The Prayer of Jabez
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of David 1 Chronicles 4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በዜና መዋዕል በመጨረሻ ጎል ዘላለማዊ ዙፋን መሆን (2ሳሙኤል) የ 1ዜና መዋዕል ትኩረት በዳዊት ልጅ ላይ ነው ፡፡ እስከዚህ ድረስ ዜና መዋዕል የይሁዳን ነገስት ዘር ይጠቅሳል ፡፡ አሁን ደግሞ ፀሀፊዉ ወደ ቀሩት ነገዶች ይሸጋገራል ፡፡
ትምህርት
1-ዜና መዋዕል (4፡ 1-24)፡ የይሁዳ ዘር ዝርዝር ይቀጥላል ፡፡
1-ዜና መዋዕል (4፡ 24-43)፡ ፀሀፊዉ የስምዖንን ዘር ይዘረዝራል ፡፡ የስምዖን ምድር በይሁዳ መካከል የሚገኝ ስፍራ ነበር፡ “ ሁለተኛዉም ዕጣ ለስምዖን ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ ፤ ርስታቸዉም በይሁዳ ልጆች ርስት መካከል ነበር …. ከይሁዳ ልጆች ክፍል የስምዖን ልጆች ርስት ሆነ ፤ የይሁዳም ልጆች እድል ፈንታ ስለ በዛባቸው የስምዖን ልጆች በርስታቸው መካከል ወረሱ “ (ኢያ 19፡ 1, 9) ፡፡ ስምዖን ይሁዳን በመርዳት እንዲያግዘዉ በይሁዳ ምድር የተካተተ ነበር ፤ ይሁዳና ስምዖን በርስታቸዉ የሚኖሩትን ህዝቦች ለማስወጣት በጋራ ሰርተዋል፡ “ ይሁዳም ወንድሙን ስምዖንን ከነዓናዉያንን እንዋጋ ዘንድ ከእኔ ጋር ወደ እጣዬ ዉጣ እኔም ደግሞ ከአንተ ጋር ወደ ዕጣህ እሄዳለሁ አለው ፡፡ ስምዖንም ከእርሱ ጋር ሄደ “ (መሳ 1፡ 3) ፡፡
በቁጥር 28 እና ቀጥሎ(አልፎ) ፀሀፊዉ የዘር ግንዶቹን መልክዓ ምድር አሳይቷል ፤ “ ዳዊት ንጉስ እስኪሆን ድረስ “ (ቁጥር 31) በእነዚህ ሁሉ ስፍራዎች ኖረዋል ፤ በንጉሱ እስከ መድረስ በእነዚህ ስፍራዎች አንድ አላማ አገልግለዋል ፡፡
1-ዜና መዋዕል (4፡ 34-43)፡ ፀሀፊዉ የግዛት መስፋፋቶችን አሳይቷል ፡፡ ህዝቡ ማደግ ሲቀጥሉ ሰፊ ምድር አስፈለጋቸው ፤ ያገኙት ምድር “ የበለፀገች “ ነበረች እና “ መልካም መሰማሪያ “ ነበራቸው እንዲሁም “ ሰፊ፣ ፀጥተኛ እና ሰላም “ ነበረች (ቁጥር 40) ፡፡ በአጭሩ ምድሪቱ ሰዎቹ ይፈልጉት የነበረውን ሁሉንም ነገር ነበረች ፡፡
ምዑናዊያን (ቁጥር 41) ከካም ዘር ከነበሩ ህዝቦች ቡድን መካከል ነበሩ ፤ እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን ከምድሪቱ እንዲያስወጡዓቸዉ ከነገራቸዉ ሰዎች መካከል ጥቂቶች ነበሩ ፡፡
አሁን በዚህ ምዕራፍ ቅድምያ ባገኘነዉ ላይ ተመልሰን እስኪ በያቤፅ ፀሎት ላይ እናተኩር ፡፡
1-ዜና መዋዕል (4፡ 9-10)፡ ይህ የመፅሀፍ አጭር ክፍል በያቤፅ ፀሎት መፅሀፍ ላይ ከ2000 በቀደመ መፅሀፍ ላይ ህዝብ አቀፍ ክስተት ሆኗል ፡፡
ኤልያስ የባዖል ነቢያቶች በገጠሙት ጊዜ የፀለየዉ በብሉይ ኪዳን ሌለኛው ኃይለኛ የፀሎት ምሳሌ ነው፡ “ መስዋዕት ሰርክ በሚቀርብበት ጊዜ ነቢዩ ኤልያስ ቀርቦ ፡፡ አቤቱ የአብርሃምና የይስሐቅ የእስራኤልም አምላክ ሆይ አንተ በእስራኤል ላይ አምላክ እንደ ሆንህ እኔም ባሪያህ እንደ ሆንሁ ይህንም ሁሉ በቃልህ እንዳደረግሁ ዛሬ ይገለጥ ፡፡ አንተ አቤቱ አምላክህ እንደ ሆንህ ልባቸዉንም ደግሞ እንደ መለሰህ ይህ ሕዝብ ያዉቅ ዘንድ ስማኝ አቤቱ ስማኝ አለ ፡፡ የእግዚአብሄርም እሳት ወደቀች የሚቃጠለዉን መስዋዕቱንም እንጨቱንም ድንጋዮቹንም አፈሩንም በላች በጉድጓዱም ዉስጥ ያለዉን ዉኃ ላሰች …… አክዓብም ሊበላና ሊጠጣ ወጣ ፤ ኤልያስም ወደ ቀርሜሎስ አናት ወጣ ፤ ፊቱንም በጉልበቱ መካከል አድርጎ በግምባሩ ተደፋ ፡፡ ብላቴናዉንም ወጥተህ ወደ ባህሩ ተመልከት አለው ፡፡ ወጥጦም ተመልክቶም ምንም የለም አለ ፡፡ እርሱም ሰባት ጊዜ ተመላለስ አለው ፤ ብላቴናዉም ሰባት ጊዜ ተመላለስ ፤ በሰባተኛዉም ጊዜ እነሆ የሰዉ እጅ የምታህል ታናሽ ደመና ከባህር ወጣች አለው ፤ እርሱም ወጥተህ አክዓብን ዝናብ እንዳይከለክልህ ሰረገላን ጭነህ ዉረድ በለዉ አለ ፡፡ ከጥቂትም ጊዜ በኋላ ሰማዩ ከደመናዉና ከነፋሱ የተነሳ ጨለመ ብዙም ዝናብ ሆነ ፤ አክዓብም በሰረገላዉ ተቀምጦ ወደ ኢይዝራኤል ሄደ “ (1ነገ 18፡ 36-38, 42-45) ፡፡
ኤልያስ እግዚአብሄር በህይወቱ መታየት እንደ ሚፈልግ ያመነ የተሟላ የእግዚአብሄር ሰዉ ነበር ፤ በፀሎቱ እሳት በአካል ከሰማይ በመዉረድ እንጨቱን እና ሙሉ በሙሉ ሁሉንም ነገር በላች ፡፡ ያዕቆብ ኤልያስን “ እንደ እኛ የሆነ ሰዉ እንደ ነበር ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ በምድርም ላይ ሰዎስት አመት ከስድስት ወር አልዘነበም ፤ ሁለተኛም ፀለየ ሰማዩም ዝናብን ሰጠ ምድሪቱም ፍሬዋን አበቀለች “ ገልፆታል (ያዕ 5፡ 17-18) ፡፡ ኤልያስ “ እንደኛዉ አይነት ሰዉ “ ከነበር እንዳደረገዉ በተመሳሳይ መፀለይ እንችላለን ፡፡
አንዳንዶች ብሉይ ኪዳን ፀሎቶች ልክ እንደ ኤልያስ እና ያቤፅ አይነት ፀሎቶች የአዲስ ኪዳን አማኞች የሚፀልዩት እና እግዚአብሄር እንዲመልሳቸዉ የሚጠብቁት ፀሎት አይደለም ይላሉ ፤ ለተለዬ ጊዜ እና ለተለዬ አላማ የሚፀለይ እንጂ ፤ ነገር ግን ያዕቆብ የኤልያስ ተፈጥሮ የኛን የሚመስል እንደ ነበር ፅፏል የያቤፅንም ስም እንደ እኛ ተመሳሳይ ተፈጥሮ እንዳለዉ በዚያ ስሙን ማስቀመጥ እንችላለን ፡፡ ሀተታ ሰጪ ቻርለስ ፕራት “ የያቤፅ ፀሎት የፀሀፊዉ ቢያንስ ሰዎስት አመት ከሚርቁት ከመጀመሪያዎቹ አንባቢዎች ፍላጎት ጋር በቀጥታ ይገናኛል ብሏል “፡
- የዜና መዋዕል አንባቢዎች በግዞት ጊዜ እና ከግዞት በኋላ ብዙ ህመሞችን ቀምሰዉ ነበር ፡፡
- የያቤፅ ፀሎት በሰዓቱ ከተመለሱት እስራኤላዊያን ከግዞት በኋላ ግዛታቸዉን ማስፋፋት ከሚለዉ ፍላጎታቸዉ ጋር ይገናኛል ፡፡
- ያቤፅ ከህመም(ከስቃይ) እንዴት መፅናናት እንደ ሚገኝ እና የግዛት ማስፋፊያ ስራዎች ምሳሌ ነበር ፡፡
በመሰረቱ የያቤፅ ስም ትርጉሙ “ ስቃይ/ህመም “ ማለት ነው ፡፡ የያቤፅ እናት ይህን ስም ሰጠቸዉ ምክንያቱም እርሱን በምትወልድበት ጊዜ በኤደን ገነት የተሰጠዉን ርግማን በመጠበቁ ብዙ ስቃይ ደርሶባት ስለነበር ፡ “ ለሴቲቱም አለ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ ፤ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል እርሱም ገዥሽ ይሆናል “ (ዘፍ 3፡ 16) ፡፡ ያቤፅ ከህይወት እረፍትን ማግኘት ፈለገ ፡፡
በቁጥር 10 ያቤፅ ወደ እስራኤል አምላክ በመጣራት በህይወቱ ጣልቃ እንዲገባ እግዚአብሄርን በእምነት ጠየቀ ፤ ያለ እምነት እግዚአብሄርን ማስደሰት አይቻልም ፡፡ ኤር (33፡ 3) የሚለው “ ወደ እኔ ጩኽ እኔም እመልስልሀለሁ ፤ አንተም የማታዉቀዉን ታላቅና ኃይለኛ ነገርን አሳይሀለሁ “ ፡፡ ኢየሱስ እርሱ ካደረገዉ የሚበልጥ ነገር ተከታዮቹ ያደርጋሉ ብሏል (ዮሐ 14፡ 12) ስለዚህ እንድናደርግ የሚፈልገዉን የሚበልጥ ነገር እንዲያሳይ እግዚአብሄርን መጠየቅ አለብን ፡፡
ያቤፅ እግዚአብሄርን እንዲባርከዉ ጠየቀዉ ፤ በዚህ ጥያቄ ምንም ስህተት አልነበረም ! እግዚአብሄር አብርሃምን እንደሚባረከዉ ቃል ገብቷል ስለዚህም አብርሃም በረከት ይሆናል (ዘፍ 12፡ 2-3) ፡፡ ያቤፅ ወደ አብርሃም የዘር ግንድ ዉስጥ ስለወደቀ ለእግዚአብሄር እንዲባርከዉ መጠየቁ የእግዚአብሄርን ተስፋ ለአብርሃም መረዳቱን ያሳያል ፡፡ በክርስቶስ በሁሉም መንፈሳዊ በረከቶች ስለ ተባረክን (ኤፌ 1፡ 3) እነዚያን በረከቶች ለመሰጠት እግዚአብሄርን መጠየቅ መጥፎ አይደለም ፡፡
በተጨማሪም ያቤፅ ዳርቻዉን እንዲያሰፋ እግዚአብሄርን ጠየቀ ፤ ጥያቄዉ ለብዙ ስለ ነበር ብዙዎች በብዙ እግዚአብሄርን ማግኘት ይችላሉ ፡፡ ያቤፅ ስለ ምድር ከተግባራዊነት ዉጪ ጠየቀ ፤ ስለ አሪፍ መኪና ወይም ስለ ሚሊዮን ዶላር ጥያቄ ጋር የሚመጣጠን አልነበረም ፡፡
ያቤፅ የእግዚአብሄርን መገኘት ለማግኘት ጠየቀ፡ “ እጃችሁን ከእኔ ጋር አድርጉ “ ፡፡
ያቤፅ “ እንዳያሳዝነኝም ከክፉ ጠብቀኝ “ ብሎ ፀለዬ ፤ የያቤፅ ፀሎት ስለ እግዚአብሄር ጥበቃ ነበር ፡፡
መደምደሚያ
በብሉይ ኪዳን የያቤፅ ፀሎት ምንም የሚሆን ከሆነ ተመሳሳይ ፀሎት መፀለይ አንችልም ፡፡ ያቤፅ በዳዊት የዘር መስመር ዉስጥ ነበር ፡፡ የእግዚአብሄርን መገኘት፣ አቅርቦት እና ጥበቃ በመፈለግ ለእግዚአብሄር እያወራ ነበር ፡፡ ከክርስቶስ ጋር የጋራ ወራሾች ስለሆንን ያቤፅ እንደ ፀለየው ትልቅ ፀሎት ለመፀለይ ተመሳሳይ መብት አለን ፡፡ የህፃን ልጅ እምነት፣ ወደ እርሱ መምጣት እና በእርሱ ጊዜ መታመን እንዲኖረን ያስፈልገናል ፡፡
Charles Pratt, “The Identity, Privileges and Responsibilities of God’s People: 1 Chronicles 1:1—9:34.” Reformed Perspectives Magazine, Vol 1, Num 2, March 8, 1999; available on- line at http://reformedperspectives.org/search.asp/kw/richard%20pratt%201%20chronicles/kwtype//scat//st/articles/au//rpc/4/apc//vpc//qpc//Rrpp/10/Vrpp//Qrpp//Arpp/. Accessed
ጥያቄዎች
-
የያቤፅ እናት ይህን ስም ለምን ሰጠችዉ (1 ዜና መዋዕል 4፡ 9) ? በ 1ዜና መዋዕል (4፡ 10) ፀሎቱን አንብቡት ፤ የፀለየባቸዉ አራት ነገሮች ምንድን ናቸው ? የጠየቀዉን እግዚአብሄር መለሰለት ፤ ምን ይመስል እንደ ነበር ይገልፃል ፡፡
-
በ 1ዜና መዋዕል (4፡ 21) የሴሎም ልጆች “ ጥሩ በፍታ እንዲሰሩ “ ተጠርተዋል ፤ ለምን አስፈላጊ ይሆናሉ ? ሴሎም ማን ነበር ? (ዘፍ 38፡ 11-14)
-
ጥቂት የስምዖን ነገዶች ለመንጎቻቸዉ ግጦች እየፈለጉ ነበር ፤ ፀጥ ያለ እና ሰላም የሆነ የበለፀገ እና መልካም የሆነ ግጦሽ አገኙ ፤ ይችን ምድር ለመዉሰድ የሁለት ቡድን ሰዎች የነበሩትን እነማን አጠፉ ? (1ዜና መዋዕል 4፡ 40-43)
-
ስምዖናዊያን አጥፍተዋቸዉ የነበሩት ሰዎች ቡድን ካማዊያን ነበሩ (ዘፍ 9፡ 22- 25) ? በዘጸ (17፡ 14) አማሌቃዊያንን በተመለከተ እግዚአብሄር ሙሴን እንዲፅፍ ነግሮት የነበረዉ ምንድን ነበር ? (ዘዳ 25፡ 17-19)
-
በ 1ዜና መዋዕል 4 በትምህርት ወይም በትናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Chronicles 4:10
“Jabez called out to the God of Israel: ‘If only You would bless me, extend my border, let Your hand be with me, and keep me from harm, so that I will not cause any pain.’ And God granted his request.”
ያቤጽ የተከበረ ሰው ነበረ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ጠራ በእምነትም ጸለየ ፡፡ በጸሎቱም ያቤጽ እግዚአብሔር ይባርከው ዘንድና ድንበሩን እንድያሰፋ ለመነ ፡፡ የእግዚአብሔርም እጅ በእርሱ ላይ ትሆን ዘንድ እንድሁም በተጨማሪ የእግዚአብሔር መገኘት በህይወቱ ላይ እንድሆን ለመነ ፡፡ የእግዚአብሔርን ጥበቃ ጠየቀ ፡፡ ያቤጽ በህይወቱ በደንብ የእግዚአብሔርን መገኘት ማየት ስለፈለገ ወደ እግዚአብሔር ለመነ ፡፡
እንዴት ነው ምትጸልየው ? በእምነት ነው የምትጸልየው እንድሁም በይበልጥ በህይወትህ የእግዚአብሔርን መገኘት ነው የምትጠይቀው? የያቤጽ ጸሎት ፎርሙላ (መመሪያ) አይደለም ይልቁንም በህይወቱ የእግዚአብሔርን መገኘት የሚሻ ታማኝ ሰው ጸሎት እንጅ ፡፡ አንተስ የምትፈልገው ይህን አይደለም ? ዛሬ ወደ እግዚአብሔር ተጣራ ፡፡ እንድባርክህና የህይወትህን ዳርቻ እንድያሰፋ ጠይቀው ፡፡ የእግዚአብሔርን ጥበቃ ለምን ፡፡ እርሱ መሸሸጊያና መከታህ እንደሆነ ይናገራል ፡፡ በክንፎቹም ጥላ ስር ይሸሽግሃል ፡፡ ወደ እኔ ጩኽ ይልሃል ፡፡ በጊዜውም ይመልስልሃል ስለዚህም ወደ እርሱ ስትለምን እርሱ እንድሚመልስልህ እመን !
“ ያቤጽም፦ እባክህ፥ መባረክን ባርከኝ፥ አገሬንም አስፋው፤ እጅህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እንዳያሳዝነኝም ከክፋት ጠብቀኝ ብሎ የእስራኤልን አምላክ ጠራ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው። “
—1ኛ ዜና 4:10
ተጨማሪ ጥቅስ
- መዝሙር 37 :23 — “ የሰው አካሄድ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይጸናል፥ መንገዱንም ይወድዳል። ”
- ኢሳይያስ 54:2 — “የድንኳንሽን ስፍራ አስፊ፥ መጋረጃዎችሽንም ይዘርጉ፤ አትቈጥቢ፤ አውታሮችሽን አስረዝሚ ካስሞችሽንም አጽኚ። “
- ኤርምያስ 33:3 — “ወደ እኔ ጩኽ፥ እኔም እመልስልሃለሁ፤ አንተም የማታውቀውን ታላቅና ኃይለኛ ነገርን አሳይሃለሁ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።