Historical Books 2 Kings

The Last Kings of Israel

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Surviving Seed 2 Kings 24-25 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 281 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዛሬ በመጨረሻዉ በእስራኤል ንጉስ ላይ ምልከታ እናደርጋለን ፡፡ ከእነዚህ ሰዎች ጋር እግዚአብሄር ጠንካራ ኪዳን ነበረዉ ነገር ግን እነዚህ በእስራኤል አስቸጋሪ ጊዜ ነበሩ ፡፡ ባለፉት ምዕራፎች እግዚአብሄር በኢዮስያስ በኩል ታላቅ መነቃቃት አመጣ ፡፡ ኢዮስያስ ንጉስ በተደረገ ጊዜ ልጅ ነበር ፤ ይሁን እንጂ በንጉስ ከንጉስ በኋላ የምናያቸዉ ነገሮች ስለ እርሱ ነበሩ ፡፡ እስራኤል ምን ያክል ፃድቅ ነገስታቶች ነበሯት ? ምንም ፤ ይሁዳ ምን ያክል ፃድቅ ነገስታቶቹ ነበሯት ? ስምንት ፡፡

እስራኤል እና ይሁዳ ከተመሳሳይ ዘር እና ኪዳን የመጡ ቢሆንም እስራኤል ከመታሰቢያዎቹ ዉስጥ አንድ እንኳን የለውም ፤ ይሁዳ ግን በእግዚአብሄር ትክክል ያደረገዉ ኢዮስያስ ነበረው ፡፡ እግዚአብሄር ደግሞ ደግሞ ሰላምታ አቀረበለት ምክንያቱም ለኃጢዓት ምክንያት የሆኑትን ወርዉሮአቸዉ ስለ ነበር ፤ በንጉስ ኢዮስያስ መነቃቃት ነበር ፡፡ ለ31 አመታት ንጉስ ነበር በፅድቅም አስተዳደረ ፡፡ ከ31 አመት በኋላ በጦርነት ኢዮስያስ ተገደ ፤ ልጁ ኢዮአክስም ወደ ንግስና መጣ ፤ ነገር ግን ወዲያዉኑ ኤልያቄም ስሙ ወደ ኢዮአቄም የተቀየረው እርሱን ተካዉ በአጭሩ ስልጣኑን ያዘ፡፡ ሁለቱም ነገስታቶች በእግዚአብሄር ፊት ክፉ የነበረዉን ነገር አደረጉ ፡፡ ወደ እነዚህ ምዕራፎች ስንመጣ እግዚአብሄር እንዴት ኃጢዓትን እንደሚመለከት እንድንረዳ እፈልጋለሁ ፡፡

ትምህርት

2-ነገስት (24፡ 1)፡ ይህን ምዕራፍ ስንጀምር በዚህ ጊዜ ጊዜያዊዉ ማን እንደ ነበር እንድትረዱ እፈልጋለሁ (ኤር 25፡ 1-7) ፡፡ እግዚአብሄር እንዴት እየሰራ እንደ ነበር እናያለን ፤ ከነቢያቶች ማስጠንቀቂያዎች ቢመጡም እስራኤላዊያን ለመስማት ባለመቻላቸዉ በባቢሎናዊያን ተወሰዱ ፤ ይህ በደንብ እንደ ማናገለግል እና በብልፅግና ጊዜ እግዚአብሄርን እንደምንረሳ እንደሚያሳይ አስባለሁ ፡፡ የሰብዓዊነትን ንድፍ እንድናይ እፈልጋለሁ ፤ እንዲሁም ደግሞ ነቢያትን ለመላክ የእግዚብሄርን ምህረት እንድናይ እፈልጋለሁ ( ዳን 1፡ 1-7) ፡፡ መረዳትን ሊሰጡን የሚችሉት ማንኞቹ ህዝቦች ናቸው ?

2-ነገስት (24፡ 2-4)፡ 2ነገ ( 21፡ 1-7) ተመልከቱ ፤ እነዚህ ቁጥሮች የምናሴን ኃጢዓት ታሪክ ይሰጣሉ ፡፡ እንድንረዳው የፈለኩት ምንድን ነው ምናሴ መሆን ትችላላችሁ ደግሞም ኢዮስያስ መሆን ትችላላችሁ የሚለዉን ነው ፡፡ በ 31 አመት የሚታመን ንጉስ በመሆን ኢዮስያስ ለምናሴ ኃጢዓት ጊዜያዊ እፎይታ እንዳመጣ ታስባላችሁ ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር እግዚአብሄር ነዉ ኃጢዓት ደግሞ ኃጢዓት ነው ፡፡ ጥያቄዉ እግዚአብሄር በእኛ ኃጢዓትን እንዴት ያየዋል ነው ? ለኃጢዓት ዉጤቶች አሉት ፡፡ መጠንቀቅ አለብን ፤ እግዚአብሄር ኃጢዓታችንን ይቅር ይላል ነገር ግን ዉጤት ይኖራቸዋል ፡፡ በፅድቅ ያስተዳደረው ኢዮስያስ ቢኖርም እንኳን ምናሴ አስፈሪ ነገሮችን በማድረጉ ይሁዳ ስለኃጢዓቶቹ ተፈረደበት ፡፡

2-ነገስት (24፡ 5-20)፡ የባቢሎን ንጉስ የግብፅ ንጉስ በበቀለ ማጥቃትየማይችላባቸዉን ብዙ ግዛቶች ወስዶ ነበር ፡፡ የኢዮአቄም ልጅም ዮአኪስ በ18 አመቱ ነገስ (ቁጥር 18) ፤ እርሱም በእግዚአብሄር ፊት ክፉ ነገር አደረገ ኢየሩሳሌምም በባቢሎን ተከብባ ነበር ፡፡ ዮአኪስ ወደ ባቢሎን እንደ እስረኛ ከመወሰዱ በፊት ስምንት አመት አስተዳደረ (ቁጥር 15) ፡፡ ባቢሎናዊያን ከእግዚአብሄር ቤት ከቤተ መቅደሱ እና ከንጉሱ ቤት ሁሉንም ንብረት ወሰዱ ፤ ብዙ ንብረቶችን በመቆራረጥ የምድሪቱ ኃያላን እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች በመወሰድ በግዞት ተቀመጡ ፡፡

አሁንም በጦርነት ዉጊያ ላይ ነን መንፈሳዊ ምክሮችን የማንንመለከት ከሆነ፣ በልባችን ዉስጥ አስቸጋሪ ስፍራዎች ካሉን እና ለመቀየር ፍቃደኞች ካልሆንን ወደ ጥፋት ይመራናል ፡፡ ለመስማት ፍቃደኞች እና የተዘጋጀን ለመናገር የዘገየን ለመመለስ ደግሞ የፈጠንን መሆን አለብን ፡፡ በአሁኑ ጊዜም እግዚአብሄር ህዝቡን ማስጠንቀቁን ቀጥሏል ፡፡

የእስራኤላዊያንን በምሰማ ጊዜ ነገሮች የራቁ እና የተሰባበሩ ይሆናሉ ይህ ለነገስታቶች እና ለይሁዳ ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሄር እይታም ጥቁር ቀን እንደ ነበር ይነግረኛል ፡፡ ሁልጊዜም እቅዱ ለእስራኤላዊያን ብልፅግና ነበር ፡፡ የመጨረሻዉ ንጉስ ስም ሴዴቅያስ ነበር ፡፡ አሁንም እንደ ገና ህዝቡ በእግዚአብሄር ፋንታ ጣዖትን አመለኩ የራሳቸዉንም ነገር አደረጉ ፡፡

በአሁኑ ጊዜ የእግዚአብሄር ቤት ምንድን ነው ? የእግዚአብሄር ቤተ መቅደስስ የት ነው ? እዉነታዉ እኛ የእግዚአብሄር ቤተ መቅደሰሶች ነን ፡፡ የህንፃ ቤትን እንደ እግዚአብሄር ቤት ማገናኘት ምቹ ነዉ ነገር ግን እዉነተኛ ቤቱ አይደለም ፡፡ የእግዚአብሄርን ቤት፣ የእግዚአብሄርን መገኘት ወይም የእግዚአብሄርን ህግ የሚያረክስ ማንኛዉንም ነገር ከቤተ መቅደሱ ማስወጣት የሚያስፈልግ ነው ፤ ህንፃዉን መስራት በጣም ቀላላችን ነው ነገር ግን ቤተ መቅደሱን ገስፁ ፡፡ እግዚአብሄር ህዝቡ ምን ያክል ፍሬአማ እንዲሆኑለት መፈለጉን በማወቅ ይህን ምርኮኝነት በመመልከት አዝናለሁ ፡፡ እግዚአብሄር እንድንበለፅግ ይፈልጋል ነገር ግን ወደ ማለፍ እንዲመጣ በመፍቀድ በመንገዱ እየሄድን ነው ?

2-ነገስት 25፡ ሴዴቅያስ ንጉስ በነበረ ጊዜ ባቢሎን በኢየሩሳሌም ላይ ሙሉ ከበባ አደረገ ፤ የባቢሎናዊያን ሰራዊትም ሁሉንም ንግድ እና የከተማይቱን የዉስጥ እና የዉጪ መንገዶችን ቆረጡት ፡፡ በዘጠነኛዉ ቀን ከተማዋ በምግብ እጥረት ዉስጥ ወደቀች ፤ ከተማዋ ተለይታ በመዉደቅ መዳን እና መትረፍ ላይ ትኩረት አደረጉ (ኤር 27፡ 12) ፡፡ ኤርምያስ ምናሴ ቢኖርም ኢዮስያስም እንኳን ቢኖር እስራኤል እንደ ሚቀጣ ተረዶቷል ፤ ኤርምያስ “ አትዋጉትም ይኖራል እግዚአብሄርም ይመልሰናል “ ብሏል ፤ ይሁን እንጂ ህዝቡ ኤርምያስን አላዳመጡትም ፡፡ ጥሩ ነገር የሚነግሯቸዉን ብቻ ሰሙ ፡፡

መደምደሚያ

የሚገርመው በአሁኑ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ስለ ቤተ ክርስቲያን የምንሰማበትን ጆሮዎችን ይሰጠናል ፤ የሚገርመው ለእግዚአብሄር የሚናገሩትን እንሰማለን ፤ ያለንበትን የምህረት እና የብልፅግና ቀንን እንረዳለን ይገርማል ፡፡ ከእስራኤል ነገስታቶች ንድፍ መማር እንችላለን እንዲሁም “ በአሁኑ ጊዜ በፅድቅ እንድንሄድ እግዚአብሄር ስለሚረዳን ስህተታቸዉን አንደግምም “ እንላለን ፡፡

ጥያቄዎች

  1. በ 2ነገ (24፡ 1) ከሰዎስት አመት በኋላ ኢዮአቄም በናቡከደነፆር ላይ ስላደረገዉ አመፅ ምን ታስባላችሁ ? (2ዜና 36፡ 6)
  2. በ 2ነገ (24፡ 14) በጣም ድሀ ሰዎች በምርኮ ለምን አልተወሰዱም ?
  3. የነገስታቶቹ ያለማቋረጥ በእግዚአብሄር ፊት ክፉ ነገር ማድረግ በእኛ ጊዜ ከመሪዎች እና ከሰዎች ጋር እንዴት ይገናኛል ? በአሁኑ ጊዜ ዉጤቶቹስ ተመሳሳይ ናቸው ?
  4. የክፉዉ ንጉስ ዮርማሮዴቅ ዮአኪንን መልቀቅ እና መርዳት የኢየሱስን ንጉስ ፀጋ እንደ አማኝ ለእኛ እንዴት ያሳዬናል ? (2 ነገ 25፡ 27-30፣ ሉቃ 4፡ 18)
  5. በ 2ነገስት (24-25) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Kings 24:3

“Indeed, this happened to Judah at the LORD’s command to remove them from His sight. It was because of the sins of Manasseh, according to all he had done.”

የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ኢየሩሳሌም ገባ እና የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ፣ የንጉሡን ቤት ፣ ታላላቅ ቤቶችንና የኢየሩሳሌምን ግንብ ሁሉንም አጠፋ ፡፡ በዳዊት ኪዳን እግዚአብሔር ሰሎሞንን እንድገነባ ያዘዘው ነገር ሁሉ አከተመ ፡፡ ሁሉም ነገር ፡፡ ከአመታት በኋላ ንጉሡ የእግዚአብሔር ያልሆነ ነገርን በቤተ መቅደሱ በመቀበል በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገርን ፈጸመ ፡፡ በዚህም ምክንያት ሰው የሰራው ነገር ሁሉ ፈጽሞ በመፍረስ አከተመ የአይሁድም ምርኮ ለግዞትና ለባርነት ወደ ባቢሎን ተወሰዱ ፡፡

ቅዱስ እንደሆነናና አንደተወደደ የክርስቶስ ተከታይ አካላችሁ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነው ፡፡ መገኘቱም በውስጣችሁ እንድኖር አናንተ ህያው መስዋዕት አድርጋችሁ አካላችሁን አቅርቡለት ፡፡ በቤተ መቅደሳችሁ ምን ትፈቅዳላችሁ ? እግዚአብሔር ምንም ቢሆን በእውነተኛ ፣በተከበረ ፣ በትክክለኛ ፣ በንጹህ ፣ በተወደደ ፣ በሚታዘዝና የላቀ ህሊና ባለው ውስጥ እንደሚያድር ተናግሯል ፡፡ እግዚአብሔር እንድትበለጽጉና እንድትታዩ ስለሚፈልግ ቤተ መቅደሳችሁን የሚያቆሽሹትን ነገሮችን እንድትገድሉ ያዛችኋል ፤ እነዚህም ፡- ዝሙት ፣ ርኩሰት ፣ ፍትወት ፣ ክፉ ምኞትና ስስት ናቸው ፡፡ ይህን እወቁ ! እነዚህ ነገሮችን በቤተ መቅደሳችሁ ላይ ከፈቀዳችሁ በህይወታችሁ ላይ ጥፋትን ያመጣሉ ፡፡ በጊዜው የምትተውት ነገር የሚጎዳችሁ ይመስላችኋል ነገር ግን ይህ እግዚአብሔርን ማምለክ ነው ደግሞም ይህ ጥሩ ዋጋ ያለው ስርዓት ነው ፡፡ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሆነውን ሰውነታችሁን ስለጠበቃችሁ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካችሁ ፡፡

“ ምናሴ ስላደረገው ኃጢአት ሁሉ ከፊቱ ያስወግዳቸው ዘንድ ይህ ነገር በእግዚአብሔር ትእዛዝ በይሁዳ ላይ ሆነ ፡፡ “

  • 1ኛ ነገሥት 24፡3

ተጨማሪ ጥቅስ

ሮሜ 12፡1 –“ እንግዲህ ወንድሞች ሆይ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ህያው ቅዱስም መስዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ እርሱም ለአዕምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው ፡፡ “

1ኛ ቆሮንቶስ 3፡16-17 –“ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንድኖርባችሁ አታውቁምን ? ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነውና ያውም እናንተ ናችሁ ፡፡ “

ቄላስያስ 3፡5 –“ እንግዲህ በምድር ያሉትን ብልቶቻችሁን ግደሉ እነዚህም ዝሙትና ርኩሰት ፍትወትም ክፉ ምኞትም ጣዖትንም ማምለክ የሆነ መጎምጀት ነው ፡፡ “