Christ's Genealogy
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Son of David 1 Chronicles 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
1 ዜና የስም ዝርዝር ነው ፤ በዚህ ላይ እግዚአብሄር የሚያድስ ነገር እንደሚሰጠን ይሰማኛል ፤ የዘር ሀረግ ዝርዝር በምታዩ ጊዜ እባካችሁ መፅሀፍ ቅዱስን በመዝጋት ወደ እንቅልፍ እንዳትሄዱ ፡፡ ብዙ ሊሆን እንደሚችል አዉቃለሁ ፡፡ 1 ዜናን በማነብበት ጊዜ ጭንቅላቴ እየዋጀ እንደ ነበር አምናለሁ ፡፡ አጥንተናቸዉ የነበረዉን ስሞች እናያለን ፤ ተስፋ እንዳትቆርጡ ! ድግግሞች እንድንማር ይረዳናል ፤ የስሞች 54 ምዕራፎች አሉ - አስቸጋሪ ስሞች -ነገር ግን ይህን ማድረግ እንችላለን !
ትምህርት
መነሻዉ(የኃላ ታሪኩ)፡ ልክ እንደ 1እና 2 ነገስት እና እንደ ሳሙኤል ሁለቱ መፅሀፍቶች 1 እና 2 ዜና በመጀመሪያ አንድ መፅሀፍ ነበሩ ፡፡ “ ዜና “ የሚለዉ ቃል “ የቀናቶች ታሪክ “ ማለት ነው በተለይም ክስተቱ ወይም ሁነቱ የሆነበትን ቀናት በመጥቀስ ፡፡ በሮምስ ላቲን ቩልጌት እነዚህ ቁጥሮች መጀመሪያ ዜና ተብለዉ ተጠርተዋል ፤ ጄ.ቬርኖን “ የግሪክ ተርጓሚዎች ዜናን “ የተዋጡ(የተሰወሩ) ነገሮች “ የሚል ርዕስ ሰጡ - በሌሎች በታሪክ መፅሀፍት ላይ ያልተከሰቱ ብዙ በዚህ እንዳሉ “ ፅፏል ፡፡ የዜና 55 ፐርሰንት በነገስት እና በሳሙኤል መፅሀፍቶች ዉስጥ የሌም ሌላዉ ሁሉም ግን የተደጋገመ ነው ፤ ይህ ከወንጌላት ጋር ተመሳሳይ ነው ዮሐንስ በማቴዎስ እና በሉቃስ ላይ የለሉት ታሪኮች እንደ አሉት ነገር ግን ሁሉም ወደ ተመሳሳይ ነገር እንደ ሚያመለክቱት ፡፡
ዜና ከ 2ሳሙኤል መፅሀፍ ጋር አጋር ነው ፤ በ 2ሳሙኤል ኢየሱስን እንደ ዘላለማዊ ዙፋን ይጠቅሰዋል ( 2ሳሙ 7፡ 16) ፤ 1ዜና ስለ ዳዊት ልጅ ስለ ኢየሱስ ነው ፡፡ የሚመጣዉ መሲህ በዳዊት ዘር በኩል ይመጣል ፡፡ በእነዚህ በመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ምዕራፎች ሙሉ የስም ዝርዝሮችን እናያለን ፤ ነገር ግን በእነዚህ በሁሉም ስሞች ዉስጥ ዳዊት የት እንደተቀመጠ እንድናይ ያስፈልገናል ፡፡ ይህ የዘር ግንድ ወደ ክርስቶስ ማመልከቱን እንዴት እናየዋለን ? ይህን በደቡቡ መንግስት ክፍል በይሁዳ ዘር በኩል እናየዋለን ፤ ዳዊት እንዴት ከይሁዳ መስመር እንደመጣ እናያለን፡፡
1ዜናን ማን እንደፃፈው ቀጥተኛ የሆነ መግለጫ የለም ፡፡ የአይሁድ ልማዶች ካህኑን እዝራን እንደ ዜና ፀሀፊ ይመርጠዋል (ዕዝ 7፡ 1-6) ፤ እስራኤላዊያን እንዴት ወደ አሶር እንደ ተላኩ እና የአይሁድ ሰዎች ደግሞ ወደ ባቢሎን እንደተላኩ በመመልከት 2ነገስትን ጨርሰናል ፡፡ 2ዜና መጨረሻ ላይ እስራኤልዊያን ከምርኮ ተለቅቀዋል ፤ እዚህ በ 1ዜና ላይ እስራኤላዊያን በምርኮ ናቸው 2ዜና መጨረሻ ድረስ ነፃነት አላገኙም ፡፡ “ እንዴት እናገኛለን ? “ በማለት ስለ እነርሱ እዉነተኛ መግለጫን እናያለን ፤ ዘሩባቤል፣ ዕዝራና ነህምያ ሁሉም እስራኤላዊያን እግዚአብሄር እንዲሆኑ በሚፈልገዉ ቦታ ተመልሰዉ ለመሆን ማድረግ ስለሚያስፈልጋቸዉ ፅፈዋል ፡፡
ዮሐንስ ማክአርቱር “ አይሁዶች ከሰባ አመት ምርኮአቸው (530 ከክርስቶስ ልደት በፊት) አንድ ጊዜ ዳዊትን እና ሰለሞን ከአስተዳደሩበት ምድር ወደ ተለየየ ምድር ተመልሰዉ እንደ ነበር ፅፏል “ ፡፡ ማክአርቱር በተመለሱ ጊዜ ለአይሁዶ ሰዎች የተለዩ የነበሩ ሰባት ነገሮች(ሁኔታዎችን) ያቀርባል፡ 1) ከዕብራዊያን ንገስ ይልቅ በፋርስ መንግስት የተዳደሩ (ዕዝ 6፡ 2፣ 6) ፤ 2) የኢየሩሳሌም ግንብ ፈርሶ ስለነበር ከተማዋ የደህንነት (የሚከላከል) ግን አልነበራትም (ነህምያ 1-7) ፤ 3) ቤተ መቅደሱ ጠፍቶ ነበርና ዘሩባቤል ከሰለሞን ክብር ጋር በትንሹ የሚመሳሰል ይገነባል (ዕዝራ 3) ፤ 4) አይሁዶች ኃይለኞች ስላልነበሩ በመከላከል ላይ ይኖራሉ (ዕዝራ 4፣ ነህምያ 4) ፤ 5) አይሁዶች በመመለሳቸዉ ከመለኮታዊ በረከት ይልቅ ጠንካራ እና አስቸጋሪ ነገር ገጠማቸው ፤ 6) አይሁዶች ተወግደዉ በነበረ ጊዜ ኃብታቸዉን በማጣት በትንሽ ተመለሱ ፤ እንዲሁም ደግሞ 7) ከቤተ መቅደሱ ዉጪ የእግዚአብሄር መለኮታዊ መገኘት በኢየሩሳሌም አልነበረም “ ፡፡
ማክአርቱር የጠቀሳቸዉ(ያመለከታቸው) ሁሉም እያሉ እግዚአብሄር ከእስራኤል ጋር ነበር ፤ ለእስራኤላዊያን በማከማቻዉ እግዚአብሄር ትልቅ ስዕል እንደ ነበረው እናዉቃለን - የዳዊት ልጅን ፡፡ የዳዊት ልጅ ተስፋ የሚጠፋ አልነበረም ፤ በእግዚአብሄር ኪዳን ከህዝቡ ጋር በነበረዉ የተመሰረተ ነበር ፡፡
2ነገስት 25 የይሁዳ ሰዎች ወደ ባቢሎን በመወሰዳቸዉ ያልቃል ፤ 2ዜና 26 መጨረሻ ላይ አይሁዶች ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶ ለመምጣት ከፋሪስ ነፃ መዉጣትን ማግኘት ጀመሩ ፡፡ አስታዉሱ የዜና 55 ፐርሰንት የተለዬ ነው ፡፡
ለ1 እና ለ2 ዜና ዋና ዋና ዝርዝር እዚህ ላይ ነው፡
- የእስራኤል የዘር ግንድ ታሪክ (1ዜና 1-9) ፡፡
- የእስራኤል የተዋሀደዉ መንግስት
- በሳዖል ስር (1ዜና 10)
- በዳዊት ስር (1ዜና 11-29)
- በሰለሞን ስር (2ዜና 1-9)
- የተለያት መንግስት (2ዜና 10-36፡ 21)
- ይሁዳ ከሰባ የምርኮ አመታት ተለቀቀ (ነፃ ወጣ) (2ዜና 36፡ 22-23)
1-ዜና (1፡ 1-27)፡ የአዳምን ዘር በመሸፈን ከሚመጣዉ መሲህ ጋር ትስስሩን እናያለን ፡፡ በእዉነት ይህ ኃይለኛ ስዕል እንደሆነ አስባለሁ ! የሚመጣዉን መሲህ መልሰን ከአዳም ጋር እናገናኘዋለን ፡፡ ቁጥር 4-27 ቃል በቃል (በግልፅ) በኖህ ልጆች እና በዘራቸዉ በኩል ይጓዛል ፤ መፅሀፍ ታላቅ ህዝብ ይሆናል ያለዉን የኖህ ልጅ ካምን እንመልከት ፤ ይህ ተፅዕኖ በካም ልጆች በኩል መምጣቱን የኩሽ ህዝቦችን (ኢትዮጲያንን)፣ ምጽራይም (ግብፅ) እና ከነዓን (ከነዓናዊያን) ተፅዕኖ አድርጎባቸዉ ማየት እንችላለን ፡፡
የሴም ልጆች በቁጥር 17 መጀመሪያ ላይ የተዘረዘሩ ናቸው ፤ ሴም ከኖህ ልጆች ሞገስ ያገኘ ተደርጎ ነበር (ዘፍ 9፡ 25-27) ፡፡ የሴም የልጅ ልጅ ዔቦር የአብርሃም፣ የይስሐቅ እና የያዕቆብ ቅድም አያት ነበር ፡፡ “ ዕብራዊ “ የሚለዉ ቃል ምናልባትም የዔቦር ስም ልዉጥ ነው ለእስራኤላዊያንም የዋለ(የተጠቀመ) ነው ፤ በዘፍጥረት ዔቦር በአብርሃም የዘር ግንድ መዐከላዊ ስፍራ ሆኗል ፡፡ 1ዜና (1፡ 24-27) በዕብራዊ እና በዔቦር መካከል ያለዉን ግንኙነት ያመለክታል ፤ ዕብራዊ “ለዔቦራዊያን “ ያመለክታል (ዘፍ 10፡ 21. 11፡ 10-26) ፡፡ የዔቦር ልጅ ፋሌቅ (ምድር ተከፍላለች ማለት የሆነው) ምድር በባቢሎን ግብ ላይ በተከፋፈለች ጊዜ በዚያ ነበር (ዘፍ 11፡ 1-9) ፡፡
1-ዜና ( 1፡ 28-27)፡ እዚህ ላይ የአብርሃም ዘር ተዘርዝረዋል ፤ ይስሐቅ በአጋር ከተገኘዉ ከሌለኛዉ ከአብርሃም ልጅ ከእስማኤል በላይ የተባረከ ነው ፡፡ እንደ ተመረጠ ይስሐቅ የእስራኤል 12 ነገዶች ለመጡበት የያዕቆብ አባት ነው ፡፡
1 J. Vernon McGee. 1 Chronicles 2 Chronicles Notes and Outlines (Pasadena: Thru the Bible Radio Network). www.ttb.org.
1-ዜና (1፡ 38-50)፡ እነዚህ ቁጥሮች የኤዶም ነገስታት የነበሩትን የኤሳዉን ዘር ይሸፍናሉ ፡፡ ኤዶማዊያን ከእስራኤላዊያን ፊት በነገስታት ተስተዳድረዋል ፡፡ በዜና ዉስጥ በጠቅላላ “ የልጅ “ የሚለዉን ቃል ታያላችሁ ፤ ማክአርቱር “ ወንድ ልጅ “ የሚለዉ ቃል “ የሚገነባ “ ማለት እንደ ሆነ ይገልፃል ፡፡ የጥንት ዕብራዊያን ልጆቻቸዉን የወደፊቱ ትዉልድ ገንቢ እንደሆኑ ያስቧቸዋል ፤ ስለዚህም ሁሉም ትዉልድ ወደ ዳዊት ልጅ ለማመልከትእርስ በእርሳቸው እየተገነባቡ/እየተሰራሩ ነበር ፡፡
መደምደሚያ
ክርስቶስ ከምድራዊ ድርጊት አንፃር ዳዊትበምድር እየሰራ በነበረው ላይ ሰራ ፤ የቀዘቀዘ የሚያምር ስዕል እንደሆነ አስባለሁ ፡፡ ጳዉል ቫን ጎርደር ለምን 1ዜና (1-9) አትራፊ እንደሆነ ሰዎስት ምክንያቶችን ይሰጣል፡
መጀመሪያ ከባቢሎን ምርኮ ለተመለሱት ለአይሁዶች ታላቅጥቅሞች ነበራቸው ፤ በዚህ በመባዘን ጊዜ እስራኤላዊያን ቤተሰባቸዉን በማጣት እና የነገዳቸዉን ማንነት በማጣት አደጋ ላይ ነበሩ ፡፡ ዝርዝሩ የተለየ ዘር ሀረጋቸዉን ለመጠበቅ ረድቷቸዋል ፡፡
ሁለተኛ የዘር ግንዳቸዉ አይሁዶችን ከእግዚአብሄር ጋር ያላቸዉን አንድነት አነቃቃ ፤ ከምርኮ እንደ ተመለሱ በዘር ግንዱ ዉስጥ እስራኤላዊያን እግዚአብሄር መልሷቸዉ የነበረው የአባቶቻቸዉ “ እዉነተኛዉ አምላክ “ እንደ ነበር አዩ ፡፡
ሰዎስተኛ የዘር ግንዱ ክርስቶስ እስከሚመጣ ድረስ በመጓዝ የመለኮታዊ አላማ ማሳያ ነበር ፡፡ የአዳም ልጅ፣ የአብርሃም ልጅ፣የይሁዳ ልጅ እና የዳዊት ልጅ የነበረዉን የአዳኛችንን የመፅሀፍ ቅዱስ ታሪክ ሙሉ ለማድረግ ረድተዋል ፡፡ ሰብዓዊነታችንን ወሰደ “ ከኃጢዓት ዉጪ “ ፡፡
ይህ መፅሀፍ በቤተሰብ ማንነትን (የእግዚአብሄር ልጆች ናችሁ)፣ በአባት ማንነትን እና በልጅ ማንነትን ያሳያል ፡፡ ዜናን ለምን ? ምክንያቱም በትክክል በእግዚአብሄር ማን እንደሆናችሁ እንድታገኙ ይረዳችኋል ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 478.
John MacArthur, p. 478.
MacArthur, p. 483.
Paul R. Van Gorder. The Old Testament Presents . . . Reflections of Christ (Grand Rapids: RBC Ministries, 1982), n.p.
ጥያቄዎች
-
በ 1ዜና መዋዕል (1፡ 10) ናምሩድ የኩሽ የዘር ግንድ ነበር ፤ ናምሩድ በምን ይታወቅ ነበር (ዘፍ 10፡ 8-9) ? በባቢሎን ግንብ ላይ ባሉት ሰዎች ቡድን ላይ እግዚአብሄር ምን አደረገ ? ለምን ? (ዘፍ 11፡ 1-4)
-
በ 1ዜና መዋዕል (1፡ 13) የከነዓን ዘር የተሰጠ ነው ፤ እነዚህ ቡድን ሰዎች ላይ ምን ይሆን (ዘዳ 7፡ 1-6) ? እንደ ሚጠፉ እግዚአብሄር ተናገረ?
-
ከኤቦር ልጆች አንዱ የስሙ ትርጉም መከፋፈል ወይም የምድር መከፋፈል ቀን የሆነ ስሙ ፋሌቅ ነበር (1ዜና መዋዕል 1፡ 19) ፤ እግዚአብሄር በፋሌቅ ህይወት ጊዜ በባቢሎን ግንብ ላይ ቋንቋቸዉን እንደ ደበላለቀዉ ይታመናል ፡፡ የፋሌቅ ቤተሰቦች የሚመጣ የስሙ ትንቢታዊ እይታ እንደ ነበር እንደተረዱት ታስባላችሁ ?
-
በ 1ዜና መዋዕል 1 የዘር ግንድ ላይ የተጠቀሱ ሁለት ሴቶች አሉ ፤ እነማን ነበሩ ? በዘር ግንድ ላይ ሴቶች ሌላ የት ላይ ተጠቅሰዉ እናያለን (ማቴ 1፡ 1-17) ? እነማን ነበሩ በምንድን ይታወቁ ነበር ?
-
በ 1ዜና መዋዕል 1 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Chronicles 1:1–4
“Adam, Seth, Enosh, Kenan, Mahalalel, Jared, Enoch, Methuselah, Lamech, Noah, Noah’s sons: Shem, Ham, and Japheth.”
የእስራኤል ህዝቦች ከባቢሎን ከግዞት ከተመለሱ በኋላ ወደ ቀድሞ ማንነታቸው የእግዚአብሔር ቤተሰብ ህዝብ ወደ መሆን ተመለሱ ፡፡ የዘር ግንድ ጥናቱም ታሪካቸውን አስታወሳቸው እንድሁም የእግዚአብሔር እጅ በእያንዳንዱ ሰው ላይ በእያንዳንዱ ትውልድ ወስጥ እንዴት እንደነበረ አስታወሱ ፡፡ በዳዊት ልጅ በኢየሱስ ውስጥ እያንዳንዱ ስም የእግዚአብሔርን ታማኝነት ፣ ቤዛነትና ጥሪ ትርጉም ይዟል ፡፡ እነርሱ እግዚአብሔርን ቢያዩት ወይም መንገዱን መከተል ቢተው እግዚአብሔር የእነርሱ ሕይወት የክርስቶስን ዘር እንድሸከም ተጠቅሞበታል ፡፡
ዛሬ የቤተሰባችሁን የዘር ሀረግ ለመመልከት ደቂቃ ውሰዱ ፡፡ ስትመለከቱም ከባድ ጊዜያትን አስባችሁ ውስጣችሁ ሊረበሽ ይችል ይሆናል ወይም ደስ የሚሉ ትዝታዎችን አስታውሳችሁ ሊሞቃችሁ ይችላል ፡፡ በየተኛውም መንገድ እግዚአብሔር ዛሬ ያላችሁበት ቦታ እናንተን ለማድረስ የዘር ሀረጋችሁን ተጠቅሟል ፡፡ እግዚአብሔር የእንደገና አምላክ ነው ፡፡ በእርሱ ውስጥ ወዳለ ማንነት ይጠራችኋል ፡፡ በእርሱ ስትታመኑ የእርሱ ናችሁ ፡፡ የዘር ሀረጋችሁ ምንም ይበል እናንተ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ እርሱም የሰማዩ አባታችሁ ነው ፡፡ ታሪካችሁን እየጸፈው ነው ፤ ለህይወታችሁም እቀድና አላማ አለው ፡፡ ስለ ትላንቱ አመስግኑ ማንነታችሁ በሆነውም ለእግዚአብሔር የተመረጠ ልጅ ተመላለሱ ፡፡
“ አዳም ፣ ሴት ፣ሄኖስ ፣ ቃይናን ፣ መላልኤል ፣ ያሬድ ፣ሄኖክ ፣ ማቱሳላ ፣ ላሜህ ፣ኖኀ ፣ ሴም ፣ ካም ፣ ያፌት ፡፡ “
- 1ኛ ዜና 1፡1-4
ተጨማሪ ጥቅስ
ዮሐንስ 1፡12 –“ ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነረስ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ስልጣንን ሰጣቸው ፡፡ “
2ኛ ቆሮንቶስ 6፡18 –“ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ ፡- እኔም እቀበላችኋለሁ ለእናንተም አባት እሆናለሁ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆቸ ትሆናላችሁ ይላል ፡፡ “
ገላትያ 3፡26 –“ በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶሰ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።