Historical Books 1 Chronicles

What's Your Role

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of David 1 Chronicles 2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 283 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

1ዜና በሌሎች የታሪክ መፅሀፍት ባጠናነዉ ላይ በመገንባት ኢየሱስን ከብሉይ ኪዳን ቀልፍ ስዕሎች ጋር በማገናኘት ወደ ክርስቶስ የዘር ግን ያመለክታል ፡፡ የኢየሱስ አገልግሎት በአዳም ላይ፣ በኖህ ላይ፣ በአብርሃም ላይ፣ በሙሴ ላይ፣ በዳዊት ላይ፣ በሰለሞን ላይ እና በቀሩት ነገስታት ላይ የተሰራ ነበር ፡፡ ይህ ምዕራፍ ከአብርሃም ዘር ወደ እስራኤል ዘር (ያም ያዕቆብ ነው) የሽግግር ነው ፡፡

ትምህርት

1-ዜና መዋዕል (2፡ 1-2)፡ የእስራኤል 12 ነገዶች በቁጥር 1እና 2 ተዘርዝረዋል ፡፡ መጀመሪያ ከአዳም ጋር ተገናኙ ከዚያም ከኖህ ጋር ከዚያም ቀጥሎ ከአብርሃም ጋር አሁን ደግሞ እስራኤል ተብሎ ከተጠራዉ ከያዕቆብ ጋር ፡፡ ያዕቆብ ከመሞቱ በፊት ልጆቹን በመሰብሰብ በትንቢት በእነርሱ ላይ ተናግሮባቸዋል፡ “ ያዕቆብ ልጆቹን ጠርቶ እንዲህ አለ በኋለኛዉ ዘመን የሚያገኛችሁን እንድነግራችሁ ተሰብሰቡ ፡፡ እናንተ የያዕቆብ ልጆች ተሰብሰቡ ስሙም ፤ አባታችሁ እስራኤልንም አድምጡ ፡፡ ሮቤል አንተ በኩር ልጄና ኃይሌ የጉብዝናዬም መጀመሪያ ነህ ፤ የክብር አለቃና የኃይል አለቃ ፡፡ እንደ ዉሃ የምትዋልል ነህ ፤ አለቅነት ለአንተ አይሁን ፤ ወደ አባትህ መኝታ ወጥተኃልና ፤ አረከስኸዉም ፤ ወደ አልጋዬም ወጣ “ (ዘፍ 49፡ 1-4) ፡፡

ሮቤል ትልቁ ስለነበር በዚህ ቤተሰብ ዉስጥ መጀመሪያ መጠቀሱ ለእርሱ ትርጉም ይሰጠዋል ነገር ግን ይሁዳ መጀመሪያ ተጠቅሶ ነበር ፡፡ ሮቤል ከአባቱ ቁባት ከባላን (ዘፍ 35፡ 22) ጋር በመተኛቱ የዝና ስፍራዉን አጣ ፡፡ ይሁዳ ሁለተኛ ትልቅ ልጅም አልነበረም ፤ አራተኛ ነበር ነገር ግን የመጀመሪያዎቹ ሰዎስቱ ልጆች ቆሽሸዋል ፡፡

1-ዜና መዋዕል (2፡ 3)፡ ዔር 1 ዜና መዋዕል እንደ ክፉ ከገለፃቸዉ ሰዎች የመጀመሪያዉ ነበር ፡፡ የዜና መዋዕል ፀሀፊ ምናልባትም ዕዝራ ቤተሰብን በመጥራት ትዉልዱን ለማገናኘት በራሱ መንገድ ሄደ ፤ ፀሀፊዉ የዳዊት ልጅ ብሎ በገለፀ ጊዜ በ 1ዜና መዋዕል ቤተሰቦች የሚጠቅም ሚና ተጫዉተዋል ፡፡

1-ዜና መዋዕል (2፡ 4)፡ ትዕማር በህግ የእስራኤል (ያዕቆብ ተብሎ በሚታወቀው) ልጅ ነበረች ፤ በቤተሰቧ ምንም ጥቅም እንዳልነበራት በማሰብ የተሰማት ቢሆንም እንኳን ፀኀፊዉ የዳዊትን ልጅ በማገልገል ጠቅሷታል ፡፡

1-ዜና መዋዕል (2፡ 5-8)፡ ፀሀፊው ከይሁዳ ወደ ፋሬስ ተጓዘ ፡፡ የይሁዳ ቤተሰብ በ 1ዜና መዋዕል ከአሁን እስከ አምስት ምዕራፎች ታዋቂ ተግባራትን ይወስዳሉ ፡፡ ሌሎቹ ነገዶች ቆይተው የራሳቸዉን የቤተሰብ ዘር ያገኛሉ ፡፡ እያንዳንዱ ነገድ በዳዊት ልጅ መምጣት አስፈላጊዉን ድርሻ ተጫዉቷል ፡፡

1-ዜና መዋዕል (2፡ 9-12)፡ ፀሀፊዉ ከይሁዳ ዘር ወደ ፋሬስ ዘር ተጓዘ ፡፡ እነዚህ ቁጥሮች ወደ አራም ልጆች ያሸጋግራሉ ፤ አራም ለኤስሮም እንደ ሁለተኛ ልጅ የተጠቀስ ቢሆንም እንኳን እግዚአብሄር የሚመጣዉ መሲህ መስመር እንዲሆን የቤተሰቡን መስመር መረጠ ፡፡ የዜና መዋዕል ፀሀፊ በቁጥር 11 ቡዔዝን ጠቅሶታል ፤ ይህ በመሳፍንት ጊዜ ከተካሄደዉ በሩት መፅሀፍ ካለዉ ቡዔዝ ጋር ተመሳሳይ ነበር ፡፡

1-ዜና መዋዕል (2፡ 13-17)፡ ፀሀፊው የእሴይን ሰባት ልጆች ዳዊትን ሰባተኛዉ በማድረግ መዘርዘረን ቀጠለ ፡፡ ሌሎች ፅሁፎች ዳዊትን እንደ ስምንተኛ ልጅ ይጠቅሱታል ፤ በ 1ዜና መዋዕል (27፡ 18) የእሴይ ልጅ ዘርዝሮ በነበር ጊዜ ኤሊሁ ሰባተኛ ስፋራ ላይ በመጨመሩ ዳዊት ተመልሶ ስምንተኛ ስፋራ ላይ ተቀመጠ ፡፡ ፀሀፊዉ ቆይቶ በሚዘረዝር ጊዜ በዚህ ፅሁፍ ለምን ኤሊሁን አይዘረዝረውም ? በዚህ አገባብ በአንዳንድ ምክንያቶች ትኩረቱ ስላልሆነ ይሆናል ፡፡

1-ዜና መዋዕል (2፡ 18-24)፡ ፀሀፊዉ ቀጥሎም የካሌብን ልጆች ዘረዘረ ፤ ይህ የኢያሱ መፅሀፍ ካሌብ አልነበረም የዘፍጥረት ካሌብ እንጂ ፡፡ ይህ የካሌብ ዘር ሰዎስት ጊዜ የተሰባበረ ነበር፡ ሁለት ጊዜ እዚህ እና አንድ ጊዜ በ 1ዜና መዋዕል 4 ፡፡ በቁጥር 20 የተጠቀሰዉ ባስልኤል ጥበበኛ ከነበረው ባስልኤል (ዘጸ 31፡ 2-5) ጋር ተመሳሳይ ነበር ፡፡ የባስልኤል በአባቱ ማንነት እና በዳዊት ልጅ መስመር ማንነቱ ምክንያት ስራ የሚመጣዉን ንጉስ ማገልገል ነበር ፡፡

1-ዜና መዋዕል (2፡ 25-41)፡ እዚህ ደግሞ ፀሀፊው የኤስሮምን ዘር ዘርዝሯል ፡፡ ከእነዚህ ስሞች አንዱም ከዚህ ፁሁፍ ዉጪ በቁጥር 25-41 ከተጠቀሱት በብሉይ ኪዳን ላይ ሌላ የትም አልተጠቀሱም ፤ ይሁን እንጂ በ 1ሳሙ ( 27፡ 10) እና ደግሞ እንደ ገና በ 1ሳሙ ( 30፡ 29) እንደ ቡድን ሰዎች በአንድ ላይ ተዘርዝረዋል ፡፡ ኤስሮማዊያን በዳዊት ልጅ የዘር መስመር ዉስጥ አልነበሩም ነገር ግን ተካትተዉ ስለ ነበር የጠቅላላ የዘሩን ትልቅ ስዕል ማየት እንችላለን ፡፡

1-ዜና መዋዕል (2፡ 42-54)፡ ፀሀፊው ወደ ካሌብ ዘር ወደ ሁለተኛዉ ቡድን ተመለሰ ፤ የካሌብ ሴት ልጅ በመሳ (1፡ 12-23) የተጠቀሰችዉ አክሳ ነበረች ፡፡ የእስራኤል የመጀመሪያዉ ፈራጅ የነበረዉን ጎቶንያልን አገባችዉ ፡፡

1-ዜና መዋዕል (2፡ 55)፡ ፀሀፊዎችም እንኳን ተጠቅሰዉ ነበር ! በዳዊት ልጅ ዘር ዉስጥ የተካተቱ ባይሆኑም እንኳን ሌሎችን ወደ እርሱ በማመልከት አስፈላጊ ሚናን ተጫዉተዉ ነበር ፡፡

መደምደሚያ

በአጠቃላይ በዚህ ምዕራፍ ዉስጥ ሁሉም ሰዎች የተለያዩ ሚናን ሲጫወቱ አይተናል ፤ ቤተሰቦችን፣ እህቶችን፣ ፀሀፊዎችን እን ብዙዎችን ሁሉንም ሌሎችን ወደ ዳዊት ልጅ በማመልከት ሚና ሲጫወቱ አይተናል ፡፡ ሌሎችን ወደ ዳዊት ልጅ ከማመልከት ሚና ዉጪ የምትጫወቱት ሮሜ ( 12፡ 11) ሁለት ታላቅ ማሳሰቢያዎች ይዟል፡” ለስራ ከመትጋት አትለግሙ ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ ፤ ለጌታ ተገዙ “ ፡፡ ትጋት ማለት ለአንድ ተግባር መሰጠት ማለት ነው ፤ በመንፈስ መቃጠል ማለት እግዚአብሄርን ስለ ማገልገል እና በሌሎች ላይ ከማየት ዉጪ ሌሎችን ለመባረቅ የተነቃቃ መሆን ማለት ነው ፡፡ ሌሎችን በመነቃቃት ሳናቋርጥ ወደ ዳዊት ልጅ ልናመለክታቸዉ እናገለግላለን ፡፡

ፓስተር ስቴቨን ኮል እግዚአብሄርን እንደሚያገለግል እንድናስታዉስ ለእኛ አራት ሀሳቦችን አስቀምጧል፡

  1. ሁሉም አማኞች ለአገለግሎት ተጠርተዋል ፤ በተለዬ የተጠራ የለም ፡፡
  2. እግዚአብሄርን የእርሱ ፍቃደኞች ሳይሆን እንደ ባሪያዎቹ እናገለግለዋለን …ኑሮአችን ወደ ዳዊት ልጅ እንዲያመለክት ከፈለግን ለእርሱ የተሸጥን መሆን አለብን ፤ ኢየሱስ ያስተማረው “ ከእናንተም የሚያርስ ወይም ከብትን የሚጠብቅ ባሪያ ያለው ከእርሻ ሲመለስ ወዲያዉ ቅረብና በማዕድ ተቀመጥ የሚለዉ ማነው ? የምበላዉን እራቴን አሰናዳልኝ እስክበላና እስክጠጣ ድረስ ታጥቀህ አገልግለኝ በኋላም አንተ ብላና ጠጣ የሚለዉ አይደለምን ? ያንን ባሪያ ያዘዘዉን ስላደረገ ያመሰግነዋልን ? እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ “ (ሉቃ 17፡ 7-10) ፡፡
  3. ራሳችንን ሳይሆን እግዚአብሄርን ነዉ የምናገለግለዉ ፡፡ በሚፈልገን ስፍራ ይህን ለመረዳት እና ለመስራት በምንጀምር ጊዜ ሰዎች ወደ ዳዊት ልጅ ያቀኑ ይሆናሉ ፡፡
  4. እግዚአብሄርን ማገልገል ማለት በመጀመሪያ ሌሎችን ማገልገል አይደለም ፤ ጳዉሎስ ይህን “ ሰዉን ወይስ እግዚአብሄርን አሁን እሺ አሰኛለሁን ? ወይስ ሰዉን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን ? አሁን ሰዉን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም “ (ገላ 1፡ 10) በዚህ መንገድ አስቀምጦታል ፡፡ ሌሎችን በምታገለግሉበት ጊዜ ልታስደስቷቸዉ አታገለግሉም ፡፡ ታገለግላላችሁ ምክንያቱም የእግዚአብሄር ልጆች እና የክርስቶስ ባሪያዎች ስለ ሆናችሁ ፡፡

እንዴት እንደ ምታገለግሉ ችግር የለዉም የምታደርጉት ለቀጣዩ ትዉልድ በመሰረት ላይ ያ ግንባታ ሊሆን እንደ ሚችል አስታዉሱ ፤ ካገለገላችሁ በንጉሱ መጨረሻ የምትደርሱ ትሆናላችሁ ፡፡

  1. Steven J. Cole, “Lesson 82: How to Serve the Lord (Romans 12:11)”; available at Bible.org. https://bible.org/seriespage/lesson-82-how-serve-lord-romans-1211.

ጥያቄዎች

  1. በ 1ዜና መዋዕል 2 ላይ የዘር ግንዱ በማን ነገድ ላይ ያተኩራል ? ፀኀፊዉ ይህን ለምን እንዳደረገ ምን ታስባላችሁ ?
  2. የእስራኤል ችግር የከሪም ልጅ አካን ማን ነበር (ኢያ 7፡ 1, 24-25) ?
  3. ዳዊት የእሴይ እንደ ሰባተኛ ልጅ መጠቀሱ የሚያወዛግብ ነው ( 1ሳሙ 16፡ 10-11) ? የመፅሀፍ ቅዱስ ምሁራን ዳዊት እንደ ሰባተኛ ልጅ የተጠቀሰበት ምክንያት ከወንድሞቹ አንዱ ያለወራሽ ስለ ሞተ ነዉ በማለት ያምናሉ ፤ ይህ የሚታመን ገለፃ ነዉ ብላችሁ ታምናላችሁ ? በመፅሀፍ ቁጥር ሰባት አስፈላጊ ነው ? አዎ ከሆነ ምን ይወክላል ?
  4. በ 1ዜና መዋዕል 2 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Chronicles 2:1–2

“These were Israel’s sons: Reuben, Simeon, Levi, Judah, Issachar, Zebulun, Dan, Joseph, Benjamin, Naphtali, Gad, and Asher.”

የእስራኤልን ወንዶች ልጆችና የይሁዳ ዘሮችን እያስታወሰ በዘር ውስጥ የነበሩት ስሞች ዝርዝር ቀጥሏል ፡፡ እያንዳንዱ ስም ቤተሰብን ፣ ሴት ልጅን ፣ ወንድ ልጅን ፣ እናትን ፣ አባትን ይወክላል ፡፡ እያንዳንዱ ስም በእስራኤላውያን ያማረ ታሪክ ውስጥ ሰዎችን ይወክላል ፡፡ ስሞችን በመዘርዘር የታሪክ ጸህፊያን እስራኤላውያን ከግዞት ሲመለሱ እንድያውቋቸው በማድረግ የዘር ሀረግን መመልከት ያለውን ጥቅም አረጋግጠዋል ፡፡ ከሮቤል እስከ ፋሬስ እስከ ካሌብ ድረስ እያንዳንዱ ቤተሰብና ሰው የሚመጣውን መሲህ ይጠቁማል ፡፡

ለእስራኤላውያውን ከግዞት በኋላ እንደታወሱላቸው ሰዎች ሁሉ አናንተ እራሳችሁ አስፈላጊ ናችሁ ፡፡ ምናልባት ዛሬ ይህን መስማት ያስፈልጋችሁ ይሆናል ፡፡ እናንተ ወንድም ፣ እህት ፣ ሚስት ፣ ባል ፣ እናት ፣ አባት ናችሁ ፡፡ ትገነባላችሁ ፣ ታስተምራላቸሁ ፣ ቴክኖሎጅ ትሰራላችሁ ፣ ትመራመራላችሁ ፣ ታጥባላችሁ እናንተ ለእግዚአብሔርና ለመንግስቱ አስፈላጊ ናችሁ ፡፡ ብዙዎች ክእናንተ በፊት በእግዚአብሔር መንግስት ስራን ሰርተው አልፈዋል ፡፡ ነገር ግን አሁን ተራው ያእናንተ ነው ፡፡ ለእግዚአብሔር እንደማትጠቅሙ የሚሰማችሁን ውሸት እንዳታምኑ ፡፡ እርሱ ፈጥሯችኋል ፤ ይወዳችሁማል በእናንተም ይተማመናል ፡፡ ስለዚህ በኩራት ቁሙ እርሱ እንድትሰሩ የጠራችሁንም ስራ ስሩ ፡፡ ንጉሡ መሲሁ ተመልሶ ይመጣል እናንተም በህይወት ስትኖሩ ለእርሱና ለእርሱ ብቻ በመኖር እርሱን ልታሳዩ አደራ አለባችሁ ፡፡

“ የእስራኤልም ልጆች እነዚሀ ናቸው ሮቤል ፣ ስምዖን ፣ ሌዊ ፣ ይሁዳ ፣ ይሳኮር ፣ ዛብሎን ፣ ዳን ፣ዮሴፍ ፣ ብንያም ፣ ንፍታሌም ፣ ጋድ ፣ አሴር ፡፡ “

  • 1ኛ ዜና 2፡1-2

ተጨማሪ ጥቅስ

ኢሳይያስ 43:1–2 — “ የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል ? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል ? በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሳር አድጎአል መልክና ውበት የለውም ፣ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም ፡፡ “

ሮሜ 12:11–12 — “ ለስራ ለመትጋት አትለግሙ ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ ፣ ለጌታ ተገዙ ፣ በተስፋ ደስ ይበላችሁ ፤ በመከራ ታገሱ ፣ በጸሎት ጽኑ ፡፡ “

ዕብራውያን 9:28 — “ እንዲሁ ክረስቶስ ደግሞ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ከተሰዋ በኋላ ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁት ሁለተኛ ጊዜ ያለ ኃጢአት ይታይላቸዋል ፡፡ “