መዉሰድ ቻሉ ምክንያቱም እግዚአብሄር ለእነርሱ ቃል ገብቶ ስለ ነበር ፡፡ በህዝቡ ላይ ኃጢዓት ቢኖርም እግዚአብሄር ለእስራኤል ቃል ኪዳኑን ጠበቀ ፡፡

ከእነዚህ ክስተቶች አራት መርሆችን ማዉጣት እንችላለን፡

  1. አንድ ትልቅ እቅድ አለ ፤ እግዚአብሄር በብዙ ተጫዋቾች አንድ ትልቅ እቅድ እንዳለዉ መረዳት እንችላለን ፡፡ በእስራኤል ስለ ነበረው አብዛሀኛዉ ህዝብም ምንም ነገር ባናዉቅም እግዚአብሄር እቅዱን ወደ መፈፀም ለማምጣት ሰራ ፡፡
  2. እግዚአብሄር ሁል ጊዜ መታመንን ይሸልማል ፤ እግዚአብሄር በፅናት የሚከተሉትን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቆሸሹ ቢመጡም እንኳን ይወዳቸዋል ፡፡
  3. እግዚአብሄር ሀቀኝነትን ይባርካል ፤ ሮቤል ትልቅ ስህተት በመስራቱ የብኩርና መብቱን አጣ ፡፡ ከእግዚአብሄር ርቆ አልተጓዘም ለእግዚአብሄር ታመነ እንጂ ፡፡ እግዚአብሄር ለእርሱና ለህዝቡ ካደረገዉ ተስፋ ፈቀቅ አላለም ፡፡
  4. ተስፋዎቹ ለሁሉም ናቸው ፤ በዚህ ጊዜ ከእግዚአብሄር ጋር እየተጓዙ የሚኖሩ ሰዎች ስለ ነበሩ እግዚአብሄር ለእስራኤል የገባዉን ኪዳን ወርሰዋል ፡፡ ስማቸዉን አናዉቃቸዉ ይሆናል ነገር ግን እግዚአብሄር ተስፋ ሰጥቶት እንደ ነበረው በተስፋይቱ ምድር እንደኖሩ እናዉቃለን ፡፡

መደምደሚያ

የእግዚአብሄር ተስፋዎች የእግዚአብሄርን ቃል ለሚቀበሉ ለሁሉም ናቸው ፡፡ በመታመን እና በሀቀኝነት በእግዚአብሄር ትልቅ እቅድ ትብብር እንጓዛለን የእርሱም እቅዶች ከራሳችን በላይ የተከበሩ ናቸው ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ለእኛ የእግዚአብሄር ተስፋዎች እግዚአብሄር በፍፁም አይተወንም በፍፁም አይጥለንም ማለት ነው ፤ ታዛዦች ባንሆንም እንኳን ቃሉን ያከብራል ፡፡ በመታዘዛችን ልናከብረዉ ይገባናል ፤ እግዚአብሄር በእኛ ላይ ተስፋ አይቆርጥም ፡፡ ወደ ንስሀ ከጠራን መልሶ አምጥቶን ለእኛ ተስፋዉን ያከብራል ፡፡ አንድ ጊዜ የእግዚአብሄር ተስፋዎች ወደ ኑሮአችን ሲመጡ ስናይ ከእርሱ ጋር በምንሆንበት ቦታ ለማጠራቀም በመዉሰድ የኑሮአችን ጌታ እንዲሆን መፍቀድ እና ከዚያም ቀጥሎ እንዴት እንደ ሚባርከን እና በእኛ እንዴት እንደሚጓዝ መመልከት ያስፈልገናል ፡፡ ሀቀኝነትና መታመን ሁል ጊዜ ከእግዚአብሄር ትልቅ እቅድ ጋር ይተባበራሉ ፡፡

ጥያቄዎች

  1. ሮቤል የእስራኤል ትልቁ ልጅ ነበር ፤ በዘር ግንድ መዝገቡ ላይ ሮቤል እንደ በኩር ያልተዘረዘረዉ ለምን ነበር ? የበኩርነት መብቱ ለማን ሆነ ?
  2. ያዕቆም በይሁዳ ላይ ምን ትንቢት ተናገረበት ? ይህን ትንቢት እንዴት ነበር የተፈፀመው ? (ዘፍ 49፡ 8-10, ሚክ 5፡ 2, ማቴ 2፡ 6)
  3. በጦርነት ላይ በነበሩ ጊዜ የሮቤል፣ የጋድ እና የምናሴ ግማሹ ነገድ ሰራዊት ምላሻቸዉ ምን ነበር (2ዜና መዋዕል 14፡ 11-13፣ መዝ 9፡ 10) ? በኃይለኛ ጦርነት ላይ በሆናችሁ ጊዜ የመጀመሪያዉ የምትጠሩት እግዚአብሄርን ነው ?
  4. እግዚአብሄር ምድሪቱን በመዉረር የራሱን ሰዎች ወደ ምርኮ እንዲወሰዱ የማያምኑ ነገስታትን እንዲጠቀም ያደረገዉ ምንክንያቱ ምንድነው ?
  5. በ 1ዜና መዋዕል 5 በትምህርት ወይም በትኛት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Chronicles 5:20

“They received help against these enemies because they cried out to God in battle, and the Hagrites and all their allies were handed over to them. He granted their request because they trusted in Him.”

ታሪክ ጸሀፊው የቀድሞውን ትውልድ ማስታወሱን ሲቀጥል የአባቱን ምንጣፍ ስላረከሰ ብኵርናውን ስላጣው ስለ ያዕቆብ የመጀመሪያ ልጅ ስለ ሮቤል ጻፈ ፡፡ ምንም እንኳ እርሱ በእርግጥ እግዚአብሔርን ቢበድልም የእርሱ ትላንት ግን እርሱን አልገለጸውም እግዚአብሔርም በእርሱና በዘሮቹ ላይ ተስፋን አልቆረጠም ፡፡ ከዚያም የሮቤልና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኵሌታ ከአጋራውያንና ከኢጡር ከናፌስና ከናዳብ ጋር ተዋጉ። በሚዋጉበትም ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኸዋልና እግዚአብሔር ረዳቸው ፡፡ ወደ እግዚአብሔር ጮኸዋልና፥ በእርሱም ታምነዋልና በውጊያ ድልን ተቀዳጁ ፡፡

በየቀኑ መንፈሳዊ ጠላታችሁ የሆነው ሰይጣን ኢየሱስን ስትከተሉ በእናንተ ላይ ለጦርነት ይወጣል ፡፡ ጦርነቱን እንዴት እንደምትዋጉ ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ ? የሮቤልን ፣ የጋድንና የምናሴን ነገዶች ምሳሌ ተከተሉ እናም በጦርነት ወደ እግዚአብሔር ጩኹ ፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ ፣ ለመዋጋትም እናንተ ኃይሉ እንደሌላችሁ እመኑ ፡፡ እግዚአብሔር ከጎናችሁ እንድሆንላችሁ ለምኑ እርሱም ይመልስላችኋል ፡፡ በእርሱ ድል እንደምትቀዳጁ ይነግራችኋል ፡፡ ብቻ ወደ እርሱ ሂዱ ፡፡ ያለፈው መተላለፋችሁ እንድገልጣችሁ ወይም እግዚአብሔርን እርዳታ ከመጠየቅ እንድከለክላችሁ አትፍቀዱ ፡፡ እርሱ ይወዳችኋል ከእርሱም ታላቅ ፍቅር ምንም ሊለያችሁ አይችልም ፡፡ ኢየሱስ የህይወታችሁ ጌታ እንድሆን ፍቀዱ እርሱም በውጊያዎቻችሁ ድልን ይሰጣችኋል ፡፡

“ በሚዋጉበትም ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኸዋልና፥ በእርሱም ታምነዋልና ተለመናቸው፤ በላያቸውም ረዳት ሆናቸው፥ አጋራውያንና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም ሁሉ በእጃቸው ተሰጡ። “

—1ኛ ዜና 5:20

ተጨማሪ ጥቅስ

  • መዝሙር 20:7 — “እነዚያ በሰረገላ እነዚያም በፈረስ ይታመናሉ፤ እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ከፍ ከፍ እንላለን።
  • መዝሙር 34:4 — “እግዚአብሔርን ፈለግሁት መለሰልኝም፥ ከመከራዬም ሁሉ አዳነኝ። “
  • 1ኛ ቆሮንቶስ 15:57 - “ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድል መንሣትን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። “