Historical Books 1 Chronicles

David's Descendants

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of David 1 Chronicles 3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 284 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ይህ በ 1ዜና መዋዕል በብዛት የሚገኝ ምዕራፍ ነው ፤ ይህ ጠቅላላ ምዕራፉ ስለ ዳዊት የዘር ግንድ ነው ፡፡ አስታዉሱ ለዘፍጥረት ቃላችን ዘር ነው ፤ ለፀሀፊዉ ተመልሶ ከተስፋይቱ ምድር ዘሩ ከዳዊት እንደ ሆነ ለማሳየት አስፈላጊ ነው ፡፡ እነዚህ የዘር ግንዶች የእግዚአብሄርን ተስፋ መስመር ይገልፃሉ ፡፡ ሁሉም ስሞች ብዙ ታሪኮች እና ግንኙነቶች አሏቸው፡፡ ወደ ዳዊት ልጅ የሚመራዉን መስመር ማሳየት ስራችን ነው ፡፡

ትምህርት

የዳዊት ቀጥተኛ ልጆቹ (1 ዜና መዋዕል 3፡ 1-9)፡

1-ዜና መዋዕል (3፡ 1-2)፡ ዳዊት በኬብሮን ለሰባት አመት አስተዳደረ ስድስት ልጆችም ነበሩት ፤ ዳዊት ብዙ ልጆች እና ሚስቶች ነበሩት ፤ መጀመሪያ የተጠቀሱት እያንዳንዶቹ ስድስት ልጆች ከተለያዩ ሚስቶች ነበሩ ፡፡ የዳዊት የበኩር ልጅ አምኖን የወንድሙን እህት ትዕማርን ደፍሯታል (2ሳሙኤል 13) ፤ ዳዊት በአምኖን ላይ ድርጊት ለመዉሰድ ፈራ ነገር ግን የአምኖን ወንድሙ አቤሴሎም በበቀል በመግደል ሸሸ ፡፡ የዳዊት በሁለተኛ የተወለደለት ዳንኤል ነበር እንዲሁም ቺሊያብ ወይም ኪሊያብ ተብሎ ይጠቀሳል “ አባቱን የሚመስል “ ማለትም ነው ፡፡ በእነዚህ የዘር ግንዶች ብዙ የስም ልዩነቶች አሉ ፡፡ ራቢኒክ ፅሁፍ በዳዊት እና በአቢጊያ ግንኙነት መካከል በነበረዉ ሁኔታ ሁለቱ ስሞች እንደ ነበሩ ይናገራል ፡፡ አቢግያምየዳዊትን ሰዎች ለመርዳት እምቢ ያለዉ ቆይቶም በእግዚአብሄር ተመትቶ የሞተዉ የናባል ሚስት ነበረች (1ሳሙ 25፡ 2-42) ፡፡ አቢግያ ከዳዊት ጋር ጓደኛ ሆነች ቆይቶም አገባት ፡፡ እነዚህ የመጀመሪያዎቹ አራት ልጆች በዘሩ መስመር ዉስጥ አልተቀመጡም ፤ አመፅ፣ መድፈር እና ሞት ነበር ፡፡

1-ዜና መዋዕል (3፡ 3)፡ ኤግላ እና ይትርኃም ከመስመሩ ጋር አይጣጣሙ እንጂ አንዳንድ የአይሁድ ምሁራን ኤግላ ሚልኮል እንደ ነበረች ያስባሉ ፡፡ ሚልኮል የሳዖል ልጅ ነበረች አንዳንዶች የዳዊት ብቸኛዋ ህጋዊ ሚስቱ ነበረች ይላሉ ፤ ነገር ግን ብዙዉ የዳዊት የመጀመሪያ ሚስቱ ሚልኮል እንዳልተወከለች አመልክተዋል ፡፡ በእርግጥ በሁሉቱ መካከል የነበረዉ ግንኙነት የሰለለ(ዉጥረት ያለበት) ነበር ፡፡ 2ሳሙ ( 6፡ 23) ሚልኮል “ እስከ ሞተጭበት ቀን ድረስ ልጅ እንዳልነበራት “ ይናገራል ፤ ለዘሩ እና ዘሩን ለሚሸከመዉ አስፈላጊነት ምክንያት ይህን እጠቅሳለሁ ፡፡ ዘሩ በዳዊት ሌሎች ሚስቶች ላይ ተቀምጧል ፡፡

1-ዜና መዋዕል (3፡ 4-5)፡ ዳዊት በኢየሩሳሌም 33 አመታት አስተዳደረ ፤ በ33ቱ አመታት ለቤርሳቤህ በአማራጭ መጠሪያ ቤሳቤህን አገባ - አራት ልጆች የወለደችለትን ! የመጀመሪያዉ ነገር ማስተዋል ያለባችሁ ዳዊት በቤርሳቤህ ላይ የፈፀመዉ ኃጢዓት (2ሳሙኤል 11-12) እንዲሁም የሞተዉ ልጅ አልተጠቀሱም ፡፡ ዝርዝሮቹ ለፀሀፊዉ አስፈላጊዎች አልነበሩም ነገር ግን ዘሩ ከየት መስመር በኩል እንደመጣ እንጂ ፡፡ ሁላችንም ሰለሞንን እናዉቀዋለን ነገር ግን ናታንን እንድትረሱት አልፈልግም ፡፡ የናታን ለዝና ጥያቄ በኢየሱስ የዘር ግንድ ዉስጥ ነው (ሉቃ 3፡ 31) ፤ የናታን ወራሾች ወደ ኢየሱስ እናት ወደ ማሪያም መርተዋል ፡፡ መጨረሻም ሰለሞን ዳዊትን ተከትሎ እንደ ንጉስ ተቀምጧል ፡፡

1-ዜና መዋዕል (3፡ 6-8)፡ የዳዊት ሌሎች ልጆች ተጠቅሰዋል ብዙም ነበሩ ፡፡ ኤሊፋላት የሚለዉ ስም ሁለት ጊዜ መጠቀሱን እንድታዉቁ እፈልጋለሁ ፤ ይህ ስም ሊደገም ይችላል ምክንያቱም በህፃንነቱ የሞት አንድ ልጅ ስለ ነበር ማስታወሻዉን ለማቆየት ስሙ በመንገድ ላይ አልፏል ፡፡ ፀሀፊዉ ሁሉም የዳዊት ልጆች እንደ ነበሩ እንደምንረዳዊ እርግጠኛ እያደረገን ነበር ፡፡

1-ዜና መዋዕል (3፡ 9)፡ ምናልባትም ትዕማር የዳዊት ብቻ ልጅ አልነበረችም ፡፡ በመሰረቱ ሴቶች በታሪኩ ላይ ተፅዕኖ ካልነበራቸዉ በቀር በዘር ግንዱ ላይ አይጠቀሱም ነበር ፡፡ ትዕማር በታሪኩ ላይ ተፅዕኖ ነበራት ፡፡ ዳዊት ምን ያክል ቁባቶች እንደ ነበሩት አናዉቅም ፤ ቢያንስ ግን አስር ነበሩት ( 2ሳሙ 15፡ 16፣ 20፡ 3) ፡፡ በልጁ በአቤሴሎም ዳዊትን ያዋረዱ ብዙ ቁባቶች እንደ ነበሩ እናዉቃለን ፡፡ እንደገና በዳዊት መስመር ላይ ትኩረቱ ዘሩ ነው ፤ ለእንደነዚህ አይነቶቹ ዝርዝር የዘር ግንድ ዋና ምክንያት የክርስቶስ መስመር ከአዳም (ሉቃ 3፡ 38) ከዚያም ከአብርሃም ወደ ዳዊት (ማቴ1፡ 10 እንደ ሆነ ያረጋገጡ ስለሆኑ ነው ይህም በክርስቶስ በመንግስቱ የእግዚአብሄርን ሀሳብ በደንብ ይገልፃል ፡፡

አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ሰዎች እዉነት ነበሩ የሚለዉን እዉነት መስመሩን ለማጣት ለእኛ ቀላል ነው ፡፡ እግዚአብሄር በሚያስደንቅ ሁኔታ ለአላማዉ በጉድለት(በእንከን) የነበሩ ሰዎችን ይጠቀማል ፡፡ የዳዊት ቤተሰብ በኃጢዓት ዉጤት ምክንያት ጤናማ ሁኔታ ላይ አልነበረም ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር ተጠቀመበት ( ለምሳሌ የኬጥያዊዉ ሚስት የቤርሳቤህ ልጅ ሰለሞን = ከመሲሁ መስመር) ፡፡ በተጨማሪም እግዚአብሄር እነዚህን ኃጢዓቶች በመንፈሳዊ እድገት ላይ እና በዳዊት መቀረፅ(መስተካከል) ላይ ተጠቅሞባቸዋል ፡፡ ለምሳሌ ዳዊት በብጥብጥ እና በትርምስ መካከል ላይ ሰላም እና ረፍት ማግኘት ባለመቻሉ ከነፍሱ መዝሙር ፅፏል ነገር ግን ለእግዚአብሄር በመታመን ፤ በኃጢዓቱ መካከል ላይ ዳዊት ወደ እግዚአብሄር ተመለሰ ፡፡

ይሁዳ እስከሚሰደድ ድረስ የዳዊት መስመር ( በሰለሞን በኩል) (1ዜና መዋዕል 3፡ 10-16)፡

1-ዜና መዋዕል (3፡ 10-12)፡ ፀሀፊዉ የንጉስ ሰለሞንን መስመር በማየት እርግጠኞች አድርጎናል አስፈላጊም ነበር፡፡ በ 1ነገስት መፅሀፍ ላይ ሰለሞንን ተመልክተነዋል ፤ የይሁዳን ነገስታት መስመርም አይተናል ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ስማቸዉን መፈለግ አሰልቺ ተግባር እንደሚሆን አምናለሁ ፤ ነገር ግን እነዚህ እግዚአብሄር በዘሩ ላይ የተሸከማቸዉ ትክክለኛ ሰዎች ነበሩ ፡፡ መልካም ነገስታቶን እና ክፉ ነገስታቶችን በመጥናት መካከል ፊት እና ኋላ ተወዛዉዘናል ፡፡ የሰለሞን ልጅ ሮብዓም የመንግስቱን መከፈል አተመ (አረጋገጠ) ፤ ከዚያም ወደ ሰለሞን ሌለኛዉ ልጁ ተጓዝን ፡፡ በእነዚህ ዝርዝሮች ብዙ የስም ልዩነቶች እንደ ነበሩ አስታዉሱ አንዳንድ ጊዜ ሌላ ስፍራ ላይ በመግለጫቸዉ ለመድረስ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል ፡፡ በጥንቃቄ እነዚህን ማጥናት በጊዜዉ ላይ እንደገና ደግሞም በጊዉ ላይ እንዴት አልፎ እንደ ነበር ለማየት ይፈቅድልናል(ያስችለናል) ፡፡

1-ዜና መዋዕል (3፡ 3-14)፡ በሰለሞን ልጆች በሕዝቅያስ እና በምናሴ ከክፉ ወደ በጎ ከዚያም ተመልሶ ወደ ክፋት እብደት የሆነ መመላለስ ነበር - ከአባት ወደ ልጅ ከዚያ ወደ አያት ፤ አምኖን በጣም ክፉ ነበር ኢዮስያስ ደግሞ በጣም መልካም ነበር ፡፡ የኢዮስያስ ልጆች የተዘረዘሩ ናቸው ፡፡

1-ዜና መዋዕል (3፡ 15-16)፡ በቁጥር 15 ይህ ጠቅላላ የኢዮስያስ ልጆች ኃጢዓት ዉጤት መጥፎ መጨረሻ ነበረው ፡፡ ኢዮአቄም ለ 11አመታት እንደ ንጉስ ተቆጣጠረ በኢየሩሳሌምም ሞተ ፤ ልጁም ኢኮንያን ለሰዎስት ወር ተቆጣጠረ ፡፡ ኢኮንያን በእግዚአብሄር ስለ ተረገመ ንጉሳዊ ዘር አለወለደም (ኤር 22፡ 24-30) ፤ ምንም እንኳን ኢኮንያን በክርስቶስ መስመር ቢሆንም መሲሁ በአካል ከዚያ መስመር አልነበረም ይህም እርግማኑን ያረጋግጣል ፡፡ በስጋ የመወለድ መብቱ በዳዊት ልጅ በሰለሞን ሳይሆን በናታን ጣልቃ በመግባቷ በማሪያም በኩል መጣ (ሉቃ 3፡ 31) ፡፡ የመንግስቱ መስመር በሰለሞን በኩል መጣ ፡፡ ማሪያም እና ዮሴፍ ሁለቱም ከይሁዳ መስመር (ግንድ) ከዳዊት መጡ ፡፡

መስመሮቹ (ግንዶቹ/ዘሮቹ) በሉቃስ እና በማቴዎስ ከሰላትያል እና ከዘሩባቤል ጋር ይቀላቀላል ፡፡ ኢኮንያን ተያዘ ወደ ባቢሎንም ተወሰደ ፤ አጎቱም ሴዴቅያስ በዙፋኑ ላይ ነገሰ ነገር ግን በመጨረሻም በመታወር በባቢሎን ወደ ምርኮ ተወሰደ ፡፡ ኃጢዓት እና ጣዖት አምልኮ የይሁዳን መንግስት አጠፋ የእግዚአብሄር ቤተ መቅደስንም ብቻዉን አስቀረው ፡፡

የዳዊት መስመር ከይሁዳ ግዞት በኋላ (1ዜና መዋዕል 3፡ 17-19)፡

1-ዜና መዋዕል (3፡ 17-18)፡ እዚህ ላይ የተዘረዘሩት ስሞች ይሁዳ ከወደቀ በኋላ የተወለዱ የዳዊት ዘሮች ናቸው ፤ የዳዊትን ንጉሳዊ መስመር ተሸክመዋል ፡፡

1-ዜና መዋዕል (3፡ 19)፡ የዘር ግንዱ በዘሩባቤል በኩል ቀጠለ ፡፡ ወደ ኢየሩሳሌም ስመለሱ የመጀመሪያዎቹን ምርኮኞች በመምራት ለእግዚአብሄር መሰዊያዉን እና ቤተ መቅደሱን እንደ ገና ለመስራት ይሞክራል ፤ ነገር ግን እዚህ ጋር ችግር አለ ፤ በ 1ዜና (3፡ 19) መሰረት ዘሩባቤል የፈድያ ልጅ ነበር ፤ ይሁን እንጂ በዕዝ (3፡ 2) መሰረት ዘሩባቤል የሰላቲያል ልጅ ነበር ፡፡ ትክክለኛ የዘር ግንድ ዝምድናዉ የትኛዉ ነው ?

በህግ እና በታሪክ መፅኀፍት ሁለቱም የሚሆኑበት እድሎች አሉ ፡፡ አንድኛዉ አማራጭ ዘሩባቤል የፈድያ ልጅ የፈድያ ታልቅ ወንድም የሰላቲያል ወንድም ልጅ ነበር ፡፡ መፅሀፍ ቅዱስ የፈድያን ሞት ባይመዝግብም ሴም ከተወለደ በኋላ በአጭሩ እንደ ሞተ መገመት ምክንያታዊ ነው እናም የኢኮንያን ትልቅ ልጅ ሰላቲያል እንደ ራሱ ልጅ ዘሩባቤልን አሳደገው ፡፡ ሁለተኛዉ አማራጭ ሰላቲያል ያለ ልጅ ስለሞተ ፤ ወንድሙ ፈድያ ሚስቱን በማግባት ዘሩባቤልን ወለደ፡፡ አንድ የአስቀጣይ ትዳር (ዘዳ 25፡ 5-10) የሞተዉን ባል ዘር መስመር ለማስቀጠል ነበር ፤ ስለሆነም ዘሩባቤል በትክክል የሰላቲያል ልጅ ነበር ፡፡ ይህ ለምን ጠቃሚ ነው ? የኢየሱስ የዘር ግንድ ዝርዝር (ማቴ 1፡ 1-16፣ ሉቃ 3፡ 23-38) ፤ በሰላቲያል እና በዘሩባቤል የጋራ መነሻ ይገኛል (ማቴ 1፡ 12-13፣ ሉቃ 3፡ 27) ፡፡

1ዜና መዋዕል (3፡ 20-24) ሌሎች ብዙ ስሞችን ይዟል ፤ የማይታዩ (የማይታወቁ) ይሆናሉ ነገር ግን ትክክለኛ ሰዎች ነበሩ ፡፡ ፀሀፊዉም ሁሉም በአንድ ላይ በማጣጣም መስመሩ እንደ ቀጠለ እንድንረዳ እርግጠና እያደረገ ነበር ፡፡

መደምደሚያ

ዝርዝሩ በብሉይ ኪዳን መዝጊያ ህግ ላይ ከክርስቶስ ልደት በፊት አምስተኛዉ ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ በተወለደዉ በዓናኒ ያበቃል ፡፡ እንደ ዳዊት ቤተሰብ ከማንኛዉም የይሁዳ ጎሳ በጣም የበዛ ነበር የዘሩ የዘር ግንድም በታላቅ ጥበቃ እና ትክክለኛነት የተጠበቀ ነበር ፡፡ የዳዊት የራሱ ቤት ህይወት እንዴት እንደ ቆሸሸ እና የሰለሞን የትዳር እዝህላልነት እንደ ጥበቡ የታወቀ እንደ ሚሆን እናዉቃለን ፤ በተጨማሪም እነዚህ ነገስታቶች በድግግሞሽ መልካሞች ወይም ክፉዎች አልነበሩም - ወይም ደግሞ ሁለቱንም ፤ ይሁን እንጂ ዘሩ እና የተስፋዉ ቃል ከትዉልድ ወደ ትዉልድ ተንቀሳቀሰ ፡፡ የዳዊት መስመር በተስፋዉ የዳዊት አምላክ በነበረው በዳዊት ልጅ ለዘላለም ይቀጥላል ፡፡ ይህ ምዕራፍ ወደ ክርስቶስ ያመለክታል - በእንዲህ አይነት የተወሳሰበ እና ሰፊ መስመር በእግዚአብሄር እጅ ብቻ በአንድ ላይ መምጣት ችለዋል !

ጥያቄዎች

  1. በ 1ዜና መዋዕል (3፡ 5) መሰረት ቤርሳቤህ ለዳዊት ምን ያክል ልጅ ወልዳለታለች ? ይህ ያስገርማችኋል ? ስለ እነዚህ ሌሎቹ ልጆች ለምን ምንም ስላለማወቃችን ምን ታስባላችሁ ?
  2. በ 1ዜና መዋዕል (3፡ 9) ያለዉ ፅሁፍ የዳዊት የቁባቶቹ ልጆች በብዙ የማያስፈልጉ እና እዉቅና የተሰጣቸዉ እንዳልነበር ያመለክታል ?
  3. የ 1ዜና መዋዕል ፀሀፊ ይህን የዘር ግንድ በተለይም የዳዊትን ዘር በደንብ ለምን እንደ መዘገበ ምን ታስባላችሁ ?
  4. በ 1ዜና መዋዕል 3 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Chronicles 3:4–5

“Six sons were born to David in Hebron, where he ruled seven years and six months, and he ruled in Jerusalem 33 years. These sons were born to him in Jerusalem: Shimea, Shobab, Nathan, and Solomon. These four were born to him by Bath- shua daughter of Ammiel.”

ለእስራኤላውያን ዘርን ማስታወሱ በዳዊት ዘሮችና በይሁዳ ነገሥታት ቀጥሏል ፡፡ ስሞቹ የክርስቶስን የዘር ሀረግ እንድሁም በዳዊት ቤተሰብና በይሁዳ ነገድ ውስጥ ያለውን ዘር እስከሚጠቁሙ ቀጥለዋል ፡፡ እያንዳንዱ የተዘረዘረ ሰው እውነተኛ ሰው ሲሆን ከእውነተኛ ታሪክና ከእውነተኛ የኃጢአት ጉዳይ ጋር ነው ፡፡ ነገር ግን በኃጢአታቸው አልነበረም የተጠቀሱት የመሲሁን ዘር በመጠበቅ እንጅ ፡፡

አንተ በኃጢአትህ አይደለም የምትገለጠው ፡፡ አዎ እግዚአብሔር ኃጢአትን ይጠላል ነገር ግን ኢየሱስ ከኃጢአት ባርነትና ከሞት ነጻ ሊያወጣህና ህይወትና ፍጻሜን ሊሰጥህ መጥቷል ፡፡ የዳዊትን የዘር ሀረግ ስትመለከት የኢየሱስ ዘር በዳዊት ልጅ ውስጥ ተቀምጦ እንደነበር አስተውል ፡፡ ያ ነው ቁልፉ ፡፡ ልክ የጌታ እጅ በአንተ በልጁ ላይ እንደሆነው ሁሉ የእግዚአብሔርም እጅ በዚህ ቤተሰብ ላይ ነበረች ፡፡ በኃጢአት ልትወድቅ ትችላለህ ነገር ግን ኢየሱስን ስትፈልግና ከኃጢአት ስትመለስ ይቅርታውን ትቀበላለህ ፡፡ በክርስቶስ ተስፋን ደግሞም ከኃጢአት ነጻ መውጣትን ታገኛለሀ ፡፡ በትላንቱ ኃጢአትህ ጸንተህ አትኑር ይልቁንም ውብ የሆነው የክርስቶስ የቤዛነት ታሪክ በህይወትህ እንድታይ አድርግ ፡፡ እግዚአብሔር ነገርን ሁሉ አያይዞ ለመልካም እንደሚያደርግ ተናግሯል ፡፡ ከገረጣ መልክ ውበትን እንድሰጥ ተናግሯል ፣ ቤዛነትንም እንድሁ ፡፡ ስማችሁ ለእርሱ ክብር ይሆን ዘንድ የቤዛነትን ፍቅር ታሪክ ያውራ !

“ስድስቱ በኬብሮን ተወለዱለት፤ በዚያም ሰባት ዓመት ከስድስት ወር ነገሠ፤ በኢየሩሳሌምም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ። እነዚህ ደግሞ በኢየሩሳሌም ተወለዱለት፤ ከዓሚኤል ልጅ ከቤርሳቤህ፥ ሳሙስ፥ ሶባብ፥ ናታን ፡፡ “

—1ኛ ዜና 3:4–5

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ኤፌሶን1:7–8 — “በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት። ጸጋውንም በጥበብና በአእምሮ ሁሉ አበዛልን። “
  • ፊልጵስዩስ3:13–14 — “ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍ ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን መጥራት ዋጋ እንዳገኝ ምልክትን እፈጥናለሁ።”
  • 1ኛ ዮሐንስ 1:9 — “በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው። “