The Spirit of Revival
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Surviving Seed 2 Kings 23 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
መነቃቂያ ጊዜ ላይ ሁሉንም ነገር እናደርጋለን ሪቫይቫል ት/ቤትም በአጠቃላይ ስለ መነቃቃት ነው ፡፡ መፅሀፍ ለዉጥ ለማግኘት በዉስጣችን ያለዉን እዉነት ማነሳሳት እንደሚያስፈልገን ያወራል ፡፡ በ 2ነገስት በንጉስ ኢዮስያስ አመራር ስር ይሁዳ በመጨረሻም ከእግዚአብሄር ጋር ኪዳኑን ለማደስ መነቃቃት እና እድል አግኝቶታል ፤ ኢዮስያስ አባቱ ከህግ መፅሀፍ ያዉቀዉ ከነበረዉ እና እርሱ ተቀብሎት ለነበረዉ እዉነት በፍጥነት ነቃ (ተነሳ) ፡፡ በተሰጠነዉ ነገር ለመነቃቃት ዝግጁዎች ነን (ዕብ 4፡ 12) ? ለመነቃቃት ጊዜ ነው !
ትምህርት
በምዕራፍ 23 በይሁዳ በኢዮስያስ ኃይማኖታዊ ተሀድሶ ዉስጥ እንጓዛለን ፡፡
2-ነገስት (23፡ 1-3)፡ መጀመሪያ ኢዮስያስ ከእግዚአብሄር ጋር አዲስ ኪዳን ዉስጥ ገባ ፤ የህጉ መፅሀፍ እንዳለዉ በተረዳ ጊዜ ኢዮስያስ የኢየሩሳሌምን እና የይሁዳን ህዝ በቤተ መቅደሱ ላይ ሰበሰባቸው (ቁጥር 1) ፤ ኢዮስያስም ወደ ቤተ መቅደሱ በመዉሰድ እግዚአብሄር ከእስራኤል ጋር አድርጎት ስለ ነበረዉ ኪዳን አነበበላቸው (ቁጥር 2) ፡፡ ኢዮስያስም በቤተ መቅደሱ አምድ አጠገብ በመቆም እግዚአብሄር ሰጥቷቸዉ የነበረዉን ትዕዛዙን፣ ምስክሩን እና ስርዓቱን ድምፁን ከፍ አድርጎ በማንበብ ኪዳን አደረገ (ቁጥር 3)( ኢያ 8፡ 34፣ 1 ሳሙ 7፡ 2) ፤ ሁሉም ህዝብ በኪዳኑም ተስማሙ (ቁጥር 3) ፡፡ ትሁት እና ዉለታ የማይረሳ ልብ በሚኖራችሁ ጊዜ ለመነቃቃት (እንደ ገና ለመነሳት) ዘዴ (መንገድ) አላችሁ ፡፡
2-ነገስት (23፡ 4-20)፡ ቀጥሎም ኢዮስያስ በመላዉ ምድሪቱ ኃያማኖታዊ ማስተካከያ አቋቋመ ፡፡ አንዴ መነቃቃት ሰብሮ ሲወጣ ለዉጥ ይሆናል - ለመማር፣ በሌሎች አማኞች ፊት ለመሆን፣ ስለ እምነታቸው አዲስ የደስታ ደረጃ መኖርን መፈለግ አለ በተጨማሪም ከሌሎች ጋር እግዚአብሄርን የመነጋገር ፍላጎት አለ ፡፡ ኢዮስያስ ለመነቃቃቱ ኃይማኖታዉ ለዉጦችን በማምጣት ምላሽ ሰጠ፡
- ኢዮስያስ በቤተ መቅደሱ ዉስጥ ጣዖት ማምለኪያ ሁሉንም ነገሮች እንዲያስወግዱ በማዘዝ ከኢየሩሳሌም ዉጪ አቃጠላቸው (ቁጥር 4) ፤ ከዚያም አመዱን ኢዮሮብዓም የጣዖት ማምለኪያ ማዕከል በማድረግ ወደ አረከሳት ወደ ቤቴል አስር ማይል ወሰደው (1ነገ 12፡ 28-33) ፡፡
- ኢዮስያስ በኮረብታዎች ላይ ለባዖል እና ለሌሎች ጣዖት ይሰዉ የነበሩትን ሁሉንም ካህናት አስወገደ (ቁጥር 5) ፡፡
- ኢዮስያስ የዐፀድን ማምለኪያ አምዶች ከእግዚአብሄር ቤተ መቅደስ ዉስጥ በማስወገድ በቄድሮን ፈፋ በማቃጠል አለመታዘዛቸዉን ለማሳየት አመዱን በሰዎች መቃብር ላይ ወረወረው (ቁጥር 6) ፡፡
- ኢዮስያስ ሁሉንም የግብረ ሰዶማዊያን ቤቶችን ወይም ድንኳኖችን አፈረሰ እንዲሁም ሴቶች ለዐጸድ ማምለኪያ በቤተ መቅደሱ ዉስጥ የሚፈትሉበትንም አፈራረሰ (ቁጥር 7) ፡፡
- ኢዮስያስ በመላዉ ይሁዳ ጣዖቶች ያመልክበት የነበረዉን ኮረብታዎች ያረከሱ ሁሉም የይሁዳ ካህናቶች ነበሩት (ቁጥር 8) ፤ የኮረብታዎች ካህናት ወደ ኢየሩሳሌም አልመጡም ነገር ግን ያልቦካ እንጀራ ከሌሎች ካህናት ጋር በሉ (ቁጥር 9) ፡፡
- ኢዮስያስ ቶፌትን ርኩስ ስላደረገው ለሞሎኮ የሚቀርብ የልጅ መስዋዕት አይኖርም (ቁጥር 10) ፡፡
- ኢዮስያስ በቀድሞዎቹ በይሁዳ ነገስታት ለፅሀይ ሰጥተዋቸዉ የነበሩት ፈረሶች አስወገደ ሰረገሎቹንም አቃጠለ (ቁጥር 11) ፡፡
- ኢዮስያስ በቤቱ ጣሪያ ላይ እና በቤተ መቅደሱ አደባባይ ላይ በክፉ ነገስታት ተሰርተዉ የነበሩትን ሁሉንም መሰዊያዎች አጠፋ (ቁጥር 12) ፤ ወደ ትናንሽ በማድቀቅም ወደ ቄድሮ ፈፋ ወረወረው ፡፡
- ኢዮስያስ ንጉስ ሰለሞን የሚስጦቹን አማልዕክቶች ለማክበር አሰርቷቸዉ የነበሩትን ሁሉንም ኮረብታዎች አፈረሱ (ቁጥር 13) ፡፡
- ኢዮስያስ የጣዖት ሀዉልቶችን እና ዐፀዶችን ቦታ ለማርከስ በሰዎች አጥንት በመሙላት አጠፋው ስለሆነም እንደ ገና ለማምለኪያ በፍፁም መጠቀም አይችሉም (ቁጥር 14) ፡፡
- ኢዮስያስ የኢዮሮብዓምን መሰዊያ እና በቤቴል ያሉ ኮረብታዎቹን አጠፋ፣ በዚያ የተቀበረዉንም የካህናት አጥንት በማቃጠል ሁሉንም ስፍራ ለማርከስ አመዱን እረጨዉ (ቁጥር 15-16) ( 1ነገ 3፡ 2) ፡፡
- ኢዮስያስ መሰዊያዎቹን እና በሰማሪያ ኮረብታዎች ያሉትን ካህናቶች አረዳቸው በሰዉም አጥንት አረከሳቸው (ቁጥር 19-20) ፡፡
ኢዮስያስ እነዚህ ነገሮች እንደ ሚሆኑ ተንብዮ የነበረዉን የእግዚአብሄርን ሰዉ መቃብር(መታሰቢያ) አገኘዉም ብቻዉም ተወዉ (ቁጥር 17-18) ፡፡ ኢዮስያስ ከሌዋዊያን ካህናት ዉጪ በይሁዳ የነበሩትን አጽድቶ በጨረሰ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ (ቁጥር 20) ፡፡
2-ነገስት (23፡ 21-23)፡ ሰዎስተኛው ኢዮስያስ የፋሲካን አከባበር እንደ ገና አቋቋመ ፡፡ ሕዝቅያስ ህዝቡን በአንድ እንዳገኘ(በአባካኝነት) ፋሲካ አከባበር መርቷቸዉ ነበር (2 ዜና 30) ፤ ነገር ግን ኢዮስያስ ሕዝቅያስ ካቀረበዉ ቁጥር ሁለት እጥፍ አቀረበ ፡፡ ዋይርስቤ “ ቢያንስ 37,000 ትናንሽ እንስሳቶች በተጨማሪም 3,800በሬዎች አቅርቦ እንደ ነበር ፤ ካህናቶቹ እና ሌዋዊያኑ ነፅተዉ በመቀደስ ለማገልገል ዝግጁ ነበሩ እንዲሁም ለእግዚአብሄር ምስጋናን የሚያዜሙና መሳሪያ የሚጫወቱ ብዙ ሌዋዊያንም እንደ ነበሩ “ ይናገራል ፡፡
2-ነገስት (23፡ 24)፡ አራተኛዉ ኢዮስያስ ታሀድሶዉን ቀጠለ ፡፡ ኢዮስያስም መናፍስት ጠሪዎችን፣ ጠንቋዮችን፣ የቤት ጣዖቶችን፣ ተራፊሞችን እና በይሁዳ እና በኢየሩሳሌም የእግዚአብሄር ያልነበረዉን የቀረዉን ማንኛዉንም ነገር አስወገደ (ቁጥር 24) ፡፡
2-ነገስት (23፡ 25-27)፡ ቁጥር 25 “ እንደ ሙሴ ሕግ ሁሉ በፍጹም ልቡ፣ በፍጹም ነፍሱ እና በፍጹም ኃይሉ ወደ እግዚአብሄር የተመለሰ ንጉስ አልነበረም ፤ እንደ እርሱም ያለ ንጉስ ከእርሱ በኋላ አልተነሳም “ ይላል ፡፡ የዳነዉ ዘርእግዚአብሄር እንዲሆን የፈለገዉን ሲያደርግ ታዩታላች ፤ ይሁን እንጂ ኢዮስያስ ያደረገዉ ሁሉ በእግዚአብሄር ላይ ያደረገዉን የይሁዳን አለመታዘዝ አመታት መመለስ(ማስቀረት) አይችልም (ቁጥር 26-27) ፡፡
መደምደሚያ
ዴል ራልፍ ዳቪስ ኢዮስያስ ያደረገዉን “ እንደ ኢዮስያስ 12 ደረጃ የምናሴ ማወራረጃ (ማስመለሻ) ፕሮግራም “ ይገልፃል ፡፡ በእግዚአብሄር ቃል መሰረት ኢዮስያስ ምናሴ አሞጽ እና ሌሎች ክፉ ነገስታቶች ወደ ይሁዳ አምጥተዉት የነበረዉን ሁሉንም ነገር ያስወግዳል ፤ በተመሳሳይ አምላካችንን የማያከብረዉን በቤተ ክርስቲያን እና በኑሮአችን ያለዉን ሁሉንም ነገር ማስወገድ ያስፈልገናል ፤ ትኩረታችንን በኢየሱስ ላይ እናድርግ ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary: 2 Kings (Colorado Springs: David C. Cook, 2003), p. 590.
ጥያቄዎች
-
እግዚአብሄር ስለ ሚያመጣዉ አስጊ ፍርድ ከሰማ በኋላ ኢዮስያስ ምን አደረገ ? የሚታደሰዉ ኪዳን አካል እንዲሆን ማንን ጠራ ?
-
ሁሉም ህዝብ ወደ ኪዳኑ ራሳቸዉን ማምጣታቸዉ ስለ እዉነት ምንድን ነዉ አስፈላጊነቱ ? በህዝቡ መካከል የመንፈስ ቅዱስን ማለፍ (መንቀሳቀስ) አይታችኋል ? በመፅሀፍት ሌላ የት ላይ መንፈስ ቅዱስ በህዝቦች ቡድን መካከል ተንቀሳቅሷል ? (ሐዋ 2፡ 4፣ 4፡ 31፣ 10፡ 44)
-
ኢዮስያስ እግዚአብሄርን ለማክበር መልሶ ያደሳቸዉ ጥቂት ነገሮች ምን ነበሩ ? በህይወታችሁ በፍጥነት ልታጠፉት እና ንስሀ ልትገቡበት የሚያስፈልጓችሁ ጥቂት ነገሮች አሉ ?
-
በብዙ ነገሮች ኢዮስያስ የፋሲካን አከባበር አካቶ የማን ምሳሌ እየተከተለ ነበር (2 ነገ 18፡ 3-6፣ 2ዜና 30፡ 1) ? የኢዮስያስ ፋሲካን ማክበር አስፈልጊነቱ ለምን ነበር ? (2 ዜና 35፡ 18-19)
-
የኢዮስያስ እግዚአብሄራዊ አመራር ቢሆንም እግዚአብሄር ለምን በይሁዳ ተበሳጨ ? (2 ነገ 21፡ 11-13፣ 22፡ 15-17)
-
ስለ ንጉስ ኢዮስያስ ትንቢቱ ለመፈፀም 300 አመታት ያክል ወስዷል (1 ነገ 13፡ 2) ፤ እግዚአብሄር ተስፋ እንደ ገባላችሁ ባወቃችሁ ጊዜ ነገር ግን ለወራት ወይም ለአመታት የምትጠብቁ ከሆነ እንዴት በእግዚአብሄር በመሆን ትጠብቃላችሁ ? (መዝ 27፡ 14፣ 2 ቆሮ 1፡ 20)
-
በ 2ነገስት 23 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Kings 23:24–25
“In addition, Josiah removed the mediums, the spiritists, household idols, images, and all the detestable things that were seen in the land of Judah and in Jerusalem. He did this in order to carry out the words of the law that were written in the book that Hilkiah the priest found in the LORD’s temple. Before him there was no king like him who turned to the LORD with all his mind and with all his heart and with all his strength according to all the law of Moses, and no one like him arose after him.”
ኢዮስያስ የእግዚአብሔርን ቃል ካነበበ በኋላ ቃሉ ህይወቱን ለወጠው ውሳኔንም ለመወሰን አነሳሳው ፡፡ ሸማግሌዎችን ሁሉ ፣ ካህናቱና ነቢያቱንም ህዝቡም ሁሉ ከታናሾቹ ጀምሮ እስከ ታላቆቹ ድረስ ሰበሰበ እና ከዚያ በቤተ መቅደሱ የተገኘውን የቃል ኪዳኑን መፅሐፍ ቃል ሁሉ በጆሮአቸው አነበበ ፡፡ ንጉሡም እግዚአብሔርን ተከትሎ ይሄድ ዘንድ ትዕዛዙንም ምስክሩንም ስርዓቱንም በፍጹም ነፍሱ ይጠብቅ ዘንድ ኪዳንን አደረገ ፡፡ የቃል ኪዳኑን ቃል ያጸና ዘንድ ቃል ኪዳን አደረገ ህዝቡም ሁሉ ቃል ኪዳን ገቡ ! ይህን ቁርጠኝነት ተከትሎ ንጉሥ ኢዮስያስ እግዚአብሔርን የሚያረክሰውን ነገር ሁሉ አስወገደ ፣ ጠረገ ፣ አቃጠለ ፣ ሰባበረ ፣ አረደ እንድሁም ቀዳዶ ጣላ ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ይህን ትውልድ በእውነት ቀይሮታል ፡፡
ሰዓቱ ነው ፡፡ በትውልድ ፣ በአለም ፣በማህበረሰብህ ፣ በቤተሰብህና በህይትህ ላይ የመነቃቃት ሰዓት ነው ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል በፍጥነት ህይወትህን እንድቀይር ፍቀድ ፡፡ ቃሉን ስታነብና የእግዚአብሔርን መንገድ ስትከተል በህይወትህ መወገድ ስላለባቸው ጣዖቶች ፣ ምስሎች እና የተለያዩ ነገሮች አስብ ፡፡ ውሳኔን ወስን ተግባሩንም ፈጽም ፡፡ እንደ ንጉሥ ኢዮስያስ በድፍረት ትኖር ዘንድ ራስህን አጥራ ፡፡ አታፈግፍግ ፤ ዛሬ በእግዚአብሔር ቃል ልብህን ማነቃቃት ጀምር እርምጃንም ውሰድ !
“ ደግሞም ካህኑ ኬልቅያስ በእግዚአብሔር ቤት ባገኘው መጽሐፍ የተጻፈውን የሕጉን ቃል ያጸና ዘንድ መናፍስት ጠሪዎቹነና ጠንቋዮቹን ተራፊምንና ጣዖታትንም በይሁዳ አገርና በኢየሩሳሌም የተገኘውን ርኩሰት ሁሉ ኢዮስያስ አስወገደ ፡፡ እንደ ሙሴም ሕግ ሁሉ በፍጹም ልቡ በፍጹምም ነፍሱ በፍጹምም ኃይሉ ወደ እግዚአብሔርም የተመለሰ እንደ እርሱ ያለ ንጉሥ ከእርሱ አስቀድሞ አልነበረም እንደ እርሱም ያለ ንጉሥ ከእርሱ በኋላ አልተነሳም ፡፡ “
- 2ኛ ነገሥት 23፡24-25
ተጨማሪ ጥቅስ
ሐዋርያት ሥራ 28፡31 –“ ማንም ሳይከለክውየእግዚአብሔርን መንግስት እየሰበከ ስለ ጌታ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እጅግ ገልጦ ያስተምር ነበር ፡፡ “
1ኛ ዮሐንስ 5፡21 –“ ልጆች ሆይ ከጣዖታት ራሳችሁን ጠበቁ ፡፡ “
ራዕይ 21፡27 –“ ለበጉም በሆነው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት በቀር ጸያፍ ነገር ሁሉ ርኩሰትና ወሸትም የሚያደርግ ወደ እርስዋ ከቶ አይገባም ፡፡ “
“
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።